TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Kombolcha

#ሙሉ_በሙሉ የግንባታ ወጭው በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የሚሸፈን መልቲ ጀነራል ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ የቀመጠ።

ሆስፒታሉ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ የሚገነባ ሲሆን ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይሆንበታል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በ1 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ወጪው ሙሉ በሙሉ በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሸፈን ነው።

በወረዳው ለሚገነባው ሆስፒታል የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዪስፍ፣ የኮምቦልቻ ወረዳ አስተዳደር አቶ አልዪ ኢብራሂም እና የዲያስፖራ ተወካይ አቶ ፈረሃን አህመድ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አድማስ_ዲጅታል_ሎተሪ ! የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ  ድጅታል ሎተሪ የአንደኛ ዙር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ/ መውጣቱን ገልጿል። የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡- 👉 የ1ኛ ዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002031699514 👉 2ኛ ዕጣ  የ800 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002294990063 👉 3ኛ ዕጣ የ350 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር…
#DigitalLottery

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመረው " አድማስ " የተሰኘው ድጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዙር እጣ ትላንት ማውጣቱን አሳውቋል

የዲጂታል ሎተሪ ዕጣው ቀጣይነት እንዳለው የገለፀው አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር  ዕጣው  መስከረም 11 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን ገልጿል።

የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ በአንደኛ ዕጣው 1.5 ሚሊዮን ብር፣ በሁለተኛ 800 ሺህ ብር፣ በሶስተኛ 350 ሺህ ብር ጨምሮ ሌሎችም የገንዘብ ዕጣዎችን ያካተተ ነው።

ከብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር እንዳገኘነው መረጃ ዕጣው በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3 ብር ነው የሚቆረጠው።

(ከላይ በትላትናው ዕለት የወጣው የመጀመሪያ ዙር ዕጣ #ሙሉ የባለዕድለኞች ቁጥር ተያይዟል)                            

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ #የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የታክስ ማሻሻያው በርካታ ዓላማዎች ያሉት ሲሆን ከዓላማው አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ ለማስቻል ነው።

በታክስ ማሻሻያው መሰረት (የቤት አውቶሞቢሎች) ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶ ሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#መታወቂያ

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ የተፈቀዱ አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የመታወቂያ አገልግሎቶችን አሳውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1/2015ዓ.ም ጀምሮ የተፈቀደ መሆኑ ያስታወሰው ኤጀንሲው አሁን ደግሞ ፦

👉 በቤተሰብ ማህደር ተመዝግበው 18 ዓመት የሞላቸው ነዋሪዎች፤

👉 ለህክምና ክትትል የሚፈልጉ እና ህጋዊ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርቡ ዜጎች፤

👉 በከተማዉ ፍ/ቤት መብት ለማስከበር የሚያበቃቸዉ የመብት ጉዳይ ኖሯቸዉ #የነዋሪነት_መታወቂያ ለሚያስፈልጋቸዉ ነዋሪዎች አሰራርን በመከተል አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟሉ አገልግሎት እንዲያገኙ መፈቀደኑን ገልጿል።

ይህ የተፈቀደው ከትላንት ዓርብ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ተገልጋዮች ሊኖር የሚችለውን ጫና ከግምት በማስገባት በተረጋጋ ሁኔታ ቀርባድ አገልግሎት እንዲያገኙ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 24 #ሙሉ_ቀን በሁሉም የወረዳ ፅ/ቤቶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን ነገ እሁድ ህዳር 25 አገልግሎት ዝግ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ #የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል። የታክስ ማሻሻያው በርካታ ዓላማዎች ያሉት ሲሆን ከዓላማው አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ…
ቁጥሮች ...

(ኢትዮጵያ - የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች)

[ ሪፖርተር ጋዜጣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ በርኦ ሐሰንን ቃለ መጠይቅ አድርጎ ካወጣው ዘገባ የተወሰደ ]

• መስከረም ወር ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ካደረገው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የታክስ ማሻሻያ በኋላ ከ7,000 በላይ ተሽከርካዎች አገር ውስጥ ገብተዋል።

• ከብሔራዊ ባንክ ጋር የኤሌክትሪክ አውቶብሶች እንዲጉ መግባባት ላይ ተደርሶ እንቅስቃሴዎች የተጀመረ ሲሆን በቅርቡ 1,300 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ወደ አገር ቤት ይገባሉ።

• የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የአሥር ዓመት ዕቅድ 48,000 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ፤ በተጨማሪም 148,000 የኤሌክትሪክ #አውቶሞቢሎችን አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ነው።

#ማስታወሻ

በመስከረም ወር ይፋ የሆነው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ ማስገቢያ ማሻሻያ ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሰልፉ ተራዝሟል " ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግስት የቤተክርስቲያኗን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያኗን ችግር ለመፍታት #በመስማማቱ ነገ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙን አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update


ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም #ሙሉ_በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Credit : EOTC TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል። በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን…
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?

ካሁን ቀደም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበትና በመቀጠል አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው 10ሩ የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመምጣት እስካሁን ድረስ በበዓታቸው ጸንተው የቆዩት 3ቱም የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ፦
👉 ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣
👉 ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
👉 ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ላይ አስቀድሞ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ #ተነስቷል፡፡

- ውግዘቱ የተነሣላቸው 3ቱም ሊቃነ ጳጳሳት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀነ 2015ዓ.ም. ጀምሮ በቀድሞ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረጋቸውና ስማቸው ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሊቀጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ሊቀጳጳስ ተብለው እንዲጠሩና አስቀድሞ ተመድበው ይሰሩበት በነበረው የሥራ ኃላፊነታቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ጥሪውን ተቀብለው ለስምምነቱ ተገዥ በመሆን በጽሑፍ ጥያቄያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያቀረቡት 20ዎቹ የቀድሞ መነኮሳት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ #ተነስቷል፡፡ ቀሪዎቹ 5ቱ ባለው ጊዜ ተጠቅመው ወደቤተ ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ ያሳሰበ ሲሆን ውግዘቱን በሚመለከት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ታይቶ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ውግዘቱ የተነሣላቸው 20ዎቹም የቀድሞ መነኮሳት አስቀድሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከዲቁና እስከ ቁምስና ባለው ማዕረገ ክህነታቸው እንዲያገለግሉ እና በምንኩስና ስማቸውም እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ሃያዎቹ (20ዎቹ) የቀድሞ መነኮሳት የሥራ ምደባን በተመለከተ በተደረሰው ስምምነት መሠረት በቀድሞው የሥራ መደብ ደረጃቸው እንዲመደቡ ቅዱስ ሲኖዶስ በመወሰን ዝርዝር ጉዳዩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አዟል።

- ምንም እንኳን አስቀድሞ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይትና ስምምነት መሠረት የታሰሩት ግለሰቦች በሙሉ እንደሚፈቱ ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በርካታ ሰዎች በእስር ላይ የሚገኙ ስለሆነ መንግስት አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ሁሉንም እስረኞች እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ አሳስቧል።

- በተከሰተው ችግር ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ላይ በኃላፊነት ተመድበው ሲሰሩ ቆይተው በችግሩ ምክንያት ተፈናቅለው የቆዩት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት በምድብ ሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

(#ሙሉ ውሳኔው እንዲሁም መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Woldia

በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ  ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል።

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል።

ክልከላዎቹ ፦

- ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

- ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00  ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ፤ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሥራ ከተመደቡ ተሽከርካሪዎች ውጭ በዚህ ምደባ ስምሪት ያልታቀፉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00  ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

- የሰው እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሥራ ከተመደበው ሰው ውጭ ከምሽቱ 3:00 እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ለጸጥታ ሥራ ስምሪት ከተመደበ አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

- የመንግሥትን የታጠቀ ኀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ፣ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሰጠ፣ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል።

- የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ሕግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ ተጥሎበታል ፤ የማይተባበር በሕግ ይጠየቃል ተብሏል።

የኮማንድ ፖስቱ በአብዛኛውን በሌሎች ከተማዎች የተጣሉ ክልከላዎችን አይነት ይዘት ያለው ክልከላ ነው የጣለው። (#ሙሉ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)

ኮማንድ ፖስቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ምክንያቶች ፦ በከተማው የተጀመሩ ልማቶችን " አመጹን መቀላቀል ሲገባህ ልማትን እያስቀጠለክ " በሚል ዛቻ ልማትን የማደናቀፍ ፤ በሙስና፥ በሌብነት፥ እና በተለያዩ ብልሹ ወንጀሎች ስጋት ያለባቸው አካላት የዕለት ጉርስ ፈላጊዎችን በገዘብ በመግዛት ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠርና ለማባባስ የሚያደርጉት ሙከራ በመረጃ ደረጃ የተገኘ በመሆኑ ነው ብሏል።

ከዚህ ባለፈ የትንሳኤ እና የረመዳን ሃይማኖታዊ ሁነቶችን በሰላም ለማጠናቀቅ ለዕኩይ ዓላማ የተሰማሩ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ነው ሲል አሳውቋል።

(የወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር ተገደሉ።

ከትላንት በስቲያ ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ጥቃቱን " አሸባሪዎች " ናቸው የፈፀሙት ያለው የአፋር ብልፅግና " በፈፀሙት ድንገተኛ ጥቃት የአቶ ኡመር ለማን ህይወት ቀጥፈዋል ብሏል።

ፅ/ቤቱ ባሰራጨው መረጃ ጥቃት አድራሾቹ ላይ የተወሰደ እርምጃ ይኖር እንደሆነ እና ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በሌሎች ላይ ጉዳት ደርሶ እንደሆነ በዝርዝር ያሳወቀው ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም በዚሁ ቀጠና እጅግ የለየለት የወንጀል ተግባር በታጠቁ አካላት እንደሚፈፀም ሲገለፅ እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ መስመር ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱና እንደ ከተማዎች ውስጥ በመግባት ጭምር ሰላማዊ ሰዎችን መግደል፣ በየመንገዱ ሰላማዊ ሰዎችን እያገቱ ከፍተኛ ገንዘብ የመጠየቅ ፤ በአጠቃላይ በቀጠናው ወጥቶ ለመግባት ከፍተኛ ስጋት የመፍጠር እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

መንግሥት ይህንን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነና ዜጎች ቀንም ማታም ያለስጋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ቀጠና ይህን ያህል ጊዜ #ሙሉ_በሙሉ ከታጣቂዎች እንቅስቃሴና የወንጀል ተግባር ነፃ ማድረግ ለምን እንዳልቻለ የብዙሀኑ ጥያቄ ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ በንፁሃን ላይ ሲፈፀሙት ለነበሩት ጥቃቶች ፣ ዝርፊያዎች ወንጀለኞቹ መቼ ነው ወደ ፍርድ አደባባይ የሚቀርቡት ? መቼስ ነው ፍትህ የሚሰጠው ? የሚለውም ጉዳይ መልስ ይፈልጋል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ  በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...

በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።

እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።

" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።

ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።

የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።

እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ በድሶ አዲሳ  ፦

" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።

ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።

ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።

ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።

እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።

ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "

ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።

እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
#Update

የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ከአንድ ወር በኃላ ነባር ተማሪዎቻቸውን እንደሚቀበሉ ከመስከረም (2016) ጀምሮ ደግሞ #ሙሉ_ለሙሉ ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ለኢፕድ የሰጡት ቃል ፦

" ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመጭው ወር ነባር ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ።

በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች ጋር በመቐለ ተደጋጋሚ ውይይት አድርጓል።

ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት ወደ ተግባር ተገብቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት ፦
- የምግብ ፣
- የመኝታ፣
- የሕክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ራያ ዩኒቨርሲቲም ይህንን አሟልቶ በትናንትናው ዕለት የተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

መቐለና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በቀጣይ ወር ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር ጨርሰው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነቱ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ ይችላል።

አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከጦርነቱ በፊት 45 ሺሕ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ነበር። ከእነዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት 22 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲወጡ ተደርጎ በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል።

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችም አሁን ላይ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ 20 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎችን ነው።

በመጪው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው ይችላል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ መቆየታቸውን ይታወሳል ፤ አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹም ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ማግኘት ይችላሉ። "

Via EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ራያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል፣ መቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ፤ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹን ይቀበላል " - ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች (መቐለ፣ ዓዲግራት፣ ራያ፣ ኣክሱም) ወደ መማር ማስተማር ስራቸው እንደሚመለሱ አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ፤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት በክልሉ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መማር ማስተማር ስራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ራያ ዩኒቨርሲቲ ከትላንት ጀምሮ ነባር ተማሪዎችን በመቀበል ምዝገባ መጀመሩን አሳውቀውናል።

መቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ነባር ተማሪዎቻቸውን መቀበል እንደሚጀምሩ የገለፁልን ዶ/ር ሰለሞን፤ የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹን መቀበል እንደሚጀምር አሳውቀውናል።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነት መጎዳቱ የመዘግየቱ ምክንያት መሆኑን አስረድተውናል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ ተማሪዎችን መሆኑን ዶ/ር ሰለሞን ገልጸውልናል።

በመጪው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው ይችላል ብለዋል።

በትግራይ ክልል ያሉ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 2016 ዓ/ም ጀምሮ #ሙሉ_በሙሉ ወደ ስራ እንደሚገቡ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በላኩልን መልዕክት አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል። በዚህም ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ 16 እና 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ። ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ገልጻ ይሰጣቸዋል። ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015…
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ

ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንዴት ሊሆን ነው ? የሚለው የብዙሃን ጥያቄ ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፤ ሰሞነኛው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ አንፃራዊ ሰላም እየታየበት በመሆኑ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፉ ብሔራዊ ፈተና ላይ እንዲሰጥ #ተወስኗል ሲል አሳውቋል።

ቢሮ ፤ ፈተናው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ በሚኖራቸው ቆይታ አስተማማኝ ጥበቃ ይደረግላቸዋልም ብሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፤ " ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል " ያለ ሲሆን በዚህም መሰረት ወላጆች ተፈታኝ ልጆቻቸውን በወረዳ ማዕከል በተዘጋጁ የትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲ እንዲልኩ ጥሪ አቅርቧል።

ቢሮው ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ በሚኖራቸው ቆይታ የፌዴራል ፖሊስ ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ እና አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤት በምን ይታያል ? " ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ላይ በዌብሳይት እና በSMS ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይቻላሉ። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ @tikvahethiopia
#ሙሉ_መግለጫ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የሰጠው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጥዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታትሎ መረጃዎችን ያደርሳል።

More - @tikvahuniversity @tikvahethmagazine

@tikvahethiopia
" የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ በደንብ ማረጋገጥ አለባቸው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን አሳወቀ።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉንም ገልጿል።

ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው " ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት " አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።

የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው 3 ግለሰቦች #ሙሉ_ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት  ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር  ገንዘቦችን በማተም  እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ ያረጋግጣል።

ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራም ተጠርጣሪዎቹ ፦
- ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣
- ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን  ፣
- በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣
- በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶች
- የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ አስታውሷል።

" መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው " ያለው ፖሊስ መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ለወንጀሉ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ መሆናቸውን በመረዳት  የተከራዮቻችውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ የማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ? " የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ  ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል…
#Update

በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ#ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ዛሬ የብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ፤ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩን አሳውቋል። ይህ ተከትሎ ዘለግ ያለ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫ ፦ - ስለ ሀገራዊ ምክክር - ስለ ሽግግር ፍትሕ - ከመንግሥት ውጭ ታጥቀው ስለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች - ስለ ተሃድሶ ኮሚሽን - ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት - ስለ ህወሓት ታጣቂዎች - ስለ ተፈናቃዮች መመለስ …
" ... ትጥቅ ሙሉ በሙሉ የማስፈታት ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው " - አቶ ኢያሱ ተስፋይ

ከቀናት በፊት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፥ በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከመከረ በኃላ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

በመግለጫው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ብዙ ውጤቶች እና እፎይታን ያስገኘ ቢሆንም አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።

ከነዚህ ቀሪ ስራዎች አንዱ የ ' ህወሓት ' ትጥቅ መፍታት እንደሆነ ጠቁሞ ፤ " በሰላም ስምምነቱ መሰረት ህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ፤ በብሄራዉ ተሃድሶ ኮሚሽን እቅድ መሰረት በፍጥነት መተግበር አለበት " ብሎ ነበር።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ህወሓት በስምምነቱ መሰረት " ከኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ / የፌዴራል ጸጥታ ኃይል ውጭ ያሉ ማንኛውም ኃይሎች ከትግራይ የአስተዳደር ወሰን እንዲወጡ መደረግ አለበት " ብሏል።

የህወሓት የፕሮፖጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢያሱ ተስፋይ ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ " ' ለዘላቂ ሰላም ትጥቅ መፍታት አለባቸው የሚለው ችግር የለውም ትክክል ነው " ያሉ ሲሆን " እንደ ትግራይ ህዝብ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻችን ከተመለሱልን ወደ ልማትና ወደ ዴሞክራሲ ግንባታ ስራችን መሸጋገር እንፈልጋለን " ብለዋል።

" ለሰላም ከማንም በላይ ጥብቅና እንቆማለን ስትራቴጃካዊ ፍላጎታችንም ነው ግን ደግሞ ያ ሰላም ከጥያቄዎቻችን መመለስ ጋር በቀጥታ መያያዝ አለበት እንጂ ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ መብታችን ሳይከበር ዝም ብሎ ሰላም የሚመጣ ነገር አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ለሰላም ብለን ቀደም ብለን ትጥቅ ማስፈታት ጀምረናል። የከባድ ማሳሪያም ርክክብም ከአመት በፊት አድርገናል፣ ከዛ አልፎ ከነበረን ሰራዊት በርካታውን demobilize አድርገናል ፤  " ሲሉ አክለዋል።

" ትጥቅ #ሙሉ_በሙሉ_የማስፈታት_ሁኔታ የሚፈጠረው ለትግራይ ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ከፌዴራል ኃይል ውጭ ያሉ የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ አሉ ህዝባችንን ለብዙ መከራ እየዳረጉ ያሉ በጸለምትም ፣ በደቡብ ትግራይም ስለዚህ አሁን ፌዴራል በጀመረው ነገር እነዚህን ኃይሎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱና ወደ ሌላ ስራቸው እንዲሄዱ የማድረግ ኃላፊነት አለበት " ብለዋል።

ለDDR የሚያስፈልገው ሁሉ በጀትም መመደብ አለበት ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IRAN🇮🇷 የኢራኑ ፕሬዝዳንት እና አብረዋቸው የነበሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጨምሮ) እየተፈለጉ ነው። ህዝቡ መሪዎቹ ምንም ሳይሆኑ በህይወት ተርፈው ይመለሱ ዘንድ ፈጣሪውን እየለመነ ይገኛል። ፕ/ት ኢብራሂም ራኢሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ኢራን ከአዘርባጀን ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ ላይ የተገነቡ 2 ግድቦችን መርቀው ከከፈቱ በኋላ በሂሊኮፕተር ወደ ታብሪዝ ከተማ ሲያመሩ ነው…
#ኢራን

የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ተሳፍረውባት በነበረው ሄሊኮፕተር በደረሰው አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ይህንንም የሀገሪቱ የመንግሥት አረጋግጧል።

ከሳቸው በተጨማሪ በሂሊኮፕተር ውስጥ አብረው የነበሩት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።

ሮይተርስ በአደጋው ፕሬዚዳንቱ ሲጓዙባት የነበረችው ሄሊኮፕተር #ሙሉ_በሙሉ መቃጠሏን " አንድ የኢራን ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

" የፕሬዜዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሄሊኮፕተር በአደጋው ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች። በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሳይሞቱ አልቀሩም " ብለዋል ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለስልጣን።

#ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሃይማኖት ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ? በኢትዮጵያ አዲስ የተዘጋጀ " #የሃይማኖት_ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ አለ። ይህ ረቂቅ አዋጅ በርካታ ጉዳዮችን ይዟል። አንዱ የአምልኮና የመቃብር ቦታን የተመለከተ ሲሆን ፥ ረቂቅ አዋጁ ለሃይማኖት ተቋማት የመሬት አቅርቦት በመሬት አጠቃቀምና የሊዝ ሕጎች መሠረት ይወሰናል ይላል። ለአምልኮ ወይም ለመቃብር ቦታ በተጠየቀበት አካባቢ ለሃይማኖት ተቋሙ ለተመሳሳይ…
#Update

" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩም የሃይማኖት ተቋማት ቅሬታ ማቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ተቋማቱ ረቂቅ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት የሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት መብትና ክብር የሚጠብቅ መሆኑ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በአብዛኛው ተከብሮ የቆየው የሃይማኖቶች ነፃነት ላይ ገደቦችን እንዳይጥል ሥጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የቀረቡ ቅሬታዎች ምንድናቸው ?

1ኛ. ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች የተነሳው ቅሬት፦

በረቂቁ አዋጁ ላይ የአደባባይ በዓላትን በሚመለከት " የአደባባይ ኩነት " ተብሎ መቀመጡን በማንሳት ይህ ትክክለኛ ትርጉም አይደለም ብለዋል፡፡

ለዚህ በማሳያ " የአደባባይ ኩነት በተፈቀደው ቦታ ብቻ መደረግ አለበት " በሚል በረቂቁ ላይ የተቀመጠውን ነው።

ለአብነት #የጥምቀት_በዓል የአደባባይ ሃይማኖታዊ በዓል ቢሆንም ፤" ከተፈቀደለት አደባባይ ውጪ መንገዶች ላይ መካሄድ አይፈቀድም " የሚል ትርጓሜ እንዳይሰጠው #ያሠጋል ብለዋል፡፡ 

ሌላው " የሃይማኖት ተቋም የሚይዘው ስያሜ፣ ዓርማ ወይም ምልክት ቀድሞ ከተቋቋመ ተቋም ስም፣ ዓርማ ወይም ምልክት ጋር ተመሳሳይ መሆን የለበትም " በሚል ረቂቁ ላይ የተቀመጠው ነው።

ይህ ፤ " #በከፊልም ሆነ #ሙሉ_በሙሉ ተመሳሳይ መሆን የለበትም " በሚል ሊስተካከል እንደሚገባው ገልጸዋል።

ለዚህ ምክንያቱ " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ስያሜ የኢትዮጵያ የሚለውን ብቻ በማውጣትና የራሳቸውን በመተካት አገልግሎት ላይ ሲያውሉ የሚታዩ አካላትን ስለተመለከትን ነው " በማለት አስረድተዋል፡፡

2ኛ. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤትን በመወከል የተገኙ ተሳታፊዎች ያቀረቡት ቅሬት ፦

ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሚከለክለው የረቂቅ አዋጁ ክፍል " በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች መፈጸም የተከለከለ ነው " በሚል የቀረበው ሊስተካከል ይገባል ብለዋል።

#ሶላት_የደረሰበት_ሙስሊም በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች እንዳይሰግድ መከልከል እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

" በከተሞች ውስጥ ለአምልኮና መቃብር የሚሰጥ ቦታ የከተማውን የዕድገትና የልማት ዕቅድ ወይም ማስተር ፕላን የማይቃረን መሆን አለበት " በሚለው ረቂቁ ላይ ይህ ወደ ተግባራዊነቱ ሲገባ አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልጸዋል።

መጀመሪያ የተገነባ ቤተ እምነት " ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የሚቃረን ነው " በሚል እንዳይፈርስ ዋስትና የማይሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች ሁሉ እምነት እንዳላቸው፣ ለአብነትም አንድ ሙስሊም በመንግሥት ተቋም ተቀጥሮ ሲሠራ ሶላቱን በሚሰግድበት ወቅት፣ በተቋሙ ውስጥ ሃይማኖታዊ ክንውን አድርጓል ሊባል መሆኑንና ረቂቁ ይህን እንዴት ማስታረቅ እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል፡፡

3ኛ. የወንጌል አማኞች ካውንስል ተወካዮች ቅሬታ ፦

ረቂቅ አዋጁ በወንጌላውያን ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

" በተለይ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ የሚከለክሉ የረቂቁ ክፍሎች፣ ወንጌል መስበክ መሠረታዊ አስተምሯችን ለሆነው ለወንጌላውያን ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል ነው " በማለት ተናግረዋል፡፡

ይህ ' መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ' በሚል የተቀመጠውን መርህ የጣሰ እንዳይሆን ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

Credit ➡️ Reporter Newspaper

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ…
#ሙሉ_ቃል

ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ምን አለ ?

" ' ግደሉ ብሎ ' ማወጅ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል እና ቅዱስ ሲኖዶስን የማይመጥን ንግግር ነው " - ቅዱስ ሲኖዶስ

ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ ያቀረቡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በንባብ ያሰሙት ፦

" በአሁኑ ሰዓት ላይ ትልቅ ተግዳሮትና የፈተና ምንጭ በመሆን ቤተክርስቲያናችንን ዋጋ እያስከፈሏት ያሉትን የአንዳንድ አባቶች መግለጫ እና የአውደ ምህረት ትምህርቶች እንደ አብነት በመጥቀስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰፊው ተወያይቷል።

በውይይቱ የተለዩ ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- አብዛኛው የአውደ ምህረት ስብከቶቻችን ከትምህርተ ወንጌል ይልቅ የነገር እና የደረቅ ትችት መድረክ እየሆኑ መምጣታቸው ፤

- በተለይም በመዋቅር ውስጥ የስራ መደብ የሌላቸው ተዘዋዋሪ " #ሰባኪ_ነን_ባዮች " የወገንተኝነት እና የፖለቲካ ትችትን እንደ ተከታይ ማፍሪያ በመቁጠር በሚዘሩት ፍጹም ከቃለ ወንጌል የራቀ ዘር ቅድስት ቤተክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት መሆኑ ፤ ይህን ለመከላከል ጥረት በሚያደርጉ አህጉረ ስብከት ላይ ትልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተፈጠረ መሆኑ ፤

- በተለይም ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበትና ምእመናንም በተሰበሰቡበት እንደ ቀኖና ቤተክርስቲያን ዕለቱን አስመልክቶ ተገቢውን ትምህርተ ወንጌል ከመስጠት ይልቅ ቤተክርስቲያንን የማይመጥን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን የተከበረ ጠቅላይ ሚኒስትር ፦

° " #ግድሉ "
° " #ዘርህ_ይጥፋ "
° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " የሚሉ ህገወጥ እና ክብረነክ የሆኑ ንግግሮች በመናገር በፈጸሙት ያልተገባ ተግባር በቤተክርስቲያኒቱ እና በመንግስት መካከል የነበረውን ግንኙነት በማሻከር ቤተክርስቲያንን ብዙ ዋጋ እያስከፈላት ከመሆኑ በላይ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶችን ክብር እና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ ያደረገ ተገቢነት የሌለው አድርጎት መሆኑን፤

- ክብር ይግባውና ጌታችን፣ አምላካችን መድሃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ በማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ አምስት ቁጥር ሰላሳዘጠኝ ላይ እንደተናገረው " እኔ ግን እላችኋለሁ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግመህ አዙርለት " ብሎ ያስተማረውን አብነት አድርጋ አትግደል የሚለውን ህገ ኦሪት አጽንታ እያስተማረች እስካሁን ድረስ ጸንታ በቆየችው እናት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ " ግደሉ " ብሎ ማወጅ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክልና ቅዱስ ሲኖዱስን የማይመጥን ንግግር መሆኑን ፤

- ልክ እንደ አቡነ ሉቃስ ፈጽሞ ጫፍ የረገጠ ባይሆንም ሌሎችም #አንዳንድ_አባቶች በተለያዩ ቦታዎች ያስተላለፏቸው መልዕክቶች አግባብነት የሌላቸውና ቤተክርስቲያንን ለትችት የዳረጉ መሆናቸውን ምልዓተ ጉባኤው በዝርዝር ገምግሟል።

ውሳኔ ፦

1ኛ. ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ " ግደሉ ፣ ዘርህ ይጥፋ፣ የአድማ ብተና ይበትንህ " ... ሌሎች ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆኑ ንግግሮች ቤተክርስቲያኒቱንም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል ከቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ እና ቀኖና ውጭ የሆነ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር መሆኑ ፤

2ኛ. በቀጣይም እንዲህ አይነት ተመሳሳይ ስህተት #በብዑጽነታቸው ሆነ በአንዳንድ አባቶች ሰባክያን ወንጌል እንዳይደገም ተፈጽሞም ቢገኝ ተገቢው የእርምት ውሳኔ ለመስጠት ይቻል ዘንድ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ አስመልክቶ ገዢ የሆነ ህገ ደንብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አገልግሎት መምሪያ እና በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ፤

3ኛ. ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ዕለት ጀምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ አህጉረ ስብከት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጸም ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ፤ ከክትትል እና ከቁጥጥር ጉድለት ምክንያት በየትኛውም የቤተክርስቲያኒቱ አውደምህረት ላይ ለሚተላለፉ የተሳሳቱና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች እና ንግግሮች በኃላፊነት የሚያስጠይቅ መሆኑን ለሁሉም ሀገረ ስብከት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ይህ ሙሉ ቃል የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ነው። "

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia