#update ታላቁ የህዳሴ ግድብ⬇️
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለምንም መስተጓጎል እየተከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የግድቡ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለን ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎ የግድቡ ግንባታ ሊቆም ይችላል የሚሉ ወሬዎች ሲናፈሱ መቆየታቸው በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬ እንዲፈጥሩ ምክንያት መሆናቸው ተነስቷል፡፡
ሆኖም የግድቡ ግንባታ በተያዘለት የግንባታ ሂደት እየተከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አዜብ አስናቀ ተናግረዋል፡፡
ኢንጅነር አዜብ ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮጀክት ነው ያሉ ሲሆን ሁሉም በእልህ ተነሰሳስቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ የሚናፈሰውን መሰረተቢስ ወሬ ወደ ኃላ በማለት ከዚህ ቀደም ለግድቡ ያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ግድቡን በስራአስኪያጅነት እንዲመሩ የኢንጅነር ስመኘው ምክትል የነበሩት አቶ #ኤፍሬም ወልደ ኪዳን ቦታውን በጊዜያዊነት ተክተው እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ህዳሴ ግድብ⬆️
አምስት የጀርመን ፓርላማ አባላት እሁድ ነሀሴ 20 ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡ አቶ #ኤፍሬም_ወልደኪዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ስለግድቡ ግንባታ አጠቃላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

#update ሜቴክ⬇️
የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተሰጠው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ኮንትራት እስካሁን አለመቋረጡን፣ የፕሮጀክቱ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ #ኤፍሬም_ወልደኪዳን (ኢንጂነር) ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ መንገዶች እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች የተሳሳተ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሆኑን የገለጹት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ልምድ ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች የንዑስ ተቋራጭነት ውሎችን ከሜቴክ ጋር በመዋዋል በርካታ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን እንዲያከናውኑ መደረጋቸው አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በተመለከተ ስምምነት ያለው ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር ስለሆነ፣ አሁንም ይኼንን ውል በተመለከተ የተለወጠ ነገር አለመኖሩን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ
ገልጸዋል፡፡
ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ኮንትራትን ማቋረጥም ሆነ አዲስ ውል መዋዋል ቀላል ተግባር አይደለም፡፡ እስካሁንም ሜቴክ ዋና ኮንትራክተር ነው፤›› ሲሉም ተደምጠዋል።
©ሪፖርተር

ከአዲስ አበባ⬆️
"ፀግሽ መስከረም 27 በአካባቢያችን ወረዳ 4 የሚገኙ ውጤታማ ተማሪዎችን "ውጤታማ ተማሪዎችን በማበረታት ለተሻለች ኢትዮጵያ እንትጋ" በሚል መሪ ቃል እንሸልማለን:: በእለቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ #ኤፍሬም የወረዳ አመራሮች የሃይማኖት አባቶች አቲስቶች የሚገኙ ይሆናል። በከተማችን የላይበራሪ አጠቃቀማችንን የንባብ ባህላችንን አስመልክቶ ግሩም ዶክመንተሪ ይቀርባል። የዚህ ግሩፕ አባላትንም ጋብዘናል። አድራሻ መሳለሚያ ወርዳ 4 ወጣት ማእከል አዳራሽ፦ ኢትዮ የልማትና መረዳጃ እድር ከቀድሞ 01 ወጣት ተስፋ መረዳጃና የልማት ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ።እናመሰግናለን!"

ሀላባ ከተማ ይቅርታ ጠየቀ🔝
ባሳለፍነው እሁድ በ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሀላባ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደበት ጨዋታ በ76ኛው ደቂቃ ላይ ከተመልካች በተወረወረ #ድንጋይ የመሐል ዳኛው #ኤፍሬም_ደበሌ ላይ ጉዳት በመድረሱ ምክንያት መቋረጡ የሚታወስ ነው። ይህንን አስመልክቶም የሀላባ ከተማ ክለብ ለፌዴሬሽኑ የይቅርታ ደብዳቤ አስገብቷል።
የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አንዋር ሲራጅ ስለ ጉዳዩ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በተፈጠረው ስርዓት አልበኝነት በጣም እንዳዘኑ ገልፀው የሀላባ ከተማ በእግርኳስ ውድድሮች ባለፉት 10 ዓመታት ሲሳተፍ እንዲህ አይነት ድርጊት ታይቶ እንደማይታወቅ በማውሳት ከጨዋታው መቋረጥ በኋላ አመራሩ እንዲሁም የከተማው አስተዳደር ማምሻውን ስብስባ አድርጎ ወደ እርምጃ በመግባት ሁለት ተጠርጣሪዎችን ወዲያው በመያዝ በቀጣዩ ቀንም 9 ወጣቶችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ለማቅረብ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ፕሬዝዳንቱ የሀላባ እግር ኳስ ክለብ እና የከተማው አስተዳደር የተፈጠረውን ሁሉ አጥብቆ እንደሚቃወምና እንዲህ አይነት ድርጊት ዳግም እንዳይፈፀም አጥብቀው እንደሚሰሩ በመግለፅ የሚመለከታቸው አካላትን በክለቡ እና በሀላባ ህዝብና አስተዳደር ስም ይቅርታ መጠየቀቸውን ለሶከር ኢትዮጽያ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ

ሀሰተኛ መረጃ‼️
አርቲስት #ኤፍሬም_ታምሩ ከጀርመን ራድዮ ጋር ቃለ ምልልስ አላደረገም። ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አርቲስት ኤፍሬም ታምሩ ከጀርመን ራድዮ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል በሚል የተሰራጨዉ መረጃ #የተሳሳተ ነዉ።
አርቲስቱ በምንም ዓይነት ጉዳይ ላይ ከጀርመን ራድዮ ጋር በቅርቡ ቃለ ምልልስ ያልሰጠ መሆኑን የዝግጅት ክፍሉ ገልጿል። አርቲስት ኤፍሬም #የአገውን_ሕዝብ አስመልክቶ ሰጠ የተባለዉ መረጃ የጀርመን ራድዮ በሚያሰራጫቸዉ የሬዲዮ፣ የፌስ ቡክ፣ የዋትስ አፕ እና የቲዩተር ገጾች ላይ ፈፅሞ ያልቀረበ መሆኑንም አድማጮች ተከታታዮች እንዲረዱለት አሳስቧል።
Via ዶቼ ቨለ