#ቮልስዋገን
" ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር እንዳይገባ ታግዷል " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
ወደ ኢትዮጵያ ከሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መካከል በቻይና ሀገር ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጲያ እየገባ የሚገኘው " ቮልስ ዋገን " የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ህጋዊ የሆነ ፍቃድ የሌለው መሆኑን የጀርመን ኩባንያ በኢንባሲው በኩል ለትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
ይህ ቻይና ሀገር የሚመረተው የ " ቮልስ ዋገን " የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከኩባንያው ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን ሚኒስቴሩ ዛሬ አሳውቋል።
ምንጭ፦ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቮልስዋገን
" ከቻይና ውጪ ያሉ ደንበኞች ለተሸከርካሪዎቹ የዋስትና መብት አያገኙም " - ቮልስ ዋገን
ባለፈው ሳምንት ID 4 እና ID 6 ክሩዝ የተባሉ የታዋቂው የጀርመን መኪና አምራች ቮልክስዋገን ስሪት የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ እግድ መተላለፉ ይታወሳል።
ቅንጡዎቹ መኪኖች ለኢትዮጵያ ገበያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይቀርቡ የታገዱት በመኪና አምራቹ ጥያቄ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አማካይነት ነው።
ጉዳዩን በተመለከተ #ቮልስዋገን ለቢቢሲ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ምን አለ ?
" ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ እግድ እንዲያጣል የተደረገው በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ነው።
በቻይና የሚመረቱ የቮልክስዋገን ID.4፣ ID.6 X እና ID.6 CROZZ የተባሉት መኪኖች መቅረብ ያለባቸው #ለቻይና ገበያ ብቻ ነው ፤ መኪኖቹ ከቻይና ውጪ እንደማይሸጡ በሕግ ተደንግጓል።
ከዚህ በተጨማሪ ለቻይና ተብለው የተሰሩ ቮልክስዋገን ID መኪኖችን ከቻይና ውጪ ያሉ ደንበኞች የሚገዙ ከሆነ ለተሸከርካሪዎቹ የዋስትና መብት አያገኙም። " ብሏል።
ቮልስዋገን ፤ ሕጋዊ ፍቃድ የሌላቸው መኪና ሻጮች፣ መኪኖቹ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዳላቸው በመግለጽ ለደንበኞቻቸው እየሸጡ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ሲልም ገልጿል።
ነገር ግን ID 4፣ ID 6 X እና ID 6 ክሩዝ ለቻይና ብቻ ተብለው የተመረቱ በመሆናቸው መኪኖቹ ከቻይና ውጪ የሚያስፈልጋቸው ዋስትና የላቸውም ብሏል።
እነዚህ ከእውቅና ውጪ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የተባሉት መኪኖች በኢትዮጵያ " የቮልክስዋገን እውቅና ባላቸው ሻጮች ወይም ቮልክስዋገን ባጸደቃቸው ሰርቪስ ማድረጊያ ተቋማት ውስጥ ሁሉንም አይነት የመኪና ‘ሰርቪስ’ እና የጥገና አገልግሎት ሊያገኙ አይችሉም " ሲል አሳውቋል።
ፍቃድ የሌላቸው ሻጮች እነዚህን መኪኖችን ሕጋዊ እና ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በተደጋጋሚ በሌሎች አገራት ለመሸጥ እየሞከሩ መሆኑን የገለፀው ቮልስዋገን ፤ ደንበኞች መኪኖችን ከመግዛታቸው በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ኩባንያው አገራት እነዚህን መኪኖች ወደ አገር ውስጥ እንዳያስገቡ ማሳሰቢያዎችን እያላከ መሆኑን ገልጾ፤ " ደንበኞች ID መኪኖችን ሲገዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ከሕጋዊ ወኪሎች ብቻ እንዲገዙ ያሳስባል " ብሏል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?
(የሕዝብ ትራንስፖርት እና አሸከርካሪ ተሽከርካሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ከድልማግስት ኢብራሂም)
" መኪኖቹን ያገድነው ለኢትዮጵያ መንገዶች ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ስለሚኖርብን ነው።
ተሸከርካሪዎቹ የደኅንነት ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ብለን አናስብም፣ ይሁን እንጂ በቅርብ ቀናት ከኤምባሲው ጋር ተነጋግረን ለሁሉም መልስ እንሰጣለን። "
መኪኖቹ በኢትዮጵያ ገበያ እንዲቀርቡ ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው እንዴት ከቻይና ሊመጡ ቻሉ ?
" የእግድ ጥያቄው ከኩባንያው የመጣው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት የሚቻልባቸው መመሪያዎች እና ደንቦች እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ነው።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስገቢያ ፍቃድ ገና በዝግጅት ላይ ነው።
ከዚህ በፊት ወደ አገር ውስጥ የገቡ የኤሌክትሪክ መኪኖች በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ሲሰተናገዱበት በነበረው መመሪያ ነው።
አሁን ላይ ወደ አገር ቤት ገብተው ለሽያጭ ያልቀረቡትን ቮልክስዋገን መኪኖችን በተመለከተ ለመነጋገር ከጀርመን ኤምባሲ ጋር በዚህ ሳምንት ቀጠሮ አለን። "
Via BBC AMHARIC