TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ፦ ዛሬ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
* የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማኅማትን፤
* የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን
* የዲፕሎማቲክ ልዑካን ቡድኖች አባላትን በ "ወንጪ ዳንዲ ኤኮ ቱሪዝም መንደር" መቀበላቸውን የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የAU እና ኢጋድ መሪዎችን እና ዲፕሎማቶችን ከመቀበል ባለፈ ውይይቶችን አድርገው እንደሆነ የተባለ ነገር የለም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ከተጋሩ በኃላ በቀጠናው ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል።

#Ethiopia #Africa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ዛሬ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር። ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ " በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች " ብለዋል። ቤተክርስቲያን…
#EOTC

" ኮብልለው አልሄዱም፣ ኮብላይም አይደሉም ! "

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶክተር) ኮብልለው አልሄዱም፣ ኮብላይም አይደሉም። ለእውነት እና ለፅድቅ ለቤተክርስቲያናቸው አንገታቸውን ከሚሰጡ አባቶች አንዱ እንጂ የሚሸሹ የሚኮበልሉ ፣ የሚደበቁ የወንጀል ሰው ሊሆኑ አይችሉም። አይደሉምም።

- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በቅዱስ ፓትርያርኩ ፍቃድ፣ እንደ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አውቆት ለአገልግሎት ቤተክርስቲያን ሊባርኩ ታቦታት ይዘው አስፈቅደው ሰሜን አሜሪካ ሄደዋል። ይሄ ደግሞ ዛሬ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው ነው የሚሄዱት።

- ቆም ብላችሁ አድምጡ ! እናተ ለፖለቲካችሁ ብዙ እንደምትሉ ብዙ እንደምታስቡ ሁሉ እኛም ለሰማያዊ መንግሥታችን እንቆማለን ፤ ለምድራዊ መንግሥታችን እንገዛለን በሃይማኖት እስካልመጣብን ድረስ በሃይማኖት ከመጣ ግን መገዛት አይደለም አትገዙ ብለን እናውጃለን። ግን ግድሉ አንልም፣ ተገዳደሉ አንልም፤ ቤተክርስቲያን ቃሏ ስላልሆነ። አትገዙ ግን ትላለች አሁን ግን እዚህ አልደረስንም። ቤተክርስቲያን እያስተማረች ያለችው ሰላምን፣ ፍቅርን ብቻና ብቻ ነው።

- ያለ ስም ስም መስጠት ይሄ ማህበራዊ ሚዲያ በሚባለው ንፋስ ፣ ምንም ጭብጥ በሌለው ሃይማኖታዊውን ሰው ሃይማኖታዊ አይደለም፤ ለቤተክርስቲያን የሚሰራውን ፣ለሀገር የቆመውን ኮበለለ ፣ ከዳ የሚባል ደካማ አስተሳሰብ የቤተክርስቲያን ህልውና አያናግም።

- " ደግሞ ሰምተናል አባ ጴጥሮስ ፣ አባ አብርሃም ... ተለውጠዋል ዝም ብለዋል አድር ባይ ሆነዋል የሚለውን ፤ ከሃይማኖት ውጭ ሌላ ማደሪያ የለንም። ለኛ ማደሪያችን መዋያችን ሃይማኖታችን ናት "

- ለመንግስትን እንደ መንግስት እንድንገዛው መፅሀፍ ቅዱስ ያስገድደናልም በሃይማኖታችን እስካለመጣ ድረስ ሃይማኖታችንም ለመንግስት እንድንገዛ ያስገድደናል።

- ከዚህ ውጭ ከውስጥ የምንሰራውን በይፋ እንዲህ ነው ብለን አናወራም በሚል ዝም ብለናል።

- የወሬ ገበያ ያለው ሰው ሁሉ የወሬ ገበያው እንዲደራ ዛሬ አባ አብርሃም ፣ አባ ጵጥሮስ አልተናገሩም በሚል ሌላ ስም ልስጥ ቢል የሱ ወሬ እንጂ የኛ አይደለም።

- አባ ጴጥሮስ ሆኑ አባ አብርሃም ስራቸውን የሚሰሩት በሃይማኖታቸው መሰረት ብቻ ነው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

- በዓለ ጥምቀቱን ለማክብረ በመንግሥት ዘንድ ቤተክርስቲያን ይሄን ትበል ፣ አለበለዚያ እንዲህ አይደለም የሚሉ መልዕክቶች ደርሰውናል።

- ቤተክርስቲያን ሰላሟን ታውጃለች።

- አሉ አሉ እየተባሉ ስለተነገሩ ንግግሮች እና ግለሰቦች፣ ጳጳሳት እና ሊቃነጳጳሳት ከሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ታያለች፣ ትመክራለች ታስተምራለች። ህግ አላት በህጓ መሰረት ትገስፃላች። ከዚህ ውጭ ሱሪ በአንገት አውጣው የሚባል ነገር ቤተክርስቲያን አትሸከምም አትቀበለም።

- ሰላሟን እያወጀች፣ ሰላሟን እየሰበከች በሰላም መንገድ ትጓዛለች።

- ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን መሞትን ስራዬ ብላው ይዛ ኖራለች ወደፊትም ሞት ከሆነ በሰላም ለመቀበል ዝግጁ ናት።

- " ይሄን ካደረግሽልኝ ይሄን አደርግልሻለሁ " የሚል መደራደሪያ የላትም ፣ ሊኖራትም አይችልም። ድርድሯ ሰላምና ሰላም ብቻ ነው።

- እኔ ያልኩሽን አድርጊ የሚል በቀኝም ይሁን በግራ ፤ ከገዢውም ክፍል ይሁን እገዛለሁ የሚል ሃሳብ ቢመጣ ያን ተቀብላ የማስተናገድ አቅምም ብቃትም የላትም።

- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ በዓሉ ዓለም አቀፍ ስለሆነ የተለያየ እምነት ያላችሁ ልጆች ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ሆናችሁ በዓሉ በዓላችን ነው የምትሉ፣ የምትደግፉ በዓሉን እራሳችሁ አክባሪዎች ፣እራሳችሁ የፀጥታው አስተናጋጆች የሰላም መሪዎች ሆናችሁ በዓሉ በሞቀና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ቤተክርስቲያን መልዕክት ታስተላልፋለች።

- የፀጥታ አካላት ትላንት እንዲህ ተብያለሁ ይሄ እንደገና በተቃውሞ ካልታወጀልኝ በስተቀር ይሄን አላደርግም የሚለውን አስተሳሰብ ትቶ ህግን በህግ ስርዓትን በስርዓት ለመፈፀም አእምሮውን አስፍቶ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

- ሌላው ሌላው ችግር በመድረክ ዙሪያ፣ ማነው ጥፋተኛ ? ምን አስቦ ነው ? ምን ብሎ ነው ? የሚለውን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመክርበት የሚዘክርበት፣  የሚገሰፀውን የሚገስፅበት ፣ ከቀኖና የወጣውን ከቀኖና ወጥተሃል የሚልበት የራሱ ስርዓት ስላለው ለህጉ እንተወዋለን።

- " ይሄን በሉ ይሄን አድርገ፣ ይሄን ካላደረጋችሁ ይሄን አናደርግም " የሚባል መያዣ ነገር ቤተክርስቲያን አስተናግዳ አታውቅም ፤ ወደፊትም አታስተናግድም።

- እገሌ እገሌ ባልልም ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ናት በዓሉም የህዝብ ነው ይሄን መያዣ አናድረግም ችግሩ ችግር ሳይሆን እንዲፈታ ይደረግ በመልካም ነገር በዓሉን በሰላም እናክብር ብለው የተናገሩ መሪዎች አሉ በዚህ አጋጣሚ ሊደነቁ ይገባል። ከመሪዎች የሚጠበቀው ይሄ ነው። ችግርን እንዴት እንፍታው ችግርን እንዴት እናስወግደው ፣ ሰላም እንዴት እናስፍን ነው መባል ያለበት።

- በየሄድንበት " ደግሞ ለኦርቶዶክስ፣ ለተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ቃሉም ይከብዳል በየቢሮው ስንሄድ ቢያንስ አይሆንም አይባልም " ያንን ያንን ያርሙ " ይላሉ።

- " ኦርቶዶክስ ሃገር ናት ፣ ለሀገር ዋልታ ናት፣ ምሰሶ ናት አምድ ናት ይሄን ታሪክ አይክደውም። ዘመን ቢያስረጃትም ዘመን ቢጥላትም ዘመን ያነሳታል።

- ዛሬም ሲደረግላት እያመሰገነች ነው። ለሀገር ሰላም ማድረግ ያለባትን እያደረገች ነው ፤ በየመስሪያ ቤቱ ስንሄድ " ደግሞ ለኦርቶዶክስ " የሚለው ቃል ሊታረም ይገባል።

- ቤተክርስቲያን ትከበር ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥም #በሃይማኖት_ስም እንደፈለገ የሚዋኙ ሰዎች ቆም ብለው ያዳምጡ፣ የሚናገሩትንም ይመርምሩ ፣ ሃይማኖታዊ ቃል ነው አይደለም ይበሉ ከሃይማኖታዊ ቃል ውጭ የሆነው ሁሉ የእኛ #አይደለም

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ? - በዓለ ጥምቀቱን ለማክብረ በመንግሥት ዘንድ ቤተክርስቲያን ይሄን ትበል ፣ አለበለዚያ እንዲህ አይደለም የሚሉ መልዕክቶች ደርሰውናል። - ቤተክርስቲያን ሰላሟን ታውጃለች። - አሉ አሉ እየተባሉ ስለተነገሩ ንግግሮች እና ግለሰቦች፣ ጳጳሳት እና ሊቃነጳጳሳት ከሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ታያለች፣ ትመክራለች ታስተምራለች። ህግ አላት በህጓ መሰረት ትገስፃላች። ከዚህ…
#EOTC

" ሀገራችን ሰላም ትሁን፤ የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው " - ብፁዕነታቸው

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምን አሉ ?

- የማይደፈር ሲደፈር አይተናል፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም።

- " ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ህይወቴም ማንነቴም ክብሬም ቤተክርስቲያኔ ስለሆናች እሷ ስትደፈር ዝም አልልም። እናገራለሁ፤ የመጣውን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ "

- ከዚህ በፊት ለመንግሥት ችግር ካለ እዚህ ጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ንገሩን ብለናቸዋል። እኛ እናርማለን፣ እኛው እናስተካክላለን፣ አላስፈላጊ እርምጃ አትውሰዱ ብለናቸዋል። ትላንት ግን ከቤተክህነት የሚወጣው በሙሉ ይፈተሻል ዛሬም፣ የሚወጣ መኪና በሙሉ ይፋተሻል፤ የሚገባው ግን አይፈተሽም። የሚገባውን የኛ ዘበኞች ይፈትሹ ይሆናል፤ የመንግሥት ወታደሮች ግን አይፈትሹም። አንዱ ሌላ ነገር ይዞ ገብቶ ሲወጣ ፈታሹ ሌላ ነገር ይዞ ተብሎ የቤተክርስቲያን ስም እና ክብር ቢዋረድ ማነው ኃላፊው?

- ምንድነው የተፈለገው? ከቤተክርስቲያን ምንድነው የሚወጣው? መድፍ ነው? መሳሪያ ነው? አከፋፋይ ናት ቤተክርስቲያኒቱ? አትታመንም? መንግሥትን ያስጮኸ ነገር አለ እኛም የጮህንበት ከመንግስት በፊት፤ ግለሰቦችን ስለተናገሩት ንግግር የማይባል ተብሏል እያልን እኛ ነን የጮህን ይሄ የቤተክርስቲያን ቋንቋ አይደለም ብለን ነበር፤ መግለጫ ለመስጠት ተዘጋጅተን ነበር መንገዱን ስናየው መጠላለፊያ እንጂ ከፅድቅ ስላልሆነ ነው ዝም ያለነው። የፅድቅ ሲሆን ገፍተን ነው የምንወጣው።

- ከቤተክህነት ምንድነው የሚወጣው ? ከተፈለገ መባል ያለበት ጥርጣሬ አለን ቤተክህነት ውስጥ ይባላል፤ እንዲህ አይነት ነገር ቢወጣ ኃላፊነቱ የናተ ነው ጠብቁ ነው ልንባል የሚገባው ወይም ሰው እንሥጣችሁ የሚያንሳችሁ ከሆነ ቤተክርስቲያኒቱን እንዳያስወቅስ ነው መባል ያለበት እንጂ ቤተክርስቲያን የማትታመን ሆነ ከትላንት ጀምሮ እስካሁን እኛ መሪዎቹ በማናውቀው ፈታሽ በር ላይ ቆሞ መፈተሽ ድፍረት ነው። ቤተክርስቲያኒቱን ህልውናዋን መፈታተን ነው። አቅሟንም መፈትን ነው ተገቢ አይደለም።

- መደፋፈሩ በዝቷል፤ መንግስትም ቤተክርስቲያኒቱን ይደፍራል አልፎ ይሄዳል።

- እንደ ግለሰብ በስሜት የሚናገሩ ሰዎች ይኖራሉ። ቤተክርስቲያኒቱን መድፈር አዳጋ ነው። ለሃይማኖቱ የማይሞት የለም፣ ከዚህ በፊት ብዙዎች ሞተዋል፤ ተከባብረን እንኑር ለሰላም እንኑር።

- ካህን ነው ሲሉት ሌላ ነጭ ለባሽ ይሆናል፣ ነጭ ለባሽ ነው ሲሉት ካህን ሆኖ ይገኛል፤ የቤተክርስቲያን መሪ ነው ሲሉት የፖለቲካ መሪ ሆኖ ይገኛል፤ የፖለቲካ መሪ ሲሉት ቀዳሽ ሆኖ ይገኛል ምን አመጣው ይሄን ቀጥ ብለን እንቁም። ደሃ ሲበደል ተበደለ እንበል ሲታሰር ፍቱ እንበል፤ እያልን ነው እኮ፤ መንግሥትን ፍቱ እያልን እንመካከራለን ይፈታል ለዚህ ደግሞ እናመሰግናለን።

- በሃይማኖት ጉዳይ አንደራደርም።

- ካህን ካህን ይሁን፣ ወታደርም ወታደር ይሁን ሌላውም እራሱን ይሁን በሚያስተሳስረን ነገር ተሳስረን ጥላቻና ሁከትን፣ ሽብርና አላስፈላጊ ነገርን እናርቅ።

- ካላስፈላጊ #ጎጠኝነት#ዘረኝነት እንራቅ።

- ሀገራችን ሰላም ትሁን የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው። አላስፈላጊ ሙገሳንም እንርሳው። ካላስፈላጊ ሙገሳ አስፈላጊ በሆነ ወቀሳና ለመጨረሻው መከራ እራሳችንን እናዘጋጅ።

ያንብቡ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-12-2

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
7 ዓመታትን ያለ ኤሌክትሪክ . . . ለ7 ዓመታት ኤሌክትሪክ በተቋረጠበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፤ ካማሽ ዞን ነዋሪዎች " የከፋ ችግር ላይ " ስለመሆናቸው ቪኦኤ ሬድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። አቶ ለማ ሮሮ የተባሉ የካማሽ ዞን፤ ካማሽ ከተማ ነዋሪ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳላገኙ  ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ እንዲጀምር ጥረት ቢደረግም ማታ ማታ ታጣቂዎች መስመሮች…
መብራት ከ7 አመት በኃላ ያገኘችው ካማሺ ...

" #በመከላከያ እጀባ እና ከክልል የፀጥታ ኃይል ጋር በመተባበር የመብራት ኃይል ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ነው የተሰራው አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም " - የካማሺ ዞን ኮሚኒኬሽን

የካማሺ ዞን አካባቢዎች ከ7 ዓመታት በኃላ መብራት አገኙ።

ቃላቸውን ለቪኦኤ የሰጡ የካሚሺ ከተማ ነዋሪዎች ፤ የመብራት አገልግሎት ባለፉት ሳምንታት ዳግም መጀመሩን ገልጸዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ " መብራት ለ7 ዓመታት ተቋርጦ ቆቷል። ከ7 ዓመት በኃላ ማህበረሰቡም በመታገል ከመንግስት ጋር በመተባበር አሁን መብራት ወደ ከተማችን ገብቷል ፤ አብዛኛው ቤትም መብራት አለ " ብለዋል።

ማህበረሰቡ ከዓመታ ጨለማ ወደ ብርሃን ሲመጣ ደስ ብሎታል ሲሉ አክለዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ደግሞ ማህበረሰቡ በመብራት እጦት ክፉኛ  ሲቸገር እንደነበር አስታውሰው አአገልግሎቱ በመጀመሩ ደስ መሰኘታቸውን ገልጸዋል። ወደ ሌሎች የካማሺ ዞን ወረዳዎች እንዲዳረስ ጥሪ አቅርበዋል።

የዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ በካማሺ ከተማ የመብራት አገልግሎት ባለፈው ሳምንት መጀመሩን ገልጸው ፤ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች እንዲዳረስ እየተሰራ ነው ብሏል።

መብራት ለ7 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ፤ ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወደ ዞኑ ይመጣ የነበረው መስመር በመቆረጡና እሱን ለማስተካከል በኦሮሚያ የነበረው የፀጥታ ችግር እንቅፋት በመሆኑ እንደሆነ አስረድቷል።

ኮሚኒኬሽን ቢሮው ፤ " የፀጥታ ችግሩ አሁንም አልፈታም ፤ በችግሩ ውስጥ ነው ማስተካከል የተቻለው በመከላከያ እጀባ እና ከክልል የፀጥታ ኃይል ጋር በመተባበር የማብራት ኃይል ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ነው የተሰራው አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም ፣ ሲል ገልጿል።

የመብራት ኃይል ጊምቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በበኩሉ ፤ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተደርጎ ህብረተሰቡ ልማቱን ለመጠበቅ ቃል ስለገባ ባለፈው አንድ ወር አስፈላጊው ነገር ተሟልቶ በካማሺ ከተማ ከታህሳስ 21 ጀምሮ አገልግሎት ጀምሯል ሲል አሳውቋል።

በ2010 በካማሺ ተዘግቶ የነበረው መ/ቤት አሁን ተከፍቶ ሰራተኞች ተመልሰው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አሳውቋል። #ቪኦኤአማርኛ

@tikvahethiopia
የሳፋሪኮምን ያልተገደበ ኢንተርኔት ጥቅልን በቅናሽ በM-PESA ሳፋሪኮም App ላይ ብቻ ያገኙታል::


🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ህጋዊ የቤት መሸጥና ማዘዋወር አገልግሎት ከህዳር 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደገና መጀመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ያረፈበት መመሪያ ያስረዳል። መሬታ በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ አገልግሎትም አርብ ህዳር 28/2016 ዓ.ም በይፋ መጀመሩንና የመቐለ ከተማ አስተዳደር 300 ቦታዎቸ በሊዝ ጨረታ ለፈላጊዎች ማቅረቡ ቲክቫህ…
#መቐለ

በመቐለ የተካሄደው የመሬት ሊዝ ጨረታ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል።

የመቐለ ከተማ የመሬት ይዞታና አስተዳደር  ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 2/2016 ዓ/ም እንደሚቆይ ጠቅሶ ይፋ ባወጣው የሊዝ መሬታ ጨረታ አሸናፊዎች እንደሚያሳየው ለአንድ ካሬ ሜትር (1ሜ × 1ሜ) መሬት እስከ ብር 131 ሺህ የተሞላ ሰነድ ተገኝቷል።

ለንግድ ቦታ በካሬ ሜትር እስከ 80 ሺህ ፣ ለመኖሪያ ቦታ ደግሞ አስከ 70 ሺህ ብር ተጫርተው ያሸነፉ ስማቸው ይፋ ተደርጎ ውል እንዲያስሩ የሶስት ቀናት እድል የተሰጣቸው በርካታ ናቸው።

እጅግ የተጋነነው የሊዝ መሬታ የጨረታ ውጤት ተከትሎ ከህዝብ የሰላ ትችት እየቀረበ ነው።

" መሬት የተዘረፈ የህዝብ ገንዘብ መደበቂያ መሆኑ ቀጥለዋል " ከሚል እስከ " መሬት በነጋዴዎችና በፓለቲከኞች እንዲወረር ማመቻቸትና መፍቀድ ስህተት ነው የፍትህ ፀሐይ ስትወጣ የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " የሚሉ መረር ከረር ያሉ ነቀፌታዎች እየተነበቡና እየተደመጡ ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በደም አፋሳሹና አስከፊው ጦርነት ምክንያት ከሶስት ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረው መሬት በሊዝና በሽያጭ የማስተላለፍ ስርዓት በመቐለ ጀምሮ ወደ ሌሎች የትግራይ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።

" በመቐለ ከ15 ዓመታት በፊት በሊዝ የተወሰደው መሬት እስከ አሁን አልለማም " የሚለው ጎይትኦም የተባለ የአክሱም ነዋሪ " በአክሱም ከተማ በሊዝ ጨረታ ለካሬ ሜትር የንግድ መሬት በ65  እና በ78 ሺህ ብር ያሸነፉ ሰዎች ስማቸው ተለጥፎ አንብቤያለሁ ፤ በመንግስት ለአንድ ካሬ ሜትር እስከ 3 ሺህ ብር የጨረታ መነሻ  የተቀመጠለት በምን ስሌት ነው በ20 እጥፍ  አድጎ በሊዝ የተሸጠው ? " ብሎ ጠይቋል።

" በዚሁ አስደንጋጭ አካሄድ ከቀጠለ የከተማ መሬት የጥቂቶች መፈንጫ ሊሆን ነው " በማለት ስጋቱ የሚያጋራው ዶ/ር ጨርቆስ የተባለ የመቐለ ነዋሪ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠው አብዛኛው ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርገው 70 ካሬ የተባለው የመሬት እድላ በአስቸኳይ እንዲጀምር " የሚል የመፍትሄ ሃሳብ አቅርቧል።

በተያያዘ በተለያዩ ጊዚያት መሬት በሊዝ ወስደው አመታዊ ክፍያ ያልከፈሉ በተያዘው የጥር ወር ውስጥ እንዲከፍሉ የመቐለ ማዘጋጃ ቤት ጥሪ አቅርቧል።

በማዘጋጃ ቤቱ የገቢ የሰራ ሂደት አስተባባሪ ሙሉጌታ ገብረየሱስ እንዳሉት ፤ በተለያዩ ጊዚያት ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል የቅድመ ክፍያ በመክፈል የወሰዱት መሬት  ያልከፈሉት ዓመታዊ ክፍያ በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ውዙፍ ገንዘብ እንዳለ መግለፃቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                
@tikvahethiopia            
#GlobalBankEthiopia

በቴሌግራም ገፃችን ግምትዎን ይስጡ!

ለቀዳሚ 5 ትክክለኛ ግምት ለሰጡ ተከታዮቻችን ሽልማቱን የምንሰጥ ይሆናል፡፡

ጨዋታው ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት ግምት መስጫውን ስለምንዘጋው ያላመኑበትን ውጤት ማስተካከል ይችላሉ፣ ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ግን ለሽልማት ብቁ ያደርግም፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

https://t.iss.one/Globalbankethiopia123

#OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #muvstot #manunited #tottenham
#ኢትዮጵያ

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " በተለይ ሀሰተኛ የሰነድ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል " ብለዋል።

" ኦዲት በማድረግ ሂደት ውስጥ የጎደሉ ካርዶች መኖራቸውን፣ ብዙ ካርድ ባይሆንም አንድ ባለሙያ ሦስት፣ አራት ካርዶች ሲጎድሉበት አይተናል” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይሄ ከፍተኛ የሆነ ከባድ ጥፋት ነው። ወደ ወንጀል የሚያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ " ሌላው ደግሞ በኦዲት ግኝት ውስጥ ‘የዲጂታል መታወቂያ ኦዲት አይደረግም’ የሚል አስተሳሰብ ነው ያለው። ነገር ግን በእኛ ተቋም ዲጂታል መታወቂያ ኦዲት ይደረጋል። ዘጠኝ የሚሆኑ ባለሙያዎች የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ለግለሰቦች ለመስጠት ባደረጉት ጥረት ነው ኦዲት ግኝቱ ይዞ የወጣው " ብለዋል።

" ከዚያ ባሻገር የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና የሥራ ክፍል ደግሞ በርካታ ሥራዎች ይሰራሉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዱት አቶ ዮናስ፣ " አገልግሎቱን በገንዘብ ለመሸጥ ሲደራደሩ የነበሩ ባለሙያዎችን፣ ደላሎችን በቁጥጥር ስር አውለናል። በተለይ ሀሰተኛ የሰነድ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል " ነው ያሉት።

ተቋሙ ሀሰተኛ መረጃን ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ገልጸው፣ " በዚያ ሂደት ውስጥ ባደረግናቸው ክትትሎች፣ በሰራናቸው ኦፕሬሽኖች ሰዎቹን ለመያዝ ችለናል። ስለዚህ በወንጀል የሚጠየቁት የኦዲት ግኝት የተገኘባቸው፣ ካርዶች የጎደሉባቸው፣ ከአሰራሩ ውጪ አገልግሎት የሰጡ ናቸው " ብለዋል።

አክለውም፣ " ከዚያ ባሻገር አመራርም ደግሞ እኛ ጋ በተቋም ግንባታችን ውስጥ መጠየቅ አለበት የሚል አቋም አለን። በዚህ መሠረት ሥራቸውን በአግባቡ ያልመሩ አመራሮች ወደ 10 የሚሆኑ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን። በፓለቲካ አድሚኒስትሬሽን ውሳኔ ነው የሚሆነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ከላይ ያሉትን ማብራሪያዎች የሰጡት ተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ የላኩትን መረጃ ተከትሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ነው።

ዋና ዳይሬክተሩ የተቋሙን የ6 ወራት አፈጻጸም በተመለከተ በላኩት መረጃ መሠረት፦
 
*የኦዲት ክትትል የተደረጉት ዋና መስርያ ቤትን ጨምሮ 11 ክ/ከተማ እና 22 የወረዳ ጽ/ቤቶች ነው።

*ተጠያቂነቱ በ2015 ዓ.ም በተሰጠው አገልግሎት ላይ የተሰራጩ የካርዶችና ሰርተፍኬቶች የቤት ለቤት አገልግሎትን ጨምሮና የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባለመከተል፣ አሰራርን በመጣስ ፣ ጉድለት በመፍጠር፣ ስራን በአግባቡ ባለመምራት እና ጉድለት በመፍጠር ላይ ያተኮረ ነው። 

*ተጠያቂ የሆኑ በጠቅላላው 63 ሰዎች ናቸው። 12 በወንጀል እና 41 በዲሲፕሊን የተጠየቁ ናቸው። ቀሪ 10 የጽ/ቤት አመራሮች ስራን በአግባቡ ባለመምራት ተጠያቂ የሚሆኑ ይሆናል። 

*አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ከ47 ባለሙያዎች መካከል 34 በከባድ እና ቀላል ዲሲፕሊን፣ 9 ባለሙያዎች በወንጀል ተከሰዋል። ከዚህ ውስጥ 6 ሰራተኞች የሌላ ተቋም ሰራተኛ የሆኑ ሠራተኞችን ጨምሮ እስከ 25 ሺህ ብር ጉቦ ለመጠየቅ ሲሞክሩ በተሰራ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እጅ ከፍንጅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

*አንድ ግለሰብ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሀሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ሲያደርግ ከሚያዘጋጅበት መሳርያዎች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል። 

*4 በወረዳ ጽ/ቤት፣ 34 በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት በድምሩ 36 ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው የተገኙ ተገልጋዮች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ከዚህም ውስጥ 3ቱ ፍርድ ተሰጥቷቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ምንም ያህል #ጫና ቢደረግ የህዳሴውን ግድብ እንዳሳካነው የባህር በሩም በተመሳሳይ ይሳካል አሉ። አምባሳደር ሬድዋን፤ " የህዳሴውን ግድብ ያሳካነው ተጨብጭቦልን ሳይሆን ከቅርብም ከሩቅም እየተላጋን፣ የሥጋት ከበሮ እየተደለቀ፣  ዛቻና ማስፈራሪያ በምድርም በአየርም ልምምድ እያስገመገመብን ፣ ሁሉንም ዓይነት ጫና…
#ኢትዮጵያ

" ስለ ስምምነቱ ቀድሞውኑ የሚመለከታቸው ሀገራት እና ተቋማት እውቅናው ነበራቸው ፤ ግን አላዋቂ ለመምሰል ጥረት እያደረጉ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር በተያያዘ ዕድል ያላት የሚመስለው ከሰሜን በኩል ነበር።

ሁሉም ሰው ስለ ባህር በር ሲወራ ቀይ ባህር ነው፤ ስለ ባህር ሲወራ ኤርትራ ነው ፤ ስለ ባህር ከተወራ አሰብ ነው። ይሄን አሁን ለመገልበጥ የሚያችል አዲስ አቅጣጫ ነው የወሰድነው።

ኢትዮጵያ ዙሪያዋ እድሎች አሏት፣ ዙሪያዋ ያሉ እድሎችን መጠቀም የሚያስችል አቅምም አላት፤ መጋራት የሚያስችል በጎ ፍላጎትም መነሻም አላት።

በአንድ ወይ በሌላ መንገድ ኢትዮጵያ አንድ የሆነ የባህር በር ሊኖራት ይገባል በሆነ መንገድ የሚለው ብዙዎች እየገዙት የመጣ ነው።

አትጋጩ፣ ችግር አትፍጠሩ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚመጣበትን መንገድ በትዕግስት ሂዱ ነው እንጂ የሚለው ኢትዮጵያ unfair የሆነ ነገር እየፈለገች ነው የሚል ብዙ ምልከታ የለም።

ኢትዮጵያ ፍላጎቷን፣ ያላት concern ትክክል ነው፣ የህዝብ እግደቷም ትክክል ነው፣ ኢኮኖሚዋም ትክክል ነው ፣ የቀጠናው ችግር ትክክል ነው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በአውንታዊነት ሚና ልጫወት ማለቷ ተገቢ ነው የሚለውን አጀንዳ ማድረግ ተችሏል።

... ይሄንን ፊርማ (ከሶማሌላንድ ጋር) እስክንፈርም ድረስ በUN ተቋማትም፣ በአንዳድን ትላልቅ ሀገሮች መረጃዎችም ፣ በእኛ Think tank በሚባሉ NGOዎችም ይሰራ የነበረው ጥናት የኢትዮጵያ መንግሥት ወይ ኤርትራን ይወራል፣ ወይ ደግሞ ሶማሌላንድን በአውዳል ግዛት በኩል ረብሻ ፈጥሮ ቀጠናውን ያተራምሳል የሚል ጥናት ነበር ሲሰራ የነበረው።

በዚህ ላይ draft ቀርቦ የቀረበው draft official ከመሆኑ በፊት የተመለሰ draft እናውቃለን። ይሄንን እነማን እንደሚሰሩት እናውቃለን፣ እሱ ውስጥ #ኢትዮጵያውያን እንዳሉበትም እናውቃለን። ስለዚህ ትላልቆቹ ሀገራት የሳቱት ነገር ፤ እኛም ባገኘናቸው ቁጥር ጦርነት አንፈልግም ውጊያ አንፈልግም ሲባል ' አይ መዋጋታችሁማ አይቀርም አናምናችሁም ' የሚባል ነው ጭቅጭቁ ከዋሽንግተን እስከ ሌሎቹ ድረስ ፤ ስለዚህ በዚህ ሊዋጉ ነው ብለው ሲገምቱ በዚህ በኩል በሰላም መጣን አልተገመትንም ግን ያልተገመትነው ለበጎ ነው።

... መንግሥት ፍላጎቱን ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለጎረቤት ሀገሮች ፣ በአጠቃላይ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ከአንዴም ሁለት ጊዜ envoy ተልኳል። የማያውቁት ነገር ቢኖር ሙሳቤሂ መቼ እንደሚመጣ (ወደ አዲስ አበባ) እና እዚህ ውስጥ የሼር ጉዳይና የእውቅና ጉዳይ MoU ውስጥ እንደሚካተት አያውቁም። ስለዚህ ከሞላ ጎደል አሰብ አካባቢ የምንከራተት አድርገው ስለወሰዱ ይሄን ጉዳይ ትርጉም አልሰጡትም።

አሁን አፍጥ ሲመጣ ነው ሰው የደነገጠው እንጂ የአብዛኛው ሰው ፍርሃት #በአሰብ በኩል ችግር ትፈጥራላችሁ ፣ ስለዚህ እጃችን ላይ በቂ ችግር አለ የዩክሬን አለ የጋዛ አለ፣ ከምትጨምሩብን በሰላማዊ መንገድ አድርጉትና በሰከነ መንገድ እኛም እናግዛችኃለን የሚል ነውና የpredictability deficit የተነሳበት angle ትክክል አይመስለኝም።

ስለ ጉዳዩ ለእያንዳንዱ ለሚመለከተው መንግሥት አስረድተናል። "

#AmbassadorRedwanHussien #etv

@tikvahethiopia