TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ብአዴን⬇️

የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የድርጅቱን #ስም እና #አርማ ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል።

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፥ ብአዴን ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ መሰረት በማድረግ የድርጅቱን ስም እና አርማ ሊቀይር ነው።

በዚህም መሰረት ድርጅቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ የምርጫ ስያሜዎች በአባላት ሙሉ ተሳትፎና ምርጫ በጉባኤ ውሳኔ ለመቀየር በሁሉም የድርጅቱ መዋቅሮች ለውይይት እንዲወርድ ተደርጓል ብሏል።

ለምርጫ የቀረቡት የቀረቡት ስሞች:-

1.የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አህዴፓ)

2.የአማራ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (አህዴአፓ)

3.የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ)

4.የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አህዴን) የሚሉ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ20/80 እና የ40/60 ቤቶች የእጣ ባለእድለኞች #ስም_ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርብላችኃለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ #12ኛክፍል

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ #ስም ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገፅ በመኖራቸው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ትክክለኛውን የኤጀንሲውን ገፅ ብቻ ብትከተሉ መልካም ነው። ትላንት እንደተሰማው የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት አርብ ወይም ከዛ በፊት ይፋ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስከዛሬ ምላሽ ያልተገኘለት የኮቪድ-19 መነሻ !

" FBI የወረርሽኙ መነሻ በቤተ ሙከራ ውስጥ ያጋጠመ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ገምግሟል " - ክርስቶፈር ውሬይ

የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (FBI) የኮቪድ 19 መነሻ የቻይና መንግሥት የሚቆጣጠረው ላብራቶሪ ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የተቋሙ ዳይሬክተር ክርስቶፈር ውሬይ ተናገሩ።

ዳይሬክተሩ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል " FBI የወረርሽኙ መነሻ በቤተ ሙከራ ውስጥ ያጋጠመ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ገምግሟል " ብለዋል።

" ቻይና የዓለም አቀፍ ወረርሽኙን ምንጭ ለማወቅ የሚደረገውን ጥረት ለመከላከልና ለማድበስበስ እየሞከረች ነው። ይህም በጣም የሚያሳዝን ነው " ሲሉ ወቅሰዋል።

FBI ወረርሽኙ እንዴት እንደተቀሰቀሰ ውስን ድምዳሜ ላይ ሲደርስ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

ቻይና ከዚህ ቀደም ወረርሽኙ በዉሃን ከሚገኝ ቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው መባሉን የተቃወመች ሲሆን የቀረበባትን ውንጀላም " #ስም_ማጥፋት " ነው ብላ ነበር።

ከዚህ በፊት ወረርሽኙ ከቤተ ሙከራ አምልጦ ስለመውጣቱ በስፋት ውድቅ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ የጤና ባለሠልጣናትም "ቫይረሱ ከማምለጡ በፊት በቤተ ሙከራ የተፈጠረ ሊሆን ይችላል" መባሉን በይፋ አጣጥለውታል።

የዓለም ጤና ድርጅት ከቤተ ሙከራ አምልጦ ወጥቷል መባሉን " የማይሆን ነው "  ያለ ሲሆን ነገር ግን በምርመራው ላይ ከፍተኛ ትችት ከደረሰበት በኋላ የተቋሙ ዳይሬክተር ጀኔራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አዲስ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ፤  " ሁሉም መላ ምቶች ቀርበዋል ተጨማሪ ጥናት ግን ያስፈልጋል " ብለው ነበር።

ኮቪድ 19 በ2019 መጨረሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ወደ 7 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia
👍371👎53😱2213😢13🤔12🕊8