TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ዛሬ በዎላይታ ዞን ሲካሄድ የዋለው ያድጋሜ የሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒድት መጠናቀቁ ተገልጿል።

አሁን ላይ በየምርጫ ጣቢያዎቹ የድምጽ ቆጠራ እየተከናወነ  እንደሚገኝ ተነግሯል።

በነገው ዕለት ማለዳ የቆጠራው ውጤት ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሕዝብ ፍሰት በመኖሩ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ተራዝሞ መጠናቀቁን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ዋቢ በማድረግ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ NEBE

@tikvahethiopia
የወልቃይት ጉዳይ !

ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ከቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ጋር ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

በዚህ ቃለምልላሳቸው ፦

- ስለ ማንነት ጥያቄ
- ስለ በጀት
- ስለ ተጠያቂነት
- ስለ ተፈናቃዮች ጉዳይ
- በእሳቸው ላይ ስለሚቀርቡ ክሶች
- ስለ ፖለቲካ ውሳኔ / ህዝበ ውሳኔ
- ስለ ውይይት ጉዳዮች ተነስቶላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ምን አሉ ?

የማንነት ጉዳይ ፦

" እኛ የእናት ቋንቋችን አማርኛ ነው፣ ባሕላችን አማራ ነው ፤ ሥነ ልቦናችን የጎንደር ማኅበረሰብ ነው።

ስለዚህ ታሪካችን እና ማንነታችን ከጎንደር ጋር እንጂ ከትግራይ ጋር የተሳሰረ አይደለም።

በ ' ህወሓት ' የበላይነት ይመራ የነበረው የፌደራሉ መንግሥት ጥያቄያችንን ለማፈን በማኅበረሰቡ ተወካዮች ላይ እንግልት እና እስር ፈፅሟል።

ሐምሌ 05/2008 ዓ.ም. እኔ የምገኝበት የኮሚቴ አባላት አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ ወደ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተሸጋግሮ ነበር።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሁኔታዎች በየጊዜው እየተቀያየሩ አሁን ላይ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በአብላጫው የተሳተፈበት አስተዳደር ተመስርቶ አካባቢያችንን እያስተዳደርነው እንገኛለን።

የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄውን ለማስመለስ ጥረት ያደረገው ገና ህወሓት የትጥቅ ትግል በማካሄድ እያለ ጀምሮ ነው።

የአካባቢው ማኅበረሰብ ‘ከፋኝ’ በሚል አደረጃጀት የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ነበር።

ከመስከረም 2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ከትግራይ ክልል እና ከፌደራል መንግሥቱ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምላሽ እንዲሰጠን ስንጠይቅ ነበር። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-AMHARIC-06-19
በአቢሲኒያ ባንክ የከፍተኛ ትምህርት ቁጠባ የትምህርት ግቦችዎን ዛሬ ያሳኩ። የባንካችንን የትምህርት ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ይጠቀሙ፣ከፍተኛ ወለድ ያግኙ።

#BankofAbyssinia #BankingService #BankinginEthiopia #SavingAccount #EducationSaving #HigherEducation #TheChoiceForAll #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthioOnlineMarket

የተለያዩ ለኑሮ ጠቃሚ የሆኑ እቃዎችን ለማየት : https://t.iss.one/EOMMarket

የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ  እናደርሳለን : 𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲  ☞0929181818 / 0909868788

ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !
አድራሻችን፦
• ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ
                 ቁጥር  G-10 ግራውንድ 
•ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ  
                ቁጥር #338
•ቁጥር 3:- አያት አደባባይ , AAT CITY   
                  CENTER G-11 ግራውንድ
𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 @EOMmarket
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቮልስዋገን

" ከቻይና ውጪ ያሉ ደንበኞች ለተሸከርካሪዎቹ የዋስትና መብት አያገኙም " - ቮልስ ዋገን

ባለፈው ሳምንት ID 4 እና ID 6 ክሩዝ የተባሉ የታዋቂው የጀርመን መኪና አምራች ቮልክስዋገን ስሪት የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ እግድ መተላለፉ ይታወሳል።

ቅንጡዎቹ መኪኖች ለኢትዮጵያ ገበያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይቀርቡ የታገዱት በመኪና አምራቹ ጥያቄ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አማካይነት ነው።

ጉዳዩን በተመለከተ #ቮልስዋገን ለቢቢሲ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ምን አለ ?

" ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ እግድ እንዲያጣል የተደረገው በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ነው።

በቻይና የሚመረቱ የቮልክስዋገን ID.4፣ ID.6 X እና ID.6 CROZZ የተባሉት መኪኖች መቅረብ ያለባቸው #ለቻይና ገበያ ብቻ ነው ፤ መኪኖቹ ከቻይና ውጪ እንደማይሸጡ በሕግ ተደንግጓል።

ከዚህ በተጨማሪ ለቻይና ተብለው የተሰሩ ቮልክስዋገን ID መኪኖችን ከቻይና ውጪ ያሉ ደንበኞች የሚገዙ ከሆነ ለተሸከርካሪዎቹ የዋስትና መብት አያገኙም። " ብሏል።

ቮልስዋገን ፤ ሕጋዊ ፍቃድ የሌላቸው መኪና ሻጮች፣ መኪኖቹ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዳላቸው በመግለጽ ለደንበኞቻቸው እየሸጡ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ሲልም ገልጿል።

ነገር ግን ID 4፣ ID 6 X እና ID 6 ክሩዝ ለቻይና ብቻ ተብለው የተመረቱ በመሆናቸው መኪኖቹ ከቻይና ውጪ የሚያስፈልጋቸው ዋስትና የላቸውም ብሏል።

እነዚህ ከእውቅና ውጪ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የተባሉት መኪኖች በኢትዮጵያ " የቮልክስዋገን እውቅና ባላቸው ሻጮች ወይም ቮልክስዋገን ባጸደቃቸው ሰርቪስ ማድረጊያ ተቋማት ውስጥ ሁሉንም አይነት የመኪና ‘ሰርቪስ’ እና የጥገና አገልግሎት ሊያገኙ አይችሉም " ሲል አሳውቋል።

ፍቃድ የሌላቸው ሻጮች እነዚህን መኪኖችን ሕጋዊ እና ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በተደጋጋሚ በሌሎች አገራት ለመሸጥ እየሞከሩ መሆኑን የገለፀው ቮልስዋገን ፤ ደንበኞች መኪኖችን ከመግዛታቸው በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ኩባንያው አገራት እነዚህን መኪኖች ወደ አገር ውስጥ እንዳያስገቡ ማሳሰቢያዎችን እያላከ መሆኑን ገልጾ፤ " ደንበኞች ID መኪኖችን ሲገዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ከሕጋዊ ወኪሎች ብቻ እንዲገዙ ያሳስባል " ብሏል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

(የሕዝብ ትራንስፖርት እና አሸከርካሪ ተሽከርካሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ከድልማግስት ኢብራሂም)

" መኪኖቹን ያገድነው ለኢትዮጵያ መንገዶች ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ስለሚኖርብን ነው።

ተሸከርካሪዎቹ የደኅንነት ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ብለን አናስብም፣ ይሁን እንጂ በቅርብ ቀናት ከኤምባሲው ጋር ተነጋግረን ለሁሉም መልስ እንሰጣለን። "

መኪኖቹ በኢትዮጵያ ገበያ እንዲቀርቡ ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው እንዴት ከቻይና ሊመጡ ቻሉ ?

" የእግድ ጥያቄው ከኩባንያው የመጣው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት የሚቻልባቸው መመሪያዎች እና ደንቦች እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስገቢያ ፍቃድ ገና በዝግጅት ላይ ነው።

ከዚህ በፊት ወደ አገር ውስጥ የገቡ የኤሌክትሪክ መኪኖች በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ሲሰተናገዱበት በነበረው መመሪያ ነው።

አሁን ላይ ወደ አገር ቤት ገብተው ለሽያጭ ያልቀረቡትን ቮልክስዋገን መኪኖችን በተመለከተ ለመነጋገር ከጀርመን ኤምባሲ ጋር በዚህ ሳምንት ቀጠሮ አለን። "

Via BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
* አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም  ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ያስታወሰው አስተዳደሩ፤ ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 /2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአ/ አ ቤተሰቦቹ በደረሰው መልዕክት ከጣራ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አከራዮች " ከፍተኛ ግብር ተጥሎብናል " በማለት በተከራዮቻቸው ላይ ከፍተኛ የኪራይ ጭማሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ለአብነት አንድ የንግድ ተቋም ፤ የተጣለብኝን ከፍተኛ ግብር አሁን ባለው ኪራይ መሸፈን ስለማልችል ብሎ በተከራዮች ላይ  60% ጭማሪ እንደሚደረግ በመግለፅ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስቧል።

ሌሎች በተመሳሳይ " ከፍተኛ ግብር ተጣለብን " በማለት ተከራዮቻቸው ላይ የኪራይ ገንዝብ እየጨመሩ እንደሆነና ይህን የማያደርጉትንም እንደሚያስወጡ እየገለፁ እንደሚገኙ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ አ/አ ቤተሰቦች ተጠቁሟል።

ውድ ቤተሰባችን እርሶስ ጭማሪ ተደርጎቦታል ? የከተማ አስተዳደሩ ያሳለፈው ኪራይ ያለ መጨመር እንዲሁም ተከራይን ያለማስወጣት ውሳኔ ተግባራዊነት ምን ያህል ነው ? @tikvah_eth_BOT

@tikvahethiopia
በዕለታዊ የዳታ ጥቅል ቅናሽ በ100% ስጦታ ታጅቦ ቀርቧል!

ከከፍተኛ ቅናሽ እና እጥፍ (100%) ስጦታ ጋር የቀረቡትን ዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ከሰፊው ገበታችን በቴሌብር ሱፐርአፕ እና ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያዎች እንዲሁም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸው በስጦታ ያበርክቱ!

ተጨማሪ ስጦታውን ከምሽቱ 4:00 እስከ ጠዋቱ 2:00 ሰዓት ፈታ ይሉበታል!

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#Tigray

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ ለነበሩ መምህራን ጥሪ ሊደረግ መሆኑን አሳውቋል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን የሰሜኑ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ተፈናቅለው በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት ተመድበው ሥራቸውን እንዲጀምሩ መደረጉ ይታወሳል።

"ነገር ግን አሁን ላይ ሁኔታዎች እየተስተካከሉ በመሆኑ መምህራኑ ወደቀድሞ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ እንደሚደረግ" በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የ " SKYTRAX " ውድድር ላይ በ5 ዘርፎች ሽልማት ተቀዳጀ።

አየር መንገዱ አሸናፊ የሆነባቸው ዘርፎች ፦

🇪🇹 " Best Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 6ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Business Class Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 5ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Economy Class Airline in Africa 2023 " ለተከታታይ 5ኛ ግዜ፣

🇪🇹 " Best Business Class Onboard Catering in Africa 2023 " ለተከታታይ 2ኛ ግዜ

🇪🇹 " Cleanest Airline in Africa 2023 " ዘርፎች ናቸው።

አየር መንገዱ ሽልማቶቹን በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው " Paris Air Show " መርሐ ግብር ላይ ተቀብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
My Wish Enterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
#RosewoodFurniture

በዘመናዊ ማሽነሪ እና በ3D ዲዛይን የታገዘ,
ለኣጠቃቀም ምቹ እና ወቅቱን የጠበቁ ዘመናዊ  የፈርኒቸር ስራዎች  ! 

ስራዎቻችንን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ 
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood

👉🏼 ስልክ    :  📲 0905848586
👉🏼 ኣድራሻ : 📍4 ኪሎ አምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ
                       📍ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ

ሮዝዉድ ፈርኒቸር 🙌
TIKVAH-ETHIOPIA
የወልቃይት ጉዳይ ! ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ከቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ጋር ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። በዚህ ቃለምልላሳቸው ፦ - ስለ ማንነት ጥያቄ - ስለ በጀት - ስለ ተጠያቂነት - ስለ ተፈናቃዮች ጉዳይ - በእሳቸው ላይ ስለሚቀርቡ ክሶች - ስለ ፖለቲካ ውሳኔ / ህዝበ ውሳኔ - ስለ ውይይት ጉዳዮች ተነስቶላቸው ምላሽ ሰጥተዋል። ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ምን አሉ ? የማንነት ጉዳይ ፦ "…
" የትግራይ እና የአማራ ሕዝብም ተገናኝቶ መነጋገር ይገባዋል " - ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፤ የወልቃይት ጉዳይ ከውይይት ውጭ በሆነ መንገድ ይፈታል ብለው እንደማያሙን ገልጸዋል።

ለአካባቢው ጦርነት መፍትሄ እንደማይሆንም አስገንዝበዋል።

ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በወልቃይት ጉዳይ ከትግራይ ክልል አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ያላቸው እንደሆነ የተጠየቁት ኮ/ሌ ደመቀ ዘውዱ ፤ " ጉዳያችን ሊያልቅ የሚችለው በመነጋገር እና በመወያየት ነው " ሲሉ መልሰዋል።

" በጉልበት የሚያልቅ ነገር የለም። " ያሉት ኮሌኔል ደመቀ " እኛ ብቻ አይደለንም መላው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ፣ መላው የአማራ ሕዝብ ሊነጋገር ይገባል " ብለዋል።

የትግራይ እና የአማራ ሕዝብም ተገናኝቶ መነጋገር እንደሚገባው ገልጸዋል።

" ጉዳያችን ከውይይት ውጪ በሆነ መልኩ ይፈታል ብለን አናስብም፣ ከየትኛውም አካል ጋርም ለመነጋገር ዝግጁ ነን " ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . " ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው (በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው) " ሰላም ለእናንተ ይሁን !! አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ…
የማዳበሪያ ነገር . . .

መንግሥት ፤ የ " አፈር ማዳበሪያ " ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ቢገልፅም አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ገበሬዎች በወቅቱ እየደረሳቸው እንዳልሆነ እየገለፁ ይገኛሉ።

የግብርና ሚኒስቴር ፤ ለምርት ዘመኑ የሚያሰፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በ2015/16 ምርት ዘመን የሚውል 12.8 ሚሊዮን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞም ወደ ሀገር ውስጥ የማጓኀጓዝ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብሏል።

እንደ ግብርና ሚኒስቴር እና ኢትሎባድ መረጃ መሰረት ፦

- በቀን በአማካኝ 8 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባነው።

- በ13 ግዙፍ መርከቦች ተጓጉዞ ጅቡቲ ከደረሰ አጠቃላይ መጠን ከ677 ሺህ 678 ሜትሪክ ቶን (90 %) በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ገብቷል።

- እስከ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም ድረስ ከ7.4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 6.6 ሚሊዮን ኩንታል ሙሉ በሙሉ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው፡፡

- በመጪው 10 ቀናት በአራት / 4 መረከቦች 220 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል። ሶስት መረከቦች መጫኛ ወደብ ላይ በመጫን ላይ ናቸው።

ግብርና ሚኒስቴር ፤ እስካሁን የማጓጓዝ ስራው በመኪና እና በባቡር በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አዳማ ካለው ባቡሩ ጣቢያ እንደደረሰም ወደ ፦
- ኦሮሚያ፣
- አማራ
- ሲዳማ ክልሎች እየተጓጓዘ መሆኑን አመልክቷል።

" በክልሎች ያሉ የተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት የማጓጓዝ ስራውን በትኩረት እየሰሩ ነው " የሚለው የግብርና ሚኒስቴር " በቀጣይም ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶናአርብቶ ለማቅረብ በትኩረት ይሰራል " ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አሁንም በክልል ያሉ አርሶ አደሮች " ማደበሪያ #በወቅቱ እየደረሰን አይደለም " በሚል ከፍተኛ ምሬት ላይ ናቸው።

ለአብነት በአማራ ክልል ያሉ አርሶ አደሮች በማዳበሪያ ችግር የተነሳ የእርሻ ጊዜያቸው እያለፈ መሆኑን አሁንም እየገለፁ ናቸው።

ጥያቄያቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ በ "ሰላማዊ ሰልፍ" ቢገልጡም አሁንም ድረስ ችግራቸውን የሚፈታ እንዳልተገኘ በምሬት ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ " የማደበሪያ ችግራችን አልተፈታም " በማለት በባሕር ዳር ላይ ለሦስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

አርሶ አደሮች የመጀመሪያው ዙር የማሽላ እና የበቆሎ የዘር ወቅት በማዳበሪያ እጥረት የተነሳ መዝራት እንዳልቻሉ እና ጊዜው እንዳለፈባቸው እየገለፁ የሚገኙ ሲሆን የቀጣይ የዘር ወቅት እንዳያልፍባቸው ድምፃቸውን ቢያሰሙም ምላሽ አላገኙም።

" ማሽላም አልዘራሁ፤ ዳጉሳም ተጎልጉሎ የማሽላውን ለዳጉሳ ጎለጎልሁ ። [ማዳበሪያ] የሚገዛልኝም አጣሁ ። ማሽላ በግንቦት ነበር የምንዘራ፤ ዝናቡ ሰጥቶ ነበር አመለጠኛ ። ገበያ ላይማ እየተሸሸገ የሚሸጥማ አለ ። ዐሥር ሺህ ዘጠን ሺህ አሉት ። ያንም እኔ አልሆንልኝ አለ፤ አጣሁት፤ አላገኘሁትም ። ጤፍ እና ዳጉሳ ዛሬ ወቅቱ ። ማሽላማ አለፈ ። " ሲሉ አንድ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ  ጣቢያ ቃላቸውን የሰጡ አርሶ አደር ተናግረዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የግብርና መምሪያ ፤ አጠቃላይ የማዳበሪያ እጥረት መኖሩን አልሸሸገም። ሆኖም የቀረበው ማዳበሪያ በተቀመጠው ስሌት መሰረት የድርሻቸውን ይወስዳሉ ብሏል።

መምሪያው ፤ " ክልሉ 43,280 አጸደቀልን። መጥቶ ኅብረት ሥራ ማኅበር የደረሰው ግን 16,343 ነው ፤ የሚታረሰው መሬት 15,000 በላይ ነው ፤ ይኼ ደግሞ በቆሎ አምራች ነው ። አንድ ኼክታር ሁለት ይፈልጋል ዳፕ ብቻ ። 16,000 ብቻ መጥቶ 43,000 ቢቀርብ ነው የተወሰነ ፍልጎቶችን ሊያረካ የሚችለው ። እና እጥረቱ በጣም ሰፊ ነው ። ያለው ግን በኮታቸው መሠረት፤ በድልድላቸው መሠረት እየተሰራጨ ነው። " ብሏል።

በአማራ ክልል እስካሁን ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደተገዛ በክልሉ ግብርና ቢሮ በኩል ቢነገርም፤ አብዛኛው አርሶ አደር ግን እስካሁን በእጁ የገባ ነገር እንደሌለ ይናገራል።

ማዳበሪያው " በሕገወጥ መንገድ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ የግለሰቦች መጠቀሚያ ሆኗል " ሲሉም አርሶ አደሮቹ ምሬት እያሰሙ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከአማራ ክልል፣ ከኦሮሚያ ክልል ቤተሰቦቹ አሁንም የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር ስለመኖሩ መልዕክቶችን እየተቀበለ ይገኛል።

" ምንም አይነት " የማዳበሪያ አቅርቦት የሌለባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን በማመልከት ህዝቡን አርሶ የሚያበላው ገበሬ የከፋ ችግር ላይ ሳይወድቅ የሚመለከተው ሁሉ ችግሩን እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም (ከበርካታ ሳምንታት በፊት) እጅግ በርካታ የቤተሰብ አባላቶቻችን " ትኩረት ለገበሬው " በሚል የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር በፍጥነት እንዲፈታ ጥሪ አቅርበው ነበር።

በተለይም መንግሥት ፤ በማዳበሪያ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ህገወጥ አካላትን፣ በህገወጥ ስራ ውስጥ ያሉ የራሱን አካላት እንዲፈትሽ ብለው ነበር።

(ለትውስታ ከምዕራብ ጎጃም ከተላኩ መልዕክቶች አንዱ) ፦

" የጤፍ ዋጋ ፣ የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየጨመረ ይገኛል።

በገበሬው ዘንድ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ መንግስት እያቀረበ ያለው የአፈር ማዳበሪያ በቀበሌ ኃላፊዎች አመቻችነት ቀጥታ በነጋዴው እጅ እንዲገባ እና ትክክለኛ ዋጋው በኩንታል 3500 ብር የተተመነ ቢሆንም በነጋዴው እጅ 9000 ብር መደረጉ ነው።

ገበሬው የሚፈልገውን የማዳበሪያ መጠን አለማግኘቱ የጤፍ ዋጋ እንዲሁም የኑሮ ውድነት ከዚህ ዓመት ይልቅ በሚቀጥለው መባባስ የማይቀር አመላካች ነው።

ስለሆነም የሚመለከተው አካል ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው። "

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT