TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . " ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው (በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው) " ሰላም ለእናንተ ይሁን !! አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ…
የማዳበሪያ ነገር . . .
መንግሥት ፤ የ " አፈር ማዳበሪያ " ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ቢገልፅም አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ገበሬዎች በወቅቱ እየደረሳቸው እንዳልሆነ እየገለፁ ይገኛሉ።
የግብርና ሚኒስቴር ፤ ለምርት ዘመኑ የሚያሰፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
በ2015/16 ምርት ዘመን የሚውል 12.8 ሚሊዮን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞም ወደ ሀገር ውስጥ የማጓኀጓዝ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
እንደ ግብርና ሚኒስቴር እና ኢትሎባድ መረጃ መሰረት ፦
- በቀን በአማካኝ 8 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባነው።
- በ13 ግዙፍ መርከቦች ተጓጉዞ ጅቡቲ ከደረሰ አጠቃላይ መጠን ከ677 ሺህ 678 ሜትሪክ ቶን (90 %) በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ገብቷል።
- እስከ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም ድረስ ከ7.4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 6.6 ሚሊዮን ኩንታል ሙሉ በሙሉ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው፡፡
- በመጪው 10 ቀናት በአራት / 4 መረከቦች 220 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል። ሶስት መረከቦች መጫኛ ወደብ ላይ በመጫን ላይ ናቸው።
ግብርና ሚኒስቴር ፤ እስካሁን የማጓጓዝ ስራው በመኪና እና በባቡር በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አዳማ ካለው ባቡሩ ጣቢያ እንደደረሰም ወደ ፦
- ኦሮሚያ፣
- አማራ
- ሲዳማ ክልሎች እየተጓጓዘ መሆኑን አመልክቷል።
" በክልሎች ያሉ የተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት የማጓጓዝ ስራውን በትኩረት እየሰሩ ነው " የሚለው የግብርና ሚኒስቴር " በቀጣይም ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶናአርብቶ ለማቅረብ በትኩረት ይሰራል " ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አሁንም በክልል ያሉ አርሶ አደሮች " ማደበሪያ #በወቅቱ እየደረሰን አይደለም " በሚል ከፍተኛ ምሬት ላይ ናቸው።
ለአብነት በአማራ ክልል ያሉ አርሶ አደሮች በማዳበሪያ ችግር የተነሳ የእርሻ ጊዜያቸው እያለፈ መሆኑን አሁንም እየገለፁ ናቸው።
ጥያቄያቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ በ "ሰላማዊ ሰልፍ" ቢገልጡም አሁንም ድረስ ችግራቸውን የሚፈታ እንዳልተገኘ በምሬት ተናግረዋል።
አርሶ አደሮቹ " የማደበሪያ ችግራችን አልተፈታም " በማለት በባሕር ዳር ላይ ለሦስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
አርሶ አደሮች የመጀመሪያው ዙር የማሽላ እና የበቆሎ የዘር ወቅት በማዳበሪያ እጥረት የተነሳ መዝራት እንዳልቻሉ እና ጊዜው እንዳለፈባቸው እየገለፁ የሚገኙ ሲሆን የቀጣይ የዘር ወቅት እንዳያልፍባቸው ድምፃቸውን ቢያሰሙም ምላሽ አላገኙም።
" ማሽላም አልዘራሁ፤ ዳጉሳም ተጎልጉሎ የማሽላውን ለዳጉሳ ጎለጎልሁ ። [ማዳበሪያ] የሚገዛልኝም አጣሁ ። ማሽላ በግንቦት ነበር የምንዘራ፤ ዝናቡ ሰጥቶ ነበር አመለጠኛ ። ገበያ ላይማ እየተሸሸገ የሚሸጥማ አለ ። ዐሥር ሺህ ዘጠን ሺህ አሉት ። ያንም እኔ አልሆንልኝ አለ፤ አጣሁት፤ አላገኘሁትም ። ጤፍ እና ዳጉሳ ዛሬ ወቅቱ ። ማሽላማ አለፈ ። " ሲሉ አንድ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን የሰጡ አርሶ አደር ተናግረዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የግብርና መምሪያ ፤ አጠቃላይ የማዳበሪያ እጥረት መኖሩን አልሸሸገም። ሆኖም የቀረበው ማዳበሪያ በተቀመጠው ስሌት መሰረት የድርሻቸውን ይወስዳሉ ብሏል።
መምሪያው ፤ " ክልሉ 43,280 አጸደቀልን። መጥቶ ኅብረት ሥራ ማኅበር የደረሰው ግን 16,343 ነው ፤ የሚታረሰው መሬት 15,000 በላይ ነው ፤ ይኼ ደግሞ በቆሎ አምራች ነው ። አንድ ኼክታር ሁለት ይፈልጋል ዳፕ ብቻ ። 16,000 ብቻ መጥቶ 43,000 ቢቀርብ ነው የተወሰነ ፍልጎቶችን ሊያረካ የሚችለው ። እና እጥረቱ በጣም ሰፊ ነው ። ያለው ግን በኮታቸው መሠረት፤ በድልድላቸው መሠረት እየተሰራጨ ነው። " ብሏል።
በአማራ ክልል እስካሁን ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደተገዛ በክልሉ ግብርና ቢሮ በኩል ቢነገርም፤ አብዛኛው አርሶ አደር ግን እስካሁን በእጁ የገባ ነገር እንደሌለ ይናገራል።
ማዳበሪያው " በሕገወጥ መንገድ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ የግለሰቦች መጠቀሚያ ሆኗል " ሲሉም አርሶ አደሮቹ ምሬት እያሰሙ ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከአማራ ክልል፣ ከኦሮሚያ ክልል ቤተሰቦቹ አሁንም የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር ስለመኖሩ መልዕክቶችን እየተቀበለ ይገኛል።
" ምንም አይነት " የማዳበሪያ አቅርቦት የሌለባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን በማመልከት ህዝቡን አርሶ የሚያበላው ገበሬ የከፋ ችግር ላይ ሳይወድቅ የሚመለከተው ሁሉ ችግሩን እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚህ ቀደም (ከበርካታ ሳምንታት በፊት) እጅግ በርካታ የቤተሰብ አባላቶቻችን " ትኩረት ለገበሬው " በሚል የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር በፍጥነት እንዲፈታ ጥሪ አቅርበው ነበር።
በተለይም መንግሥት ፤ በማዳበሪያ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ህገወጥ አካላትን፣ በህገወጥ ስራ ውስጥ ያሉ የራሱን አካላት እንዲፈትሽ ብለው ነበር።
(ለትውስታ ከምዕራብ ጎጃም ከተላኩ መልዕክቶች አንዱ) ፦
" የጤፍ ዋጋ ፣ የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየጨመረ ይገኛል።
በገበሬው ዘንድ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ መንግስት እያቀረበ ያለው የአፈር ማዳበሪያ በቀበሌ ኃላፊዎች አመቻችነት ቀጥታ በነጋዴው እጅ እንዲገባ እና ትክክለኛ ዋጋው በኩንታል 3500 ብር የተተመነ ቢሆንም በነጋዴው እጅ 9000 ብር መደረጉ ነው።
ገበሬው የሚፈልገውን የማዳበሪያ መጠን አለማግኘቱ የጤፍ ዋጋ እንዲሁም የኑሮ ውድነት ከዚህ ዓመት ይልቅ በሚቀጥለው መባባስ የማይቀር አመላካች ነው።
ስለሆነም የሚመለከተው አካል ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው። "
@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT