TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
7 ዓመታትን ያለ ኤሌክትሪክ . . . ለ7 ዓመታት ኤሌክትሪክ በተቋረጠበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፤ ካማሽ ዞን ነዋሪዎች " የከፋ ችግር ላይ " ስለመሆናቸው ቪኦኤ ሬድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። አቶ ለማ ሮሮ የተባሉ የካማሽ ዞን፤ ካማሽ ከተማ ነዋሪ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳላገኙ  ገልጸዋል። የኤሌክትሪክ እንዲጀምር ጥረት ቢደረግም ማታ ማታ ታጣቂዎች መስመሮች…
መብራት ከ7 አመት በኃላ ያገኘችው ካማሺ ...

" #በመከላከያ እጀባ እና ከክልል የፀጥታ ኃይል ጋር በመተባበር የመብራት ኃይል ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ነው የተሰራው አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም " - የካማሺ ዞን ኮሚኒኬሽን

የካማሺ ዞን አካባቢዎች ከ7 ዓመታት በኃላ መብራት አገኙ።

ቃላቸውን ለቪኦኤ የሰጡ የካሚሺ ከተማ ነዋሪዎች ፤ የመብራት አገልግሎት ባለፉት ሳምንታት ዳግም መጀመሩን ገልጸዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ " መብራት ለ7 ዓመታት ተቋርጦ ቆቷል። ከ7 ዓመት በኃላ ማህበረሰቡም በመታገል ከመንግስት ጋር በመተባበር አሁን መብራት ወደ ከተማችን ገብቷል ፤ አብዛኛው ቤትም መብራት አለ " ብለዋል።

ማህበረሰቡ ከዓመታ ጨለማ ወደ ብርሃን ሲመጣ ደስ ብሎታል ሲሉ አክለዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ደግሞ ማህበረሰቡ በመብራት እጦት ክፉኛ  ሲቸገር እንደነበር አስታውሰው አአገልግሎቱ በመጀመሩ ደስ መሰኘታቸውን ገልጸዋል። ወደ ሌሎች የካማሺ ዞን ወረዳዎች እንዲዳረስ ጥሪ አቅርበዋል።

የዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ በካማሺ ከተማ የመብራት አገልግሎት ባለፈው ሳምንት መጀመሩን ገልጸው ፤ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች እንዲዳረስ እየተሰራ ነው ብሏል።

መብራት ለ7 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ፤ ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወደ ዞኑ ይመጣ የነበረው መስመር በመቆረጡና እሱን ለማስተካከል በኦሮሚያ የነበረው የፀጥታ ችግር እንቅፋት በመሆኑ እንደሆነ አስረድቷል።

ኮሚኒኬሽን ቢሮው ፤ " የፀጥታ ችግሩ አሁንም አልፈታም ፤ በችግሩ ውስጥ ነው ማስተካከል የተቻለው በመከላከያ እጀባ እና ከክልል የፀጥታ ኃይል ጋር በመተባበር የማብራት ኃይል ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ነው የተሰራው አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም ፣ ሲል ገልጿል።

የመብራት ኃይል ጊምቢ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በበኩሉ ፤ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተደርጎ ህብረተሰቡ ልማቱን ለመጠበቅ ቃል ስለገባ ባለፈው አንድ ወር አስፈላጊው ነገር ተሟልቶ በካማሺ ከተማ ከታህሳስ 21 ጀምሮ አገልግሎት ጀምሯል ሲል አሳውቋል።

በ2010 በካማሺ ተዘግቶ የነበረው መ/ቤት አሁን ተከፍቶ ሰራተኞች ተመልሰው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አሳውቋል። #ቪኦኤአማርኛ

@tikvahethiopia