TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ItsMyDam🇪🇹

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የጅማ ፣ አዲስ አበባ ፣ ባህር ዳር እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች በውጭ ካሉ ተመራማሪዎች ጋር የሚመክሩበት የኦን ላይን ሲምፖዚም ይካሄዳል።

ሲምፖዚየሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ውሃ ጉዳዮች መማክርት ነው።

ይህን ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ለማካሄድ መነሻ ሃሳቡን በተመለከተ ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት ፕ/ር አቻምየለህ ደበላ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል ፦

" ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው አንድ ተለቅ ያለ ይዘት ያለው ጉባኤ ብንፈጥር በዛ ጉባኤ አማካኝነት በተለይ ኢትዮጵያውያኖችን እና የውጭ ሰዎችን ጋብዘን የኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ድምፅ የሚሰማበትና በተለይ እውነታው ከምን ጋር እንደሆነ እንዲያውቁ ያደርጋል በሚል ነው የተነሳነው። "

በሲምፖዚየሙ ላይ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ የኢትዮጵያን ትርክት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስረዳት በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ህጋዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ ታልሟል።

ይህን ሲምፖዚየም በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች እና የህዳሴድ ግድብ ዋና ተደራዳሪ እና አማካሪ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ነው ይከፍቱታል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ሲምፖዚየሙ የአባይን ጉዳይ ከብዙ አቅጣጫ ለማየት የሚሞክር መሆኑን ደግሞ ከአስተባባሪዎች መካከል አንዷ የሆኑት መቅደላዊት መሳይ ተናግረዋል።

አስተባባሪዋ ሲምፖዚየሙ ኢትዮጵያውያን ስለህዳሴ ግድቡ በሚገባ አውቀው ለሀገራቸው ትልም እንዲሞግቱ ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል።

ሲምፖዚየሙ ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ እንዲሁም በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ (ለ4 ቀናት) በኦንላይን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚካሄድ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ዶቼ ቨለ) ከአስተባባሪዎች መስማቱን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ትላንት (ጥቅምት 6/2014 ዓ/ም) ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ምን ተላከ ?

📩የአቶ ሌንጮ ለታ ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ማግኘታቸው : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63772?single

📩የአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሕገ መንግሥት ረቂቅን አስመልክቶ በቤንች ሸኮ ዞን እና በዳውሮ ዞን የተደረጉ ውይይቶች : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63774?single

📩39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ መጠናቀቅ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63780

📩የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች በሚበዙበት አካባቢ የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ (በአ/አ) : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63781?single

📩የጥቅምት 6 የኮቪድ-19 ሪፖርት : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63783

📩በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረግ ሲምፖዚየም : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63786?single

📩አሜሪካ በድሮን ለገደለቻቸው ንፁሃን አፍጋኒስታውያን ዘመዶች ካሳ ልትከፍል መሆኑ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/63770

(ውድ ቤተሰቦቻችን #ትላንት ተልኮላችሁ ያላያችሁትን መረጃ ሊንኮቹን በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ)

@tikvahethiopia
የመውሊድ በዓል ነገ ይከበራል።

የመውሊድ በዓል ነገ ጥቅምት 8/2014 እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Hawassa : የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ይጀመራል።

ሊጉ በሀዋሳ ዘጠኝ ሳምንታት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን ቲክቫህ ስፖርት (@tikvahethsport) ከሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል እና ቤቲካ ጋር በመተባበር ውድድሩን ለቤተሰቡ ለማድረስ ስምምበት ፈፅሟል።

@tikvahethsport
የእንግሊዙ ኩባንያ ከፊ ጎልድ በቱሉ ካፒ አካባቢ የተገኘውን የወርቅ ማዕድን ለማውጣት፣ ወደ ሙሉ የፕሮጀክት ልማት እንዲገባ የተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲራዘምለት ያቀረበውን ጥያቄ የማዕድን ሚኒስቴር ውድቅ ማድረጉን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
 
የእንግሊዝ ኩባንያ የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ልማትን በፀደቀው ዕቅድ መሠረት ማከናወን ባለመቻሉ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና የጊዜ ገደቦች እየተሰጠው ለበርካታ ዓመታት የቀጠለ ሲሆን፣ በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ነበር። 

ነገር ግን ኩባንያው የፕሮጀክት ልማቱን ለመጀመር የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በማግኘቱ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ተሻሽሎ እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 2021 መጨረሻ ቀን ድረስ ልማቱን እንዲጀምር አዲስ የጊዜ ገደብ ተቆርጦለት ነበር። 

ይሁን እንጂ ኩባንያው በመስከረም ወር 2014 ለማዕድን ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ቱሉ ካፒ አካባቢ የፀጥታ ችግር መኖሩን ጠቅሶ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የወርቅ ማዕድን ልማቱን መጀመር እንደማይችል አስታውቆ፣ የጊዜ ማራዘሚያ ጠይቆ ነበር።

የማዕድን ሚኒስቴር በበኩሉ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለተቋቋመው እህት ኩባንያ በጻፈው ደብዳቤ የተጠየቀውን የጊዜ ማራዘሚያ ከነምክንያቱ በመጥቀስ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-10-17

@tikvahethiopia
#UNSC : ደቡብ ሱዳን " ጎክማቻር " የሚባለው አካባቢ ከተመደበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ጥበቃ ኃይል ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ ስላለው ሁኔታ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ገልፃ ተደርጓል።

ገለፃውን ያደረጉት በድርጅቱ የፖለቲካና የሰላም ግንባታ ክፍል የአፍሪካ ጉዳይ ምክትል ዋና ፃሃፊው ናቸው።

እኤአ መስከረም 14 ቀን የአንድ ኢትዮጵያዊ 🇪🇹 ሰላም አስከባሪ ህይወት የጠፋበትን ጨምሮ በ " ጎክማቻር " በቅርብ ጊዜያት በሰላም አስከባሪዎች ላይ የተደቀኑት አደጋዎች በጥልቅ የሚያሰጓቸው ሆነው እንዳገኟቸው የፀጥታ ምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግስት የሰላም አስከባሪውን ኃይል የተልኮ ስልጣን ያለእንቅፋት እንዲያከናውን የማስቻል ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን የምክር ቤት አባላት ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሕገ መንግሥት ረቂቅን አስመልክቶ በቤንች ሸኮ ዞን ከሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተደረገ ነው። የክልሉ ህገ መንግስት በ11 ምዕራፍና በ124 አንቀጾች የተዋቀረ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል። በተመሳሳይ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ ህገ-መንግስት ረቂቅ ላይ በዳውሮ ዞን ውይይት እየተደረገ…
#Update

ዛሬ በካፋ ዞን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስት ላይ ያተኮረ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተደርጓል።

በዛሬው የውይይት መድረክ የካፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሠማ ፥ "በአዲሱ ክልል ሁሉም ህዝብ የፍትሐዊ በሆነ መልኩ የልማት ተጠቃሚ የሚሆንበት፣ እኩል የሚለሙበት ፣ የሚበለጽጉበት እንዲሁም ወንድማማችነት የሚጠናከርበት ይሆናል'' ብለዋል።

የተዘጋጀው ረቂቅ ህገ-መንግስት የክልሉን የሥራ ቋንቋ ፣ ክልላዊ መዝሙር፣ ሰደቅ አላማ እና የመሳሰሉትን ያካተተ ሲሆን ለውይይት ቀርቦ ከተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የረቂቅ ህገ መንግስት የውይይት መድረኩ በቀጣይ በየደረጀው ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል።

ትላንት ቅዳሜ በዳውሮ ዞን እንዲሁም በቤንች ሸኮ ዞን በአዲሱ ክልል ረቂቅ ህገመንግስት ዙሪያ ውይይት መደረጉ ይታወሳል።

Credit : ሀብታሙ ኃይሌ (ከቦንጋ)

@tikvahethiopia
#Jigjiga : የሶማሊላንድ ም/ ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው ጅግጅጋ ገብቷል።

በሶማሊላንድ ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ የተመራው ልዑክ ዛሬ ከሰዓት ጅግጅጋ መግባቱን የሱማሊ ክልል ማስ ሚዲያ ዘግቧል።

ለም/ፕሬዝዳንቱና ልዑካቸው በቶግወጃሌ ከተማ የሶማሊ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች አቀባበል እንዳደሩጉለቸው ተገልጿል።

የሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ እና ልዑካቸው በነገው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ የሚመሠረተው አዲሱ የሶማሊ ክልል የመንግሥት ምስረታ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 20 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 20 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,456 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 508 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 599 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቦረና ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ ፦ - 539,679 ዜጎች የውሃ እጥረት ገጥሟቸዋል ፤ ከነዚህ ውስጥ 177,553 ዜጎች ብቻ በቦቴ ውሃ አግኝተዋል። - በምግብ እጥረት 6,398 ህፃናት ፣ 9,078 እናቶች ፣ 2,226 አዛውንቶች ላይ የጤና ችግር ታይቷል። - 188,864 ሰዎች የምግብ እርዳታ አግኝተዋል ፤ 166,136 ዜጎች ተጨማሪ እርዳታ ይፈልጋሉ። - በድርቅ ምክንያት 7,540 ከብቶች ሞተዋል…
"...ችግሩ የቦረና ወንድም ህዝብ ህመም ነውና እኛም ታመናል" - አቶ ዳዊት ገበየሁ

የኮንሶ ዞን አስተዳደር በበልግ ዝናብ መጥፋት ምክንያት የእንስሳት መኖና ውሃ መጥፋት ለተጎዳው የቦረና ህዝብ ድጋፍ አደረገ።

ዞኑ ዛሬ 18 የጭነት መኪና የእንሰሳት መኖና 2 ቦቲ ውሃ በድርቅ ለተጎዱ እንሰሳት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እና አማካሪዎቻቸው እንዲሁም የዞን ካቢኔ፣ ከተማና ወረዳ መዋቅር አስተዳዳሪዎች ያቤሎ ድረስ ይዘው ሄደው አስረክበዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ድጋፉን አስመልክተው በሰጡት ቃል፥ " ችግሩ የቦረና ወንድም ህዝብ ህመም ነውና እኛም ታመናል፤ የጎረበ ወገን ችግር ነውና አስከፊነቱ አሳዝኖናል፤ የእንሰሳት ሞት የቤተሰብ ጉዳት ነውና አብረን ተጎድተናል" ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው፥ የኮንሶ ዞን ለወንድም ህዝቦቹ ችግር ለመድረስ የተደረገው ይህ ድጋፍ የመጀመሪያ እንደሆነ ተናግረዋል።

አክለው፤ "የተከሰተው ጉዳት ሠላምና እንቅልፍ የሚነሳ፣ ኢኮኖሚን የሚያቃውስ፣ አንገት የሚያስደፋና ለችግር የሚዳርግ አሳዛኝ ክስተት መሆኑን የኮንሶ ወንድም ህዝብ ልባዊ መልዕክቱን ይገልፃል" ብለዋል።

"ኦሮሞና ኮንሶ አንድ ህዝቦች ናቸው" ያሉት አቶ ዳዊት፥ "የቦረና ህዝብ ችግር የኮንሶ ህዝብ ችግር ነው፤ ስለሆነም አስደንጋጭ የእንሰሳትን ሞት ከሰማን ቀን ጀምሮ እኛም በአካል ራቅናችሁ እንጂ የህሊና ተጎጂዎች ነበርን" ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ዳዊት፥ " በዝናብ መጥፋት ምክንያት የተከሰተው የእንሰሳት ሞትና ድካም ችግር እጅግ አሳዛኝ ቢሆንም ከመከራ የምንማርበት፣ የጉዳቱ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦቻችን ስነ ልቦናቸውን የሚንገነባበት ወቅት እንዲሆን ብርታትን ከልብ እንመኛለን" ብለዋል።

መረጃው የኮንሶ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Mewlid

1496ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በዛሬው እለት በመላ ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል።

1496ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል በተለይ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Jigjiga : የሶማሊላንድ ም/ ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው ጅግጅጋ ገብቷል። በሶማሊላንድ ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ የተመራው ልዑክ ዛሬ ከሰዓት ጅግጅጋ መግባቱን የሱማሊ ክልል ማስ ሚዲያ ዘግቧል። ለም/ፕሬዝዳንቱና ልዑካቸው በቶግወጃሌ ከተማ የሶማሊ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች አቀባበል እንዳደሩጉለቸው ተገልጿል። የሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ…
#Somali : የሶማሌ ክልል መንግስት ምስረታ የምክር ቤት ጉባኤ በጅጅጋ ከተማ ዛሬ እየተካሔደ ነው።

ባለፈው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በክልሉ የተካሄደውን 6ተኛ አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ነው በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የሚመሰረተው።

272 መቀመጫዎች ያለውና ዛሬ የሚካሔደው የክልሉ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ ይመርጣል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የክልሉን ርዕሰ-መስተዳድር የሚመርጥ ሲሆን የተመረጡት ርዕሰ መስተዳድርም የክልሉን መንግስት አስፈጻሚ አካላት ሹመት በምክር ቤቱ አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉን አዲስ መንግስት የምስረታ ጉባኤ ለመታደም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የመጡ እንግዶች ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somali : የሶማሌ ክልል መንግስት ምስረታ የምክር ቤት ጉባኤ በጅጅጋ ከተማ ዛሬ እየተካሔደ ነው። ባለፈው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በክልሉ የተካሄደውን 6ተኛ አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ነው በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የሚመሰረተው። 272 መቀመጫዎች ያለውና ዛሬ የሚካሔደው የክልሉ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ…
#update

የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አያን አብዲን አፈ ጉባዔ አድርጎ ሰየመ

6ኛው ዘመን 1ኛ አመት የሶማሊ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አያን አብዲ ዋና አፈ ጉባዔ እንዲሆኑ ሰይሟል፡፡

ም/ቤቱ በመስራች ጉባኤው ኢብራሂም ሀሰንን ምክትል አፈ-ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

አዲሷ አፈጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡

Credit : SMMA

@tikvahethiopia