TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#NewsAlert የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
በስበባውም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን ሁኔታ ተመልክታል።
ምክር ቤቱ ፤ እኤአ ጥር 1 በኢትዮጵያ እና ሰሜናዊ የሶማሊያ ክልል ሲል በጠራት " ሶማሌላንድ " መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከተፈረመ በኃላ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።
ሁኔታው በቀጠናው ሰላም፣ ፀጥታ እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚልም ስጋት እንደገባው አመልክቷል።
ምክር ቤቱ ፦
➡ እኤአ ጥር 3/2024 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የኢትዮጵያን እና የሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት አንድነት፣ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሊከበር እንደሚገባው አፅንኦት የሰጡበትን መግለጫ እንደሚደግፍ አሳውቋል።
➡ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ጨምሮ የሁሉም አባል ሀገራት አንድነት፣ የግዛት አንድነት፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት መጠበቅ እንዳለበት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ በማያሻማ መልኩ አረጋግጧል።
➡ ኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የሁለትዮሽ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነታቸውን የአፍሪካ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ህግ መርሆዎችን ባከበረ መልኩ እንዲመሩ አሳስቧል።
➡ የውጭ አካላት በሁለቱ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን መርህ እንዲያከብሩ አሳስቧል።
➡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ጠንካራ መልካም ጉርብትና፣ ወዳጅነት እና አብሮነት ትስስር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ተጨማሪ እርምጃዎች እና መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አበረታቷል።
➡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትርጉም ያለው ውይይት እንዲያደርጉ እና ውጥረቶችን እንዲያረግቡ ጥሪ አቅርቧል።
➡ ምክር ቤቱ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ውይይት እንዲያመቻቹና በየወቅቱ ለምክር ቤቱ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ብሏል።
➡ ኢጋድ በዩጋንዳ ካምፓላ ለነገ የጠራውን ልዩ የመሪዎች ስብሰባ በደስታ እንደተቀበለው ገልጿል።
ምክር ቤቱ ጉዳዩን በንቃት እንደሚከታተል አሳውቋል።
@tikvahethiopia

🤩የአፍሪካን ምርጦችን በአፍሪካ ዋንጫ🏆
👉አንድም ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ፈጥነው የዲኤስቲቪ ዲኮደር ይግዙ!
👉የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።
የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
@DStvEthiopiaBot
#AFCONonDStv #AFCON2023 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

“ የWHO መረጃ ትክክለኛ አይደለም ” - የአማራ ክልል ጤና ቢሮ
የዓለም ጤና ድርጅት በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ 61 የጤና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ፣ 39 በከፊል እንደወደሙ ሰሞኑን ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ “ትክክለኛ መረጃ አይደለም” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “መረጃው የቆዬ ነው። ከWHO ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የገለጹት ደግሞ የአሁን አድርገው ነው። በጣም የማይገናኝ ነገር ነው” ብለዋል።
“ያኔ በሰሜኑ ጦርነት ከ1,100 ቀላይ ጤና ተቋማት ኤግዛክትሊ የወደሙ አሉ። ፖርሻሊ ደግሞ እንደዚሁ አሉ” ያሉት ኃላፊው፣ “ይኼኛው (‘100 የጤና መሠረተ ልማቶች ወድመዋል’) ተብሎ የወጣው መረጃ ግን በሰሜኑ ጦርነት ጊዜ ሰሜን ጎንደር ላይ ያደረግነው አሰስመንት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፣ “ትክክለኛ መረጃ አይደለም በመጀመሪያ ደረጃ። በጥናት ራሱ እኛ ጋ የወጣ ነው። ግን ደግሞ ይሄ ‘100’ የተባለው ጥናቱ የተካሄደው ሰሜን ጎንደር ዞን ላይ ነው። ሰሜን ጎንደር ዞን ላይ ያሉ ተቋማት በሰሜኑ ጦርነት ጊዜ 100 ተቋማት ዳሜጅ ሆነዋል ነው የሚለው” ብለዋል።
“ይህ አሰስመንት ከኖቬበር 2022 እስከ ዲሴምበር 4/2023 ያለ ጥናት ነው። ይሄ ጥናት ግን ኮምፕሌትሊ አሁን ‘100ዎቹ ወደሙ’ የሚለው በዚያ ልክ ነው እንጂ እነርሱ ባወጡት መረጃ አይደለም” ያሉት አቶ አብዲልከሪም፣ “ጥናቱም የተጠናው ጠለምት፣ ኢስት ጠለምት፣ ዌስት ጠለምት፣ ማይ ጸብሪ፣ አደርቃይ፣ ደባርቅ ዙሪያ ዳባት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
ኃላፊው ባደረጉት ገለጻ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን 5 ሂል ፋሲሊቲ፣ 1 ሆስፒታል፣ 10 ሂል ሴንተር ጤና ጣቢያዎች፣ 45 ጤና ኬላዎች በአጠቃላይ 61 የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ፣ 1 ሆስፒታል፣ 9 ጤና ጣቢያዎች፣ 29 ጤና ኬላዎች በአጠቃላይ 39 የጤና ተቋማት በከፊል እንደወደሙ የሚያስገነዝበውን የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጥናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።
አክለውም፣ “ጥናቱ ይህን ጉዳይ ይህ ‘in north gondar zone a total of 100 health facility were looted and damaged during the northern Ethiopia war conflict’ ነው የሚለው። በቃ ይሄ ነው የወጣው ሪፓርት” ብለዋል።
የዓለሞ የጤና ድርጅት እንዴት አሁን ሊያወጣው እኖደቻለ ባስረዱበት አውድም፣ ሰሜን ጎንደር ላይ የተከሰተውን ድርቅ በተመለከተ አጠቃላይ የመኸር ሁኔታውን አሰስመንት ሲሰራ የጤና ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ የግብርና ተቋማት አብሮ ኢፍራስትራክቸር መታዬት ስላለበት ጥናቱ ውስጥ ኮሽነር እንደነበር፣ በመሆኑም የበፊቱን ዳታ አብሮ ስለታየ እንጂ ሌላ ምንም አይነት የተለየ ውድመት እንዳልሆነ ነው የገለጹት።
የሆነው ሆኖ በክልሉ በመከላከያና በፋኖ ተጣቂዎች መካከል በየወቅቱ በሚደረገው የተኩስ ልውውጥ ታዲያ ምን ያህል ተቋማት ናቸው የወደሙት? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ አብዱልከሪም፣ “ከዚህ ውጪ በተኩስ ልውውጥ ፉሊም ሆነ ፓርሻሊ ዳሜጅ የሆኑ ጤና ተቋማት እስካሁን ባለን መረጃ (ገና ሂደን አላረጋገጥናቸውም) 7 አካባቢ ናቸው። ከእነዚህ ውጭ እኛ የምናቀው መረጃ የለንም እስካሁን” ብለዋል።
በአማራ ክልል በሚስተዋለው ግጭቶ ሳቢያ በክልሉ 61 የጤና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ፣ 39 ደግሞ በከፊል በድምሩ 100 ተቋማት ላይ ውድመት እንደደረሰ የዓለም የጤና ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው ሪፓርት ማስታወቁ ይታወሳል።
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#መምህራን " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን እንዲከፍለን እንጠይቃለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የመምህራንን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፍል ጠየቀ። ማህበሩ ይህን ያለው ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ነው።…
“ የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል መግባባት ላይ ተደርሷል ” - የትግራይ መምህራን ማህበር
የትግራይ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ባካሄደው ውይይት ላቀረባቸው ጥያቄዎች የሚጨበጥና ተስፋ ሰጪ መልስ ማግኘቱን ለሁሉም የወረዳ መምህረን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ማህበሩ ምን አለ ?
- የመምህራን መብትና ጥቅም አስመልክቶ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተቀናጀ መልኩ እየጠየቀ መምጣቱን ማህበሩ ገልጿል።
- የመምህራን መብት እንዲጠበቅ በተለይ በጦርነቱ ምክንያት ሳይከፈል የቀረው የ17 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ አስመልክቶ ታህሳስ 17 / 2016 ዓ.ም በማህበሩ ማኔጅመንት ደረጃ አስቸኳይ ውይይት በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አስታውሷል።
- ከውሳኔዎቹ አንዱ በተለይ የመምህራን ውዝፍ ደመወዝ ጥያቄ እስከ ጥር 15 /2016 ዓ.ም ካልተመለሰ በትግራይ ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ እናካሂዳለን የሚል ነው ፤ ስለዚሁ ጉዳይ የመምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ባጠረ ጊዜ ውስጥ ውይይት እንዲካሄድ የሚልም የውሳኔ ሃሳብ እንደነበር አመልክቷል።
- በተቀመጠው ውሳኔ መሰረት የትግራይ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ጥር 4 / 2016 ዓ.ም ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳና ከትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ውይይት ማካሄዱን የውይይቱ ዋና ነጥቦችም ፦
➡ የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
➡ የ2014 ዓ.ም የ 12 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
➡ ከደደቢት ማይክሮፋይናስ ስለተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ፣
➡ የመምህራን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰርቪስ ስለማግኘት፣ የሚሉ እንደነበሩ አሳውቋል።
- በውይይቱ በተለይ ውዝፍ ደመወዝን በሚመለከት የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት በአጭር ጊዜ #እንደሚከፈል ፣ የ2014 ዓ.ም የ12 ወራት ውዝፍ ደመወዝ መከፈል የሚመለከት ጥያቄ ወደ ፌደራል መንግስት መቅረቡ ፣ ከደደቢት ማይክሮፋይናንሰ የተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ ፣ የከተማ የመምህራን ሰርቪስ የሚመለከት ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንደሚመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።
- በአጠቃላይ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የተደረገው ግንኙነት ገንቢ እንደነበረ ፣ አቅጣጫ የተቀመጠላቸው ጉዳዮች አፈፃፀማቸው የሚመለከት ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ መተማመን ላይ መደረሱን ማህበሩ ገልጿል።
መረጃውን ማህበሩ ለሁሉም የትግራይ ወረዳ መምህራን ማህበር ጥር 7 / 2016 ዓ.ም ፅፎ የላከውን ሰርኩላር ደብዳቤ ዋቢ በማድረግ ያደረሰን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#IGAD
ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል።
ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው።
ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው።
ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦
➡ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ
➡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐሙድ
➡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት
➡ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ መሃመድ ሃምዳን ደጋሉ ካምፓላ ይገኛሉ።
#Sudan : የሱዳንን ብሔራዊ ጦር የሚመራው የሱዳን መንግሥት ኢጋድ የተፋላሚውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ በስብሰባው እንዲሳተፉ መጋበዙ ‘የሃገሪቱን ሉላዊነት ጥሷል’ በሚል ውንጀላ ከኢጋድ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጧል።
የኢጋድ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇰🇪 ኬንያ
🇺🇬 ኡጋንዳ
🇸🇩 ሱዳን
🇩🇯 ጅቡቲ
🇪🇷 ኤርትራ
🇸🇸 ደቡብ ሱዳን
🇸🇴 ሶማሊያ ናቸው።

#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ ➡ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ ➡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#USA #IGAD
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ካምፓላ እና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል።
ማይክ ሐመር መጀመሪያ ካምፓላ ገብተው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ እንዲሁም በሱዳን ጦርነት ላይ በሚመክረው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ።
ከዛም ወደ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አባባ ይመጣሉ።
ልዩ መልዕክተኛው በአዲስ አበባ ቆይታቸው፦
" - ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በተለይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ስላለው ግጭት ውይይት ያደርጋሉ።
- በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ።
- ሰላማዊ ሰዎች እንዲጠበቁ እንዲሁም ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥሪ ያቀርባሉ።
- ከአንድ ዓመት በፊት በስምምነት የተቋጨውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ የሚከናወነውን ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ተሃድሶ እና ማሰናበትን በተመለከተ እንዲሁም ተጎጂዎችን መሠረት ስላደረገው የሽግግር ፍትህ ሂደት ይወያያወሉ። " ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ቢቢሲ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን ዋቢ አደርጎ ካሰራጨው ዘገባ ነው የወሰደው።

" ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች " - አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።
የአረብ ሊግ መግለጫ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለዋል።
" ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት። " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው " ሆኖም ግን የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።
የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
በዚህም ስበሰባ ፤በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልፅ የጣሰ በሚል አውግዟል። ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚፃረር ነው በሚል ተቃውሟል። የአረብ አፍሪካና የዓልም አቀፍ መርሆች ላይ በግልፅ የተሰነዘረ ጥቃት ነውም ብሏል።
የዚሁ የአረብ ሊግ አባሏ ግብፅ ኢትዮጵያ በአካባቢው #የአለመረጋጋት ምንጭ አይሆነች ነው ማለቷም ተሰምቷል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ልታገኝ የሚያስችላት የኢትዮ ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግስት በቅድሚያ ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ናት። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ጉዳዩን አስመልክቶ ቀድመው ስልክም የደወደሉት ወደ ግብፅ ነበር።
ኢትዮጵያ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ህግን እንዳልጣሰና የትኛውንም ሀገር/አካል የሚጎዳ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ አሳውቃለች።
ሶማሌላንድ በበኩሏ፤ ከሶማሊያ ከተነጠለች ሶስት አስርት ዓመታት ማለፉንና ሉዓላዊት ነፃ ሀገር መሆኗን አመልክታ የትኛውንም ዓለም አቀፍ ስምምነት ለመፈረም ከሶማሊያ ፍቃድ መጠየቅ እንደማይጠበቅባትና ሶማሊያንም እንደማይመለከት አሳውቃለች። ስምምነቱ ሌሎች ሀገራት ከሚፈፅሙት የሊዝ ስምምነት ምንም የተለየ ነገር እንደሌለውም አሳውቃለች።
(ከላይ የተያያዘው የአረብ ሊግ አቋም ነው)

#FDREDefenseForce
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ምን አሉ ?
" ለኢትዮጵያ ዕድገት እንቅፋት ለመፍጠር የሚጥሩ በአካባቢያችን ያሉ #ታሪካዊ_ጠላቶቻችን እና #አዳዲስ_ኃይሎች እየተሰባሰቡ እንዳለ እያየን ነው።
እነኝህ ጠላቶች ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ በቅርበት እየተከታተልን እንገኛለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንንም ሃገር ብሔራዊ ጥቅም መንካት ተገቢ አለመሆኑን በማመን በዘመኗ የሌላ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ነክታ አታውቅም አሁንም አትነካም ታሪኳም አይደለም።
የሌላን ሀገር ብሔራዊ ጥቅም እንደማንነካው ሁሉ እኛም የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም።
ለሃገራችን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ዘብ እንቆማለን። "
ጄነራሉ ይህን የተናገሩት " አዋሽ አርባ " የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሜካናይዝድ ጦርን እና እየወሰደ ያለውን ስልጠና ከጎበኙ በኃላ ነው።
ሰልጣኞቹ በስነ-ልቦና ዝግጁነት ብቁ በመሆን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እና ክብር መረጋገጥ ሲባል የሚወስዱትን ሙያዊ ስልጠና በፍጥነት ማጠናቀቅና ለሚሰጣቸው #ማንኛውም_ግዳጅ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው #አፅንኦት ሰጥተዋል።

#CBE
በርካታ አማራጮች...
***
ለጥምቀት በዓል ከውጭ ሀገር በመረጡት
ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ገንዘብ ያስልኩ!
መልካም የጥምቀት በዓል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial