TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አልዓዛር_ተረፈ

" ወለጋ ላይ አማራ ተጨፍጭፏል የሚል ጹሑፍ ጽፈሃል፤ የስሪላንካን አመጽ ደግፈሃል፤ ችግኝ ተከላን ተቃውመሃል " በሚል ተጠርጥሮ የታሰረው የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ሚዲያ አል ዓይን ኒውስ አማርኛ አገልግሎት ጋዜጠኛ ዓላዛር ተረፈ ሃምሌ 21 ከእስር ተፈቷል።

ጋዜጠኛ አልዓዛር በ10 ሺህ ብር ዋስ ነው የተፈታው።

የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ10 ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ፈቅዶለት፤ ፖሊስ ይግባኝ ብሎ የነበረ ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሰበር ሰሚ ችሎትም ይህንኑ ውሳኔ አጽንተውት ሃምሌ 21 ቀን ከእስር ተለቋል፡፡

@tikvahethiopia
#UN #USA

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ጃኮብሰን እና የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ኢትዮጵያ ከሚገኙት የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን ኮሚሽን ኤክስፐርቶች ጋር መከሩ።

ምክክሩ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ ላይ በዚህ ሳምንት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያደረጉትን ውይይት የተመለከተ ነበር።

የተመድ መርማሪዎች እንዲሁም የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ኢትዮጵያ እንደሚገኙ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#ENDF

" የአልሸባብ ታጣቂዎች ያሉበት ቦታ በአየር ተደበደበ " - የሶማሊያ ሚዲያዎች

የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የትላንቱን የአልሸባብ አሻባሪ ቡድን የ " አቶ "ን ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላኖች የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ባሉበት ጋራስዌይን ላይ የአየር ድብደባ መፈፀማቸውን ዛሬ ምሽት እየፃፉ ይገኛሉ።

ቦታው ከሁዱር ወረዳ ከባኮል ክልል ዋና ከተማ በስተሰሜን 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ስለደረሰ ጉዳት ያሉት ነገር የለም።

መረጃውን በተመለከተ እስካሁን በመከላከያ በኩል የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መከላከያ እንዲሁም የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሀገርን ሊዳፈር የሞከረውን እና አጠቃላይ የቀጠናው ስጋት የሆነው አልሸባብ ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት እስከወዲያኛው እርምጃ ሲወሰድባቸው በህይወት የተያዙም አሉ ፤ በርካታ የጦር እና የመገናኛ መሳሪያዎችም መያዝ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#Facebook

• " ፌስቡክ በገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን #ሆን_ብሎ የማሰራጨት አደጋ አለ " - ግሎባል ዊትነስ

• " የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች ተላልፈዋል። ችግሩ የተፈጠረው የምንጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው " - ፌስቡክ

በጎረቤት ኬንያ በነሐሴ ወር ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን ከገፁ ላይ እንዲያጠፋ የኬንያ ባለስልጣናት ጠይቀዋል።

ፌስቡክ ማስተካከያ ካላደረገ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

ግሎባል ዊትነስ የተባለ የመብት ቡድን ባወጣው ሪፖርት ፌስቡክ የዘር ግጭት የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ንግግሮች ያሉባቸው ማስታወቂያዎችን ማፅደቁን ይፋ አድርጓል።

ግሎባል ዊትነስ በጥናቱ ሂደቱ 10 በእንግሊዘኛ እና 10 በስዋሂሊ ቋንቋ የተሰሩ የጥላቻ ንግግር ያዘሉ ማስታወቂያዎችን ለፌስቡክ ያስተላለፈ ሲሆን ሁሉም ማስታወቂያዎች መፅደቃቸውን የተቋሙ ዋና አማካሪ ጆን ሎይድ ተናግረዋል።

በኬንያ ፌስቡክ #ከ10_ሚሊየን_በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በነሐሴ ወር የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በማህበራዊ ድህረገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን #ሆን_ብሎ የማሰራጨት አደጋ መኖሩን ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

ሪፖርቱን ተከትሎ ፌስቡክ ትላንት ባወጣው መግለጫ የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች በገፁ መተላለፉን አምኖ ችግሩ የተፈጠረው ድህረገፁ የሚጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው ብሏል።

አክሎም፣ በተለይ የስዋሂሊ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ቴክኖሎጂዎች ጎጂ መረጃዎችን በማስወገድ እንዲያግዙት እና ምርጫው ሰላማዊ እና ስጋት የሌለበት እንዲሆን በሰዎች ላይ እና ቴክኖሎጂዎች ላይ እንዲሰራ መጠየቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#DY_Technology

ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ በጣም በዝቅተኛ ሃይል መስራት የሚችል፤ ዝርዝሩን ያንብቡ👉https://t.iss.one/pls_see_more/335
የመንገደኞች እንግልት እና የመንግስት አካላት ምላሽ !

ከአማራ ክልል በተለይም #ከሰሜን እና #ደቡብ_ወሎ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ብዙዎች እየተንገላቱ ነው።

ይህ ጉዳይ አንድ ወቅት ጠንከር አንዴ ላላ ፤ ያዝ ለቀቅ እያደረገ አሁንም ድረስ ቀጥሏል።

አንዳንዶች በብዙ ልመና ነው የሚያልፉት።

ወደ መጣችሁበት ተመለሱ የሚባሉ ወገኖች ምክንያት ቢጠይቁም በግልፅ አስረድቶ የሚነግራቸው አላገኙም።

ለመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ምን አሉ ?

👉 " ... መላ ሊባልለት የሚገባ ነገር ነው። ከደሴ ተነስተን ወደ አ/አ እየሔድን ነበር ግን " ሸኖ " ላይ የአማራ ክልል መታወቂያ ይዛችሒ አትገቡም ተብለን ስንጉላላ ቆይተን ሹፌሩ ይዘሐቸው ተመለስ ተብሏል። ሌሎቹ ተመልሰዋል። እኔ ግን ግድ መሔድ ስላለብኝ ለፈተና ባጃጅም በግሬም ኡ/ ገብቻለሁ ፡፡ እባካችሁ ዛሬ ብቻ አደለም ያዝ ለቀቅ እያደረጉ ነው እንጅ ከብዶናል "

👉 " እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም ድረስ ከወሎ መዳረሻቸውን አ.አ አርገው የሚመጡ ተሳፋሪዎች ከበኬ ኬላ አየተመለሱ አሌልቱ ላይ ብዙ እንግልት እየገጠማቸው ይገኛል "

👉 " ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለው ብዙዎች ሲንገላቱ ቆይተው ወደ ኃላ እንዲመለሱ ተደርገዋል። እኛ በብዙ ልመና ለህክምና ነው ብለን አልፈናል። "

#ሪፖርተር_ጋዜጣ ያነጋገራቸው ፦

👉 " ሐምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. መነሻችንን ከወልዲያ ከተማ አድርገን ወደ አዲስ አበባ ስንጓዝ የአማራ ክልልን አልፈን ኦሮሚያ ክልል ስንገባ ተደጋጋሚ ፍተሻ ተደርጎልናል። ለገዳዲ ከደረስን በኃላ ግን የአዲስ አበባ መታወቂያ የላችሁም በሚል ምክንያት ወደ ደብረ ብርሃን መልሰውናል። ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ነው ።

ከሸኖ ከተማ ጀምሮ እስከ ሰንዳፋ ድረስ የተደረገብን ፍተሻ በጣም አድካሚ ከመሆኑም በላይ፣ የአዲስ አበባ መታወቂያ የላችሁም በሚል ሲሳለቁብን ማየት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አሳፋሪ ተግባር ነው።

ፖሊሶች ፍተሻ ካደረጉ በኋላ የአዲስ አበባ መታወቂያ የሌላቸውን እዚያው ክልላቸው ወስደህ አውርዳቸው በማለት ለሾፌሩ ተናግሯል።

በዚህም የተነሳ በግዴታ ለገዳዲ ከደረስን በኋላ እንደገና ተመልሰን ደብረ ብርሃን ከተማ አድረናል። በስተመጨረሻም በነጋታው የቤት መኪና ተከራይተን ለቅሶ እንደምንሄድ በመናገር አዲስ አበባ ገብተናል።

የተፈጠረውን ክስተት አስከፊ ነው። በጊዜው ገንዘብ ስለነበረን ከፍለን ተመለስን ነገር ግን ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ሲደረጉ ሕፃን ልጅ የያዙ እናቶች ጭምር ለመመለሻ የሚሆን ገንዘብ አጥተው ሜዳ ላይ ወድቀው ነበር።

ይህን ያህል አማራ ምን አድርጎ ነው ? ወስደህ አውርዳቸው እንዴት ይባላል ? ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ ? ብዙ ግፍ ያለበት ክልል እኮ ነበር፣ በአማራ ላይ ይህ ሁሉ ሲደረግ ሕግ አለ ወይ ያስብላል ? "

👉 " አደራው ኃይሌ እባላለሁ ከደሴ ከተማ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝኩ ነበር 100 ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ውስጥ ከጫጫ ከተማ እስከ ለገዳዲ ከተማ ቢያንስ 7 ጊዜ ተፈትሸናል።

የመጨረሻው የአዲስ አበባ መግቢያ ፍተሻ በነበረው ለገዳዲ ስንደርስ ከጥቂት የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ ከያዙ ሰዎች ውጪ ቀሪዎቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ድርጊቱ በጣም የሚያሳዝን ነው።

ከመኪና እንድንወርድ ከተደረገ በኋላ ስልካችንን ከፍተን በውስጥ ያሉ ምሥሎችና ድምፆችን ከፍተን እንድናሳይ ተደርጓል።

👉 " ሁኔታው የሕግ ድጋፍ ያለው እንደማይመስልና አልፎ አልፎ ፖሊሶቹ በመሰላቸው አሠራር እንጂ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈቅድ ምንም ዓይነት የሕግ መሠረት ማቅረብ አይቻልም።

ድርጊቱ አሳፈሪ በመሆኑ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለጉዳዩ አፋጣኝ መልስ መስጠት ካልቻለ፣ እንደ አገር አብሮ በኖረ ሕዝብ ላይ አሁን ያለው የፖለቲካ ግለት ተጨምሮበት የባሰ ቁርሾ፣ እርስ በርስ የመለያየትና ከፋፋይ የሆነ አጀንዳ ይሆናል "

የመንግስት አካላት ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

▪️የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፦

" ጉዳዩ ስለመከሰቱ መረጃ አለኝ። ነገር ግን የሕወሓት ሠርጎ ገቦችን ለመያዝ በሚል ግልጽ ባልሆነ መንገድ ዜጎች እየተንገላቱ በመሆኑ ጉዳዩን ለኦሮሚያ ክልል መፍትሔ እንዲሰጥበት አሳውቀናል። "

▪️የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አራርሳ መርዳሳ ፦

ጥያቄ ከሰሙ በኋላ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

▪️የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ፦

" ጉዳዩ መከሰቱን መረጃ አለኝ።

ተሳፋሪዎች ደብረ ብርሃን ከተማ ካለፉ በኋላ እንዲህ ዓይነት ችግር ተፈጥሯል።

ከኦሮሚያ ክልልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ደውላችሁ አጣሩ "

▪️የአዲስ አበባ የፀጥታ ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ፦

" ስለሚባለው ጉዳይ ምንም ዓይነት መረጃ የለንም "

▪️የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፦

" የተጠቀሰው ጉዳይ አይመለከተንም "

▪️ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሪት ሰላማዊት ካሳ ፦

" ጉዳዩ የሕወሓት የሽብር ቡድን በወረራ ይዟቸው ከነበሩት የአማራ ክልል አካባቢዎች የተለያዩ የመታወቂያ ማኅተሞችና የአስተዳደር ሰነዶችን በመዝረፉና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ሐሰተኛ መታወቂያዎች ሰነዶችን የያዙ ሠርጎ ገቦች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ በመያዛቸው ምክንያት የሚደረግ የክትትል ሥራ ነው።

የጥፋት ተልዕኮ የያዙና ከአማራ ክልል ተዘርፈው በተወሰዱ ሰነዶች ተመሳስለው የተሰሩ መታወቂያዎችን የያዙ ግለሰቦች አሁንም ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዳለ ለፀጥታ ኃይሎች መረጃው በመድረሱ ይህንን ለመከላከል ጥብቅ ፍተሻዎችና ማጣራቶች እየተደረጉ ነው።

ይሁን እንጂ አዲስ አበባን የጥፋት ተልኳቸው መዳረሻ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉትን አካላት ለመከላከል በሚወሰደው ዕርምጃ፣ በመንገደኞች ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩንና ዜጎችም ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የተመለከቱ ቅሬታዎች ደርሰውናል።

ይህም በደኅንነት ፍተሻና ማጣራት አፈጻጸም ላይ መሻሻል ያለበትን ሁኔታ ለይቶ የፀጥታ ኃይሉ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወስድ ይደረጋል ። "

▪️የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የአብን ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ፦

" ... ከአማራ ክልል የወሎ አካባቢዎች ተነስተው መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዜጎች ኦሮሚያ ክልል ሸኖ ሲደርሱ መታወቂያቸው እየታየ ከተሳፈሩበት መኪና እንዲወርዱና ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን ተጨባጭ መረጃዎች አሉ።

የሚመለከታቸው የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የሥራ ኃላፊዎች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን መጉላላትና አግላይ የነውር ተግባር ታስቆሙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ደቡብ ክልል ? እስካሁን የክልልን አደረጃጀትን በምክር ቤቶች የፀደቁ እነማን ናቸው ? - ወላይታ - ጋሞ - ጌዴኦ - የም ልዩ ወረዳ - ቡርጂ ልዩ ወረዳ - ኮንሶ - ባስኬቶ ልዩ ወረዳ - ኧሌ ልዩ ወረዳ - ደቡብ ኦሞ - አማሮ ልዩ ወረዳ በአንድ የክልል ስር ለመሆን በየምክር ቤቶቻቸው አፅድቀዋል። - ከምባታ - ሀላባ - ሀዲያ - የም ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ከጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ጋር በአንድ…
#ስልጤ_ዞን

በዛሬው ዕለት የስልጤ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔዉን ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ከሚወያይባቸው አጀንዳዎቹ መካከል ቀዳሚው #የክልል_አደረጃጀትን በተመለከተ በቀረበ መነሻ ሀሳብ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ትላንት የከምባታ፣ ሀላባ ፣ ሀዲያ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ከጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ጋር በአንድ ላይ በመሆን በአንድ ክልል ስር ለመጠቃለል በምክር ቤቶቻቸው መወሰናቸው የሚታወስ ነው።

የክልል አደረጃጀትን በተመለከተ የጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች በም/ቤት ገና ውሳኔ እንዳላሳለፉ መነገሩም አይዘነጋም።

ዛሬ የስልጤ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ስልጤ_ዞን በዛሬው ዕለት የስልጤ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔዉን ማካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ተገልጿል። ምክር ቤቱ ከሚወያይባቸው አጀንዳዎቹ መካከል ቀዳሚው #የክልል_አደረጃጀትን በተመለከተ በቀረበ መነሻ ሀሳብ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ትላንት የከምባታ፣ ሀላባ ፣ ሀዲያ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ከጉራጌ እና ስልጤ…
#Update #ፀድቋል

የስልጤ ዞን ም/ቤት የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ለመመለስ በመፍትሄነት የቀረበዉን የዉሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ አጽድቋል።

የዞኑ ም/ ቤት የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ለመመለስ በመፍትሄነት የቀረበዉን መነሻ ሀሳብ ይኸውም ፦
- ስልጤ፣
- ጉራጌ፣
- ሀዲያ፣
- ካምባታ ጠምባሮ ፣
- ሀለባ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳ አንድ ላይ ይደራጁ የሚለዉን መነሻ የዉሳኔ ሀሳብ በአንድ ተቃዉሞ በአብላጫ ድምጽ ተቀብሎ ማፅደቁን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ጎፋ ዞን አፅድቋል !

ዛሬ የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሳውላ ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም የክልል አደረጃጀትን በተመለከተ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ከሌሎች አጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጋር አብሮ ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

በአዲስ የክልል አደረጃጀት በጋራ የሚደራጁ 11 መዋቅሮች ፦
- ወላይታ፣
- ጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ጌዴኦ፣
- ኮንሶ፣
- አማሮ፣
- ደቡብ ኦሞ፣
- ኧሌ፣
- ባስኬቶ፣
- ቡርጂ እና ደራሼ መሆናቸው በምክር ቤቱ ተገልጿል።

#የማዕከል_ጉዳይ ሳይንሳዊ፣ ምክንያታዊ በሆነ እንዲሁም ውይይት ተደርጎበት በህዝብ ድምፅ የሚወሰን መሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#AwaQi

ነፃ የስልጠና እና የተለያዩ እድሎችን እንዲሁም አዝናኝ እና አነቃቂ ቪድዮዎችን በየጊዜው ለማግኘት አዋቂን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/+fM0ANWxp33Y2ZjM8

@awaqiethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
' 2015 ለኢትዮጵያ የተሻለ እንዲሆን እመኛለሁ '

ኮማንደር አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል ወቅት የተናገረችው ፦

" ዛሬ ያወደስናቸው የትግራይ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው ይሩኑ አይኑሩ ፤ ይብሉ አይብሉ ፣ ይታከሙ አይታከሙ የሚለውን የሚያውቁት ነገር የለም።

ስለዚህ እዚህ ጋር ጥሩ ጎናቸውን ተቀብለን እዛ ጋር ያ ጉድለታቸውን መሙላት ስላለብን እነዚህ አትሌቶች የሚፈለግባቸውን ነገር ሁሉ አድርገዋል መንግስት ደግሞ እንደመንግስት ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመነጋገር የተሻለ ነገር አድርጎ ቤተሰቦቻቸውን እንዲያገኙ ፣ የትግራይ ህዝብም የተሻለ መሰረታዊ ነገር እንደ ስልክ፣ መብራት፣ ባንክ የመሳሰሉትን ነገሮች እንዲያገኝ ቢያደርረግ ደስ ይለናል።

ምክንያቱም እኛ ለእነዚህ አትሌቶች ቅርብ ነው ያለነው። ቅርብ ስትሆን ትሳቀቃለህ ፣ ከአንዱ አንዱን ስታይ ትሳቀቃለህ ሁለተኛውን ፣ ሶስተኛውን ስታይ ትሳቀቃለህ ብዙ ነገር ነው ያለው እዛ በቅርብ ስናይ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው።

እኛም እስከመቼ ነው የምንጨነቅው ከእነዚህ አትሌቶች ጋር ? ስለዚህ እኔስ ብሆን ፣ እናቴስ ብትሆን፣ አባቴስ ቢሆን፣ ወንድሜስ ቢሆን፣ ልጄስ ቢሆን ብለን ማሰብ አለብን የኢትዮጵያ መንግስት ከአፅንኦት ጋር የማሳስበው ይሄን ነገር ያደርጋል ብዬ ገምታለሁ።

እነዚህ አትሌቶች ልዩነታቸውን ጠብቀው ፣በሀገራቸው ጉዳይ ጠንክረው ፣ ጠንክረን ይሄን ውጤት አምጥተናል ያሉንን ልዩነቶች አጥበን መሰረታዊ ነገሮች አሟልተን እዛ ያሉትን አትሌቶች ረድተን እዚህ ያሉትንም አጠንክረን ሞራል ሰጥተን የተሻለ ዓመት 2015ን እንድንቀበል የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትንም የኢትዮጵያ መንግስትንም እጠይቃለሁ። እግዚአብሔር ይርዳን።

2015 ለኢትዮጵያ የተሻለ እንዲሆን እመኛለሁ። ህዝብ ተፈናቀለ፣ ሞተ፣ ተሰደደ፣ ተራበ የሚባለው ነገር ጠፍቶ በአትሌቶቻችን ደስ እንዳለን ሁሉ ኢትዮጵያን ደስ የሚላት ነገር እንዲመጣ ከልቤ ፀልያለሁ፤ ከልቤ እመኛለሁ፤ እኛ ከለመነው እግዚአብሔር ያን ያሳካዋል።

ሁላችንም የጥላቻ ልብ ወደጎን አድርገን የይቅር ባይነት ልብ ካቀረብን ይሆናል። ጥላቻን ባቀረብን ቁጥር ሁለመናችን ወደጥላቻ ይሄዳል፤ ጥላቻን ትተን በጎ ባሰብን ቁጥር ሁሉ ነገር በጎ ይሆናል።

የጥላቻ ልብን እንደምንም አሸንፈነው የይቅር ባይነት ልብ፣ የመረጋጋት ልብ፣ የማስተዋል ልብ ፣ ከጭካኔ የራቀ የርህራሬ ልብ እግዚአብሔር እንዲሰጠን የሁል ጊዜ ፀሎቴ ነው።

ህዝቤ የተሻለ ነገር እንዲያገኝ ከልቤ እመኛለሁ "

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

@tikvahethiopia