TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጠናቋል
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል።
ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን።
በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም የጀርባ አጋዥ / አካል በራሳቸው መፅሀፍ ያበረከቱ ፣ ያስላኩ፣ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
የአዲስ አበባ አባላት በዚህ ዙር ከ7 ሺህ መፅሀፍ በላይ አበርክተዋል።
@tikvahethiopia

#ተጠናቋል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል። ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን። በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም…
#እናመሰግናለን
በኮቪድ ወረርሽኝ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍትን ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱን ለት/ቤቶች አድርሰናል።
በአጠቃላይ የተሰበሰበው መፅሀፍ እንዲከፋፈል ያደረግነው ፦
- መርሳ 2ኛ ደረጃና ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ፣ ውርጌሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሲሪንቃ ሁለተኛ ደረጃ እና ሙሉ ሳይክል ት/ቤት እነዚህ በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና የነበሩ ት/ቤቶች ሲሆን የመማሪያ መፅሀፍት እጥረት እንዳለባቸው ከአካባቢው ቤተሰቦቻችን በደረሰን መረጃ ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ አከፋፍለናል። ለእነዚህ ት/ቤቶች በቀጣይም ተጨማሪ ለመላክ ታቅዷል።
- ዶሮ ግብርና ወደዪ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አጋዥ እና በቀድሞው ካሪኩለም የታተሙ መፅሀፍትን የላክን ሲሆን በአዲሱ ካሪኩለም የታተሙትን ኮፒ ለመላክ እየተዘጋጀን ነው። በተላኩት መፅሀፍት ውስጥ የልጆች መማሪያ የሚሆኑ የተረት መፅሀፍት አሉበት።
- ማላካ ፣ ኢርባኖ ፣ ህዳሴ የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ት/ቤቶቹ የሚገኙት በደቡብ ክልል ከጅንካ ከተማ በ50 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ሲሆን በስፍራው ያሉ ቤተሰቦቻችን በመማሪያ መፅሀፍ ግብዓት እጥረት ሳቢያ በት/ቤቶቹ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የሚፈለገውን ያህል ውጤት አይመዘገብም ብለውናል። በዚህም ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ በማካፈል ልከናል። ካለው ተማሪ ብዛት በቀጣይ ዙርም ተጨማሪ ለመላክ አቅደናል።
- ቤተሰብ የህዝብ ቤተመፅሀፍ አ/አ ከተማ መካኒሳ አካባቢ የተከፈተ አዲስ ቤተመፅሀፍ ሲሆን መፅሀፍ እንደሚያስፈልጋቸው በገለፁልን መሰረት ተመልክተን ከተሰበሰበው መፅሀፍ አካፍለናል ፤ በተጨማሪ 10 ሺህ ብር ሰጥተናል። በቀጣይ ተጨማሪ መፀሀፍ ለመስጠት ታቅዷል።
- ፈንታው ድንቁ መታሰቢያ አፀደ ህፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #ቆቦ የሚገኝ ሲሆን በጦርነት ወቅት ለህትመት የሚገለገሉበት ኮምፒዩተር በመሰረቁ 2 ኮምፒዪተርና መፅሀፍትን ልከናል።
(መፅሀፍቱ የተበረከተው ከአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ነው፤ መፅሀፍ ያበረከቱ ቤተሰቦቻችን ስም ዝርዝራቸው በ @tikvahuniversity ላይ ይገኛል ፤ በዚህ ዙር በየቤቱ እየተኬደ ከተሰበሰበው መፅሀፍ በተጨማሪ ከመቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መፅሀፍት በቤተሰቡ ስም ተገዝተው ተጨምረዋል)
ያጋጠሙ ችግሮች ፦ በዚህ ዙር #በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ እንዲሁም መፅሀፉን ለመላክ ከገጠመ የትራንስፖርት ችግር ውጭ ሁሉንም በቤተሰቡ አቅም ለማድረግ ተሞክሯል።
በቀጣይ ፦ አሁን የጎደሉትን መሙላት እና ተጨማሪ መላክ እንዱሁም በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለመድረስ ታስቧል።
ከአንድ ወር በኃላ በድጋሚ ሌላ ዙር በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ የሚሰራ ሲሆን በዚህ ዙር በቲክቫህ ላይ ማስታወቂያ የሚያሰሩ / መልዕክት የሚያስናግሩ ሁሉም ድርጅቶች የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው የማስታወቂያ / መልዕክት ለቤተሰቡ መላኪያ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል።
ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ ፦
👉 #ንፁህ_ወረቀቶችን (ኮፒ ለማድረግ) ፣
👉 ያገለገሉ በየቤቱ ያሉ ኮምፒዩተሮችን ፣ ታብሌቶችን
👉 ከከተማ ለወጡት ትምህርት ቤቶች ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ አስተማሪ እና ጥላቻ የማይዘሩ የልብ ወለድና ሌሎች መፅሀፍትን የምናሰባስብ ይሆናል።
(ከዚህ ቀደም በነበሩ 4 ዓመታት በየዓመቱ የነበረውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለው ችግር በየአንድ እና ሁለት ወር ለማድረግ ይሰራል)
እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የምናድረገው እጅግ በጣም ጥቂት ቢሆንም ይህን ለማስፋት እንሰራለን ፤ ሁሉም በያለበት #የራሱን ጥቂት አስተዋፆ ማድረግ ከቻለ ብዙሃንን መድረስ ይቻላል። ለማድረግ አቅም ቢያንሰን እንኳን ለወገናችን በጎ በማሰብ ችግሩን እንካፈለው።
#TikvahFamily❤️
0919743630
0703313630
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#MoE
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
መውጫ ፈተና በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል።
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ ተማሪዎች ባሻገር #የማታና #የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን እንደሚመለከት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለመንግስትና ለግል ዩኒቨርስቲዎች የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ሲከፍቱ እንዳሉት መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣የማታና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት መታቀዱንም ዶክተር ሳሙኤል ጠቁመዋል።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) በዚሁ ጊዜ ሲናገሩ የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር የተማሪዎችንና የተቋማቱን ብቃት ለማሳደግ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።
በምክክር መድረኩ ሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገኝተዋል።
በምክክር መድረኩም በመውጫ ፈተና ዙሪያ እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ፣ የመሠረተ ልማትና የ2015 ምሩቃን መረጃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

#Ethiopia
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ #ኢትዮጵያ ይገኛሉ።
የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ፤ ከአንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንዲሁም ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሐመት ጋር ውይይት እንዳደረጉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተደረገ መሆኑና ውጤታማ ውይይት እንደሆነ አመልክተዋል።
" ትብብራችንን እንደሚጠናከር አልጠራጠርም " ሲሉም ገልፀዋል።

#Update " በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ሽረ ላይ ስብሰባ ይደረጋል ፤ በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች ዘሪያ የሁለቱም ጦር ተወካዮች ተገናኝተው ይወያያሉ " ትላንት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተካሄደውን የሰላም ድርድር / ስምምነቱን የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዜዳንት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የትግራይ መዲና ፤ #መቐለ መግባታቸው…
#Update #ሽረ
የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽረ ላይ እየመከረ መሆኑን አሳውቋል።
" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ሕዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽረ ላይ ሥራውን ጀምሯል " ያለው የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ " ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተውጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል " ብሏል።
ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ እንደሚሆንም ተመላክቷል።
የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽ ፤ ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱን ገልጿል።
ፎቶ ፦ ፋይል

#MoE የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። መውጫ ፈተና በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል። የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ ተማሪዎች ባሻገር #የማታና #የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን…
#ExitExam
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦
" የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ። "

#Tigray በናይሮቢው የሰላም ስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ጄነራል ታደሰ ወረደ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ባለፉት ቀናት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን በቀጣይ ሁለት ቀን እንቀሚያልቅ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት በክልሉ ለሚገኙት የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ነው። ጄኔራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ? " በናይሮቢው…
#Update #Peace
በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች በስራቸው ከነበሩ የውግያ ግምባሮች ለቀው መውጣት እንደጀመሩ ተገልጿል።
ታጣቂዎቹ ከደቡብ ፣ ማይ ቅነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት ፣ ጨርጨር ፣ ኩኩፍቶ ፣ ሕጉምብርዳ ፣ በሪተኽላይ እና አበርገለ ለቆ ግንባሮች ነው መውጣት እንደጀመሩ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተሰማው።
ከጥቂት ቀናት በፊት ጄነራል ታደሰ ወረደ (የትግራይ ኃይሎች አዛዥ) በሰጡት መግለጫ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን እንዳለቀ ኃይላቸው ካለበት ቦታ Disengage አድርጎ / ተላቆ የውጊያ ግንባሮች #የማፍረስ እና ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ እንደሚጓጓዝ መግለፃቸው አይዘነጋም።
ጄነራል ታደሰ ፤ " የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም ልናነሳው እንችላለን ምናልባት የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል " ማለታቸውም የሚወስ ነው።