TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህወሓት ጉባኤውን ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤  የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ…
#TPLF : ህወሓት የጉባኤ መክፈቻ እያደረገ ይገኛል።

ድርጅቱ " 14ኛው ጉባኤ መክፈቻ እየተካሄደ ነው " ብሏል።

በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ቡድን ነው ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት ! / የመዳን ጉባኤ ! " በሚል መሪ ቃል የጀመረው።

እንደወጣው መርሀ ግብር ጉባኤው ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተነገረው።

የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞና በሌሎችም ምክንያቶች አይሳተፉም።

የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ነፍገዋል።

በተለይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉና ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ በሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ቀድሞ አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

ፎቶ፦ TPLF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥተዋል።

ጉባኤው " በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ  ' ይቃወሙናል ' የሚሉዋቸው የተወሰኑ #አመራሮች_ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው " ብለውታል።

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " ሲሉ ገልጸዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ  ፤ " የተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ህወሓት እንደ አዲስ እንደሚዘገብ የሚያደርግ ፣ ወርቃዊው የትግራይ ህዝብ ትግል የሚያጎድፍ በቀጣይ ቅርቃር ውስጥ የሚከት መሆኑን በመገንዘብ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ በማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መግባባት ተደርሶ ነበር " ብለዋል።

" ይሁን እንጂ የተደረሰው መግባባትና መተማመን ወደ ጎን በመተው ' ከፌደራል መንግስት ተማምነናል ' በሚል ማደናገሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመነጋገር  ከማእከላዊ ኮሚቴ እና ካድሬ በመደበቅ የተሄዴበት ሂደት ወዳልተፈለገ ወጥመድ እንድንገባ ተደርገናል " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ተጠያቂው ለጠባብ ቡድናዊ ፍላጎቱ ብቻ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝቡ ሰላም እንዳይደፈርስና እንዳይረበሽ ከህዝባችንና ከመላ አባላችን በመሆን እንታገላለን " ብለዋል።

" ሁሉም የትግራይ አቅሞች በማቀናጀት በተደራጀ ትግል ከፍተኛ ፓለቲካዊ ድርድር በማካሄድ የህወሓት ህጋዊነት በመመለስ ካጠላብን ዙርያ መለስ ፈተና በመውጣት የትግራይ የተሟላ ደህንነትና እድገት እንደሚረጋገጥ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ህወሓት / TPLF በአመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል የፈጠረውን እና በምርጫ ቦርድም እውቅናን የተነፈገውን አወዛጋቢ ጉባኤ መክፈቻ እያካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው በሊቀመንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ቡድን ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ጉባኤውን አንሳተፍም " በማለታቸው አልተገኙም።

ሊቀ መንበሩን ደብረጽዮን  ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ፣ አዲስዓለም (ዶ/ር)ን ጨምሮ በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙትን አመራሮች ከላይ በተያያዘው ፎቶ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert🚨

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል። ... ይህ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል !! " - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)


በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።

በዚህም " በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ  አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው " ብለዋል።

" ህግ እና ስርዓት ከማንኛውም ሰው ፣ ተቋም ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ  የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ለገሰ (ዶ/ር) ፥ " የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው " ያሉ ሲሆን " ህወሓት ደጋግሞ  እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል " ብለዋል።

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል፡፡ " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ድርጊቱ  የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡ " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና  የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም  ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል " በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አሁኑኑ ወደ አቢሲንያ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን በመሄድ የATM ካርድ በጠየቁበት ፍጥነት ወዲያውኑ ይውሰዱ!

አጠቃቀሙን ለማየት ሊንኩን ይጫኑ:

https://www.tiktok.com/@abyssinia_bank/video/7387019078206098694
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
🎁 ቴሌብርን ይጠቀሙ ተጨማሪ ስጦታዎችን ያግኙ!

🚀 ቴሌብር ሱፐርአፕን onelink.to/fpgu4m ሲያወርዱ 100ሜ.ባ፣ የመጀመሪያውን ግብይት ሲፈጽሙ ደግሞ የ15 ብር ስጦታ ይበረከትልዎታል!

በተጨማሪም በቴሌብር 100 ብር እና ከዚያ በላይ የሞባይል አየር ሰዓት ሲሞሉ 25%፣ ከ100 ብር በታች ሲሞሉ 15% እንዲሁም ጥቅል ሲገዙ 10% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

▶️ ለተጨማሪ፡ https://youtu.be/l7sSDPhPig4 ይመልከቱ!

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ t.iss.one/EthiotelecomChatBot 24/7 ያግኙን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Ethiopia

ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ፥ በፓሪስ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ 7 ሚሊዮን ብር እና የወርቅ ኒሻን ሽልማት አበርክተዋል።

ለሀገራቸው የብር ሜዳልያ ላመጡት አትሌት ትግስት አሰፋ፣ አትሌት በሪሁን አረጋዊ እና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለእያንዳንዳቸው የ 4 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡

የታምራት ቶላ እና ትግስት አሰፋ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ የሁለት ሚልዮን ብር ሽልማት ቢሰጣቸውም ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

አሰልጣኙ ፥ " ፕሬዝዳንታችን እኛ አሰልጣኞች ለረጅም ጊዜ ለፍተናል ፣ ልፋታችንን አይመጥንም " ብለዋል።

" እኔ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የወርቅና የብር ሜዳሊያ እንዲሁም ዲፕሎማ አስመጥቼ፤ ለዚህ ሀገር ተጋድዬ ለእኔ ሁለት ሚሊዮን ብር የስድብ ያህል ስለሆነ እርሶን ካላስከፋዎት ይህንን ሽልማቴን መመለስ እፈልጋለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የሚመጣውን ሁሉ እቀባለለሁ " ሲሉም ተናግረዋል።

ቪድዮ ፦ ኢቢሲ መዝናኛ

Via @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ድርጅቱ ጉባኤውን እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ ከፍተኛ አመራር አለ " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ለሁለት የከፈለውና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድም እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ጉባኤ መክፈቻ ዛሬ ተደርጓል።

የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በመክፈቻው ባሰሙት ንግግር ምን አሉ ?

ሊቀመንበሩ " ድርጅቱ ህጋዊ እውቅና እንዳያገኝና ጉባኤው እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ #ከፍተኛ_አመራር አለ " ብለዋል።

" በፓርቲያችን ውስጥ ተፈልፎሎ ያደገ፣ ፓርቲያችን ለመበተን እየሰራ ያለው የጥፋት ቡድን ያደረገውና አሁንም እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ፥ በየሰዓቱ እየፈጠረው ባለው ማደናገርያ ሁኔታችን ከመጥፎ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህንም ለማስቆም በዘላቂነት ለመቀየር ብቸኛ መፍትሔው 14ተኛ ጉባኤ ማካሄድ እና ማካሄድ ብቻ ነው " ብለዋል።

" ህወሓት አድኖ ህዝብ ከጥፋት መታደግ የጉባኤው ዋነኛ አላማ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የድርጅቱና የህዝቡ የተሟላ ድህንነት ማረጋገጥ በሚችል መልኩ በዴሞክራሲያዊ ውይይትና ክርክር ብቃት ያላቸው አመራሮች መምረጥ ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የአሁኑ ጉባኤ ለድርጅቱ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው " በማለት አክለዋል።

" ህወሓት ፈረሰ ማለት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ፈረሰ ማለት ነው " ብለው " በዚህ ግዜ ህወሓት ከፈረሰ የፕሪቶርያው ስምምነት አይኖርም ብቻ ሳይሆን ከነአካቴው ታሪክ ሆኖ ይረሳል ማለት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ከፈረሰ የትግራይ ህዝብ ለበይ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" ስለዚህ እነዚህ ችግሮችና አደጋዎች ለመፍታት ነው ጉባኤአችን በዚህ ፈታኝ ወቅት ለማድረግ የፈለግነው ብቻ ሳይሆን የግድም ልናደርገው የተገደድነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#ጉምሩክ

° “ ጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅን በደብዳቤ ሽሮ ከእጥፍ በላይ ቀረጥ ‘ ክፈሉ ’ እያለን ነው ” - አስመጪዎች

° “ ከአፈጻጸም አኳያ ምን ሊያስቸግረን ይችላል ? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” - ጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ኮሚሽን ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ምክንያት በማድረግ ከተቀመጠው አዋጅ ውጪ የቀረጥ ክፍያ እየጠየቃቸው መሆኑን አስመጪ ነጋዴዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል፡፡

ነጋዴዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ጉምሩክ እስከዛሬ የሚሰራበት አዋጅ ነበር።

አዋጁ፣ ‘ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡም ሆነ ከአገር የሚወጡ እቃዎች የቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ የሚሰላው ስለእቃዎቹ የቀረበው የእቃ ዲክላራሲዮን በተመዘገበበት ቀን በብሔራዊ ባንክ የተገለጸውን የገንዘብ ምንዛሪ በመጠቀም ይሆናል ’ ይላል፡፡

ግን አዋጁን በደብዳቤ ሽረው ‘እቃው በተመዘገበበት ሳይሆን እቃው ከጉምሩክ መልቀቂያ ባገኘበት ቀን ባለው ሬት ተሰልቶ ልዩነቱን እንዲከፍሉ>’ የሚል አዲስ መመሪያ አውጥተዋል፡፡

አዋጅ በደብዳቤ ይሻራል ወይ ? ግን ሽረውት ቅሬታ ለማቅረብ ከዋና መስሪያ ቤት ስንሄድ የተወሰንን ነጋዴዎች ተሰባስበን ቅሬታ ለማቅረብ በነበርንበት ጥያቄችንን ሳይሰሙን ፌደራል ፖሊስ መጣ የተሰበሰበውን ሰው እንዳለ በመኪና ጭኖ ይዟቸው ሄደ ፤ ወደ 40 ነጋዴዎችን፡፡

አዋጅን የሚያክል ነገር በአንድ ደብዳቤ ተሽሮ፣ ' ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ክፈሉ ' የሚል አሰራር አመጡ፡፡

ሲቀጥል ጭማሪው እጅግ በጣም የተጋነነ ነው፡፡ በ57 ብር የተመዘገበን እቃ 100 በላይ ብር ክፈሉ እያሉ ነው፡፡ ከእጥፍ በላይ ነው የሚጠይቁት።

ለምሳሌ ፦ የቀድሞ የተመዘገበው ቀረጥ 2 ሚሊዮን ብር ከነበረ አሁን በእጥፍ 4 ሚሊዮን ብር ይሆናል፡፡ ጉምሩክ ያሉት ኦፊሰሮች እንኳ የሚሰሩበት ሲስተም የላቸውም፡፡ ' ዝም ብላችሁ አቻኩሏቸው ' ተብለው እቃችን እናዳለ ተይዟል ” ብለዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የነጋዴዎቹን ጥያቄና ቅሬታ ይዞ ለምን እንደዚህ ሆነ? ሲል የጠየቃቸው የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ተከታዩን ምላሽ ሰጥጠዋል፡፡

ምን አሉ ?

“ እንደሚታወቀው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ አስፈጻሚ ተቋማት የራሳቸውን ሚና አላቸው፡ አንዱ አስፈጻሚ ተቋም ጉምሩክ ኮሚሽን ነው፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ ህጎችን ያስፈጽማል፡፡ አንዱ የብሔራዊ ባንክ ጋር ተያይዞ ያሉ ህጎችን የሚያስፈጽም ነው፡፡

በምን መልኩ መስተንግዶ መሰጠት እንዳለበት ውይይቶች ሲደረጉ ቆይቶ ነበር፡፡ ያ ሰርኩላር ከዛ ጋር በተያያዘ ነው የመጣው፡፡ ሰርኩላሩ አጠቃላይ ነገሮችን የያዘ ነው፡፡

ከተጠቀሱት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አስመጪዎች ዋናው መስሪያ ቤት (አዲስ አበባ) አካባቢ ቅሬታውን ለማሰማት እንደመጡ ሰምቻለሁ፡፡

ከምን አንጻር ነው ይሄ ሰርኩላር ? ለሚለው ተጨማሪ ውይይቶች የሚያስፈልጉ ከሆነ ውይይቶች እየተደረጉ ነው፡፡ አጠቃላይ ሰርኩላሩን አንልም ሰርኩላሩ ተፈጻሚ ነው የሚሆነው፡፡ ግን ያነሷቸው ጉዳዮች ታይው ምላሽ ይሰጣል፡፡

በኋላ ብዙ አመጪዎችን ማወያየት እንደተቻለም ከአመራሮች ያገኘሁት መረጃ አለ፡፡

ግን አንዳንዴ እንዲሁ በጋራ መጥቶ አቤቱታዎችን የማሰማት ሁኔታዎች ሲኖሩ እዚያ አካባቢ ያሉትን ነገሮች ጸጥታ የማስከበር ሥራዎች ተሰርተው ሊሆን ይችላል፡፡

በኋላ ላይ ግን የተወሰኑ አስመጪዎችን በማናገር ያላቸውን ቅሬታ ኮሚሽኑ እንደሚያየው፣ ተገቢነት ያለው ከሆነ ሊፈታ፣ ከህግ አንጻር የሚያስኬድም ከሆነ በዚያው ሊቀጥል የሚችልበት እድል እንዳለ ነው የሰማሁት፡፡

አስመጪዎቹ የሚያነሳቸውን ጉዳዮችን ኮሚሽኑ ተረድቷል፡፡

ከህግ አንጻር ምን መሆን ነው ያለበት ? ከአፈጻጸም አኳያስ ምን ሊያስቸግረን ይችላል? የሚለውን ውይይት እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጉዳዩ ከምን እንደሚደርስ ኮሚሽኑን ጠይቆ ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🎁 በተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች ለወራት ያለሃሳብ ዳታ እንጠቀም! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት!⚡️

🤖 የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
  
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether