TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Passport

ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ አስቸኳይ ፓስፖርት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው።

የኢሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በማንሳት፣ ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲያገኙ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቅድመ ሁኔታዎች ሲነሱ አሁኑ ላይ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች ማቅረብ ሚጠበቅባቸውን የሕክምና ደብዳቤ ፣ ነፃ የትምህርት ዕድል ማስረጃ... የመሳሰሉትን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡

በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት በፀደቀው የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ፓስፖርት በአንድና በአምስት ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት የተቀመጠውን ክፍያ " መክፈል የቻለ ሁሉ " ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ግንበቶ መናገራቸውን ሪፖርተር ገልጿል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

- #በአስቸኳይ_ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማንሳት ዝግጅት እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጡ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

- " አስቸኳይ ፓስፖርት ከውስጥ ሠራተኞች ተነጋግረን እናስጨርሳለን " የሚሉ ደላሎች አሉ ከብልሹ አሠራሮች ጋር በተያያዘ ፣ በዓመት ግፋ ቢል ከ50 ሰዎች በላይ እያባረርን ነው። ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ያስችላል ተብሎ የታሰበው መፍትሔ አገልግሎቱን ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማንሳት ነው።

- አሁን ባለው አሠራር ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት ከሚያስችሉ ማስረጃዎች መካከል ፦

• ወደ ውጭ ሄደው መታከም እንዳለባቸው የሚገልጽ የሕክምና ደብዳቤ ፣
• ለሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆነ የትምህርት ዕድል ማግኘትን የሚገልጽ ደብዳቤ
• የዲቪ ሎተሪ ዕድል ማግኘትን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተነስተው ሥራ ሲያስጀምር ደንበኞች የሚስተናገዱት በአዲሱ የክፍያ ተመን ይሆናል።

- ቅድመ ሁኔታዎችን አንስቶ አገልግሎቱን ለመጀመር ጥናት ተጠንቷል፤ ይህንን አገልግሎት ለማስጀመር የፓስፖርት ወረቀት ፣ ላምኔት ፣ የማተሚያ ቀለም እና የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ መለዋወጫዎችን ... የመሳሰሉ ግብዓቶች መሟላት እንዳለባቸው በጥናቱ ታይቷል።

የሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት የኦንላይን ፓስፖርት ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል የሻነው ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

• በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጥባቸው መስኮቶች ሁለት ናቸው የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎትን ያለገደብ ለማስጀመር እንዲቻል ቢያንስ ስድስት መስኮቶች መኖር አለባቸው።

• አገልገሎቱን ለማስጀመር ሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጀምሯል ፤ ምን ያህል ብር እንደሚጠይቅም አዘጋጅተን ለሚመለከተው ክፍል አቅርበናል።

• አገልግሎቱ እንዲጀመር ተጨማሪ በጀት ይጠይቃል ፤ በጀቱ የሚፈቀድልን ከሆነ #በቅርብ_ወራት ውስጥ ይኼንን አስጀምረን አገልግሎት አሰጣጡን እናሻሽላለን።

አሁን ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት ክፍያና የሚሻሻለው ክፍያ ምን ይመስላል ?

አሁን በሥራ ላይ ባለው አሠራር መሠረት ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት 2,186 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ ይኼንኑ ፓስፖርት በሁለት ቀናት ውስጥ ለማግኘት 3,279 ብር ክፍያ ይፈጸማል፡፡

በቅርቡ በሥራ ላይ መዋል ይጀምራል የተባለው አዲስ የአገልግሎት ክፍያ ተመን በ5 ቀናት ውስጥ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠየቀውን ገንዘብ ወደ 5,000 ብር አሳድጎታል፡፡

ፓስፖርቱን በአንድ ቀን ለማግኘት ደግሞ 6,500 ብር ክፍያ መፈጸም እንዳለበት ደንቡ ያስረዳል፡፡

የባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ ለማግኘት 6,500 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ በአንድ ቀን ለማግኘት የሚከለፈለው ክፍያ 8,000 ብር ይደርሳል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ (ethiopianreportr.com)

@tikvahethiopia
ከ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ተሽከርካሪ በጨረታ አሸንፎ የወሰደው ግለሰብ ያቀረበው ሰነድ ሲረጋገጥ ሃሰተኛ ሆኖ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን የፈፀመው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለጨረታ ባቀረባቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ተጫራች ሆኖ በመሳተፍ ነው፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ/ም በተካሄደው በዚሁ ጨረታ ላይ የተሳተፈው ተጠርጣሪው፤ ለማስያዥያነት በዳሽን ባንክ ስም የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሲፒዮ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርንጫፍ 3 ሚሊዮን 565 ሺህ ብር  ገቢ ተደርጓል የሚል ሃሰተኛ ደረሰኝ ለድርጅቱ በማቅረብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-B87869 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ወስዶ ከአካባቢው መሰወሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰነድ የማረጋገጥ ስራ በሚሰራበት ወቅት ጨረታውን አሸንፎ ተሽከርካሪውን የወሰደው ግለሰብ ያቀረበውን ሰነድ ትክክለኛነት ተጠራጥሮ ለፖሊስ ካመለከተ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ግለሰቡን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር  በማዋል እና የሰነዱን ሃሰተኛነት በማረጋገጥ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ።

ተቋማት በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡላቸውን ገንዘብን ተክተው የሚሰሩ እና ከገንዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ሰነዶች አስቀድመው በማረጋገጥ ሊፈፀምባቸው ከሚችል ወንጀል ራሳቸውን ሊከላከሉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ  መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ከተለያዩ የዓለም አገራት የመጡ ተወካዩች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን “ ለዲጅታል አካታችነት መሰረተ ልማት መልካም ተሞክሮዎችና ምክረ ሀሳቦች ” በሚል ሃሳብ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በተጨማሪም የበይነ መረብ ዝርጋታ ፣ የሳይበር ደህንነት ፣ የበይነ መረብ አስተዳደር እና የወጣቶች ተሳትፎ በዛሬው እለት ምክክር እየተደረገባቸው ካሉ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው።

የ17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ዋናው መክፈቻ በነገው እለት እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን ጉባኤ እስከ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ይነሱበታል ተብሎ ይጠበቃል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Save_the_Children #Tigray

የህጻናት አድን ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መድረሱን ድርጅቱን አሳውቆናል።

የህጻናት አድን ድርጅት በላከልን መልዕክት ፤ የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ እርዳታን #በአምስት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ማጓጓዙን ገልጾልናል።

" ህጻናት በዚህ ግጭት  ክፉኛ ተጎድተዋል፤ አፋጣኝ እርዳታም ሊያገኙ ይገባል፡፡ " ያሉት፣  በኢትዮጵያ የድርጅቱ ኃላፊ ዣቬር ዡቤር፣ ተጨማሪ ምግብና ሌሎች የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ተጨማሪ ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የህጻናት አድን ድርጅት በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በአፋርና አማራ ክልሎች  ለችግር ለተጋለጡ ህጻናትና ቤተሰቦቻቸውም ተመሳሳይና ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾልናል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን ባከናወናቸዉ እና በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ እየሰጠ ነው።

የኮሚሽኑ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#DigitalEqub

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ዲጂታል እቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ስምምነቱ ምንድነው ?

ስምምነቱ በባህላዊ መንገድ ይሰበሰብ የነበረውን እቁብ በዘመናዊና አስተማማኝ መንገድ መሰብሰብ ለማስቻል ያለመ ነው።

" ዲጂታል እቁብ " የሁሉንም ህብረተሰብ አቅም በማገናዘብ የተለያዩ የእቁብ አማራጮች ያሉት ሲሆን እቁብን በዘመናዊ መንገድ በመሰብሰብ ቁጠባን እንደሚያበረታታ ተገልጿል።

እቁቡ በሲቢኢ ብርና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የሚሰበሰብ ሲሆን Digital Ekub በተሰኘ መተግበሪያ አማካኝነት የሚሰራ ነው።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.digital.equb

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎቱ በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ተቋሙ ከሀገር ውጭ በሚገኙ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመሮች ላይ አጋጥሞኛል ባለው ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑ አሳውቋል።

በዚህም የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ወይም የፍጥነት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል በመግለፅ ይቅርታ ጠይቋል።

አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ከአገልግሎት አቅራቢዎቹ ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ መሆኑና ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁት ጠይቋል።

@tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ?

• " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ)

• " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ ቨለ)

• " መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው #የኢትዮጵያ_መምህራን_ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ ነው " - ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል (ከትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየሰሩ ያሉ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ከህዳር 26 ቀን 2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ የሚገልፅ ፅሁፍ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከሰሞኑን ተሰራጭቷል።

መምህራኑና ቴክኒካል ረዳቶቹ አድማ እንደሚያደርጉ የተገላፀበት ይኸው ፅሁፍ ለትምህርት ሚንስቴር እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፃፉን የሚገልፅ ሲሆን " ያቀረብነው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም " በሚል ምክንያትነው አድማው ይደረጋል የሚለው።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ለ " አዲስ ስታንዳርድ " ሚዲያ የሰጡ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ተከታዩን ብለዋል ፦

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ ፦

" እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።

ስራ የማቆሙ ሃሳብ ሁሉም መምህራን የሚጋሩት ነው። በቀጣይ የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር መግለጫ ያወጣል። "

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህር ጥላሁን ረጋ ፦

" የመምህራን ደሞዝ አነስተኛ በመሆኑ በአገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም አልተቻለም።

በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ላሉ መምህራን የሚደርሳቸው የተጣራ ደሞዝ  8 ሺህ 5 መቶ ብር ብቻ ነው። ይህ እንዲሻሻልልን የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ድረስ አልተመለሰልንም።

መንግስት የመምህራንን ጥያቄ ባለመመለሱና ችላ  በማለቱ በትምህርት ጥራቱ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ነው። ከምስራቅ አፍሪካ በኢኮኖሚ ትልቅ ሆና ለመምህራን ዝቅተኛ ደሞዝ የምትከፍል ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት።

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ ስራ ለማቆም ዝግጁ ናቸው። "

አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፦

" የመምህራን ማህበር #ለጥያቄዎቻችን ትኩረት መስጠት ባለመቻሉ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ መምህራን ተመካክረንበት ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች በኩል መግለጫችንን ይፋ አድርገናል።

መምህራን ወር በደረሰ ቁጥር የቤት ኪራይ ምን እከፍላለሁ ልጆቼን ምን አበላለሁ እያለ በመጨናነቅ ለማስተማር በቂ ዝግጀት ስለማያደርግ የትምርት ጥራቱ ላይ ተፅኖ እያደረሰ ነው። "

(መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ የሚገልፀው ፅሁፍ በዚህ የተያያዘ ነው ፦ https://telegra.ph/University-11-29

የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች መምህራን እና ቴክኒክ ረዳቶች ማኅበር ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል  በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የፊታችን ሰኞ ኅዳር 26 ቀን/2015 ይደረጋል የተባለውን የሥራ ማቆም አድማ
እኔ አልጠራሁትም ሲል አስታውቋል።

ፕሬዜዳንቱ ዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ ፤ የመምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም ብለዋል። ተናግረዋል።

ዶክተር በፍቃዱ ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ሲሆን የሚመሩት ማኅበር ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረቡት 14 ጥያቄዎች በእርግጥም ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መሆናቸውን ቢያረጋግጡም የሥራ ማቆም አድማ ግን አልጠራንም ሲሉ ገልጸዋል።

ማኅበሩ ይህንን ያደረጉት " የማናውቃቸው የተደራጁ አካላት ናቸው " ብሏል። ይህን ያደረጉ ያላቸውንም አካላት እንደሚከስ ለዶቼቫለ ሬድዮ አሳውቋል።  

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " መምህራን የሚያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ለመፍታት ከመምህራን ማህበር ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን " ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ትላንት ለህ/ተ/ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል።

መምህራኑ ባነሱት ጉዳይ አስተያያታቸውን ለቲክቫህ  የሰጡት የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል በበኩላቸው ፤ መመህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ መሆኑን አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የወደዱትን የሥዕል ሥራ ይምረጡ!

በሪድም ዘጀነሬሽን አዘጋጅነት ወደ 80 የሚጠጉ ወጣቶችን ያሳተፈውና በ16 ቡድኖች የተከናወነው የሥዕል ውድድር አሸናፊ በነገው ዕለት በይፋ ይገለጻል።

ወጣቶቹ ወጣት ሰዓሊያን አወንታዊ የሰላም ግንባታ፤ የአብሮነትና የግጭት አፈታት እንዲሁም ዕርቀ ሰላም ላይ ያተኮረ መልዕክታቸውን በሥዕላቸው አስተላልፈዋል።

አሸናፊው የሚለየው በዳኞች 70 በመቶ ውጤትና የቲክቫህ ቤተሰቦች 30 በመቶ ድምጽ ነው። ተወዳዳሪዎቹ ሥዕሎቻቸውን እንዲሁም የስዕሉ ጽንሰ ሀሳብ የያዘ መግለጫ አዘጋጅተው አቅርበዋል።

እርሶም የሥዕል ሥራዎቹን በመመልከት ለወደዱት የሥዕል ሥራ ድምጽ https://redeem.tikvahethiopia.net/ ላይ በመግባት ይስጧቸው።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ  የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ፤ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት የመለያ ቁጥር (0000039688) የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀምው አሳስቧል።

ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት (NIDO FORTIFIED 400g Full Cream Milk Powder, Batch No. 0000039688) የተባለው ምርት መያዣ ዕቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ድብቅ ጽሁፍ (Barcode) ሲነበብ የምርቱ የመጠቀሚያ ጊዜ እ.ኤ.አ 09/2021 የሚል ሲሆን ከምርት መያዣ እቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ደግሞ እ.ኤ.አ 01/2024 እንደሆነ ያሳያል፡፡

በመሆኑም በድብቅ ጽሁፉ (Barcode) የሚወጣው የምርቱ ሙሉ መረጃ ላይ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት የመለያ ቁጥር (0000039688) የሆነውን ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀምው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia