TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ሰባት የመቐለ ከተማና ሁለት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ከፍተኛ ካድሬዎች " ጠባብ ቡድን " ሲሉ በጠሩ አካል ተጠርቷል ባሉት የህወሓት ጉባኤ እንደማይሳተፉ አስታወቁ። አመራሮቹ ፤ " ባሁኑ ወቅት የሚካሄደው ጉባኤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ላለመሳተፍ ወስነናል " ብለዋል። በጉባኤው እንዳማይሳተፉ በደብዳቤ ያስታወቁ የህወሓት ከፍተኛ ካድሬዎች ፦ 1. ነጋሽ ኣርኣያ - የመቐለ ጀተማ የህወሓት ፅህፈት…
#Update

" ለሚፈጠረው ችግር እኛ ተጠያቂ አይደለንም " - የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን

የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ ባወጣው ባለ 3 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፥ " ጤናማ ያልሆነ  ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው " ብሏል።

" ጤናማነት  ሂደት የሌለው ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር አይችልም " ብሎ በማመን ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱን ማግለሉን አሳውቋል።

" በቡድናዊ ማን አለበኝነት የሚካሄድ " ብሎ የጠራውን ጉባኤ ተከትሎ በሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ተጠያቂ አለመሆኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ የህወሓት ህጋዊ እውቅና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት መመለስ ሲገባው ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ እውቅና መሰጠቱ እንደማይቀበለው ገልጿል።

በህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መካከል እና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግባባት ያልተደረሰበት በእልህ የሚካሄደው ጉባኤን እንደሚቃወምም የገለጸው የቁጥጥር ኮሚሽኑ ፤ " ጉባኤው ተከትሎ በትግራይ ህዝብና በህወሓት የሚፈጠረው አደጋ ተጠያቂው በማንአለበኝነትና በእኔነት ስሜት በመጓዝ ላይ ያለው ቡድን ነው " ብሏል።

" በህወሓት የተፈጠረው ችግር መፍትሄው የቡድን ፉክክር ፣ እኔነትና እልህ አይደለም " ያለው ኮሚሽኑ " ደርጅቱ የሚድነው በስርአታዊና ተቋማዊ ትግል ነው " ሲል ገልጿል።

የህወሓት የፅ/ቤት ሃላፊና የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብሄር ትላንት የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በጉባኤ እንዲሳተፉ በፃፉት ደብዳቤ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00  ጀምሮ በመቐለ የሰማእታት ሓወልት አዳራሽ ይካሄዳል " ብለዋል።

ኮሚሽኑ ግራ ራሱን ከጉባኤው አግልሏል።

ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ ደግሞ ህወሓት በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ነገ ለሚጀምረው ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ አባላት ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ መቐለ እየተጓዙ እንደሆኑ እያሳወቀ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelle 

@tikvahethiopia
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ አዲሱን የኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልኩን እጅግ ደማቅ በሆነ የጌሚኒንግ እና የሙዘቃ ዝግጅት በቃና ስቱዲዮ ለተጠቃሚዎች አስተዋውቋል!

በተለይም ለጌመሮች እና ለሙዚቃ አድናቂዎች የተለየ ነገርን ይዞ የመጣው አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ ነሀሴ 4 በቃና ስቱዲዮ በአይነቱ ለየት ባለ ዘግጅት አዲሱን ስልኩን አንዲሁም የኢንፊኒክስ ቲቪ፣ ላፕ ቶፕ ፣ ስፒከሮች፣ ስማርት ዋች እና ኤር ፖዶችን ለተጠቃሚዎች አስተዋውቋል፡፡ አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ የኔትወርክ ቴክኖሊጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን በጌመሮች እና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ስራዎችን በስልካቸው በሚከውኑ ስዎች ተመራጭ የሆነውን የ Mediatek Dimesnty 7020 ፕሮሰሰርን የተገጠመለት ፈጣን ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
#SafaricomEthiopia

ምን እየጠበቅን ነው? ቲክቶክ ላይ የሙዚቃች ችሎታችንን እያሳየን እስከ 400,000 ብር ድረስ እንሸለም እንጂ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#1Wedefit
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ። ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም። " ከፍተኛ የሆነና…
#Update #GambellaUniversity

“ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ' ይነሳልን ' ያሉት ሰው #ተነስቷል ” - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ዩኒቨርሲቲው ሪፎርም ቢያደርግም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው የፋይናንስ ጉዳይ እንዳልተደረገ፣ በዚህም ችግሩ በተለይ ከክፍያና ከስልጠና ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ፒቲሽን አሰባስበው ዩኒቨርሲቲውን ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ገልጸው፤ “ በቢብስብን ነው ወደ ህዝብና ፊትና ሚዲያ የመጣነው ” ብለው የነበረ ሲሆን፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለቅሬታው ምላሽ ተሰጥቶ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ደሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) ምን ማላሽ ሰጡ ?

“ ከዚህ በፊትም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ቅሬታውን አቅርበው ቅሬታውን አክኖሌጅ አድርገን በአሰራር ለውጥ ለማምጣት ከተወሰኑ መምህራን ጋር ውይይት አድርገናል፡፡

እንደተባለው በዩኒቨርደሲቲ ደረጃ ሪፎርም ተደርጓል፡፡ ያ ማለት ከዚህ በፊት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካለው አፈጻጸም አንጻር መዘጋት አለበት ተብሎ፤ ከሚዘጋ ደግሞ ሪሮርም መደረግ አለበት ተብሎ ከፍተኛ የአመራር ለውጥ ተደርጓል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል አለበት የሚል እምነት አለን እኛም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ያለተማሪዎችና ያለመምህራን የሚሰራው ሥራ የለም፡፡

ስለዚህ መምህራን የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ላለመመለስ ሳይሆን ወደ ሚዲያም የወጡበት 'በ72 ሰዓታት ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እርምጃ ካልተወሰደ ከዩኒቨርሲቲ በላይ ላሉት አካላት ሪፖርት እናደርጋለን ' ብለው ነው፡፡ ያንን ደግሞ እኛ መከልክል አንችልም፡፡

ፋይናንስ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጣቸውን በዬጊዜው እንዲያሻሽሉ አድርገናል፡፡

ሪፎርም አልተደረገም ማለት አልችልም ምክንያቱም እኛ ሥራ ስንጀምር የነበረውን ዳይሬክተር (ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ክፍተት አለበት የተባለውን ሰው) አንስተናል ከዛም በፊት፡፡

አሁን እዛው ክፍል የነበረ በቡድን ደረጃ ያለውን በጊዜያዊነት ነው ያስቀመጥነው፡፡ እሱንም ደግሞ ለማንሳት መጀመሪያም ፒቲሽን አቅርበው ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ፒቲሽን በሚያቀርቡበት ጊዜ ያለውን አብረን ተነጋግረናል እንደምናስተካክል፡፡

ትልቁ ችግር በቂ ፋይናንስ ባለመኖሩ ሁሉንም ጥያቄ በአንዴ መመለስ አይቻልም፡፡ ብዙ ሪፎርም ያደረግንባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ 'በ72 ሰዓታት ውስጥ' የሚባለው ግን ፋይናንስ ላይ የሚሰራ ሰው ሰነድ ማስረከብ አለበት፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ክፍተት ነበረ ይህንን ሲያስተባብሩ ከነበሩ መምህራንና በከፍተኛ ማኔጅመንት።

የ10 ዓመት እድሜ ታሪክ ያለው ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ እንዳሉትም ላብራቶሪ በትክክል ሰርቪስ አልተደረገም፡፡ ግን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ ነው ያለው አሁን፡፡ ለመምህራን እውነት ለመናገር ትልቅ አክብተሮት አለን፡፡

የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ስለሚፈልጉ፣ ስለጓጉ ነው እንጂ፡፡ ይህም መብታቸው ነው፡፡ ለምን ይህንን አደረጉ አንልም፡፡ ግን መሻሻል እንዳለበት ከእነርሱ ጋርም ተነጋገረናል፡፡ ግልጽ ነው፡፡ እነርሱ ፒቲሽን አመጡም አላመጡም ያው ሪፎርሙ ይቀጥላል፡፡

ችግሩ ወዲያው የማይቀረፈው በኢትዮጵያ ደረጃ አዲስ የሠራተኛ ምደባ ተደርጓል፡፡ አዲስ ቅጥር ደግሞ በሲቪል ሰርቪስ አይፈቀድም፡፡ ቅጥር ተፈቅዶ ገና በፕሮሲጀር የሚከድበት ነው፡፡ የሰለጠነ ባለሙያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማግኘት ይከብዳል፡፡ ጠይቀናል፤ ሊሳካ አልቻለም፡፡

' በ72 ሰዓት ምላሽ ስጡን ' የሚለውም ቢያልፍ እኛ ወስነን ስለነበረ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ይነሳልን ያሉት ሰው ከዛ ተነስቷል፡፡ ባይሉም እኛ እንደ ከፍተኛ አመራር ይህንን ወስነናል፡፡ መወሰናችንን ደግሞ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁን ያለው እውነታ ይሄ ነው፡፡

በቂ በጀት የለም፡፡ ፍላጎትና በጀት ስለማይመጣጠን ቅድሚያ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ የ2015 ዓ/ም ያልተከፈሉ እዳዎች እንደተባለው የ12ኛ፤ የዊኬንድ፤ የኦቨርሎድ ክፍዎች እየተከባለሉ መጥተው 2016 ዓ/ም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡

ለመምህራን ስልጠና አለመስጠት፣ ወርክሾፕ ላይ ላብራቶሪ አለማሟላት የተፈጠረው የበጀት እጥረት በመኖሩ ነው፡፡ እጥረቱ ደግሞ እንዲፈታ ከፌደራል ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተበነጋርን ነው፡፡

በጀትና የምናቅፀደው እቅድ አለመጣጣም ነው፡፡ አንዱ ያነሱት ቅሬታ 'እዛ ያለው ኃላፊ ይነሳልን' የሚል ነው ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ኮሚዩኒኬት አድርገናል፡፡ መምህራንም አሁን ሥራዎችን እየሰሩ ነው፡፡ እንደተባለው ግን በ72 ሰዓት የተባለውን አንደርስታንድ መደራረግ ያስፈልግ ነበር፡፡

ይህንን ፒቲሽን ከተፈራረሙ በኋላ መምህራንን ለማነጋር እየሄድንብት ያለውን ፕሮሲጀር ለማስረዳት ቀጠሮ ይዘንላቸው እኔ ሌላ ስብሰባ ነበረኝ፤ የአስተዳደርና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲያገኟቸው ወደ አዳራሽ ሲሄዱ አንድም ሰው እዛ አልተገኘም፡፡

ነገር ግን አሁን አዲሱ ሪፎርም ላይ ባለው አመራር 24 ሰዓት በራችን ክፍት ነው፡፡

ከእነርሱ የምንደብቀው ነገር የለም አንድ ላይ ነው የምንሰራው፡፡ ቀጠሮም ይዘንላቸው እዛ ላይ አልተገኙም ” ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ክፍተት እንደነበረበት መረጃዎች መውጣታቸው ይታወሳል፤ ለመሆኑ እርምጃ ተወስዷል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፤ የማስተካከያ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

“ ኮመንት የተደረጉት የፌደራሉ ኦዲት መስሪያ ቤት የአመቱን የኦዲት ሪፖርት ይጠይቃል፡፡ ግኝቶቹ ላይ በቂ ማብራሪያ ወይንም ግብረ መልስ ተሰጥቷል ” ነው ያሉት፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ  ቦርዱ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና አይሰጥም "- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከህወሓት ጉባኤ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለድርጅቱ ደብዳቤ ጽፏል።

ቦርዱ ፥ ነሐሴ 3/2016 ዓ/ም ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፖርቲው በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም እንደሰጠው አስታውሷል።

ፓርቲው የቦርዱ ደብዳቤ እና የምስክር ወረቀት ከደረሰው ቀን ጀምሮ የሚተዳደረው የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ና ይህን አዋጅ ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 እንዲሁም እነዚህን አዋጆች መሰረት ተደርገው በወጡ መመሪያዎችና የቦርዱ ውሳኔዎች መሰረት እንደሆነ አስገንዝቧል።

ቦርዱ ውሳኔ የሰጠባቸውና በደብዳቤ ከገለፃቸው በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች እንደሆኑ አመልክቷል።

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ፖርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ሊያደርግ መሆኑን ቦርዱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየተዘገበ መሆኑ መመልከቱን ገልጿል።

በዚህም ቦርዱ " ለአንድ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲያውቅ ባልተደረገበት፣ ባልተከታተለበትና ባላረጋገጠበት እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎች ባልተገኙበት ተጠራ የተባለው ጠቅላላ ጉባኤ ሊካሄድ አይችልም " ሲል አሳውቋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

#TPLF #NEBE

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ከዛሬ ጀምሮ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ የተቃራኒ ጉዞ ተከልክሏል " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ፣ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ ድረስ በስራ የመውጫ እና የመግቢያ ሰዓቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በጊዜያዊ መፍትሄነት ከአያት አደባባይ እስከ ሴንቸሪ ሞል በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ ተፈቅዶ ነበር።

ነገር ግን መጨናነቁን ይፈጥር የነበረው የሳዕሊተ ምህረት አደባባይ በመቀየሩ ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ይሄን ተገንዝበው የመደበኛ የጉዞ መስመሮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#AddisAbaba #TMA

#TikvahEthiopia
@TikvahEthiopia
#Infinix_Note40_Pro_Plus

የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ካሜራ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን የ 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና ባለ 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ ቴክኖሊጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል ድንቅ አቅም ያለው ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት ጉባኤውን ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል።

የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤  የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ መካሄድ እንዲጀምር ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተቆርጦለታል።

ጉባኤውን አስመልክቶ የተሰራጨው መርሃ ግብር እንደሚጠቁመው ከዛሬ ነሀሴ 7 እስከ 12 / 2016 ዓ.ም ባሉት 6 ቀናት ይከናወናል።

የህወሓት ፅህፈት ቤት እና ማህተም የተቆጣጠረውና በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው ሃይል ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት!" ማለትም " የመዳን ጉባኤ! " በሚል መሪ ቃል ነው የሚያካሂደው።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመሩት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ " ጉባኤው ህወሓት የሚያጠፋ ፣ ለትግራይ ህዝብ ሌላ ችግርና የእርስ በርስ ግጭት የሚጋብዝ አደገኛ ጉባኤ " በማለት በይፋ ባወጡት መግለጫ ተቃውሞውታል።

በእነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ክንፍ ግን በከፍተኛ ተቃውሞ ታጅቦ ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በሚቀጥሉት 6 ተከታታይ ቀናት ጉባኤውን ማካሄድ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፍቃዱ ውጭ ለሚካሄድ ለዚህ ጉባኤ ምንም አይነት እውቅና እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-13

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ : የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጨመረ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
የሌሎችም ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል።

(ንግድ ባንክ)

💵 አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 102.9899 ፤ መሸጫ 113.2889

💷 ስተርሊግ መግዣ ው125.5507 ፤ መሸጫው 138.7004

💶 ዩሮ መግዣ 112.5577 ፤ መሸጫ 123. 8134

🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 321.2233 መግዣ ፤ መሸጫው 354.8592

🇦🇪 የUAE ድርሃ መግዣ 28.0428 ፤ መሸጫው 30.8471

በግል ባንኮች ደግሞ የአንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ከ103 ብር አንስቶ እስከ 119 ብር ደርሷል።

(ዕለታዊ የባንክ ምዛሬ ከላይ ተያይዟል)

(ነሐሴ 7/2016 ዓ/ም

@tikvahethiopia
የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ጉዳይ !

🔵 " ተመዝግበን አሻረ ከሰጠን አመት ሊንሞላ ነው እስካሁን ምንም የለም " - በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች

🟢 " አንድ ሰው ስለተመዘገበ ብቻ ይሄዳል ማለት አይደለም ፤ ለጉዳዩ ተፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች ማሟላት ያስፈልጋል " - ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመዘዋወር በጎ ተግበራት ሲያከናውኑ የቆዩ ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል።

እነዚህ ወጣቶች ከዚህ ቀደም የውጪ የሥራ እድል በሚኖርበት ወቅት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸው እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ወደ ወጪ ለመሄድ ተመዝግበው አሻራ ቢሰጡም እስካሁን የተባሉት ነገር እንደሌለ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ባቀረቡት ቅሬታ፣ " ተመዝግበን አሻረ ከሰጠን አመት ሊንሞላ ነው እስካሁን ምንም የለም " ብለዋል።

" ' ቅድሚያ ለብሄራዊ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰልጣኞች ተብለን ' ከተመዘገብን ቆየን። እናም ከስራ እድል አኳያ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ በብዙ የሀገራችን ወጣቶች ላይ እየተሰተዋለ ይገኛል እባካችሁ በፍጥነት መፍትሄ ስጡን " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ " ምዝገባ ይደረጋል ማስታወቂያ እየወጣ በተለያየ የስራ መስክ። ታዲያ እንዴት ነው ወደ ውጭ የሚኬደው ? የተመዘገበ ሁሉ ይሄዳል ? ውድድር አለው ? " የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የወጣቶቹን ጥያቄ በቀጥታ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አቅርቧል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ምን ምላሽ ሰጡ ?

(ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል)

ኮሚዩኒኬሽኑ ላይ ያልነው ቃል በቃል እደዛ ባይሆንም እንደዛ እንደሚሉ እኛም እናውቃለን፡፡

በሰዓቱ በነበረን ስምሪት የሰጠነው መረጃ ማንም ሰው ሰልጥኖ ብቁ ሆኖ በፍቅር አገሩን አገልግሎ እስከተገኘ ጊዜ ድረስ እንደሚሆን ነው። 

ሰው ስለተመዘገበ ብቻ ይሄዳል ማለትም አይደለም፡፡ ለጉዳዩ ተፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ያስፈልጋል፡፡ 

ለምስሌም ፦ ' የሰለጠነ የሰው ኃይል እንልካለን ' ስንስል አገራቱ በሚፈልጓቸው የሙያ መስኮች የሚላኩ ወጣቶችን ሰርቲፋይ የሚያደርጓቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መኖር አለባቸው፡፡  ዘንድሮ ይህንን ከሚመለከታቸው ጋር ሆነን ማሳካት ተችሏል።

ስለዚህ አንዳንዶቹ የሙያ መስኮች ላይ በዬጊዜው ይፋ እያደረግን ነው ያለው። በቅርብ የሱዊድንና የኖርዌይ ገበያ ጭምሮ ይፋ አድረገናልል፡፡ በርካታ የሙያ መስኮች ላይ የሰለጠኑ ሰዎች ይፈለጋሉ።

የተመዘገቡ ሰዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው በደብን (ኦንላይን የምናዘጋጃቸውን ይዞቶች አሉ፡፡ ተመዝግበው ደግሞ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች አሉ መውሰድ ያለባቸው የሥልጠና የፈተና አይነት) ያሟላ ሰው መሄድ ይችላል።

ስርዓት አልምተናል ፤ ይህም ስርዓት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማስተናገድ የሚችል በቴክኖሎጅ የታገዘ ነው፡፡ የሰው ጣልቃ ገብነት የለውም፡፡ የአክስቴ የአጎቴ የሚባል ነገር የለም። ሪኳየርመንት ያሟላ በሙሉ ይህንን እድል ማግኘት ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ናቸው ማለት ነው፡፡

በ2014 ዓ/ም ላይ 40 ሺሕ ገደማ ሰው ነው የተላከው። የሥራው ባህሪ የሚጋብዝ አልነበረም፣ ምሩቃን ለሆኑ ሴትና ወንድ ወጣቶች፡፡ ቢያንስ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ የተማሩ ሴት ወጣቶችን በአመዛኙ የሚጋብዝ ነው የነበረው።

ሙሉ ንግግራቸውን ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-13-2

🌐 lmis.gov.et 🌐

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM