TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እስከዛሬ ምላሽ ያልተገኘለት የኮቪድ-19 መነሻ !

" FBI የወረርሽኙ መነሻ በቤተ ሙከራ ውስጥ ያጋጠመ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ገምግሟል " - ክርስቶፈር ውሬይ

የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (FBI) የኮቪድ 19 መነሻ የቻይና መንግሥት የሚቆጣጠረው ላብራቶሪ ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የተቋሙ ዳይሬክተር ክርስቶፈር ውሬይ ተናገሩ።

ዳይሬክተሩ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል " FBI የወረርሽኙ መነሻ በቤተ ሙከራ ውስጥ ያጋጠመ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ገምግሟል " ብለዋል።

" ቻይና የዓለም አቀፍ ወረርሽኙን ምንጭ ለማወቅ የሚደረገውን ጥረት ለመከላከልና ለማድበስበስ እየሞከረች ነው። ይህም በጣም የሚያሳዝን ነው " ሲሉ ወቅሰዋል።

FBI ወረርሽኙ እንዴት እንደተቀሰቀሰ ውስን ድምዳሜ ላይ ሲደርስ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

ቻይና ከዚህ ቀደም ወረርሽኙ በዉሃን ከሚገኝ ቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው መባሉን የተቃወመች ሲሆን የቀረበባትን ውንጀላም " #ስም_ማጥፋት " ነው ብላ ነበር።

ከዚህ በፊት ወረርሽኙ ከቤተ ሙከራ አምልጦ ስለመውጣቱ በስፋት ውድቅ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ የጤና ባለሠልጣናትም "ቫይረሱ ከማምለጡ በፊት በቤተ ሙከራ የተፈጠረ ሊሆን ይችላል" መባሉን በይፋ አጣጥለውታል።

የዓለም ጤና ድርጅት ከቤተ ሙከራ አምልጦ ወጥቷል መባሉን " የማይሆን ነው "  ያለ ሲሆን ነገር ግን በምርመራው ላይ ከፍተኛ ትችት ከደረሰበት በኋላ የተቋሙ ዳይሬክተር ጀኔራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አዲስ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ፤  " ሁሉም መላ ምቶች ቀርበዋል ተጨማሪ ጥናት ግን ያስፈልጋል " ብለው ነበር።

ኮቪድ 19 በ2019 መጨረሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ወደ 7 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia