TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ዓሲምባ የተባለው የፓለቲካ ፓርቲ " ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ " በሚል መፈክር ጳጉሜን 2 /2015 ዓ.ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ራሱን ማግለሉ አስታወቀ።
ፓርቲው ይህንን ያሳወቀው በሊቀመንበሩ አቶ ዶሪ አስገዶምና በፓርቲው በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨው መረጃ አማካኝነት ነው።
" የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ እንደሆነ የሚመለከታቸው አካላት በማስረጃ አስደግፈው አስረድተውናል " ያሉት ሊቀመንበሩ " ህግ ይከበር እያልን ህግ መጣስ ህዝባችንን ስለማይመጥን ከተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ራሳችን ለማግለል ወስነናል። ሁሉም ከህግ በታች ነው " ብለዋል።
መረጃው ከመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
@tikvahethiopia

#Update ዓሲምባ የተባለው የፓለቲካ ፓርቲ " ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ " በሚል መፈክር ጳጉሜን 2 /2015 ዓ.ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ራሱን ማግለሉ አስታወቀ። ፓርቲው ይህንን ያሳወቀው በሊቀመንበሩ አቶ ዶሪ አስገዶምና በፓርቲው በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨው መረጃ አማካኝነት ነው። " የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ እንደሆነ…
#Update
ጳጉሜን 2/2015 ዓ/ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ፓሊስ የፓርቲ አባላት እና አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቀጠሉን የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
በዚሁ መሰረት፦
- የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር ሃያሉ ጎዲፋይ ፣
- የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ.ር ደጀን በርሀ ፣
- የባይቶና ዓባይ ትግራይ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርሀ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ረፋድ 4:00 ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቀዋል።
ነሃሴ 30 / 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ላይ ገብረኣብ ወልዱና ብርሃነ ኣርኣያ ከሳልሳይ ወያነ ፣ ብርሃነ ዘመን ዮሃንስና ገብሩ ከባይቶና ፣ ጠዓመ ሓጎስና ኣፅብሃ ተኽለ ከውድብ ናፅነት ትግራይና እንዲሁም የድምፅ ማጉያያና መኪና ያካራዩና ባለሙያዎች ፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል።
መረጃው የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
More : @tikvahethiopiatigrigna

በቅበት የሆነው ምንድነው ?
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በስልጤ ዞን ውስጥ " ቅበት ከተማ " የሰው ህይወትን የቀጠፈ አለመረጋጋት መከሰቱን ለማውቅ ተችሏል።
ጉዳዩን በተመለከተ ምን ተባለ ?
የእስልምና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ የሚዲያ ምንጮች እንደገለፁት ከሆነ የችግሩ መነሻ " ተደርጓል በተባለ መተት / ድግምት ምክንያት የልጆች ጤና እየታወከ ፣ ከትምህርት ገበታቸውም እንዲርቁ እየሆነ ነው " የሚል ነው።
ይህንን መሰል ጉዳይ ከዚህ ቀደምም በቅበት ከተማ ሲስተዋል የነበረ ነው የሚሉት የአካባቢው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዚህም ምክንያት በ2015 ከ260 በላይ ተማሪዎች ቤታቸው እንዲውሉ ሆነዋል ሲሉ ጠቁመዋል።
ከሰሞኑን ደግሞ በቅበት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመዝገብ የሄዱ ተማሪዎች እራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት በከተማው የሱቅ ባለቤቶች ፣ የስራ ቦታ ያላቸው ሰዎች እና ወጣቶች ለዚህ ችግር መፍትሄ ነው በሚል በተለያዩ ቦታዎች ሞንታርቦ በሚባለው የድምፅ ማጉያ " ቁርዓን " በመክፈት ተከስቷል ያሉትን በሽታ ለመከላከል በሚሞክሩበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ሞንታርቦዎችን መሰብሰብ መጀመራቸውና ወጣትና አባቶችን መደብደብ መጀመራቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት ግጭት ተፈጥሮ የ1 ሰው ህይወት ጠፍቷል፤ በርካታ ወጣቶችም ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። በከተማው ውስጥ የሚገኝ " አብድልአዚዝ መስጂድ " መጎዳቱንም ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
በከተማው ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ግን የኦርቶዶክስ አማኞች ላይ ትንኮሳና ጥቃት መፈፀሙን የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት አሳውቋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ ሕይወት ንጉሴ ባወቀ ለቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ፤ በከተማይቱ ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተፈፅሟል ብለዋል።
" ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በአካባቢው ስላለው ጉዳይ ስንከታተል ነበር ፤ ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ አንዳንድ ትንኮሳዎች ነበሩ። ' የሙስሊም ልጆች ይወድቃሉ ' በሚል እነ እከሌ ደግመውባቸው ነው ፤ እንዲህ ተደርጎባቸው ነው በሚል ለኦርቶዶክሳዊነት እና ለትምህርቷ የማይመጥን ነገር እየሠጡ ካህናትን እየወንጀሉ ከጀርባ ሌላ ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች እንዲህ ሲያደርጉ ቆይተዋል " ብለዋል።
" ልጆች ይወድቃሉ፣ ታመውብናል፣ ይሄን ያደረጉት ኦርቶዶክሶች ናቸው። ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ፣ ባጃጅ የሚነዱ እነሱ ናቸው እየተባለ ማጥቃት፣ በሞተራቸው ሰው እንዳይገለገል ማድረግ ፣ ከጎረቤት መለየት ፣ ማግለል ሲደረግ ነበር በዚህም በብፁዕ አባታችን ፍቃድ ከዞኑ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ጋር ተወያየን ሀዋሳም ደብዳቤ አስገብተናል ይህን ነገር ተከታትለው እንዲያስቆሙ ጠይቀናል " ብለዋል።
" በኃላም ጉዳዩ ይበርዳል ብለን ስንጠብቅ ሞንታርቦ በየበራቸው አቁመው የመፈወሻ ትምህርት ነው ፀሎት ነው ብለው ነገር ግን የስድብ ፣ ኦርቶዶክስን የሚያጥላላ ፣ ሃይማኖትን የሚያንቋሽሽ ብዙ ነገር ማድረግ ጀመሩ ፣ ግለሰቦችንም እየያዙ መደብደብ ሲጀምሩ ነው የፀጥታ ኃይል ገብቶ ሞንታርቦውን አንሱ ልዩነት የሚፈጥር ነው ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው ፣ ድብደባውንም አቁሙ ብሎ ወደ እርምጃ ሲገባ ነው ለምን ይሄን ተባልን ብለው መንገድ መዝጋት የጀመሩት። መንገዱን ለማስከፈት የፀጥታ ኃይል ሲሞክር ወደ ፀጥታ ኃይሉ ጥቃት ተጀምሮ ነበር " ሲሉ ተናግረዋል።
" የነበረው የፖሊስ ኃይል ጥቂት ስለነበር እነሱ ዞር ሲሉ ወደ ምዕመናን ቤት ጥቃት ተሰንዝሮ 13 ቤቶች እና ንብረቶቻቸው መኖሪያ፣ ሆቴል፣ ሱቅ ተሰብረው ተዘርፈው ተቃጥለዋል ፤ ፈርሰዋል። ይሄን ለምን አስቆማችሁ በሚልም የአመራሮችን ቤቶች የማፍረስ እና የማቃጠል ተግባር ተፈፅሟል " ብለዋል።
ይህ ሁኔታ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይመጣ የሰዎችም ህይወት እንዳይጠፋ ስጋት ስላለ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥት ከለላ እንዲያደርጉ መጠየቁን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
የቅበት ከተማ አስተዳደር ምን አለ ?
አስተዳደሩ ባወጣው መግለጫ ፤ በህዝቡ መካከል ያለውን የዘመናት አብሮነትና አንድነት ሊሸረሽሩና ሊያቃቅሩ የሚችሉ ፀብ አጫሪ ጉዳዮች አልፎ አልፎ እየተከሰቱ ነው ብሏል።
ከትላንት በስቲያ የተፈጠረውን ችግር " የሀይማኖት መልክ " ለመስያዝ ጥረት ቢደረግም በሃይመኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች፤ በወጣቶችና በፀጥታ አካላት ትብብር ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
ግጭቱ የአካባቢውንና የስልጤ ህዝብ የዘመናት እሴት የማይገልፅ ነው ብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ግጭት የሚፈጥሩ አካላትን ለይቶ በማውገዝ ፤ ጉዳዩ እንዲባባስና ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄድ ሩቅ ሆነው በተሳሳተ መንገድ እያራገቡ ያሉ አካላትን ህዝቡ ሊታገላቸው ይገባል ብሏል።
በተፈጠረው አለመግባባት የአንድ / 1 ሰው ህይወት ማለፉን ያረጋገጠው የከተማው አስተዳደር 3 ሰዎች በቅበት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና 6 ሰዎች በወራቤ ኮ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል።
በተፈጠረው ግጭት በንብረት ላይም ውድመት መድረሱን ገልጷል።
ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ አለመግባባቱ ሰፍቶ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ አስተዋዕፆ ማበርከታቸውን ጠቁሟል።
አጠቃላይ በተፈጠረው ጉዳዩ ዙሪያ የቅበት ነዋሪዎች ተቀራርቦ በመወያየት ለመፍትሄው በጋራ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

ስለ መምህራን ጥያቄ ምን ተባለ ?
የዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ " በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ " መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች መግለጻቸውን የማኅበሩ አመራሮች ተናገሩ፡፡
አመራሮቹ ይህን ያሳወቁት ትላንትና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመምህራን እና በሀገር ጉዳይ ከተወያዩ በኃላ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።
የማህበሩ ፕሬዜዳንት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፤ እንደተለመደው አሠራር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን በሚሠሩበት አካባቢ የመኖሪያ ቦታ የማግኘት አሠራሩ የሚቀጥል ሆኖ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን መኖሪያ ቤት በሚመለከት ግን ውይይት እየተደረገበትና ጥሩ ምላሽ ሊገኝ እንደሚችል እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡
" የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት ጥያቄን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን ዕልባት እንዲያገኝ እየተሠራበት እንደሆነ ነው የተገለጸልን " ሲሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላገኙት ምላሽ አስረድተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከዚህ በፊት ሲያነሱት ስለነበረው #የደመወዝ ጥያቄን በሚመለከት ማኅበሩ አንደኛው ይዞት የሄደው ጉዳይና የተወያየበት ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ ለደመወዝና መሰል ጥያቄዎች በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንዳደረጉባቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል፡፡
የደመወዝ ጭማሪውን በሚመለከት፣ የኑሮ ውድነትን በአጠቃላይ የማቅለል ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹላቸው፣ ይህንንም ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ በውይይታቸው ላይ እንደተነሳ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
የማኅበሩ አመራሮችም ስለ ደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለማግኘት ጠብቀው እንዳልሄዱም ተናግረዋል፡፡
" ማናችንም ደመወዝን በሚመለከት ‹ከዛሬ ጀምሮ ይህን ያህል ጨምረናል› የሚል መልስ አንጠብቅም፡፡ ችግሩ እንዳለና ትኩረት ተሰጥቶ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲፈጽም ነው ያነሳነው " ሲሉ የማህበሩ ፕሬዜዳንት ገልጸዋል።
የማኅበሩ አመራሮች ከመምህራን ጥያቄዎች በተጨማሪ ፦
- የሙያ ጥያቄና የመምህርነት ሙያ ምንነትን በሚመለከት፣
- የት/ቤቶች አቅምና ግብዓት ፣
- ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠርን በሚመለከት
- ማህበሩ ለመገንባት ስላቀደው ህንፃና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

#Update ጳጉሜን 2/2015 ዓ/ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ፓሊስ የፓርቲ አባላት እና አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቀጠሉን የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል። በዚሁ መሰረት፦ - የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር ሃያሉ ጎዲፋይ ፣ - የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ.ር ደጀን በርሀ ፣ - የባይቶና ዓባይ ትግራይ ከፍተኛ አመራር…
#Update
የታሰሩ 3 የፓለቲካ አመራሮች ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ተፈተዋል።
ጳጉሜን 2/2015 ዓ/ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ፦
- የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር ሃያሉ ጎዲፋይ ፣
- የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ.ር ደጀን በርሀ ፣
- የባይቶና ዓባይ ትግራይ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርሀ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ረፋድ 4:00 ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸው መገለፁ ይታወቃል።
አመራሮቹ ከሰዓታት እስር በኋላ መፈታታቸውን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

#itel_Ethiopia
itel 23+ በልዮነት እና በጥራት ቀርቦሎታል !
ከዘመኑ ጋር አብሮ ለመራመድ አዲሱን የአይቴል S23+ ሞዴል በእጆ ያስገቡ።
ለእይታ ማራኪ፣ ለአያያዝ አመቺ እና ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ በልዮ ዲዛይን ውበትን በማላበስ የተመረተው አዲሱ የአይቴል ኤስ23+ ሞዴል በየተኛውም ቦታ እና በማንኛውም ጊዜ የሚተማመኑባቸውን ካሜራ፣ እስክሪን፣ ሜሞሪ እንዲሁም ከፍተኛ የባትሪ አቅምን የካተተ ነው። አስደናቂ 6.78 ኢንች ኤፍ ኤችዲ+ አሞልድ ከርቭ ስክሪን፣የፊት ለፊት 32ሜጋ ፒክስል እና የኃላ 50ሜጋ ፒክስል ካሜራ፣ 16ጂቢ ራም ከ 256ጂቢ የሜሞሪ ጋር በማጣመር ለእርሶ ቀርቧል።
አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us : Facebook Instagram

#ሌዘርቴክ_ዲዛይን
ሌዘርቴክ ዲዛይን የቤት፣ የቢሮ፣ የህንፃ ፣ የሪል ስቴት፣ የአፓርትመንት የተለያዩ የሜካኒካል እና የአርክቴክቸር ብረታ ብረት ስራዎችን ያቀርባል።
በዋናነት ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል
✅Handrail, Gates & Fences
✅Wall art & Logo/Adverts
✅Partitions & Facades
✅AC Installation & Garbage Chutes
ስልክ : 0970094777 / አድራሻችን : መስቀል ፍላወር ከdreamliner hotel አጠገብ፤ ቻናሉን ይቀላቀሉ : t.iss.one/lasertechethiopia
ለበለጠ መረጃ Contact : @lasertech_design
Website : lasertechplc.com
ፈጠራ, ጥራት እና ፍጥነት የስራችን መሰረት ነው!

" ሰላማዊ ሰልፍ መፍቀድና መከልከል የሚባል ነገር የለም ፤ ማሳወቅ ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው ። የሚካሄድበት ቦታ መምረጥ የመንግስት ስራ ነው " ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ መጪው አዲስ ዓመት 2016 ዓ.ም በማስመልከት ለሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት " ሰልፍ እንዳይካሄድ ተብሎ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ ነገ ሰልፍ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ የለም " ብለዋል።
" ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ አይደለም እየከለከልን ያለነው ፤ ተጨባጭ የሆነ የፀጥታ ስጋት ስላለብን ነው እንዳይካሄድ የከለከልነው " ሲሉ አክለዋል ፕረዚደንቱ።
" ሰልፍ ማድረግ መብታቸው መሆኑ ተግባብተናል " ያሉት ፕረዚደንቱ ፤ " ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ሰልፍ ለማካሄድ አይፈቅድም " ብለዋል።
" የሚገርመው ከሰላማዊው ሰልፉ ጋር ተያይዞ ትግራይ ለማፈራረስ የሚሰሩ አካላት ሳይቀር የዴሞክራሲ አዋላጆች ሆነው እየታዩ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው፤ " በትግራይ ላይ የተፈፀመው ጄኖሳይድ እንዲፈፀም ዋና ተዋናይ የነበሩት የሰልፉ ተቆርቋሪና ቀንደኛ አስተባባሪ ሆነዋል " ብለዋል።
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያልፈቀደው ሰላማዊ ሰልፍ ፤ በህገ-መንግስቱ የተቀመጠው መብቶቻችን እንጠቀማለን ያሉት የ5 ቱ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ለጳጉሜን 2/2015 ዓ.ም የጠሩት ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ እንደሚያካሄዱ መወሰናቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በተከታታይ ዘግቧል።
ነሃሰ 30 / 2015 ዓ.ም ተፎኳኳሪ ፓርቲዎቹ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ የቅስቀሳ ስራ እያካሄዱ አባሎቻቸው ቁሳቁሳቸውና የሚቀሰቀሱበት መኪና ጭምር ፓሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ዘግበናል።
ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ በጥምር ለማካሄድ ከወሰኑ 5 የፓለቲካ ፓርቲዎች የሶስቱ ከፍተኛ አመራሮች በቅስቀሳ ላይ ሳሉ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ከጥቂት ሰአታት እስር በኋላ የተለቀቁ ሲሆን ፤ከሰአት በኋላ 10:35 አከባቢ የቅስቀሳ ወረቀቶች እየለጠፉ ፓሊስ በድጋማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቲካቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በቦታው በመገኘት ታዝበዋል።

#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጷጉሜን 3 እስከ 5 ሁሉም የእምነት ተቋማት በየቤተ እምነታቸው የጸሎት መርሐ ግብር እንዲያካሂዱ ጥሪ አቅርቧል።
ጥሪውንም የሃይማኖት ተቋማት ተቀብለው ለምዕመናን እያሳወቁ ናቸው።
ጷጉሜን 5 ቀን 2015 ዓ/ም በወዳጅነት አደባባይ በጋራ ጸሎት የሚያደርጉበት መርሐ ግብር መዘጋጀቱ የተነገረ ሲሆን በመርሐ ግብሩ የየቤተ እምነቱ የሃይማኖት አባቶች መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ፤ ሁሉም ልጆቿ አዲሱን ዓመት ከዳንኪራ እና ከዘፈን በመራቅ በጸሎት ፣ በምህላ የቻለም በመጾም እና እግዚአብሔርን በመለመን እንዲያሳልፉ ጥሪ ማቅረቧ ይታወቃል።
ቤተክርስቲያኗ ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘን የሚሰማበት ዘመን ስለሆነ ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ ፤ በዚህ ወቅት ከዘፈን እና ከዳንኪራ እንዲርቁ ማሳሰቧ አይዘነጋም።
ሀገር በሚያልቀስበት፣ የንፁሃን ደም በሚፈስበት ፤ ሰቆቃ በበዛበት ረሃብ ችግር በሰፈነበት አስቸጋሪ ወቅት እየቀረቡ ላሉት የዘፈን እና የዳንኪራ ግብዣዎች ጆሮ ባለመስጠት በጾም ፤ በጾሎት አዲሱን ዓመት እንዲቀበሉ መላው ልጆቿን በጥብቅ አሳስባለች።