TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" መንግስት የሚወስነውን የሆነ አካል ተነስቶ ' ይህ ይሁን ፤ ይህ ደግሞ አይሁን ' ማለት ትክክል አይደለም " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ወቅቱን ያልጠበቀና ህገወጥ ነው " በማለት እንዳይካሄድ ክልከላ ያስተላለፉበት የህወሓት የካድሬዎች ስብሰባ የአጠራሩን አግባብነት ከተነጋገሩበት በኃላ ፓርቲው ያጋጠሙትን አደጋዎች አስመልክቶ ባፀደቀው ዋና አጀንዳ ላይ ከ2 ሳምንት በኃላ ተገናኝቶ ለመወያየት ወስነው ተበትነዋል።
ምንም እንኳን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ክልከላ ቢጥልም የህወሓት ካድሬዎች ቅዳሜና እሁድ መቐለ ሰማዕታት አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው ነበር።
የስብሰባው መጠናቀቅን ተከትሎ ፓርቲው ባሰራጨው መግለጫ ፤ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አስቀድሞ ካድሬዎችን ሰብሰበው ባለማናገራቸው ወቅሷል።
በፓርቲው ላይ ያጠላው አደጋ ምንድነው ? በሚል በተቀረፀ ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ ላይ ችግሩን በተረጋጋ መንፈስ ለመገምገምና የውስጥ ማጥራት ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱን ፓርቲው ገልጿል።
በዶክተር ደብረፅዮ ገ/ሚካኤል የተመራው የፓርቲው የካድሬዎች ስብሰባ የስብሰባው ዋና አጀንዳዎች በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሁለት ሳምንታት በኃላ እንዲታዩ ውሳኔውን አሳልፎ ተበትኗል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ በፓርቲው ካድሬዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ተቋማዊ አሰራርን ያልተከተለ ነው በሚል የተቸው ፓርቲው እርምት እንዲደረግ ጠይቋል።
ባለፈው ሳምንት ከመንግስት የስራ ኃላፊነት ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 6 ከዞን አመራሮች ከአቶ ጌታቸው ረዳ በተላከላቸው ደብዳቤ ከስልጥን እንዲነሱ መደረጉ አይዘነጋም።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምን አለ ?
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ስብሰባው እንዳይካሄድ ያገድነው ተሳታፊዎቹ የመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቅድሚያ የሰጣቸው ተግባራት በመኖራቸው ነው ብለዋል።
አቶ ረዳኢ ሃለፎም ፦
" ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስብሰባው ትክክል አይደለም ያለው በአሁን ሰዓት መሰራት ለሚገባቸው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በምርት ላይ ጉዳት ሳያደርስ የመሰብሰብ እና አንበጣን የመከላከል ተግባራት የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጡ ነው።
ይኸውም ቅድሚ እንዲሰጠው በጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን በህወሓት መሪዎችም ጭምር መግባባት ላይ ተደርሶ ስብሰባው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ስለተወሰነ ነው።
ስብሰባው የተካሄደው ከዚህ የጋራ ውሳኔ በኃላ ነው። መንግስት የሚወስነውን የሆነ አካል ተነስቶ ' ይህ ይሁን ፤ ይህ ደግሞ አይሁን ' ማለት ትክክል አይደለም።
ከኃላፊነት የተነሱት ሰዎች ከአሁን በፊት የተመደቡት በስብሰባ አይደለም፤ ከስራ ቦታ ሲነሱም በስብሰባ አይሆንም። በስብሰባ እገሌን መድቡት እገሌን ደግሞ አቆዩት ማለት ትክክል አይደለም።
ሹመት በሚገባቸው ቦታዎች ላይ ሰዎች ይሾማሉ ከስራ ምድብ ማንሳት በሚያስፈልግበት ጊዜ ደግሞ ይነሳሉ። ከዚህ ውጭ ያለው ስክነትና ማስተዋል የጎደለበት ጩኸት ነው። "
የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን እንገልፃለን።
@tikvahethiopia

#ድሬዳዋ 🔹" የትውልድን ስነምግባር የምትቀርጽ እና በይዞታዋም ህጋዊ የሆነችን ቤተክርስቲያን አፍርሶ ሆቴል መስራት አግባብነት የለውም " - ቤተክርስቲያን 🔸" ቦታውን ለልማት ተፈልጎ ነው ፤ ካቢኔው የልማት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ሃላፊነት አለበት " - የድሬዳዋ ከንቲባ ጽ/ቤት የድሬደዋ መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ቤተክርስቲያኗ ካለችበት ቦታ እንድትነሳ የሚል ደብዳቤ…
የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ መፍትሄ አግኝቷል ?
ዛሬ የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናንን ወቅታዊ ሁኔታ በመሚመለከት በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መግለጫ ሰጥታለች።
በዚህም መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፤ የድሬዳዋ ማህበረ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን ህንጻና ሌሎች ተያያዥ ህንጻዎች ያሉበትን ይዞታ ለሌላ አገልግሎት ለማዋል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተላለፈው ውሳኔ ቤተ ክርሰቲያኗን ብቻ ሳይሆን መላውን ህዝበ ምዕመን በእጅጉ ማስደንገጡ ተገልጿል።
ይህ ውሳኔ እንደገና እንዲጤን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ብርቱ ክትትል በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ተመላክቷል።
የከተማው አስተዳደርም በተለይም ከንቲባው ሁኔታውን በጥንቃቄና በሃላፊነት ስሜት እየተከታተሉ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ጋርም ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸው በመግለጫው ላይ ተመላክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉዳዩ የማይመለከተውና በየትኛም መንገድ ድርሻ የሌለው አንድ አካል፤ ችግሩ መፍትሔ እንዳገኘ አድርጎ በዛሬው ዕለት በራሱ ማህበራዊ ገጽ (Facebook) የተሳሳተ መረጃ አውጥቷል ብሏል የቤተክርስቲያንኒቱ መግለጫ።
ስም ያልጠቀሰው መግለጫው ይኸው አካል ይህንን ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርም ጥብቅ ማሳሰቢያ የደረሰው መሆኑን ገልጿል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከምታውቀው ድረስ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምንም ዓይነት ውሳኔ ያልተሠጠ መሆኑንና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ አሠራር ኦፊሴላዊ መረጃ እስከምትሰጥ ድረስ ህዝበ ምዕመኑ በትዕግስትና በጸሎት እንዲጠባበቅ አሳስባለች።

ብርቱ አጋር!!
ለስኬትዎ መዳረሻ ለህልምዎ እውን መሆን ብርቱ አጋር ነን
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
#globalbankethiopia #GBE #banksinethiopia #fintech #bank #finance #ethiopia #ethiopian #digitalbanking #Globaldigital

#ምደባ
ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ማብራሪያ ፦
- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፤ በነዚህ ውስጥ ይመደባሉ።
- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል።
- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ መደረጉ ተገልጿል።
- የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን እንደሚያግፅ ተነላክቷል። ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል።
- የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር እንደሚያግዝ ተገልጿል።
- የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው ተብሏል። በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል።
- በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።
- የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።
ትምህርት ሚኒስቴር ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርብ ተማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከምደባ ውጭ የሚሆን መሆኑን አሳስቧል።
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia
ቡና በምንገባበዝበት ብር የሳፋሪኮምን 4GB YouTube ጥቅል ገዝተን 200ደቂቃ ሙሉ ባልተገደበ የኢንተርኔት ፍጥነት በአዝናኝ ቪዲዮዎች ፈታ እንበል። ዛሬውኑ ወደ *777# በመደወል ጥቅሉን እንግዛ።
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

መምህራን ምን አሉ ?
• " የመምህራን ደመወዝ ይቆረጣል የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ አሳማኝ አይደለም "
• " የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች አይልኩም "
• " አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው ይጠብቃሉ፤ ግማሽ ደመወዝ ብቻ የሚከፈልበት ጊዜም አለ "
የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው 36ኛው ጉባዔ ላይ፣ በክልሎች የበርካታ መምህራን ደመወዝ ያላግባብ እንደሚቆረጥ በስፋት መነሳቱ ተገልጿል።
የማኅበሩ ጉባዔ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከሲዳማና ከሌሎቸም ክልሎች መምህራን ደመወዛቸው ያላግባብ እንደሚቆረጥ በስፋት መነሳቱን በስብሰባው የተሳተፉ የማኅበሩ አመራሮች ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ እንደገለጹት፣ በክልሉ እስከ 60 በመቶ የሚደርስ የመምህራን ደመወዝ እንደሚቆረጥና ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ አይደለም ብለዋል።
የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች እንደማይልኩ፣ በጀቱ ለማዳበሪያ ክፍያ ዋለ በሚል ወደ መምህራን ሳይደረስ እንደሚቀር መምህራን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው እንደሚጠብቁና ግማሽ ደመወዝ ብቻ እንደሚከፈላቸውም ተነግሯል፡፡
መንግሥት በአንድ በኩል ስለትምህርት ጥራት እየተናገረ፣ በሌላ በኩል የመምህራን ደመወዝ እንደማይከፈል፣ የደረጃ ዕድገትና የትምህርት ማሻሻያ እንደማይደረግ በጉባዔው ላይ መነጋገሪያ ነበር ተብሏል፡፡
የማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዳሉት፣ በክልሉ በርካታ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ውስን መሆናቸውን፣ የበጀት እጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃቸው መምህራን በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሚከናወን ሥራ ከ2017 ዓ.ም. በጀት መበደራቸው ተገልጿል፡፡
ማኅበሩ በጅግጅጋ ባከሄደው ወይይት የመምህራኑ ጉዳዩ በስፋት መነሳቱ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ለዚህ ችግር ክልሎች ጉዳዩን በባለቤትነት ወስደው መፍትሔ እንዲፈልጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) መናገራቸውን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይትም ማኅበሩ ከዚህ ቀደም በደብዳቤና በሪፖርት መልክ ሲያቀርባቸው የነበሩ ጥያቄዎችን፣ የትምህርት ሚኒስትሩን በአካል በማግኘት የመምህራኑን ሕይወት ሊቀይሩ የሚችሉ ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ብለዋል፡፡
በሁሉም ክልሎች የሚገኙ መምህራን በጉባዔው የኑሮ ሁኔታቸው እንዲሻሻል ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበው ሚኒስትሩ እንደ ሁኔታው እየታየ ወደፊት የመምህራኑን ሕይወት ሊቀይር የሚችል ሥራ ይከናወናል ማለታቸውን ዮሐንስ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ከአፋር ክልል ተፈናቅለው ወደ ትግራይ ክልል የሄዱ 500 መምህራን ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ምክክር ተደርጎበታል ብለዋል፡፡
በ2015 ዓ.ም. ክረምት ተቋርጦ የነበረው የመምህራን የክረምት ትምህርት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ጉባዔውን በተመለከተ ሚኒስትሩን ጠቅሶ በድረ ገጹ እንዳሠፈረው፣ አገሪቱ አሁን ላለችበት አገራዊ ችግር የትምህርት ሥርዓት መውደቁ ምክንያት በመሆኑ፣ የመምህራን ማኅበር ችግሩን ተነጋግሮ መፍታት እንዳለበትና ማኅበሩ የሙያውን ክብር ለመመለስ ከኅብረተሰቡ ጋር ወይይት በማድረግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

#አማራ በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ዛሬ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተላከልን መግለጫ መረዳት ችለናል። ከኢሰመኮ በደረሰን መግለጫ ፤ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል። …
" ሪፖርቱ የመንግሥትን እንቅስቃሴ አውድ ከግምት ያላስገባ፣ በበቂ መረጃ ላይ ያልተመሠረተ እና ከእውነታ ያፈነገጠ ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአማራ ክልል የሰብዓዊ ሁኔታን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ " ከእውነታው ያፈነገጠና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው " አለ።
ዛሬ መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ኢሰመኮ በአማራ ክልል ጉዳይ ያወጣው ሪፖርት የመንግሥትን እንቅስቃሴ አውድ ከግምት ያላስገባ፣ በበቂ መረጃ ላይ ያልተመሠረተ እና ከእውነታ ያፈነገጠ ነው ብለዋል።
በተጨማሪ ፤ መንግሥት ክልሉ ወደ ሰላማዊና መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ያደረገውን ጥረት ከግምት ያላስገባ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
" መንግሥት ገለልተኛ ተቋማት እንዲኖሩ የሚፈልገው የተዛቡ መረጃዎች አንዲታረሙ እና ዴሞክራሲ እንዲጠናከር አስቦ ነው " ያሉት ሚኒስትሩ " ነገር ግን እነዚህ ገለልተኛ ተቋማት በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ባሉ የተዛቡ መረጃዎች ከተጠለፉ የምንፈልገውን ዴሞክራሲ ልንገነባ አንችልም " ሲሉ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ፤ ኢሰመኮ የሚያወጣቸውን መረጃዎች ከትክክለኛ መንጭ በመረዳት እና ትክክለኛውን አውድ ከግምት ያስገባ መሆን እንሚገባው ገልጸዋል።
ከሰሞኑን ያወጣውን መግለጫም ቆም ብሎ እንዲገመግም አሳስበዋል።
መንግሥት በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እና የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ለማረጋገጥ ጥንቃቄ የተሞላባቸው እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዛሬው መግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል።
ኢሰመኮ ከቀናት በፊት በላከልን መግለጫ ፤ በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ፣ እንዲሁም በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ግድያ መፈፀሙን አሳውቆ ነበር።
በተለይም #የአየር /#ድሮን መሣሪያን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው መሸሻቸውን የኢሰመኮ መግለጫ ያስረዳል።
በተለይም በመጥተህ ብላ ከተማ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የአንድ አመት ከ7 ወር ህፃንን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸውን ፣ በደብረ ማርቆስ በተመሳሳይ በድሮን 8 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን ፤ እንዲሁ በደንበጫ በከባድ መሳሪያ ሲቪሎች መገደላቸውን በመግለጫው አሳውቋል።
ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ቀጥሏል ባለው ከፍርድ ውጭ ግድያ ግጭት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦ " ፋኖን ትደግፋላችሁ " ፤ " ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ " ፤ " መሣሪያ አምጡ "፤ " የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች መገኘታቸውን ገልጿል።
ከዚህ ባለፈ ፤ በየደረጃው የሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና እገታዎች በታጠቁ ኃይሎች መፈፀማቸውን ኢሰመኮ በመግለጫ አሳውቆ ነበር።
ኢሰመኮ ልኮት የነበረው ሙሉ መግለጫ በዚህ ይገኛል፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82610

" በከተማ ውስጥ ረጅም የመኪና ማብራት ፈጽሞ አይፈቀድም ፤ ልዩ ክትትልም እናደርጋለን ፤ ... ደንብ የሚተላለፉት ላይ ቅጣቱ ከመደበኛ ቅጣቶች ከፍ ያለ ይሆናል " - ትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ
በአዲስ አበባ ከተማ የረጅም የመኪና መብራት አጠቃቀም ላይ ልዩ ክትትል ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳወቀ።
ረጅም የመኪና መብራት አጠቃቀም ላይ ልዩ ክትትል ይደረጋል ያለው ኤጀንሲው ፤ በከተማ ውስጥ ረጅም የመኪና ማብራት ፈጽሞ አይፈቀድም፤ ህጉም በግልፅ ይሄንን ይከለክላል ሲል አስገንዝቧል።
ነገር ግን አሁን ላይ ረጅም የመኪና መብራት የሚጠቀሙ አካላት በብዛት እየተስተዋሉ እንደሚገኝ የጠቆመው ኤጀንሲው ይህን የሕግ መተላለፍ ለመግታት ረጅም የመኪና መብራት አጠቃቀም ላይ ልዩ ክትትል ይደረጋል ሲል አሳውቋል።
በቁጥጥር ሂደቱ ውስጥ ሕግ ተላልፈው የተገኙ አካላት ተቆጣጣሪዎች ሕጉን መሠረት ያደረገና ከመደበኛው ቅጣት ከፍ ያለ ርምጃ እንዲወስዱ እንደሚደረግ ተገልጿል።
በከተማ ውስጥ ረጅም የመኪና መብራት መጠቀም አሽከርካሪዎች በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ እንደሚያደርግ ኤጀንሲው አስገንዝቧል።
ከዚህ ባለፈ በተሽከርካሪ ላይ ያልነበረ ሌላ ተጨማሪ የመብራት አካል እየገጠሙ የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች መኖራቸውን አንስቶ ተግባሩ በቀጥታ ደንብ የተላለፈ በመሆኑ ቅጣቱ ከመደበኛ ቅጣቶች ከፍ ያለ እንዲሆን ተደርጓል ሲል አሳውቋል።
አሽከርካሪዎች ይህ ድርጊት በሰውና በንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ፤ አሁን ላይ የሌላ ተሽከርካሪ የፊት መብራት አስገጥመው የሚጠቀሙ በርካታ አሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው ያለ ሲሆን በአጠቃላይ የመኪና መብራት አጠቃቀም ላይ ልዩ ክትትል ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንና ልዩ ክትትሉ ራሱን የቻለ ፦
- እቅድ፣
- የአፈፃጸም ሥርዓት፣
- የቅጣት ደረጃ፣
- የሰው ኃይል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በውስጡ መካተታቸውን አመልክቷል።
ደንብ ጥሰቱ ከሌሎች ጥሰቶች እኩል የሚታይ አለመሆኑን አሽከርካሪዎች ሊገነዘቡ ይገባል ሲል ማሳስቡን ኢፕድ ዘግቧል።
ከዚሁ ከረጅም የመኪና መብራት ጋር በተያያዘ በርካቶች የተማረሩበት ጉዳይ ስለመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች ገልጻዋል።
አንዳንዶች የትኛው ረጅም የትኛው አጭር እንደሆነ በማያውቁበት ሁኔታ እንደሚያሽከርክሩ የገለፁት እኙሁ አስተያየት ሰጪዎች ይህ ድርጊት ለከፍተኛ አደጋ እንደሚያጋልጥ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል አንዳንድ የከተማው መንገዶች የመንገድ ላይ መብራት ስለሌላቸው በምሽት ለማሽከርከር አዳጋች እንደሚሆን ገልጸው መንግሥት አስፈላጊውን ነገር ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
እርምጃዎች ሲወሰዱም ያሉትን ችግሮች ታሳቢ ያደረገ ፣ የመንገዶቹን የጥራት እና ለረጅምም ሆነ ለቅርብ እይታ በቂ የመንገድ መብራት መኖራቸውን ከግምት ያስገባ ሊሆን እንደሚገባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል።
* የመረጃው መነሻ ኢፕድ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ተንተርሶ የቤተሰቡን አባላት አነጋግሮ ነው ያቀረበው።

#CBE
ይመልሱ፤ ይሸለሙ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑርን 10ኛ ዓመት በማስመልከት በማኅበራዊ ትስስር ገፆቹ የጥያቄና መልስ ውድድር አዘጋጅቷል፡፡
እርስዎም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በመቀላቀል ከጥቅምት 23 ቀን 2016 ጀምሮ በሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡
🔗 ፌስቡክ 🔗 ኦሮምኛ የፌስ ቡክ ገፅ
🔗 የሲቢኢ ኑር የፌስቡክ ገፅ
🔗 ቴሌግራም 🔗 የሲቢኢ ኑር ቴሌግራም ገፅ
*****
ማሳሰቢያ፡
ለአሸናፊዎች ሽልማቱ የሚደርሰው በሲቢኢ ብር በመሆኑ የሲቢኢ ብር ደንበኛ በመሆን ሽልማቱን ይቀበሉ፡
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
ይመልሱ፤ ይሸለሙ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑርን 10ኛ ዓመት በማስመልከት በማኅበራዊ ትስስር ገፆቹ የጥያቄና መልስ ውድድር አዘጋጅቷል፡፡
እርስዎም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በመቀላቀል ከጥቅምት 23 ቀን 2016 ጀምሮ በሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡
🔗 ፌስቡክ 🔗 ኦሮምኛ የፌስ ቡክ ገፅ
🔗 የሲቢኢ ኑር የፌስቡክ ገፅ
🔗 ቴሌግራም 🔗 የሲቢኢ ኑር ቴሌግራም ገፅ
*****
ማሳሰቢያ፡
ለአሸናፊዎች ሽልማቱ የሚደርሰው በሲቢኢ ብር በመሆኑ የሲቢኢ ብር ደንበኛ በመሆን ሽልማቱን ይቀበሉ፡
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስራ ሲከመር፣ ስራ ሲበዛ፣ #መክሰስTime አለልና! - ከ #ሰንቺፕስ ጋር #ሰኒሞመንትስ
Work is piling up and all that we could say is, it is time for #SnackTime with #SUNChips have your #SunnyMoments.

#ትግራይ
በትግራይ ሁሉም ትግራዋይ አቀፍ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የሶስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጥምር የሆነው 'ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ' ጠየቀ።
የሳልሳይ ወያነ ፣ የባይቶናና የናፅነት ትግራይ ጥምር ፓርቲዎች ስብሰብ የሆነው 'ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ' ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ " ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው በትግራይ መሰረታዊ የፓለቲካዊ ለውጥ የሚያመጣ ፤ ሁሉም ትግራዋይ ያቀፈ ፤ የሁሉም ትግራዋይ የሆነ የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት " ብሏል።
" ህወሓት ከትናንት ሳይማር አሁንም ህዝቡ እርስ በራሱ እንዲጠፋፋ እየሰራ ነው " ሲል የከሰሰው 'ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ' ህዝቡ የህወሓት የጥፋት ሴራ ለመግታት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጎን መሰለፍ አለበት ብሏል።
" የትግራይ ህዝብ ህልውናው ለማስቀጥልና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመትከል ከባድ መስዋእትነት ከፍለዋል " ያለው የኪዳን መግለጫ ፤ " ቢሆንም የተፈናቀለ ህዝብ እስከ አሁን ወደ ቄየው አልተመለሰም ፤ የትግራይ ግዛታዊ እንድነት አልተረጋገጠም " ብሏል።
ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አለመመለስና የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ሳይረጋገጥ እስከ አሁን መቆየቱ በህወሓት ስንፍና መሆኑ የከሰሰው የኪዳን መግለጫ ፤ ህዝቡ ይህንን ለአንዴና ለመጨረሻ እንዲቀየር አልሞ መሰረታዊ ለውጥ ለማጥት ከሚታገለው " ኪዳን ንሱር ቦቀስ ለውጢ " ጎን እንዲሰለፍ ጠይቋል።
" ኪዳን ንሱር ቦቀስ ለውጢ ' በሚል የሚታወቀው የትግራይ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጥምረት በጳጉሜን 2015 ዓ.ም በጠራው የአደባባይ ሰልፍ ምክንያት አመራሮቹ ለእስር ተዳርገው ፤ ለሰልፍ በወጡ የአካል ጉዳት መድረሱና እስር መፈፀሙ መዘገባችን ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#Ethiopia
" ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በገንዘብ መድን ፈንድ ዋስትና ያገኛል "
በኢትዮጵያ በባንኮች ገንዘብ ከሚያስቀምጡት አብዛኛዎቹ ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በባንክ ያለው የገንዘብ መጠን ከ100,000 ብር በታች መሆኑ ተገለፀ።
ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ወደ ሥራ መግባቱን በተነገረበት ጊዜ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
በተለያዩ ገንዘብ ተቋማት ላለ ተቀማጭ ገንዘብ ዋስትና የሚሰጥ የገንዘብ መድን ፈንድ ተቋቁሞ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡
ይህ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው ተብሏል።
ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በዚሁ ፈንድ ዋስትና ያገኛል የተባለ ሲሆን ጥበቃው የሚመለከተው 100,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሆነን ብቻ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መርጋ ዋቆያ ተናግረዋል።
ይህም በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከተፈፀሙ ለውጦች አንዱ ነው ተብሏል።
ፈንዱ አደረጃጀቱ ምን ይመስላል የሚለውን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል። የፈንዱ ስልጣንና ተግባር በክፍያ ካዝናነት የተገደበ ነው ተብሏል።
አላማው ህዝባዊ ነው የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ በመንግስት እንደሚተዳደር ተገልጿል።
ምክትል ገዢው አንድ የፋይናንስ ተቋም የሚወድቅ ከሆነ ኮሽታ ሳያሰማ ህዝቡን ሳይረብሽ ኢኮኖሚውንም ሳይረብሸው እንዲወጣ ፈንዱ ይሰራል ብለዋል።
ይህ በሚሆን ጊዜም በመድን የተሸፈነውን ገንዘብ ለአስቀማጩ ከ 7 ቀን እስከ 90 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚመለስ አስረድተዋል።
147 ሀገራት የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተቋም አላቸው የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ 148ተኛ ሀገር ሆናለች።
የዚህ መረጃ ባለቤት ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
ፎቶ፦ ኢዜአ