ከፖላንድ ቲክቫህ አባል፦
እኔ የምገኘው ፖላንድ ነው። አውሮፓ በኮሮና ወረርሽኝ እየታመሰች ነው። እኔ ባለሁበት ሀገር 425 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 5 ሰዎች ሞተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ማስክ እና ግላቭ ዋጋ መጨመሩ እጅግ በጣም አስገርሞኛል። ሰዎች ላይ ራስ ወዳድነት ይታያል።
እዚህ ፖላንድ ውስጥ ማስክ በመደበኛ ዋጋ ከሚሸጥበት ዋጋ #ቀንሶ ነው የሚሸጠው። እርስ በእርስ ሰዎች በጣም ይተሳሰባሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥም እርስ በእርስ መረዳዳት እና መተሳሰብ ቢኖር መልካም ነው። ሰዎች አጠቃቀሙንም ሊረዱት ይገባል፤ ማስክ ማድረገን ቫይረሱ አይዘውም ማለት አይደለም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የምርቶች ዋጋ ...
መንግስት በፍራንኮ ቫሉታ ከውጪ እንዲገቡ የፈቀዳቸው ምርቶች ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው #መጨመር አሣሣቢ ሆኗል ተባለ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምርቶቹን በፍራንኮ ቫሉታ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።
ዘይት ፣ ስኳር ፤ ሩዝና የህፃናት ወተት በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ የተፈቀዱ ምርቶች መሆናቸው ይታወሳል።
ምርቶቹ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ በመፈቀዱ ባለፉት አስር ወራት ብቻ መንግስት በታክስ መልክ ማግኘት የነበረበትን ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አጥቷል ተብሏል።
ነገር ግን የምርቶቹ ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው ሲጨምር እንደሚታይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ተናግረዋል።
ጭማሪው እየታየ ያለዉ በአለም ላይ ዋጋቸው #ቀንሶ ባለበት ወቅት ጭምር ነው ብለዋል።
ምርቶቹ ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ስርጭታቸውም ላይ ብዙ ግልፅነት እንደሌለ ተነግሯል።
እንደ ማሣያም ዘንድሮ በአስር ወራት ወደ ሀገር ውስጥ የገባው የምግብ ዘይት 97 ሚሊየን ሊትር እንደሆነ ተጠቅሷል። አምና በተመሣሣይ ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ግን ከአንድ መቶ ሚሊየን ነበር ተብሏል።
እንዲያም ሆኖ በገበያው ላይ የምርት አቅርቦት ችግር የለም ተብሏል። ሁኔታው በስርጭቱ ላይ ችግር መኖሩን አመላካች እንደሆነ ተጠቅሷል።
አስመጪዎች በበኩላቸው በብርና ዶላር መካከል ያለው ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መስፋት የምርቶቹ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ማለታቸውን ከሬድዮ ጣቢያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@tikvahethiopia