TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ላይ ቅሬታ አቀረበ!

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ #የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ላይ ቅሬታውን አቀረበ። የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል ካህሳይ ብሔራዊ ፈተናው በተሰጠበት ወቅት "በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የፈተና አሰጣጥ ሥነ-መግባር ጉድለት" ነበር ብለዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል ካህሳይ ለቢቢሲ ሲናገሩ "በክልላችን ፈተናው ሲካሄድ የፈተና አወሳሰድ ስነ-መግባርን ጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ስርዓቱን የጠበቀ አልነበረም" ብለዋል።

ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል ካህሳይ በወቅቱ ተስተውሏል ስላሉት የፈተና አሰጣጥ ስነ-ምግባር ጉድለት ለትምህርት ሚንስቴር አሳወቀው እንደነበረ ተናግረዋል።

"ከክልላችን እና ከሌሎች አከባቢዎች የተነሳው ቅሬታ ምላሽ ሳያገኝ ውጤቱ ይፋ ሆኖዋል። በዚህም ቅሬታ አለን።" ብለዋል። ዶ/ር ኢንጅነር ገብረመስቀል "የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተና ውጤቱን አልቀበልም አለ" ተብሎ የተዘገበው ስህተት ነው ሲሉም አክለዋል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሄር በበኩላቸው በውጤቱ ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች በሙሉ አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ምላሽ ይሰጠዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አረያ ጨምረው እንደተናገሩት ከፈተና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የቀረበ ቅሬታ የለም ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር ሲካሄድ ውሏል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና የፈተና ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በፈተናው አሰጣጥ ላይ ምክክር ማካሄዱን አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሠነዱ ዙርያ የተለያዩ አስተያቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ግልጽነትና የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለሚና አካላት ጋር በመሆን እየተከናወነ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia