TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባለፉት ቀናት የጥቅምት መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያኗ እና ለሀገራም ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተገልጿል።…
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች በውይይት እና በስምምነት እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቀረበች።

ይህ ጥሪ የቀረበው ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት 2016 ዓ/ም ጉባኤውን ካጠናቀቀ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት በእጅጉ አሳዝኖናል " ብሏል።

በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላቸው በሁሉም አካባቢ የምሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ የበኩላቸው ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።

ከዚህ በተጨማሪ ስለ ሀገር ሰላም እና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም ተወስኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን #ሲዳማ የሲዳማ ክልል ም/ ቤት አስቸኳይ ጉባዔ በሀዋሳ እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው እያካሄደ ያለው። ለአንድ ቀን ብቻ ይካሄዳል በተባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ በሶሰት የተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል። - ለጉባኤው ሞሽን ቀርቦ ይጸድቃል። - የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ለምክር ቤቱ አቅርበው…
#Update

ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስረኞች ማቆያ እንዲገቡ የተደረጉት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።

የሲዳማ ክልል መንግስት ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ 3 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ማቶ ማሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል ያሏቸውን ፦
- ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ፣
- አቶ አበራ አሬራ
- አቶ ተሰማ ደንጉሼ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ማብራሪያ መሰረት ም/ ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ በህግ እንዲጠየቁ ውሳኔ አሳልፏል።

ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከቀናት በፊት ወደ ሀገር ሲገቡ ቦሌ ኤርፖርት ላይ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በሀዋሳ በሚገኝ የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሆኑ የክልሉ ፖሊስ ማሳወቁ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በክልሉ አራት ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እንዲቋቋሙ በቀረበለት ሞሽን ላይ ተወያይቶ አፅድቋል። የፍ/ቤቶቹ መቀመጫም በአለታወንዶ፣ በበንሳ፣ ይርጋለምና ሀዋሳ ከተሞች ላይ እንዲሆን ወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የቀረበለትን የተለያየ ሹመት አፅድቋል።
- አቶ ጎሳዬ ጎዳና የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ፣
- አቶ ወሰንየለህ ሰለሞን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ፣
- ወይዘሮ ሰላማዊት መኩሪያ የንግድ ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
#አማራ : ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው

" ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል። "

በአማራ ክልል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

መግለጫው በክልሉ በተለያዩ ጊዜ በድሮን / አየር ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ፣ በርካታ ሰዎች ግጭት ሽሽት አካባቢያቸውን ጥለው መሸሻቸውን፣ ከፍርድ ውጭ የሚፈፀመው ግድያ መቀጠሉን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ግድያም መፈፀሙን ያስረዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ : ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው " ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል። " በአማራ ክልል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። መግለጫው በክልሉ በተለያዩ…
#አማራ

በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ዛሬ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተላከልን መግለጫ መረዳት ችለናል።

ከኢሰመኮ በደረሰን መግለጫ ፤ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል።

በተጨማሪም እነዚህ አካባቢዎችና ወረዳዎች በአንድ ወቅት ላይ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሌላ ወቅት ደግሞ በታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የትጥቅ ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር / ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው።

በግጭቱ ዐውድ ውስጥ #የአየር /#ድሮን መሣሪያን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።

ለምሳሌ ፦

- በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በረኸት ወረዳ፣ ' መጥተህ ብላ ' ከተማ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የአንድ ዓመት ከሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች #ተገድለዋል፤ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ማርቆስ ከተማ ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት  ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

- በደንበጫ ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት ሲቪል ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል።

ኮሚሽኑ እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የአካባቢውን ነዋሪዎች እና የዓይን ምስክሮችን በማነጋገር ነው።

በአንዳንድ አካባቢዎች ጥቃትን አልያም ግጭትን በመሸሽ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።

በምንጃር ወረዳ ውስጥ የአውራ ጎዳና ጎጥ ነዋሪዎች ከመስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከቀያቸው ተፈናቀለው ቢያንስ 3ዐዐዐ የሚሆኑት አሞራ ቤቴ ቀበሌ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤትና ክፍት ሜዳ ላይ (በዛፍ ሥር) ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቀ መተሃራና አዋሽን ጨምሮ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል።

ለተፈናቃዮች የተወሰነ ድጋፍ በማኅበረሰቡና እና በአንድ ተራድዖ ድርጅት የተደረገ ቢሆንም፣ በቂ ባለመሆኑ በአሳሳቢ ሁኔታ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

የነዋሪዎችን መፈናቀል ተከትሎ ሰብላቸው እንደወደመ፣ ንብረታቸው እንደተዘረፈ፣ የቤቶቻቸው ጣራያ እና በር እየተነቀለ እንደተወሰደ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ቤቶቻቸውን ከአጎራባች ክልል በመጡ ኃይሎች በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ጭምር ማፍረስ እንደተጀመረ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት ኃላፊዎች አስረድተዋል።

በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት የሚፈጸሙ ከሕግ ውጪ የሆኑ ግድያዎች አሁንም መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ተዓማኒ መረጃዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል።

ግጭቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦

- " ፋኖን ትደግፋላችሁ "

- " ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "

- " መሣሪያ አምጡ "


- " የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች ተገኝተዋል።

እንደማሳያ ፦

▪️በባሕር ዳር ሰባታሚት አካባቢ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2016 ዓ.ም. #ሦስት_ወንድማማቾችን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

▪️በሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፍልሰታ ደብረ ማሪያም የሚኖሩ 12 የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

▪️ በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ አማኑኤል ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች በቤት ለቤት ፍተሻ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።

▪️በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ ግንደወይን ከተማ ሞጣ በር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አንድ በጥይት የቆሰለን ግለሰብ እናቱና እህቱ በባጃጅ አሳፍረው ወደ ሕክምና ተቋም በመውሰድ ላይ እያሉ፣ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባጃጁን አስቁመው ሁሉንም ተሳፋሪዎች ካስወረዱ በኋላ " የቆሰለው እኛን ሲዋጋ ነው " በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራቱን ሰዎች በጥይት እንደገደሏቸው ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

በባሕር ዳር፣ በፍኖተሰላም፣ በጎንደር እና በወልድያ ከተሞች በትጥቅ ግጭቱ ቆስለው ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የተወሰኑ ሲቪል ሰዎች እና የታጣቂ ቡድኑ አባላት በመሆን በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተጠረጠሩ ሰዎች ሕክምናቸው እዲቋረጥ ተደርጎ #ወዳልታወቀ_ስፍራ ከተወሰዱ በኋላ ፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ወደ ሕክምና ተቋማቱ ሲመለሱ ቀሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ማረጋገጥ አልተቻለም።
 
በሌላ በኩል በየደረጃው የሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና እገታዎች በታጠቁ ኃይሎች ተፈጽመዋል።

ለምሳሌ ፦

መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ሲሄዱ ' አለምበር ከተማ ' አካባቢ በታጣቂዎች ተገድለዋል።

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች እንዲያመልጡ ተደርጓል። 
 
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ፤ በተለይም ከመንግሥት ተቋማት ጭምር በሚደርሱት መረጃዎች መሠረት በግጭቱ ዐውድ የሚፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች በጣም አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ተገቢው ምርመራ ተደረጎ አርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ነው፡፡

የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት በተለያዩ የጤና ተቋማት መድረስ የቻሉትን ተጎጂዎች ቁጥር ብቻ መሠረት በማድረግ ከሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ ቢያንስ #2ዐዐ_የአስገድዶ_መድፈር ተጎጂዎች በጤና ተቋማት ተመዝግበዋል፤ ከተጎጂዎች መካከልም የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሴቶች እና የጤና ባለሞያ ሴቶች ጭምር ይገኙበታል።

ከትጥቅ ግጭቱ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ፦
🔹ሲቪል ሰዎች እና የሲቪል የንግድ እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ዝርፊያ ተፈፅሟል።
🔹የማሳ ላይ ሰብል ውድመት ጨምሮ በሲቪል ሰዎች፣ በሕዝብ እና በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል።
🔹ሕፃናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል በአንዳንድ አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት ለወታደራዊ አገልግሎት ውለዋል። ይህ ደግሞ አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ ነው።

በክልሉ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው ተቋማት በስተቀር ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን፣ በተለይም በግጭት ላይ ባሉ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎትም ጨምሮ ተቋርጧል።

(ዛሬ ከ #ኢሰመኮ የተላከል ሙሉ መግለጫ በዚህ ታገኛላችሁ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82609?single)

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎች ላይ #የታሪፍ_ጭማሪ አድርጓል።

አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 20 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢሮው አስታውቋል፡፡

(ዝርዝር ታሪፉን ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
በቴሌኮም ዘርፍ፣ ዲጂታል ሶሉሽኖች፣ በቴክኖሎጂ እና በአገልግሎቶቻችን ዙሪያ:-

👉 የሚወያዩበት
👉 ሃሳብ የሚሰጡበት
👉 ልምድና ተሞክሮ የሚጋሩበትን

ቴሌፎረም የድረ-ገጽ መድረክ https://teleforum.ethiotelecom.et ቤተሰብ ይሁኑ!
#ጥቆማ #ከጠቀማችሁ

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወርሰው የሚገኙ 171 ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ተጨራቾች የጨረታ ሰንድ በመግዛት በጨረታው ላይ የሚወጡትን ተሽከርካሪዎች በአካል በመመልከት መጫረት ትችላላችሁ ተብሏል። ጨረታው በ26/02/2016 ዓ/ም ጥዋት 4 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:15 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0221118429 ላይ መወደል ይቻላል።

አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የቤትና የጭነት ተሸከርካሪዎች ፦
- DUMP TRUCK፣
- IVECO FIAT፣
- TOYOTA HAILUX፣
- TOYOTA COROLLA፣
- TOYOTA  VITZ፣
- TOYOTA HAICE፣
- TOYOTA YARIS፣
- TOYOTA CHR፣
- HYUNDAI፣
- SUZUKI፣
- MISTUBUSHI ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። የተጠቀሱት ተሸከርካሪዎች የጨረታ ሰነድ ከቀን 20/02/2016 ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት ይቻላል።

(ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ በምስሉ ይመልከቱ)

  የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከፎኔክስ ኢንደስትሪ ኃ/የ/የግ/ማህበር የተያዘ፦
- የኘላስቲክ ወንበር ማምረቻ ማሽን፣  የማሽኑ ማቀዝቀዣ (cooler)፣ የማሽኑ ጥሬ ዕቃዎችና ሌሎች ተጓዳኝ ዕቃዎች፣

ከተክለብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ ፦
- የተለያዩ መጠን ያላቸው የመብራት አምፖሎች፣
- ፍሎረሰንቶች፣
- ፖውዛዎች እና የውሃ ተቀባሪና ተንጠልጣይ የተለያዩ ቧንቧዎች፣

🚘 ከቲ.አይ.ቢ ኬተሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህ እና ኦክስፎርድ አማልጌትድ ኃ/የተ/ የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን 3 ተሽከርካሪዎች ናቸው።

(ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ በምስሉ ይመልከቱ)

#ጉምሩክኮሚሽን #አዲስዘመን #ገቢዎችሚኒስቴር

* ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በጥቆማ መልክ የቀረበ።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በአፖሎ ሲገበያዩ ሁሉም ነገር ቅናሽ አለው! ምን ቅናሽ ብቻ ከንክኪ ነጻ የሆነ ቀልጣፋ እና  ፈጣን አገልግሎትም ያገኛሉ!
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። 
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo 

የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/BoAEth
 
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all