TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፤ መተከል ዞን፤ ማንዱራ ወረዳ ከዕሁድ ሌሊት ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ13 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ታደሰ #ለቢቢሲ ገልፀዋል። https://telegra.ph/BG-07-08-2
ከሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነው የፍየሎች እስር!

ከሰሞኑ ባለቤትነታቸው #የአረና ትግራይ ፓርቲ አባል ናቸው የተባሉ አስራ ስድስት ፍየሎች የመታሰራቸው ዜና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የአረና ፓርቲ ሊቀመንብር አቶ አብርሃ ደስታ በላፈው ረቡዕ የፓርቲው አባል ንብረት የሆኑ 16 ፍየሎች በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ንኡስ ወረዳ ወርቅ አንባ ቀይሕ ተኽሊ ቀበሌ ውስጥ መታሰራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፍየሎቹ ባለቤት የሆኑት አቶ ዜናዊ አስመላሽ 16 ፍየሎቻቸው ታስረውባቸው እንደነበረ ተናግረው፤ ታስረው ከነበሩት ፍየሎች ሶስቱ አምልጠው ወደ ቤት መመለሳቸውን #ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህን ጉዳይ ሌሎች የውጭ ሀገር ሚዲያዎችም ሲቀባበሉት ታይቷል👇
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦነግ 600 የሚሆኑ አባላቶቹ በመንግስት እንደታሰሩበት አስታወቀ! የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል፤ ኦነግ በመግለጫው 600 የሚሆኑ አባላቶቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታውቋል። ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ብንወስንም የድርጅታችን አመራሮች እና አባላትን ማሰር እና ማጠልሸት እየተሰራ ነው ብሏል። በኦነግ እና በሕወሓት መካከል አለ እየተባለ የሚወራው ግንኙነት…
#UPDATE

የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ የተሰጠው መግለጫ የፓርቲያቸው እውቅና እንደሌለውና እርሳቸውም ስለ መግለጫው መረጃ እንደሌላቸው #ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ ዳውድ ፥ ስለዚህ መግለጫ ምንም የማውቀው ነገር የለም ፤ አንጀንዳውም ሆነ አላማው ምን እንደሆነ አይገባኝም፤ ምክትሌም ስለ መግለጫው አላውቅም ብሎ ዛሬ ግን በመግለጫው ላይ ተገኝቷል፤ በአጠቃላይ የማምታት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በቅርቡ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ በተደረጉበት ሰዓት በምክትላቸው አቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ስብሰባ ብዙ የተምታታ ነገር አለበት ብለዋል፤ ጉዳዩን የፓርቲው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እያጣራ እንደሆነም ተናግረዋል።

አቶ ዳውድ በፓርቲያቸው ውስጥ እየተፈጠረ ላለው ልዩነት ኦነግ በመንግስት ኢላማ ተደርጓል በሚል መንግስትን ተጠያቂ አድርገዋል ሲል ቢቢሲ በዛሬ ምሽት ስርጭቱ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia