#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና
የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር ሲካሄድ ውሏል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና የፈተና ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በፈተናው አሰጣጥ ላይ ምክክር ማካሄዱን አሳውቋል።
በውይይቱ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሠነዱ ዙርያ የተለያዩ አስተያቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ግልጽነትና የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለሚና አካላት ጋር በመሆን እየተከናወነ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት ! የልጁን ሕይወት ለማዳን ከጀልባ ላይ የዘለለው እንግሊዛዊ አስክሬኑ ጣልያን ተገኘ። ዛሬ ጥዋት ቢቢሲ በደረገፁ አንድ አሳዛኝ ክስተት አጋርቷል። አረን ቻዳ የተባለ እንግሊዛዊ ልጁን ለመታደግ ከጀልባ ከዘለለ በኋላ ለሳምንታት ጠፍቶ አስክሬኑ ጣልያን ውስጥ ተገኝቷል። አረን ባለፈው ወር " ጋርዳ " የተባለ ባሕር አካባቢ ከትዳር አጋሩና ከሁለት ልጆቹ ጋር…
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት !
የልጁን ህይወት ለማትረፍ ናይል ወንዝ የገባው አባት አስከሬኑ ተገኘ።
ስሙ ሮበርት ክዌሲ ይባላል የኡጋንዳ ተወላጅ ዜግነቱ ደግሞ እንግሊዛዊው ነው ፤ እድሜው 48 ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ ነበር።
ሮበርት ከባለቤቱ ጀስቲን ካታንታዚ እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ወደ ኡጋንዳ ለእረፍት ይመጣሉ። ኡጋንዳ መጥተው እየተዝናኑ ሳለ የ12 አመት ልጁ እየዋኘ በነበረበት ወቅት በነበረው ማዕበል ችግር ስላጋጠመው አባት ልጁን ለመርዳት ዘሎ ይገባል። ምንም እንኳን አባት ልጁን ቢያተርፍም የእሱ ደብዛ ግን ከዛች ደቂቃ አንስቶ ይጠፋል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች እና ጠላቂ ፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው በጎ ፍቃደኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ፍለጋ ያደርጋሉ በኃላም የሮበርትን አስክሬን አግኝተዋል።
ሮበርት ክዌሲ አስክሬኑ የተገኘው በናይል ወንዝ በአንደኛው ክፍል ነው ተብሏል።
ሮበርት በእንግዚዝ ፍሪጅ እና አየር ማቀዝቀዣዎችን በመጠገን በተቋራጭነት ይሰራ ነበር። ከባለቤቱ ጋር ጋብቻቸውን የፈጸሙት ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኡጋንዳ እንደነበር #ቢቢሲ ፅፏል።
ትላንትም አንድ እንግሊዛዊ አባት የልጁን ህይወት ለማትረፍ ሲል ከጀልባ ዘሎ ልጁን አትርፎ እሱ ግን ህይወቱ እንዳለፈ አስክሬኑም ጣልያን ውስጥ መገኘቱን የሚገልፅ መረጃ ማንበባችን ይታወሳል።

Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#አድማስ_ዲጅታል_ሎተሪ !
የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ ድጅታል ሎተሪ የአንደኛ ዙር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ/ መውጣቱን ገልጿል።
የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡-
👉 የ1ኛ ዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002031699514
👉 2ኛ ዕጣ የ800 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002294990063
👉 3ኛ ዕጣ የ350 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002318579148
👉 4ኛ ዕጣ የ200 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002210849268
👉 5ኛዕጣ የ160 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002133487616
👉 6ኛ ዕጣ የ120 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002305487051
👉 7ኛ ዕጣ የ90 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002137548817
ሌሎችም በርካታ ዕጣዎች መውጣቱን የገለፀው ብሄራዊ ሎተሪ ሙሉውን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

Photo
#ExitExam
የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?
ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።
ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦
" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።
በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።
ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።
ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።
ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።
ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።
በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ ሚኒስትር ተሾሞለታል ፤ አዲሷ ሚኒስትር ማን ናቸው ?
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ዓይንዓለም ንጉሴ ናቸው።
ሹመቱ አቶ ላቀ አያሌው በትምህርት ምክንያት ወደውጪ ሀገር ለመሄድ በሚኒስተሮች ምክር ቤት መሸኘታቸውን ተከትሎ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።
ወ/ሮ ዓይንዓለም ንጉሴ በምን ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል ?
• በወሎ ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ፤
• የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
• በአማራ ክልል በኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪነት ሰርተዋል።
አዲሷ ሚኒስትር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ከቀድሞ ሚኒስትር የስራ ርክክብ አካሂደዋል።
Credit : Ministry of Revenues of Ethiopia

#አድማስ_ዲጅታል_ሎተሪ ! የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ ድጅታል ሎተሪ የአንደኛ ዙር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ/ መውጣቱን ገልጿል። የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡- 👉 የ1ኛ ዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002031699514 👉 2ኛ ዕጣ የ800 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -002294990063 👉 3ኛ ዕጣ የ350 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር…
#DigitalLottery
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመረው " አድማስ " የተሰኘው ድጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዙር እጣ ትላንት ማውጣቱን አሳውቋል
የዲጂታል ሎተሪ ዕጣው ቀጣይነት እንዳለው የገለፀው አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር ዕጣው መስከረም 11 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን ገልጿል።
የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ በአንደኛ ዕጣው 1.5 ሚሊዮን ብር፣ በሁለተኛ 800 ሺህ ብር፣ በሶስተኛ 350 ሺህ ብር ጨምሮ ሌሎችም የገንዘብ ዕጣዎችን ያካተተ ነው።
ከብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር እንዳገኘነው መረጃ ዕጣው በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3 ብር ነው የሚቆረጠው።
(ከላይ በትላትናው ዕለት የወጣው የመጀመሪያ ዙር ዕጣ #ሙሉ የባለዕድለኞች ቁጥር ተያይዟል)

#ጥንቃቄ
የወገኖቻንን ህይወት እየቀጠፈ ፤ ንብረትም እያወደመ ያለው የጎርፍ አደጋ !
በያዝነው ክረምት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ ንብረትም እየወደመ ነው።
ለአብነት በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ ህፃናት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ንብረት ወድሟል፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ የአርሶ አደሮች ንብረትም እንዳልነበር ሆኗል።
ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን ማና ወረዳ ሃሮ ቀበሌ እንደተሰማው የአንድ ቤተሰብ አባላትን የሆኑ ወገኖቻችን በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አልፏል።
ከወረዳዋ ከተማ የቡ ተነስተው ሃሮ ወደተባለች ቀበሌ 3 ልጆቻቸውን ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ቤተሰብ አንድ የ13 ዓመት እና ህጻን ልጅ በደራሽ ጎርፍ ሲወሰዱ አንድ ታዳጊ በህይወት ማግኘት ተችሏል።
በጎርፉ ከተወሰዱት የቤተሰብ አባላቱ የአባት አስከሬን በዕለቱ ሲገኝ፤ የሟች እናትና ሁለት ልጆች አስከሬን ትላንት ጠዋት ተገኝቷል።
የቤተሰብ አባላቱ ፤ በጎርፉ የተወሰዱት ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ በነበረበት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የወረዳውን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።
በአማራ ክልል በአምባሰል ወረዳ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እና በመሬት መንሸራተት ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል።
በአጠቃላይ 150 አባወራዎች እና እማወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከል፣ በገበሬ ማሰልጠኛዎችና በዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል።
በወረዳው በቂ ለድጋፍ የሚሆን ሐብት ባለመኖሩ ለተጎጅዎች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑን በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል ፤ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፤ ከፍተኛ የሀብት ጥፋትም ደርሷል።
በሠመራ ከተማ ብቻ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች #ህይወት_አልፏል።
በኤሊደአር ወረዳ ዶቢ ቀበሌ ደግሞ በጎርፍ አደጋ ከ3 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የጨው ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
በአካባቢው ላይ ከ300 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች በጨው ምርት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ሁለት መቶ የሚሆኑት አምራቾች በጎርፉ ምክንያት ኪሳራ ደርሶባቸዋል።
በተጨማሪም ጨው ለማምረት ተዘጋጅተው የነበሩ የጨው ማምረቻ ቦታወችም በጎርፉ ምክንያት ተበላሽተዋል።
አንድ አምራች የምርት ቦታዎችን ለማዘጋጀት ከ200 ሺ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል የተባለ ሲሆን ባጠቃላይ አምራቾች ላይ የደረሰው ኪሳራ ቀላል ሊባል የሚችል አይደለም።
በተጨማሪም ፤ በአሳይታና አፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቤት እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አሳይታ በርጋ ቀበሌ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል፣ ቤታቸው እንዳልነበር ሆኗል ፣ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ ላይ ጉዳት አድርሶባቸዋል።
በአሁን ሰዓት ከቤታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ናቸው።
የመንግስት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሚሰጡ ተቋማት በውሃ ውስጥ ናቸው ያሉት።
በተመሳሳይ ፤ በአፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላትና በከባንድ ዝናብ ሳቢያ ቤት ንብረታቸው በጎርፍ አደጋ እንዳልነበር ሆኗል እነሱም ተፈናቅለዋል ፤ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ እነኚህ ወገኖቻችን የመንግስት ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።
በዚሁ ወረዳ 6 ሺህ ሄክታር የጥጥ እና ሰሊጥ እርሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።
መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ፣ ከኤሊዲአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን፣ ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ፣ ከአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም !
ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት ጤና ስፔሻሊስት መሆን ለሚሹ ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት ህክምና ትምህርት ላይ ላሉ የተዘጋጀ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም አጋርቶናል።
ይህ ዕድል በዓለማችን ላይ ስላሉት ከአንጀት ቁስለት ህመም ህክምና ጋር የተያያዙ ጉድለቶች እንዲሁም ከዚህ ህመም ጋር ያሉ ወጣት እና ጎልማሳ ሰዎች ምን አይነት የህክምና ትኩረት ይፈልጋሉ የሚለውን ይዳስሳል።
ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 👉https://bit.ly/3c6VBdL
ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስር ስለሰደዱ ህመሞች ዘወትር ረቡዕ በ @tikvahethmagazine መረጃዎችን ያቀርባል።

#AddisAbaba
" እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተለምዶ መሀል አዳራሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የህንፃ መናድ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳወቀ።
ህንፃው የተደረመሰው ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መሃል አዳራሽ በሚባል አካባቢ ሲሆን የተደረመሰው አንድ አሮጌ ህንፃ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።
በዚህም ምክንያት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ 6 ሰው የሞተ ሲሆን ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ላይም ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እና ያስከተለውን ጉዳት እያጣራ ይገኛል፡፡

#መልዕክት
1. የፌስቡክ እና ዩትዩብ አድራሻ የለንም !
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚገናኙበት ወይም እርስ በእርስ መልዕክት የሚለዋወጡበት ምንም አይነት የፌስቡክ (Facebook) ሆነ ዩትዩብ-Youtube (አክቲክቭ) አድራሻ #የለም። በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም አይነት የፌስቡክ ገፆች እና ግሩፖች እንዲሁም አክቲቭ የሆኑ ዩትዩብ አካውንቶች ቤተሰቡን አይወክሉም።
2. ማስታወቂያ እንሰራል ከሚሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ !
ቲክቫህ የድርጅት ባለቤት፣ ለተቋማት አመራር፣ የማርኬቲንግ ባለሞያ ለሆኑ የቤተሰቡ አባላት መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ የሚያመቻች ቢሆንም በፕሮግራምና በተመጠነ መንገድ ብቻ ነው። የተለያዩ ግሩፕ በቲክቫህ ስም ከፍተው ማስታወቂያ እንሰራለን የሚሉ አጭበርባሪዎች ናቸው። (በዚሁ አጋጣሚ የዚህ ዓመት ማስታወቂያ ያበቃ ሲሆን ከመስከረም 20/2015 ጀምሮ በአዲስ መልክ ይጀምራል)
3. ገንዘብ ከሚሰበስቡ ተጠንቀቁ !
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ውስጥ በምንም ጉዳይ ገንዘብ አይሰበሰብም፤ ለሰዎች እገዛ ሲሆን የሚነገረው እገዛውን የሚሹ አካላት አድራሻ ብቻ ነው። በቲክቫህ ቤተሰብ ስም ገንዘብ የሚሰበስቡ አጭበርባሪዎች ናቸውና ተጠንቀቋቸው። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ከአባላት ጋር በተገናኘ በምንም ጉዳይ ገንዘብ አይጠየቅም አይሰበሰብም፤ ከገንዘብ ጋር የሚገናኝ ምንም ስራ የለም።
4. የመልዕክት መቀበያ አድራሻ !
ይህ መልዕክት መለዋወጫ @tikvahethiopiaBOT ስላስቸገረ በአዲሱ @officialtikvahethiopiaBOT መልዕክችሁን ላኩ። ባለፉት ሳምንታት መልዕክት ልካችሁ ያልታየም በአዲሱ መቀበያ አልያም (0919743630) አሳውቁ።
5. የመማሪ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (አዲስ አበባ) ለማበርከት 0919743630 ይደውሉ።

በ2014 ዓ/ም 21 ሰዎች በስራ ላይ እያሉ ከህንፃ ወድቀው ሞተዋል !
በ2014 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ በግንባታ ሥራ ላይ ተገቢው የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓቶችን ለሠራተኞቻቸው ባላሟሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ችግር 23 ሰዎች በሥራ ላይ እያሉ ከሕንፃ ወድቀው ከፍተኛ የአካል ጉዳትና ሞት እንዳጋጠማቸው ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
ከ23ቱ ሰዎች 21 ያህሉ የሞት አደጋ የደረሰባቸው መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለጋዜጣው በሰጠው ቃል ፤ በግንባታ ሥራ ላይ ተገቢውን የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓቶችን ለሠራተኞቻቸው በማያሟሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ግዴታቸውን በማይወጡ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ከደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።
በሌላ በኩል በ2014 የበጀት ዓመት ከተፈቀደላቸው የግንባታ ቦታ ውጪ የሚጠቀሙና በእግረኛ መንገድ ላይ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች በማስቀመጥ የእግረኛ መንገድን በማጨናነቅ አካል ጉዳተኞችን ለከፍተኛ ችግር እያጋለጡ የሚገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ፣ ከደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ መዘጋጀቱን ባለስልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል።
በ2014 ዓ.ም. ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር በተገናኘ በ136 ድርጅቶች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
በ136 ድርጅቶቹ ላይ የግንባታ ግብዓቶችን እንዲያነሱ ከማድረግ አንስቶ ንብረታቸውን የመውረስ እንዲሁም የመጨረሻ ጽሑፍ ማስጠንቀቂያና የዕገዳ ውሳኔ የማስተላለፍ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን ባለስልጣን መ/ ቤቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጿል።