TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ህዳሴ ግድብ⬆️

አምስት የጀርመን ፓርላማ አባላት እሁድ ነሀሴ 20 ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡ አቶ #ኤፍሬም_ወልደኪዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ስለግድቡ ግንባታ አጠቃላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ⬇️

የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተሰጠው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ኮንትራት እስካሁን አለመቋረጡን፣ የፕሮጀክቱ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ #ኤፍሬም_ወልደኪዳን (ኢንጂነር) ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ መንገዶች እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች የተሳሳተ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሆኑን የገለጹት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ልምድ ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች የንዑስ ተቋራጭነት ውሎችን ከሜቴክ ጋር በመዋዋል በርካታ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን እንዲያከናውኑ መደረጋቸው አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በተመለከተ ስምምነት ያለው ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር ስለሆነ፣ አሁንም ይኼንን ውል በተመለከተ የተለወጠ ነገር አለመኖሩን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ
ገልጸዋል፡፡

ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ኮንትራትን ማቋረጥም ሆነ አዲስ ውል መዋዋል ቀላል ተግባር አይደለም፡፡ እስካሁንም ሜቴክ ዋና ኮንትራክተር ነው፤›› ሲሉም ተደምጠዋል።

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia