TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SNNPRS #SouthWestEthiopia

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

👉 ለወንዶች 41፣
👉 ለሴቶች 40 እና
👉 ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

👉 ለወንዶች 39፣
👉 ለሴቶች 38 እና
👉 ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USAID

" ... ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነዳጅ መልሱ  " - ሳማንታ ፓወር

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ ህወሓት (TPLF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚጠቀምበትን 150,000 ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን በመግለፅ ድርጊቱን አጥበቀው አውግዘዋል።

በተጨማሪም በእርዳታ ሰራተኞች ላይ እንግልት መድረሱን በመጠቆም ፤ ህወሓት (TPLF) በእርዳታ ሰራተኞች ላይ ያደረሰውን እንግልት ድርጅታቸው አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው " ያሉት ፓወር ህወሓት (TPLF) የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን እንዲያከብር በድርጅታቸው ስም ጥሪ አቅርበዋል።

ከነዳጅ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ አሁንም ዓለም አቀፍ ተቋማት ድርጊቱን እያወገዙ ሲሆን ህወሓት (TPLF) በሰጠው ምላሽ " ከወራት በፊት ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስድኩ እንጂ ዘረፋ አልፈጸምኩም " ብሏል።

ነዳጁን ለድርጅቱ ያበደርኩት ከጥቂት ወራት በፊት በነዳጅ እጥረት ምክንያት የምግብ እርዳታ ማከፋፈል ባለመቻሉ ነው ያለው ህወሓት ድርጅቱ ነዳጅ መበደሩንና እንደሚመልስ ግንዛቤ ነበር ሲል ገልጿል፤ " ስምምነታችን በጽሁፍ ተሰንዶ ተቀምጧል " ሲል እየቀረበበት ላለው ክስ ምላሽ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

በአፍሪካ ግዙፉና በደህንነቱ አስተማማኝ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማት ተበረከተለት።

አየር መንገዱ " Global Travel Magazine " ከመንገደኞች ባሰባሰበው ድምፅ መሰረት " የ2022 ዓ.ም ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ " ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ! " ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት…
#እንድታውቁት

ለቀጣይ 6 ወራት ተከራይ ማስወጣት ፤ ኪራይ መጨመር አይቻልም !

በአዲስ አበባ የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት #ስድስት ወራት ተራዝሟል።

ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል ተገልጿል።

👉 አጭር ቁጥር ፡- 9977

👉 የሞባይል ስልኮች 09-00640830 ፣ 09-00640789

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተመድ #አፍሪካ_ህብረት አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ፤ ዛሬ ከሚካሄድ የፀጥታው ም/ ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ በጣም ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን የገለፁት…
#UNHCR

የተመድ ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዴ በኢትዮጵያ የቆመው ግጭት መቀጠሉ ስጋት እንዳሳደረ እና አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀዋል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን መልዕክት እጋራለሁ ያሉት ግራንዴ አዲስ ግጭት መቀስቀሱ በሲቪሎች ላይ የበለጠ ስቃይን እንደሚያስከትልና በሀገሪቱ ውስጥ እና በድንበር የተፈናቃዮችን ቁጥር እንደሚጨምር ገልፀዋል።

ያሉ ችግሮች እንዳይባባሱ የተኩስ አቁም ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USAID " ... ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነዳጅ መልሱ  " - ሳማንታ ፓወር የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ ህወሓት (TPLF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚጠቀምበትን 150,000 ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን በመግለፅ ድርጊቱን አጥበቀው አውግዘዋል። በተጨማሪም በእርዳታ ሰራተኞች…
#UN_OCHA

" ውጤቱ እስከፊ ሊሆን ይችላል " - ማርቲን ግሪፊትስ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በትላንት በስቲያ በትግራይ ክልል፣ መቐለ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል የነዳጅ ታንከሮች መወሰዱን መስማታቸው እጅግ እንደረበሻቸው ገልፀዋል።

የነዳጅ ታንከሮቹ 12 መሆናቸውን ያመለከቱት ግሪፊትስ 570,000 ሊትር ነዳጅ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ነዳጁ ተመድ እና አጋሮቹ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሰዎች አስፈላጊ ድጋፍ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን አመልክተዋል።

ያለዚህ ነዳጅ ሰዎች ያለ ምግብ፣ ያለ ድጋፍ ሰጪ ንጥረነገሮች፣ ያለ መድሃኒት እና ያለሌሎች ወሣኝ አስፈላጊ ነገሮች ይቀራሉ ብለዋል።

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የምግብ ዋስትና እጦት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት #ውጤቱ_አስከፊ_ሊሆን_ይችላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ይህን መሰሉን ድርጊት አወግዛለሁ ያሉት ግሪፊትስ " የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች በመላው ኢትዮጵያ ሊጠበቁ ይገባል። የሰብዓዊ ዕርዳታ ማደናቀፍ መቆም አለበት " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የባንክ ፣ የመብራት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ የጠየቁ ሲሆን ይህ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዋፆ እንዳለው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#KonsoZone

በኮንሶ ዞን ፤ ካራት ዙሪያ ወረዳ ታችኛው " ሶሮቦ ቀበሌ " አንድ አይን ብቻ ያላት የበግ ግልገል ተወለደች።

የካራት ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት ሃኪም ዶ/ር ኢሳያስ እስጥፋኖስ በኮንሶ ዞን አከባቢ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት መሆኑን ገልፀው ክስተቱ ከብዙ ሺህ ውልደቶች መካከል ሊከሰት የሚችል እንደሆነ ገልፀዋል።

ዶክተሩ እንደዚህ አይነት ክስተቶች ያልተለመዱ መሆኑና " ኮንጄንታል ማልፎርመሽን " የሚባል ተፈጥሯዊ ክስተት መሆኑን አስረድተዋል።

በአንድ አይን የተወለደችው የበግ ግልገሏ የላኛው መንጋጋ እና አፍንጫ እንደሌላት በዚህም በአፏ እንደምትተነፍስ የእንስሳት ሃኪሙ ገልፀዋል።

ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማታ የተወለደችው ግልገሏ እስካሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች ተብሏል።

መረጃው ፦ የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#Update

በአዲስ አበባ ከተማ የላዳ  ታክሲዎችን በአዲስ ለመቀየር የሚያስችል ስምምነት በተሽከርካሪ አቅራቢና በባለንብረቶች መካከል በ2013 ዓ.ም ቢፈረምም ወደ ተግባር አለመግባቱ ብዙ ቅሬታ ሲያስነሳ ቆይቷል።

የመጀመሪያው ዙር የሚገጣጠሙ የላዳ ቅያሬ ተሽከርካሪዎች ግብዓቶች ወደ ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው የመገጣጠም ሥራው በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩ ተጠቁሟል።

በአጠቃላይ 10 ሺህ 500 መቶ የላዳ ቅያሬ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና ከአሽከርካሪ ማሕበራት ጋር ስምምነት መደረጉን የኤል አውቶ ኢንጂነሪንግና ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ አበበ አስታውሰዋል።

ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከሚገኘው ፋብሪካ በተጨማሪ የዱከሙ መገጣጠሚያ ፋብሪካም በቀጣይ ሳምንት መጀመሪያ ቀናት መኪናዎችን መገጣጠም እንደሚጀምርም ነው የገለጹት። ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅም ጥረት ይደረጋል ተብሏል።

አብዛኛዎቹ የላዳ ቅያሬ ተሽከርካሪዎች ባለ 7 ወንበር ያላቸው ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ገልጸው፤ የተወሰኑት ባለ 5 ወንበር ሲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎቹም አንድ ሺህ ሲሲ ጉልበት ያላቸው በመሆናቸው ለነዳጅ ቁጠባም አዋጭ ናቸው ብለዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተር አቶ ሙላይ ወልዱ በበኩላቸው ከቀረጥ ነጻ ዕድሉ መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችል የሕግ ዝግጅት በማስፈለጉ መመሪያው ተግባራዊ ሳይሆን ለተወሰኑ ወራት ዘግይቶ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ወደ ሚኒስቴሩም መጥተው የተመዘገቡ ከ200 በላይ የታክሲ ማሕበራት አሉ ያሉት ዳይሬክተሩ አስፈላጊውን መስፈርና ዶክመንት ያሟሉ ማኅበራት አገልግሎቱን እያገኙ ነውም ብለዋል።

Via EPA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት ዳግም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ድርጅቱ በላከልን አጭር መግለጫ ግጭቱ ዳግም መቀስቀሱን አውግዟል።

በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላት ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጡ አሳስቧል።

ከዚህም በተጨማሪ በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የንፀሐንን ዜጎች ህይወት እና ሰብዓዊ መብት በመጠበቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#NorthernEthiopia

በሰሜን ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል ዳግም ጦርነት ካጋረሸ በኃላ ሁኔታዎች ከመርገብ ይልቅ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ እንደሚገኙ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ።

ትግራይ ክልልን ከአማራ እና አፋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ አርብ በመቐለ የአየር ድብደባ እንደነበር እና በዚህም ሳቢያ ህፃናትን ጨምሮ እስካሁን አራት ሰዎች መሞታቸውን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሳውቋል።

ሆስፒታሉ ፤ የአየር ጥቃቱ ጉዳት ያደረሰው በህፃናት መጫወቻ ቦታ አካባቢ መሆኑን ገልጾ በጥቃቱ የተጎዱ እስከሁን 13 ሰዎች በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና ከነዚህ ውስጥ 4ቱ መሞታቸውን አመልክቷል። ከአራቱ 2ቱ ህፃናት መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት በመቐለ ከተማ የአየር ጥቃት ተፈፅሟል ይህን ተከትሎም ደርሷል ስለተባለው ጉዳት እስካሁን ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia