TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እስራኤል ኔታኒያሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለማስወጣት ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸው ተነገረ። በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ተፈጥሮ ነበር። ይህን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ደም በተቃባው ግጭት ላይ የተሳተፉት ስደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።…
#Update #UN

እስራኤል ኤርትራውያንን በጅምላ ከማባረር እንድትቆጠብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠይቋል።

የእስራኤል ባለሥልጣናት በዛቱት መሠረት ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሀገሪቱ የሚያስወጡ ከሆነ፣ “ዓለም አቀፍ ሕግን እንደሚተላለፉ” እና ከፍተኛ ሰብዓዊ ችግር እንደሚያስከትልም ድርጅቱ አስታውቋል።

በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከል፣ ባለፈው ቅዳሜ በቴል አቪቭ - እስራኤል በተፈጠረ ግጭት፣ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውንና ንብረት መውደሙን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት፣ በግጭቱ የተሳተፉ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሀገር እንደሚያስወጧቸው ዝተው ነበር፡፡

የኤርትራን 30ኛ ዓመት የነፃነት ቀን አስመልክቶ፣ በቴል አቪቭ ተዘጋጅቶ በነበረ ክብረ በዓል ላይ፣ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በአንድ ወገንና ተቃዋሚዎች በሌላ ወገን ተሰልፈው በተፈጠረ ኀይል የተቀላቀለበት ግጭት ዐያሌዎች ተጎድተዋል።

የፖሊስ አባላትም ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የተፈጠረው ግጭት እጅግ እንዳሳሰበው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ገልጾ፣ መረጋጋት እንዲኖር እና ሁለቱም ወገኖች ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ጠይቋል።

ባለፈው ሰኔ በወጣ መረጃ፣ 17 ሺሕ 850 ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በእስራኤል እንደሚገኙ ታውቋል።

በግጭቱ 170 ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በደርዘን የሚቆጠሩ የእስራኤል ፖሊስ አባላት እንደተጎዱ የስደተኞች ኮሚሽኑ ገልጿል።

(ቪኦኤ)
ቪድዮ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update 

" ኪዳን ሱር በቆስ ለውጢ " በሚል ለተሰየመው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ሲያነሳሱ የተገኙ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት ታሰሩ። 

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ ፣ ባይቶና ዓባይ ትግራይ ፣ ዓረና ለሉኣላውነትና ለዴሞክራስና ፣  ዓሲምባ የተባሉ 5 ቱ የትግራይ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከጳጉሜን 2 እስከ 4 /2015 ዓ.ም በጥምር ለሚያካሂዱት ሰላማዊ የተቓውሞ ሰልፍ በመቐለ ከተማ በመኪና በመዞር በድምፅ ማጉልያ በመታገዘ እየቀሰቀሱ ሳሉ ነው አባላቱ የታሰሩት።

ነሃሴ 30 / 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 በፓሊስ የታሰሩት ገብረኣብ ወልዱና ብርሃነ ኣርኣያ ከሳልሳይ ወያነ  ፣ ብርሃነ ዘመን ዮሃንስና ገብሩ ከባይቶና ፣ ጠዓመ ሓጎስና ኣፅብሃ ተኽለ ከውድብ ናፅነት ትግራይና እንዲሁም የድምፅ ማጉልያና መኪና ያካራዩና ባለሙያዎች መሆናቸ የአይን አማኞች አረጋግጠዋል። 

ታሳሪዎቹ በቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ጣብያ ይገኛሉ ብለዋል የአይን እማኞቹ። 

የባይቶና ከፍተኛ አመራር አቶ ኪዳነ አመነ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው  "... 'ኪዳን ንሱር ቦቆስ ለውጢ ' በሚል በወርሃ ጳጉሜን እንዲካሄድ ለጠራነው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ሲያነሳሱ የነበሩ አባሎቻችን መታሰራቸው ለክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አባሎቻችን ያለ ቅድመ ሁነት በአንድ ሰዓት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ደብዳቤ ፅፈናል ። " ብለዋል። 

የመቐለ ከተማ አስተዳደር የተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ  ነሃሴ 25/2015 ዓ.ም ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ  ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በኢፌዴሪ አዋጅ ቁጥር  3/1991 የተቀመጠ መብት ቢሆንም የተመረጠው ጊዜ አዲስ አመትና ሃይማኖታዊ በአላት የሚበዙበት በመሆኑ ለማስተናገድ እቸገራሎህ ብሎ ነበር።

የከተማው አስተዳደር ለተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ፀጥታ የማስከበር  ግዴታና ሃላፊነት እንዳለበት በመጥቀስ ፤ ይሁን እንጂ በበዓሉ በሚኖረው የህዝብና የመኪና ሰፊ እንቅስቃሴ ምክንያት በሚፈጠር የስራ መደራረብ ምክንያት የቀረበውን ጥያቄ ማስፈፀም አልችልም በማለትም አክለዋል።

የተቋውሞ ሰልፉ የጠሩ 5 ቱ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የከተማ አስተዳደሩ ላወጣው መግለጫ በሰጡት ይፋዊ የፅሑፍ መግለጫ ስልፉ ለማድረግ የሚያግድ የህግ ማእቀፍ የለም በማለት መቀጠላቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።
      
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

በአዲሱ አመት በአዲስ ስልክ ማርሻችንን ወደ ስኬት! በ M-PESA እንክፈል በተመረጡ ስልኮች ላይ እስከ 20% ቅናሽ እናግኝ። በወሎሰፈር ፣ ቦሌ ፣ ጀሞ፣ መስቀል ፍላወር ወደሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች እንዲሁም ሚሊኒየም አዳራሽ በሚገኘው ባዛር ጎራ በማለት ለአጭር ጊዜ የሚቆየው ቅናሽ እንጠቀም!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#ኢትዮጵያ

አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ተጠየቀ።

ጥያቄውን ያቀረቡት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ነው።

እነዚህ ድርጅቶች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ነውጥ አዘል ግጭቶች የተቀሰቀሱት / የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባሕል በመኖሩ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉንም የማኅበረሰብ አካላት የሚያሳትፍ አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ (የሰላም ኮንቬንሽን) ተመቻችቶ የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ ጊዜ እና የረዥም ጊዜ ግጭትን የመከላከል፣ የመፍታት እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የሚጠናከሩበት አገራዊ ፍኖተ ካርታ እንዲዘጋጅ ይፋዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ የሲቨል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ  ፤ ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት እንዲሰፍን አበክረው ጠይቀዋል።

ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ (victim centered) የተጠያቂነት ስርዓት መስፈን በሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ፍትሕ የሚሰጥ ከመሆኑም ባሻገር፥ የበቀል እዙሪትን ለመግታት እና ለፍትሕ ተቋማት ተዓማኒነትም ዋልታ እንደሆነ ገልጸዋን።

- ለነውጥ አዘል ግጭቶች መንስዔ የሆኑ፣
- ሕዝባዊ እና ብሔራዊ ጥቅምን የሚጎዱ እና ሕጋዊ መሠረት የሌላቸው ውሳኔዎችን ያሳለፉ፣
- በነውጥ አዘል ግጭቶች ውስጥ በመሳተፍ ንፁኃንን ያጠቁ፣
- የጥላቻ ንግግሮችን እና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮችን በአደባባይ ያደረጉ እና ንፁኃንን ለጥቃት ያጋለጡ አካላት በነጻ እና ገለልተኛ የፍትሐዊ የምርመራ እና የዳኝነት ሒደት ተጠያቂ እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በሐቀኝነት እና ሕዝባዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ ወደ ተግባር እንዲገባና በሒደቱም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ዓለም ዐቀፍ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቶቹ የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም ዘንድ ጠይቀዋል።

" የጥላቻ ንግግሮች እና ግጭት ቆስቋሽ መልዕክቶች ነውጥ አዘል ግጭቶችን የሚያዋልዱ እና የሚያፋፍሙ መሆናቸውን ባለፉት ዓመታት አስተውለናል " ያሉ ሲሆን " የፖለቲካ ልኂቃን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የብዙኃን መገናኛተቋማት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች እና ሌሎችም የተዛቡ መረጃዎችን ከማሰራጨት፣ ብሎም ሕዝብን በጅምላ ከሚፈርጁ ወይም ግጭቶችን ከሚቆሰቁሱ እና ከሚያባብሱ የቋንቋ አጠቃቀሞች እና መልዕከቶች ራሳቸውን እንዲቆጥቡ " አሳስበዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ተጠየቀ። ጥያቄውን ያቀረቡት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ነው። እነዚህ ድርጅቶች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ነውጥ አዘል ግጭቶች የተቀሰቀሱት / የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባሕል በመኖሩ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። …
የአዲስ አመት የሰላም ጥሪ !

35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ፦

- አገር አቀፍ የሰላም መድረክ ይመቻች
- ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት ይስፈን
- ፆታዊ ጥቃቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጣቸው
- የተጋላጭ እና ግፉአን ጥበቃ ማዕቀፍ ይዘርጋ
- ሕዝባዊ ተሳትፎ ይረጋገጥ
- የቅድመ ግጭት መጠቆሚያ እና መከላከያ ስርዓት (Early warning System) ይኑር
- የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሳይስተጓጎል ይቀጥል
- የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም
- የሲቪክ ምኅዳሩ ጥበቃ ይደረግለት
- ባለድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ይወጡ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ጥሪያቸውን ያቀረቡት ዛሬ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሰጡት ይፋዊ መግለጫ ነው።

35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አዲስ አበባ ተመሳሳይ " የሰላም ጥሪ " ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ከመንግስት መጣን ባሉ አካላት መከልከላቸውና መግለጫቸውን በኦንላይን ለመስጠት መገደዳቸው ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ከላይ ያንብቡ።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia