TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሽንኩርት

በቤንች ሸኮ ዞን የደቡብ ቤንች ወረዳ ገበሬዎች ለሚያመርቱት የሽንኩርት ምርት የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።

በተለያየ ጊዜ ሽንኩርት በሀገሪቱ ያሉ ገበያዎች ላይ ከዋጋዉ መናር ባለፈ የአቅርቦት ችግሩም ጎልቶ ሲነሳ ይታያል።

በቤንች ሸኮ ዞን የተመረተው የሽንኩርት ምርት ግን የሚያነሳዉ አጥቶ ሊበላሽ መሆኑ ገበሬዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተናግረዋል።

ዞኑ በኩታ ገጠም አሰተራረስ ስልት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ዉጤታማ ከሆኑ ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን የደቡብ ቤንች ወረዳ ደግሞ ግንባር ቀደም ነው።

ይሁንና የገበያ ትስስር አለመኖሩ ሽንኩርቱ ከማሳ ሳይነሳ ይቆይ ዘንድ ምክንያት ሆኗል።

በመሆኑም የወረዳዉ ገበሬዎች ሽንኩርቱ ከመበላሸቱ በፊት የሚመለከተዉ አካል ለኛም ሆነ በሀገር ደረጃ ፋይዳ ያለውን ሸንኩርት እንዲነሳ እንዲያደግ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ አመት በሰሩት ጠንካራ ስራ በሄክታር 1200 ኩንታል ሽንኩርት መገኘቱንና ባጠቃላይ 1622 ሄክታር መሬት በምርት መሸፈናቸዉን ገልጸዋል።

የገበያ ትስስሩን በተመለከተ በተደጋጋሚ መጠየቃቸዉን የሚገልጹት ገበሬዎቹ በዚህ ምክኒያት ችግር ላይ መዉደቃቸዉን ያነሳሉ።

የደቡብ ቤንች ወረዳ አስተዳደር  በበኩሉ የዞንና የክልል የንግድ ማህበራት እንዲሁም  በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነጋዴዎች ፣ በተማሪ ምገባ ፕሮግራም የሚሳተፉ ትምህርትቤቶችና የከተማ መስተዳድሮች  የሰንደይ ማርኬቶች ሽንኩርቱን በማንሳት ገበሬዉን በማገዝ ራሳቸዉም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጥሪዉን ያስተላለፉት የወረዳዉ ም/ አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ተስፋዬ እንደገለጹት ባካባቢዉ ካሁን በፊት ባልነበረ መልኩ ከፍተኛ የሽንኩርት ምርት መመረቱን ጠቅሰዉ ለገበሬዉ የንግድ ትሰስር ለመፍጠር አየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ቤተሰብ ሀዋሳ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ዜጎች በኑሮ ውድነት / በዋጋ ንረት ምክንያት ክፉኛ እየተማረሩ፤ እየተቸገሩ ይገኛል።

በተለይም የምግብ ነክ ምርቶች ላይ በየጊዜው የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ዜጎች ኑሯቸውን ከባድ ካደረገው ቆይቷል።

ከምንም በላይ በዚህ ወቅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ተስኗቸዋል።

ልጆች ወልደው ለማሳደግ ፣ ለማስተማር፣ ፣ በልቶ ለማደር፣ ህልማቸውንና ሀሳባቸውን ለማሳካት በየጊዜው አየናረ ያለው የኑሮ ውድነት ለዜጎች እንቅፋት ሆኗል።

የዋጋ ንረትን በተመለከተ አሀዱ ሬድዮ ዛሬ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ጠቅሶ ባሰራጨው አንድ ዘገባ ላይ ፤ ሚኒስቴሩ " የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠንና የፀጥታ ችግር ለንግድ ስርአቱ እንከን ሆኖበታል " ብሏል።

ህዝቡን እያማረረ ላለው የኑሮ ውድነት ምክንያት " በክልሎች የሚፈጠረዉ የሰላም መደፍረስ እንዲሁም የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን " እንደሆነ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በልሁ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

" መንግስት የኑሮ ዉድነት እንዳለ ያምናል " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዉ " ፍላጎትን የሚያሟላ አቅርቦትን ለማከናወን ከዉጭም ከዉስጥም ያለዉ ችግር እንከን ሆኗል " ብለዋል።

ሆኖም እነዚህ ተግዳሮቶች እንዳሉ ሆነዉ፤ ህብረት ስራ ማህበራት በቀጥታ ከቦታዉ ምርት አምጥተዉ እንዲያሰራጩ ስምምነት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
መላው የኦርቶዶክስ ልጆች አዲሱን ዓመት በዘፈንና ዳንኪራ ሳይሆን በቤተክርስቲያናቸው በጸሎት ፣ በምህላ፣ የቻለም ደግሞ በመጾም፣ እግዚአብሔርን በመመለመን እንዲቀበሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አስተላለፈች።

ቤተክርስቲያን ይህን ጥሪ ያስተላለፈችው የአዲሱን ዓመት አቀባበል በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ ነው።

በዚህም የጷጉሜን ወር ፮ ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ ታውጇል።

ቤተክርስቲያን ፤ ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ ስትል ጥሪዋን አቅርባለች።

ምዕመናን በዚህ ወቅት ከዘፈን እና ከዳንኪራ እንዲርቁ አሳስባለች።

ብፁህ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ ፤ " አንዳንድ የዘፈን ግብዣዎችን እየሰማን ነው ፤ ሀገር በሚያልቀስበት፣ የንፁሃን ደም በሚፈስበት ሰቆቃ በበዛበት ረሃብ ችግር በሰፈነበት የዳንኪራ ግብዣ እየሰማን ነው " ብለዋል።

" ለምንም የማይጠቅሙ ብዙ ነገሮች እየተስተጋቡ ነው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይህን እየሰማን ያለነው መደፋፈሩ በዝቶ ፣ ከመጠን በላይ ኑሮ፣ ንቀቱ በዝቶ፣ ማንአለብኝነቱ እንደልብ ተናጋሪው ፣ ፀብ አጫሪው ሃይ የሚለው ጠፍቶ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው አለኝ ባሉት መረጃ " ቤተክርስቲያን ዘቅዝቆ እሳት ያያያዘ ፣ መስቀል ዘቅዝቆ አንገቱ ላይ ያጠለቀ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊዘፍን ተዘጋጅቷል፤ ግብዣም ተደርጓል። " ብለዋል።

" የሰዎችን መብት መንካት ስለማንችል እንደ ኢትዮጵያውያን እገሌ እገሌ ሳይል ከእንዲህ አይነቱ ማንም ተካፋይ ሳይሆን እንደ ኦርቶዶክሳዊያን ዳግሞ የኦርቶዶክስ ልጆች ለፀሎት ታውጇል ፣ ለጾም ለጸሎት እራስን ከማዘጋጀት ውጭ ምንም ትርፍ የሌለው ከሳንቲም ውጭ ትርፍ ለሌለው የሀገርን ገፅታ የሚንድ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከመሆን #እንድትቆጠቡ " ብለዋል።

" አባቶቻችን ቅድሚያ የሚሰጡት ለጾም ፣ለጸሎት ለፍቅር፣ ለሰላም ነው ፤ ውሃ ሙላት እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚሉት አባቶች በዘፈን እና በዳንኪራ እያሳሳቀ ወደ ሞት፣ ወደ ማዕበሉ የሚገፋ ነገር ላይ ተሳታፊ እንድንሆን ቤተክርስቲያን አትፈቅድም ፣ የሃይማኖት ሰዎችም ድርሻ አይደለም " ሲሉ አስግዝበዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " እኔ ምን አገባኝ በሚል በዘመናዊ ስሜት እንደልብ ተካፋይ መሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ነውር ነው ፤ ወንጀልም ነው " ያሉ ሲሆን " ፀብ አጫሪ መሆንም አስፈላጊ ስላልሆነ የኦርቶዶክስ ልጆች በቤታችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ተቀመጡ፤ የሚመለከተው እንደፈለገ ይሁን ፤ ኦርቶዶክሳውያን ከቤተክርስቲያናችሁ ተገኝታችሁ ጸልዩ፣ እግዚአብሔርን ለምኑ አብረን ተያይዘን እንዳንጠፋ " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በጳጉሜን 6 ቀናት ሁሉም ምዕመናን እግዚአብሔር መጪውን ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ የአንድነት፣ ብሶተኛ የማይኖርበት ተራብኩ ተጠማሁ ተፈናቀልኩ ተሰቃየሁ ተንገላታሁ የሚል የማይኖርበት ፣ ኢትዮጵያውያን በፍቅር በአንድነት የምንኖርበት ዘመን እንዲሰጠን ጸሎት በማድረግ እናሳልፍ ስትል አደራ ብላለች።

ጸሎት ለሁሉም የታወጀ ሲሆን ፤ ጾምን በተመለከተ የወደደ ይጹም ፤ ያልወደደም / ፕሮግራሞች ቀደሞ የያዘም እንዲጾም አይገደደም በነፃነቱ መጠቀም ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

ለመጪዎቹ የአዲስ አመት፣ የመስቀልና የመውሊድ በዓላት ከውጭ አገራት በአቢሲንያ ባንክ በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ ሲቀበሉና ሲመነዝሩ የሞባይል አየር ሰዓት ያገኛሉ።
ከነሐሴ 26 ቀን 2015 እስከ መስከረም 19 ቀን 2016 የሚቆይ።

#holiday #newyear #Ethiopiannewyear #finance #transfer #Visa #Mastercard #BankofAbyssinia #BankingService #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
🌼10% ስጦታ🌼

ለአውደ ዓመት ወዳጅ ዘመድ ከባህር ማዶ በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር ዓለም-አቀፍ ሃዋላ የበዓል መዋያ ሲልክልዎ፤ የተላከልዎትን መጠን 10% በስጦታ ያገኛሉ!

🌼 መልካም አዲስ ዓመት!🌼
#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል

የፕሪቶሪያ የ ' ሰላም ስምምነት ' ከተፈረመ በኋላ የ " ኤርትራ ወታደሮች " በትግራይ ወሲባዊ ባርነት ፣ ግድያዎችን እና ሌሎች ከባድ ጥሰቶች መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

- ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ምድር ወሲባዊ ባርነት፣ ግድያ፣ ከባድ ጥሰቶችን ፈፅመዋል።

- የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት መድፈር፣ ሴቶችን ለወራት ለወሲባዊ ባርነት መዳረግ፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ ዘረፋዎችን እየፈጸሙም እንደሆነ ተገልጿል።

- የተፈፀሙት ጥሰቶች የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ሊሆን ይችላል።

- ሸዊቶ በተሰኘች ወረዳ ቢያንስ 20 ነዋሪዎች በዋነኝነት ወንዶች ከጥቅምት15 - ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ወቅት በኤርትራ መከላከያ ኃይል መገደላቸውን ገልጿል።

- የፕሪቶሪያው  ስምምነት ከተፈረመ በኃላ የኤርትራ መከላከያ ኃይል ወታደሮች 24 ሰላማዊ ነዋሪዎችን በኮኮብ ጽባህ ወረዳ መግደላቸውን ሪፖርት ተደርጓል።

- አምነስቲ በኮከብ ጽባህ የተደፈሩ እና ለወሲባዊ ባርነት ተዳርገው የነበሩ 11 ሴቶችን  አነጋግሯል። ከ40 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችም እንደተደፈሩ እና ለወሲባዊ ባርነት እንደተዳረጉ ለአካባቢው ለሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ መናገራቸውም ሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።

ሙሉ ሪፖርቱ በዚህ ይገኛል ፦ https://www.amnesty.org/en/latest/news/2023/09/eritrean-soldiers-committed-war-crimes-and-possible-crimes-against-humanity-in-the-tigray-region-after-signing-of-agreement-to-end-hostilities/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ ሰልፉን እንደምናካሂደው ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን " - ሶስቱ ፓርቲዎች ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ፣ ትግራይ ውድብ ናፅነት ትግራይ ለመቐለ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ሰጡ። ፓርቲዎቹ ፤ በቀን 24 ቀን 2015 ዓ.ም በትግራይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት " ኪዳን ንሱር ቦቆስ ለውጢ " በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜን…
#Update

5ቱ የትግራይ የፓለቲካ ፓርቲዎች 
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ
ውድብ ናፅነት ትግራይ
ባይቶና ዓባይ ትግራይ
ዓረና ንሉኣላውነትን ንዴሞክራስን
ውድብ ዓሲምባ
ከጳጉሜን 2 እስከ 4 /2015 ዓ.ም በጥምር ለሚያካሂዱት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በመቐለ ከተማ በመኪና በመዞር በድምፅ ማጉልያ በመታገዘ እየቀሰቀሱ መሆናቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታዝቧል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ቀደም የተቃውሞ ሰልፉን በተመለከተ ከፓርቲዎቹ በተላከለት " የእወቁልኝ " ደብደቤ በሰጠው ምላሽ ሰልፍ ማድረግ በኢፌዴሪ አዋጅ ቁጥር  3/1991 የተቀመጠ መብት ቢሆንም የተመረጠው ጊዜ አዲስ አመትና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚበዙበት በመሆኑ ለማስተናገድ እንደሚቸገር ማሳወቁ ይታወሳል።

አስተዳደሩ ፤ ለተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ፀጥታ የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት እንዳለበትም ቢገልጽም በበዓሉ በሚኖረው የህዝብና የመኪና ሰፊ እንቅስቃሴ ምክንያት በሚፈጠር የስራ መደራረብ ምክንያት የቀረበውን ጥያቄ ማስፈፀም እንደማይችል ማስታወቁ አይዘነጋም።

ለከተማው አስተዳደር ምላሽ የሰጡት ፓርቲዎቹ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ምክንያት አሳማኝ ባለመሆኑ ሰልፉን በተያዘው ጊዜ እንደሚያካሂዱ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
እናንተም መሆን ትችላላችሁ!

የጃሲሪ ታለንት ኢንቨስተር በተለያየ የንግድና ስራ ፈጠራ ስራዎች ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ስራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ክህሎትን ያስታጥቃቸዋል፡፡

“ለምን?” የሚለውን ጥያቄዎን ከማወቅ አንስቶ ፣ የቡድን አደረጃጀት፣ እድልን መለየት፣ የሲስተም አስተሳሰብ ፣በሃላፊነት የተሞላ ስራ ፈጣሪነትና አስከ ንግድ ስራ ፈጣሪነት ሁሉንም እውቀት ይጨብጣሉ፡፡

አሁኑኑ ለ Cohort 5 በመመዝገብ የስራ ፈጠራ ጉዞዎን ያፋጥኑ፤ ይመዝገቡ https://jasiri.org/application

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/jasiri4ethiopia
#itel_mobile

የሚማርክ ዲዛይን እና ልዪ የስክሪን ቅርፅን በማካተት አዲሱ itel S23+ ቀርቧሎታል!

አዲስ የሆነው የአይቴል ሞባይል S23+ ሞዴል የምስል ልቀትን ወደ አዲስ ከፍታ እንዲወስድ ታስቦ አስደናቂ 6.78 ኢንች ኤፍ ኤችዲ+ አሞሌድ ከርቭ ስክሪን የተገጠመለት ሲሆን በግራ እና በቀኝ ጫፎቹ 59 ዲግሪ ከርቭ ዲዛይኑ እጅግ ማራኪ የሆነ ምስልን እንዲያሳይ ያደርገዋል። የጣት አሻራ ቴክኖሎጂን ያካተተ፣ የደህንነት መቆለፊያ የሚጠቀም እንድሁም ለአያያዝ አመቺ እና ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ በልዮ ዲዛይን ውበትን ተላብሶ ለእርሷ ቀርቧል።

አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us :  Facebook Instagram