#NorthernEthiopia
በሰሜን ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል ዳግም ጦርነት ካጋረሸ በኃላ ሁኔታዎች ከመርገብ ይልቅ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ እንደሚገኙ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ።
ትግራይ ክልልን ከአማራ እና አፋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።
በሌላ በኩል ፤ ዛሬ አርብ በመቐለ የአየር ድብደባ እንደነበር እና በዚህም ሳቢያ ህፃናትን ጨምሮ እስካሁን አራት ሰዎች መሞታቸውን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሳውቋል።
ሆስፒታሉ ፤ የአየር ጥቃቱ ጉዳት ያደረሰው በህፃናት መጫወቻ ቦታ አካባቢ መሆኑን ገልጾ በጥቃቱ የተጎዱ እስከሁን 13 ሰዎች በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡና ከነዚህ ውስጥ 4ቱ መሞታቸውን አመልክቷል። ከአራቱ 2ቱ ህፃናት መሆናቸውን ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት በመቐለ ከተማ የአየር ጥቃት ተፈፅሟል ይህን ተከትሎም ደርሷል ስለተባለው ጉዳት እስካሁን ያለው ነገር የለም።
@tikvahethiopia

አሜሪካ ፤ " ኤርትራ በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ ዋነኛውን ሚና በመጫወት ላይ ናት " ስትል ገልፃ ኤርትራ በአስቸኳይ ወደ ድንበሯ እንድትወጣ ጠይቃለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አሜሪካ ፤ ኤርትራ ወደ ድንበሯ እንድትወጣ መጠየቋን ገልፀዋል።
ፕራይስ ፤ " ለኤርትራ እና ለኤርትራ ባለስልጣናት በአስቸኳይ ወደ ድንበራቸው እንዲወጡና ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማባባሱን እንዲያቆሙ ግልፅ አድርገንላቸዋል። ይህ ግጭት ያስከተለው የሰብአዊ መብት ረገጣ በጣም አሳስቦናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ወደ ሰላም እና ደህንነት የሚመለሰው ብቸኛው መንገድ አሜሪካ የምትደግፈው በአፍሪካ ኅብረት (AU) የሚመራው የሰላም ሂደት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አክለውም ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ወታደራዊ ግጭት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ሰላማዊ ድርድር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበናል " ያሉት ፕራይስ " በዚህ የዲፕሎማሲ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከአህጉሪቱ አጋሮች ጋር ተቀራርበን ሰርተናል" ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ባለፈው በመስቀል በዓል ዕለት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ " አዲ ዳዕሮ " እየተባለች በምትጠራ በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ከተማ በተፈፀመ የአየር ጥቃት 6 ሰዎች መሞታቸውን አንድ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኛን ዋቢ አደርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።
የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው " ህወሓት " ይህ ጥቃት የተፈፀመው በኤርትራ መሆኑንና በዕለቱ ተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን ቤቶችን ወደ ፍርስራሽነት መቀየራቸውን፣ ንፁሃንም ሰለባ መሆናቸውን ገልጿል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-Region-09-30