#KonsoZone
ኮንሶ ዞን ካራት ከተማ በዛሬው ዕለት የተከበረው የጥምቀት በዓል እንዲሁም ትላንት የተከበረው የከተራ በዓል ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገልጾልናል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#konsoZone
በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ወደ ደራሼ ቀበሌያት የተፈናቀሉ ዜጎች እስካሁን ሰብዓዊ እርዳታ እንዳላገኙ ገልፀዋል።
አንድ ከአዲስ ገበሬ አካባቢ እንደተፈናቀሉ የሚናገሩ ግለሰብ እሳቸውን ጨምሮ 25 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ወደ ደራሼ ልዩ ወረዳ ገብተው እንደተጠለሉ ተናግረዋል።
በተጠለሉበት ስፍራ ተገኝተው ያነጋገሯቸው የደቡብ ክልል ባለስልጣናት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ወደ ቄያቸው ሲመለሱ የሚያገኙ እንደሆነ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
ተፈናቃዩ ፥ "...ቤት የለም፣ ንብረት ተቃጥሏል፣ ጎተራው የለም ምን ላይ ነው የምንመለሰው ? መጀመሪያ ሰላም ነው የሚያስፈልገው እዛ ሰው እንዳይመለስ አሁንም ጥይት አለ፣ ስለዚህ ምን ላይ ነው የምንመለሰው ብለን በየቦታው ቁጭ ብለን እርዳታም ተከልክለናል። እርዳታ ወደ ቄያቹ ስትመለሱ ነው ተብለናል" ሲሉ ገልፀዋል።
የኮንሶ ዞን የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት መምሪያ ሃላፊ ከበደ ካይታ ፥ በባለፈው ሳምንት ግጭት ወደ ደራሼ ልዩ ወረዳና ሌሎች ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች 15 ሺህ ነው ብለዋል።
ከነዚህ መካከል በቀጥታ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተፈናቀሉ በጣም ጥቂት ሲሆኑ ኣብዛኞቹ ፌስቡክን ጨምሮ በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ የተሳሳተ መረጃ ተደናግጠው የሸሹ ናቸው ብለዋል።
አቶ ከበደ ተፈናቃዮች ወደቄያቸው ተመልሰው የሚደረገው ድጋፍም በዛው የሚደረግበት ሁኔታ መመቻቸት ይኖርበታል ብለዋል።
አክለውም፥ "የመንግስት የፀጥታ ኃይል አለ፥ እኛም አለን፣ ወደ ቄያቸው ይመለሱ፣ መንግስት አስተማማኝ ሰላም እና ጥበቃ ያደርጋል" ሲሉ ገልፀዋል።
Via ዶቼ ቨለ

#KonsoZone : አቶ ዳዊት ገበየሁ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።
የኮንሶ ዞን የሽግግር ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ዳዊት ገበየሁ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
ሹመቱን ተከትሎ አቶ ዳዊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
@tikvahethiopia

በኮንሶ ዞን ፤ ካራት ዙሪያ ወረዳ ታችኛው " ሶሮቦ ቀበሌ " አንድ አይን ብቻ ያላት የበግ ግልገል ተወለደች።
የካራት ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት ሃኪም ዶ/ር ኢሳያስ እስጥፋኖስ በኮንሶ ዞን አከባቢ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት መሆኑን ገልፀው ክስተቱ ከብዙ ሺህ ውልደቶች መካከል ሊከሰት የሚችል እንደሆነ ገልፀዋል።
ዶክተሩ እንደዚህ አይነት ክስተቶች ያልተለመዱ መሆኑና " ኮንጄንታል ማልፎርመሽን " የሚባል ተፈጥሯዊ ክስተት መሆኑን አስረድተዋል።
በአንድ አይን የተወለደችው የበግ ግልገሏ የላኛው መንጋጋ እና አፍንጫ እንደሌላት በዚህም በአፏ እንደምትተነፍስ የእንስሳት ሃኪሙ ገልፀዋል።
ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማታ የተወለደችው ግልገሏ እስካሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች ተብሏል።
መረጃው ፦ የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ነው።