TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች " - አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።

የአረብ ሊግ መግለጫ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት። " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው " ሆኖም ግን የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።

የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

በዚህም ስበሰባ ፤በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልፅ የጣሰ በሚል አውግዟል። ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚፃረር ነው በሚል ተቃውሟል። የአረብ አፍሪካና የዓልም አቀፍ መርሆች ላይ በግልፅ የተሰነዘረ ጥቃት ነውም ብሏል።

የዚሁ የአረብ ሊግ አባሏ ግብፅ ኢትዮጵያ በአካባቢው #የአለመረጋጋት ምንጭ አይሆነች ነው ማለቷም ተሰምቷል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ልታገኝ የሚያስችላት የኢትዮ ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግስት በቅድሚያ ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ናት። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ጉዳዩን አስመልክቶ ቀድመው ስልክም የደወደሉት ወደ ግብፅ ነበር።

ኢትዮጵያ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ህግን እንዳልጣሰና የትኛውንም ሀገር/አካል የሚጎዳ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ አሳውቃለች።

ሶማሌላንድ በበኩሏ፤ ከሶማሊያ ከተነጠለች ሶስት አስርት ዓመታት ማለፉንና ሉዓላዊት ነፃ ሀገር መሆኗን አመልክታ የትኛውንም ዓለም አቀፍ ስምምነት ለመፈረም ከሶማሊያ ፍቃድ መጠየቅ እንደማይጠበቅባትና ሶማሊያንም እንደማይመለከት አሳውቃለች። ስምምነቱ ሌሎች ሀገራት ከሚፈፅሙት የሊዝ ስምምነት ምንም የተለየ ነገር እንደሌለውም አሳውቃለች።

(ከላይ የተያያዘው የአረብ ሊግ አቋም ነው)

@tikvahethiopia