TIKVAH-ETHIOPIA
#update የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አያን አብዲን አፈ ጉባዔ አድርጎ ሰየመ 6ኛው ዘመን 1ኛ አመት የሶማሊ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡ በጉባዔው የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አያን አብዲ ዋና አፈ ጉባዔ እንዲሆኑ ሰይሟል፡፡ ም/ቤቱ በመስራች ጉባኤው ኢብራሂም ሀሰንን ምክትል አፈ-ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል። አዲሷ አፈጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት…
#Update
አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።
አዲሱ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የመጀመሪያ አመት ጉባኤው ላይ አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመርን የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።
አቶ ሙስጠፋ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ባለፉት 3 አመታት የሶማሊ ክልልን መምራታቸው ይታወሳል።
Credit : SMMA
@tikvahethiopia

#Update አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። አዲሱ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የመጀመሪያ አመት ጉባኤው ላይ አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመርን የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል። አቶ ሙስጠፋ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል። አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ባለፉት 3 አመታት የሶማሊ ክልልን መምራታቸው ይታወሳል። Credit :…
#Update
አቶ ኢብራሂም ኡስማን የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።
አዲሱ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የመጀመሪያ አመት ጉባኤው ላይ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህን የሶማሊ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።
አቶ ኢብራሂም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
Photo Credit : SMMA

#GONDAR
" ለመንገድ ስራ ደማሚት ይፈነዳል፤ እንዳትደናገጡ " - የጎንደር ፖሊስ
ከዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከኮሌጅ ብሪጋታ የመንገድ ስራ ለመስራት ደማሚት ይፈነዳል፡፡
ነዋሪዎች ጉዳዩን አውቀው ያለ ምንም መደናገጥ የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ መልእክት አስተላልፏል።
#ሼር #Share

#Mekelle : ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ መዘገቡን ሮይተርስ በድረገፁ አስነብቧል።
ሮይተርስ ፤ በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የትግራይ ቴሌቪዥን ሪፖርት እንዳደረገው በአየር ጥቃቱ በርካታ ሲቪሎች እንደተጎዱ ገልጿል ብሏል።
የክልሉ ቴሌቪዥን 3 ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ10 በላይ ደግሞ መቁሰላቸው ዘግቧል።
የመጀመሪያው ድብደባ ዛሬ ጠዋት በመቐለ ዳርቻ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሚገኝበት አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን ሁለተኛዉ ድብደባ እኩለ-ቀን በመቐለ ማዕከላዊ ክፍል ባለሥልጣናት የሚያዘወትሩት ፕላኔት ሆቴል አካባቢ ነው።
ሮይተርስ የእርዳታ ሰራተኞችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም አንድ ዶክተር ዛሬ በመቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን እንደገለፁለት ዘግቧል።
የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት እንዳልሰጡት ፤ ከኢትዮጵያ ጦርም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው ፤ "መንግሥት ለምን የራሱን ከተማ ያጠቃል? መቐለ የኢትዮጵያ ከተማ ነች" ሲሉ ለሬውተርስ ተናግረዋል።
ሮይተርስ ከከተማው ስለወጡት ሪፖርቶች ገለልተኛ ማጣራት ማድረግ እንዳልቻለ ጠቁሟል።
@tikvahethiopi

#Wuchale : የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ ህወሓት በውጫሌ እና ጭፍራ አካባቢዎች በፈፀመው ጥቃት 30 የሚሆኑ ንፁሃንን መገደላቸውን አስታወቀ።
30 ንፁሃን የተገደሉት ህወሓት ከሰሞኑ በውጪሌ እና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈፀመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት መሆኑ ተገልጿል።
ይህን ያሳወቁት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።
ዶ/ር ለገሰ ፥ " አሸባሪው ህወሓት ወሮ በያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ላይ ንጹሀንን በግፍ እየገደለ ነው። ከሰሞኑም ቡድኑ በከባድ መሳሪያ በፈጸመው ድብደባ በውጪሌ እና ጭፍራ አካባቢዎች ንጹሀንን ገድሏል" ብለዋል።
ሚኒስትሩ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ አዲስ ስልት ጀምሯል ያሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ተኩስ በከፈተባቸው አካባቢዎች ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልሙን ለማሳካት የህዝብ ማዕበል ስልትን እየተከተለ የትግራይ ህጻናትን እያስፈጀ ነው ብለዋል።
መንግስት በተረጋጋና በተጠና ሁኔታ እርምጀ ይወስዳል ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ፥ " ይሄ ጦርነት የማይመለከተው ሰው ስለሌለ አሸባሪው ህወሓት በአሁኑ ወቅት የከፈተውን ጦርነት ሁሉም ወገን ከመከላከያ ጎን በመሆን ይመክት " ሲሉም ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

#AddisAbaba : በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2 ሰዎች በእሳት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን የአ/አ ፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።
አደጋው ወረዳ 10 ኬብሮን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ የተከሰተ ሲሆን የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል 6 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
ትላንት ምሽት 12:42 ሰዓት ላይ የተከሰተው በዚህ የእሳት አደጋ መንስኤው በካፌና ሬስቶራንት ውስጥ የነበረው ሲሊንደር በመፈንዳቱ ምክንያት ነው ብሏል ፖሊስ።
እሳቱ ወደ ሌሎች እንዳይዛመት በእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ ፖሊስና የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ጥረት እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።
መሰል አደጋዎች በተለይ የንግድ ተቋማት አካባቢ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠትና ለአደጋ አጋላጭ የሆኑትን ነገሮች በማስወገድ እንዲሁም ለአደጋ ጊዜ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይገባል ብሏል ፖሊስ።

#Dessie : ዛሬ ሮይተርስ በድረገፁ ከደሴ ከተማ የተሰራ ሰፋ ያለ ዘገባ አስነብቧል።
በዚሁ ዘገባ አንዲት ሀብታም አከለ የምትባል እናት በምግብ እጥረት ምክንያት ልጇን እንዳጣች ተናግራለች።
ሀብታም የ3 ዓመት ህፃን ልጇን በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ባለፈው ወር ነው ያጣችው (ከቆቦ) ወደ ደቡብ የአማራ ክልል ክፍል ከመሸሻቸው በፊት።
ሀብታም ፥ ዶክተሮች ልጇ በምግብ እጥረት በጣም እንደተጎዳች በዚህም ምክንያት ልጇን ሊረዷት እንዳልቻሉ እንደነገሯት ተናግራለች። ዶክተሮቹ መድሃኒት ቢሰጧትም ትንሿ የሀብታም ልጅ ከሳምንት በኃላ ህይወቷ አልፏል።
ሀብታም የሰሜኑን ጦርነት ሽሽት ወደ ደሴ ከተሰደዱ በሺዎች ከሚቆጠሩ የአማራ ቤተሰቦች አንዷ እንደሆነች ሮይተርስ ፅፏል።
በደሴ ተፈናቃዮች በትምህርት መማሪያ ክፍል ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ በረድፍ ነው የሚተኙት ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ያገረሸው ግጭት ደግሞ ይህን ያባብሰዋል ተብሎ ይሰጋል።
ሀብታም በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች አነስተኛ ምግብ እንዳለ እንዲሁም የትግራይ ኃይሎች በአካባቢው ከሚገኙ ፋርማሲዎች ያለውን አነስተኛ መድኃኒቶችን እንደዘረፉ ተናግራለች።
የህወሓቱ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ይህንን ክስ እንደማይቀበሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል፤ ይልቁንም ሃብታም ትኖር በነበረበት አካባቢ በጄኔሬተር ያለውን ውሃ እጥረት ለመቅረፍ መስራታቸውን ገልፀዋል።
ሌላ በካምፕ ውስጥ የምትገኝ እና ሮይተርስ ያነጋገራት አንዲት ሴት በታጠቀ የትግራይ ኃይል መደፈሯን ገልፃለች። ይህ የተፈፀመባት በትግራይ ኃይሎች ስር ባለ የአማራ ክልል አካባቢ ነው።
ስሟ ሰዓዳ ይባላል እድሜዋ 26 ሲሆን ከደሴ 80 KM በምትገኘው በመርሳ ከተማ ቤቷ ውስጥ እያለች ነው ይህ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባት።
ሰዓዳ ትክክለኛውን ቀን ባታስታውሰው። ድርጊቱ ነሐሴ መጨረሻ አካባቢ መፈፀሙን ተናግራለች።
ሰዓዳ እንደደፈራት የገለፀችው የትግራይ ኃይል ፥ " እኛ ቤታችንን ጥለን የወጣነው ለመግደልም ለመሞትም ነው። እኔ ከጫካ ነው የመጣሁት የፈለኩትን የማድረግ ሙሉ መብት አለኝ፤ ልግድልሽም ሁሉ እችላለሁ" ብሎ ጠመንጃውን ከፍ አድርጎ ካስፈራራት በኃላ እንደደፈራት ለሮይተርስ ተናግራለች።
ሰዓዳ ሮይተርስ ሙሉ ስሟን እንዳይጠቀም የጠየቀች ሲሆን ከተደፈረች በኃላ ለህክምና ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሄዷንም የሚያሳይ ካርድ አሳይታለች።
የደሴ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ልዑል መስፍን ስለሲቪል ጉዳት፣ ስለ አስገድዶ መድፈር ወይም ስለ ግለሰብ ጉዳይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል ፤ ለዚህ ምክንያታቸው የውጭ ጋዜጠኞችን ስለማያምኑ መሆኑ እንደገለፁ ሮይተርስ ፅፏል።
https://telegra.ph/Dessie-10-18-2

Telegraph
Dessie
#Amhara ዛሬ ሮይተርስ በድረገፁ ከደሴ ከተማ የተሰራ ሰፋ ያለ ዘገባ አስነብቧል። በዚሁ ዘገባ አንዲት ሀብታም አከለ የምትባል እናት በምግብ እጥረት ምክንያት ልጇን እንዳጣች ተናግራለች። ሀብታም የ3 ዓመት ህፃን ልጇን በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ባለፈው ወር ነው ያጣችው ወደ ደቡብ የአማራ ክልል ክፍል ከመሸሻቸው በፊት። ሀብታም ፥ ዶክተሮች ልጇ በምግብ እጥረት በጣም እንደተጎዳች በዚህም ምክንያት ልጇን…
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia : ኢሰመኮ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደህንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚሳስብ ነው ብሏል። በዚሁ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 /2014 ዓ/ም በደረሱ ሶስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። መስከረም 8 ቀን 2014 ደግሞ በውልማይ ቀበሌ በተፈፀመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ከነዋሪዎች ሪፖርት እንደደረሰው…
" በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ የሲቪል ሰዎችን ደህንነት ለማስከበር በቂ የፀጥታ ኃይሎች በቋሚነት ሊሰማሩ ይገባል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በመስፋፋት ላይ በመሆናቸውና ባሕሪያቸውን እየቀየሩ ብሔር ተኮር ወደ ሆነ የእርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ የሚችል በመሆኑ፣ መንግስት በቂ የፀጥታ ኃይሎችን በአፋጣኝና በቋሚነት በአካባቢው ሊያሰማራ እንደሚገባ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

#ETHIOPIA😷
ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 21 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 21 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,743 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 248 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 601 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#Mekelle : ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ መዘገቡን ሮይተርስ በድረገፁ አስነብቧል። ሮይተርስ ፤ በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የትግራይ ቴሌቪዥን ሪፖርት እንዳደረገው በአየር ጥቃቱ በርካታ ሲቪሎች እንደተጎዱ ገልጿል ብሏል። የክልሉ ቴሌቪዥን 3 ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ10 በላይ ደግሞ መቁሰላቸው ዘግቧል። የመጀመሪያው ድብደባ…
#Mekelle : ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት እንደነበር መገለፁ ይታወሳል።
የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ኃላፊ አቶ አበበ ሃብቱ ለጀርመን ሬድዮ ማምሻውን በሰጡት ቃል በዛሬው ሁለት ጥቃት 8 ተጎጂዎች ወደሆስፒታሉ እንደመጡ ሁለት ህፃናትም እንደሞቱ ገልፀዋል።
የሆስፒታሉ የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ፤ በሞሶቦ አሬና በነበረው ጥቃት 2 እድሜያቸው 12 እና 14 የሆኑ ልጆች ሞተው ወደሆስፒታል እንደመጡ ፤ አንድ ሰው ደግሞ ወደ ድንገተኛ ክፍል መግባቱን አስረድተዋል።
በሁለተኛው ጥቃት ከፕላኔት ጀርባ ከ5 በላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደሆስፒታሉ እንደመጡና ድንገተኛ ህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ከዛሬው የአውሮፕላን ጥቃት በኃላ በመቐለ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ ነው የዋለው።
ዛሬ ከሰዓት ላይ ጥቃቱን መፈፀሙን በተመለከተ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተጠይቀው ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ "መንግሥት ለምን የራሱን ከተማ ያጠቃል? መቐለ የኢትዮጵያ ከተማ ነች" ሲሉ መልሰው ነበር።
ማምሻውን ደግሞ የኢፌዲሪ አየር ሃይል በመቐለ ህወሃት ሲጠቀምባቸው በነበሩ የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች ላይ የተሳካ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።
እንደኢፕድ ዘገባ አየር ኃይሉ የወሰደው እርምጃ የፈደራል መንግስት ይዞታ በነበሩና ህወሓት አገር ለማፍረስ እየተጠቀመባቸው በቆዩ ይዞታዎች ላይ መሆኑ ገልጿል።
የአየር ድብደባው እንደ ፋና በመሰሉ የሚዲያና የኢንሳ ታወሮች እና መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበረና ተልዕኮውም በስኬት መጠናቀቁን ኢፕድ ዘግቧል።
ኢፕድ የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በፈጸመው ድብደባ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉንና ይህም በተሳካ ሁኔታ መፈፀሙን ገልጿል።

ዛሬ ማምሻውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ TPLF በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመሸፈን ጩኸቱን ቀጥሎበታል ብሏል።
TPLF በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈጸም በዜጎች ላይ ከፍተኛ አካላዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ቡድኑ በውጫሌና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ30 በላይ ንጹሃን ዜጎች በግፍ መግደሉን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
TPLF እያደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግድያ እንዳይታወቅበት ለመሸፋፈን የተለመደውን "የተኩላ ጩኸት ቀጥሎበታል" ሲል ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ የህወሓት ቡድን በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉና የሰብዓዊ እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን አመላክቷል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በTPLF የሐሰት መረጃ ሳይወናበድ በሰሜን ወሎ፣ በጎንደር በዋግ ህምራ እና በአፋር ክልሎች የዜጎችን ጉዳት ሊመለከት እንደሚገባ መንግስት ጥሪ ያቀርባል ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካንና አጋሮቿ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ሚዛናዊ ያልሆነ አቋም ዳግም እንዲመለከቱት መጠየቁን እንዲሁም የአውሮፓ ፓርላማ ያወጣው መግለጫ ከእውነታው የራቀ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስፍሯል።

" ከትግራይ የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ መፍትሔ ያገኛሉ" - የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከ150 በላይ ከትግራይ ክልል የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በማቅናት ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ይሁን እንጂ "ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ" የተማሪዎቹ ተወካዮች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል። በመቀጠልም በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር…
ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎች ምደባ ሊሰጣቸው ነው።
ከክልሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጊዚያዊ ምደባ ለመስጠት የትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ እንደሚገኝ የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ነገ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
More : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎች ምደባ ሊሰጣቸው ነው። ከክልሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጊዚያዊ ምደባ ለመስጠት የትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ እንደሚገኝ የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ነገ የምናደርሳችሁ ይሆናል። More : https://t.iss.one/joincha…
#Update
በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡
በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡
በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ 09/02/21014 ዓ.ም እስከ 12/02/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ታግዷል።
የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች #እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አሳውቋል።
የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የካፍ የስታዲየም መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን እዲያስተናግድ መደረጉ ይታወሳል።
የተለያዩ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ስታዲየም ከዚህ በኋላ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን እና ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮችን እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ በትናንትናው እለት ጥቅምት 7/2014ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
በደብዳቤውም ላይ ከኦክቶበር 20 በፊት ኢትዮጵያ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ጋር የምታደርገውን ጨዋታ በማን ሀገር በየትኛው ስታዲየም ለመጫወት እንደምትመርጥ ለካፍ በአስቸኳይ እንድታሳውቅ ካፍ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ካፍ ጨዋታውን ወደ ተጋጣሚዋ ሀገር እንደሚወስድ አሳውቋል ።
ለመታገዱ ምክንያት ምንድነው ? ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethsport

የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ታግዷል። የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች #እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አሳውቋል። የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የካፍ የስታዲየም መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን እዲያስተናግድ መደረጉ ይታወሳል። የተለያዩ የብሔራዊ…
#Hawassa #Jimma #AbebeBikela
ካፍ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መሟላት ካለበት መስፈርት አንጻር በርካታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ አሳውቋል።
ስታዲየሙ ለወደፊት የተጓደሉትን ነገሮች ካሟላ ወደፊት የካፍ የገምጋሚ ቡድን በመምጣት ጨዋታ ማስተናገድ ይችል እንደሆነ ይመልከተዋል።
ይህ እስካልሆነ ድረስ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም የኢንተርናሽናል ውድድር ማስተናገድ እንደማይል ተገልጿል።
የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በእድሜ ደረጃ ሚዘጋጁ ውድድሮችን እና የሴት የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎችን በጊዚያዊነት ማስተናገድ እንደሚችል ካፍ አሳውቋል።
የካፍ ማረጋገጫ ደብዳቤውም በአጭር ቀናት ውስጥ ይላካል ተብሎ ይጠበቃል።
የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በኢ.እ.ፌ ክለብ ላይሰንሲግ የተገመገመ እና ሪፖርቱ የደረሰው ካፍ መጫወቻ ሳሩ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ሜዳው አጠገብ ያለው መሮጫ መም በምርጫ መም እንዲሰፍን ወይም በሳር ሙሉ በሙሉ እንዲሸፈን ከዚህ ቀደም የገለፀ ሲሆን መልበሻ ክፍሎቹ በአዲስ መልክ ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
Credit : EEF
Photo : File