TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።

በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረ የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ነው።

በዓላቱ አማራ ክልል ባለብዙ ዘርፍ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት መሆኑን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባሕላዊ ትውፊቶች ያሉት፣ ሕዝቦች በመተሳሰብ በመፈቃቀር እና በአንድነት የሚኖሩበት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ሶለል በዓል የአዲስ አመት መምጣቱን ተከትሎ የሚከበር ብስራት ነው።

ልጃገረዶች ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን አልፈው ብሩህ ዘመን እየመጣ መሆኑን የሚያበስሩበት፣ እጮኛ የሚያጩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር የሚጨፍሩበት እና የሚጫወቱበት ባሕላዊ ጨዋታ ነው።

በተጨማሪ እናቶች እና ህጻናት ያለ ልዩነት ሚሳተፉበትም ነው።

በዓላቱ በህዝባዊ አንድነት የሚያከብሩ፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና አብሮ የመኖር እሴትን ለትውልድ ማስተላለፊያ ጠንካራ ገመድ ናቸው።

ለውጭ ሀገራት ብርቅ በመሆኑም የገቢ ምንጭም ነው።

(ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው)
ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

በአሸንዳ በዓል ዙሪያ የተደረገ ጥናት...

#መብራህተን_ገብረማሪያም

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከበረው የአሸንዳ በዓል ፍቅር፣ ይቅር ባይነት እና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ነው።

በዓሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበረል፤ ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው።

የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ጭፈራዎችና ትእይንቶችም እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በአሸንዳ በዓል ላይ የሚነገሩ ስነ ቃሎች ይዘት በአብዛኛው ህብረትን የሚሰብኩ፣ መድልዎን የሚጠየፉና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ ናቸው።

ልጃገረዶች በዓሉን በህብረሰቡ ውስጥ ያለውን እርስ በርስ የመተባበር፣ የመረዳዳትና የጀግንነት መልካም እሴቶችን አጉልተው ለማሳየት ይጠቀሙበታል።

በዓሉ ሴቶች ያላቸውን የፈጠራ፣ የመደራደር፣ የውሳኔ ሰጭነት ብቃት በተግባር የሚያሳዩበትና መልካም ስሜታቸውን የሚገልጹበትም ነው።

በተጨማሪም በህዝቡ ውስጥ ያሉትን ጉድለቶች በስነ ቃልና በዘፈን መልክ እንዲስተካከሉ የሚነቅፉበት፣ ማህበረሰቡ መድልዎን እንዲጠየፍ፣ የሴቶችን መብት የሚጋፋ የአስተዳደር መዋቅር አሊያም ወንድ ካለ እንዲስተካከል መልዕክት የሚያስተላልፉበት ጭምር ነው።

‘አሸንዳ በዓል ለትግራይ ህዝብ ባህል የመሰረት ድንጋይ ተደርጎ ይወሰዳል፤ በዓሉ ማንነትን አጉልተው የሚያሳዩ እሴቶች አሉት።

አሸንዳ ለሴቶች መብት አጥብቆ የሚታገል፣ መከባበርንና መረዳዳትን አብዝቶ የሚሰብክ ፣ ሰዎች ባላቸው የሃብት መጠን ሳይሆን በሰውነታቸው ብቻ ክብር እደሚገባቸው በስነ ቃልና በዘፈን መልክ ያስየምታል።

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ሃክ ተደርጓል ?

ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ ተደርገ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ትክክል እንዳልሆነ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አሳወቁ።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይህን ያሳወቁት ኢትዮጵያ ቼክ ለተሰኘው የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።

ባለፉት ቀናት ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ እንደተደረገ የሚጠቁሙ የተለያዩ መልዕክቶች እና መረጀዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ነው፤ በርካቶች ደግሞ አንድ ኮድን በመጠቀም በነፃ የኢንተርኔት ፓኬጅ ማግኘት እንደቻሉ ሲፅፉ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ፥ "ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ አልተደረገም። ስራችን ሳይቋረጥ አዳዲስ አገልግሎቶች ላይ ማስተካከያ (configuration) እያረግን ነው። በዚህ ምክንያት ጥቂት ደንበኞቻችን አንዳንድ አገልግሎቶችን [በነፃ] ሊወስዱ/ሊያገኙ ችለዋል። ሁኔታውን እኛም አውቀነው እየሰራንበት ነው፣ በቁጥጥራችን ስር ነው" ብለዋል።

የመረጃ ባለቤት ፡ ኢትዮጵያ ቼክ (www.ethiopiacheck.org)

@tikvahethiopia
#COVID19

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 785 የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ8 ሰዎች ህይወት ደግሞ ጠፍቷል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 6,108 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 785 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 8 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ከአፋር እና አማራ ክልል እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቧን ቀጥላለች።

የUSAID ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ዛሬ ምሽት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ግጭቱን እንዲያረግብና ከአፋር እና አማራ ክልሎች ወጥቶ ለድርድር እንዲቀመጥ ጥሪ ማቅረቧን ትቀጥላለች ብለዋል።

ሳማንታ ፓወር ፥ የህወሓት /TPLF/ ጥቃት ይህንን ግጭት እና የኢትዮጵያን ህዝብ ስቃይ ብቻ ያራዝመዋል ሲሉ ፅፈዋል።

በተጨማሪ USAID በዚህ ሳምንት በአፋር እና አማራ ክልል በግጭት ለተጎዱ ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች ምግብ ማድረስ መጀመሩን አሳውቀዋል።

በአፋር እና አማራ ክልል ህወሓት /TPLF/ በፈፀመው ጥቃት በመቶ ሺዎሽ የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤታቸው መፈናቀላቸውን ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

@tikvahethiopia
'A Grammar of Mursi'

በሙርሲዎች ባህል፣ አኗኗር አና ቋንቋ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ተመርቋል።

መፅሀፉ የሙርሲ ቋንቋ ሰዋስው/'A grammar of Mursi' የተሰኘ ሲሆን በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና መምህር በሆኑት ፍሬው ግርማ (ዶ/ር) የተፃፈ ነው።

684 ገፆች እና 14 ምዕራፎች ያሉትን መፅሀፍ ለማዘጋጀት አምስት ዓመት እና 13 ሚሊዮን ብር መውሰዱን ፀሀፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ስለሙርሲዎች ፦
-ታሪክ፣
- አኗኗር፣
- ባህላዊ አስተዳደር እና ፍልስፍና የሚገልጽ ሲሆን ቀሪዎቹ ምዕራፎች በሙርሲዎች ቋንቋ ሰዋስው ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

መፅሀፉ የሙርሲዎችን ስርዐተ ጽህፈት ለመቅረፅ ይጠቅማል ያሉት ተመራማሪው፤ መደበኛ ትምህርት በሙርሲዎች ለማስጀመር ያገለግላል ብለዋል።

በተለይ ለፔዳጉጂስቶች፣ ለታሪክ ፀሀፊዎች፣ ለጎብኚዎች፣ ለመምህራን እና ለተማሪዎች በማጠቀሻነት እንደሚያገለግል ገልፀዋል።

ፀሀፊው ካገኟቸው ስድስት ኮፒዎች፤ ሦሥቱን ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና አንድ ኮፒ ለደቡብ ኦሞ ምርምር ማዕከል ማበርከታቸውን ገልፀውልናል።

በእንግሊዝኛ የተጻፈውን መፅሀፍ፤ ብሪል የተባለ የኔዘርላንድስ አሳታሚ ድርጅት በ139 ዶላር በአውሮፓ ለገበያ አቅርቦታል።

@tikvahuniversity
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በህወሓት ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ማስለቀቁን አስታወቀ።

የመከላከያ ሰራዊት ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ ጋር በመሆን በወሰደው እርምጃ፦ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይ፣ ጎብጎብ፣ ሳሊና ንፋስ መውጫ ነፃ ማውጣቱን ገልጿል።

የንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ህወሓት በንፋስ መውጫ ከተማ ንፁሃንን መግደሉንና በርካታ ውድመት ማድረሱን የተናገሩ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደከተማቸው ሲገባ አቀባበል አድርገዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፤ ከሰሞኑን ህወሓት ህዝቡን በጣም እንደጎዳው፤ የቀረ ነገር ሳይኖር ዘርፊያ እንደፈፀመ ገልፀው፥ "ህዝባችን እንዲህ ያለ ወራዳ ተግባር ማየቱ የሚያሳዝን ነው፤ ነገር ግን አሁን ላይ ቡድኑ ዋጋውን እያገኘ ነው" ብለዋል።

ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ፥ "ህወሓት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች በሙሉ የማስለቀቅ እና የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ከመኪና ወርዶ እየተበታተነ ነው እሱን የመልቀም ስራ እየተሰራ ነው፤ የሚሸሽበትም መንገድ ተዘግቷል፤ ትግራይ ውስጥ ያየውን ጉድ እዚህም ያየዋል፤ እዚህ ገብቶ መውጣት የሚባል ነገር እንደሌለ ያየዋል" ብለዋል።

አዛዡ ፥ ህወሃት ስርዓት መቀየር ነው ፍላጎቴ ይላል እንጂ ተግባሩ ሀገር ማፍረስ እና ሀገር ማውደም ነው ፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው የማፍረስ ምልክቱም ህዝቡን ምን እያረገው እንዳለ ማየት በቂ ነው ፤ የከተማውን ህዝብ ጠይቁ ምን አድርጓቸው እንደሄደ፤ እነሱ የስርዓት አራማጅ አይደሉም ፤ ድሆች ናቸው ፤ ከድሆቹ አፍ ነጥቆ ሽሮ ሳይቀር እየጫነ እየወሰደ ያለው" ሲሉ አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/ENDF-08-23

@tikvahethiopia
ሙሐመድ አወል ሙሐመድ ሳላህ አረፉ።

በበርካታ የጥበብ ስራዎች የሚታወቁት ድምፀ መረዋው ሙሐመድ አወል ሳላህ በልብ ህመም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ትውልዳቸው በደሴ ከተማ አራዳ አካባቢ ሲሆን ከእናታቸው ከወ/ሮ ሰዕዲያ ሰዒድ አህመድ እና ከአባታቸው ሐጅ ሙሐመድ ሳላህ አህመድ በ1958 ነበር የተወለዱት።

ትምህርታቸውን በወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ውትድርናው አለም በመቀላቀል ሃገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በወታደር ቤትም በሙዚቀኝነት ሲያገለግሉ ቆይተው ወደሳውዲ ዓረቢያ በማቅናት ለ7 ዓመታት ቆይታ አድርገው ወደ ሃገራቸው በመመለስ የጥበብ ስራቸውን ቀጥለው ነበር።

በኋላም የዓለማዊውን የሙዚቃ አለም በመተው ወደ መንፈሳዊ ህይወት በማዘንበል ህይወታቸው እስካለፈችበት እለት ድረስ ሙሉ በሙሉ የበተለያዩ የኢስላማዊ የኪነጥበብ ስራዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሙሐመድ አወል በሙዚቃ ዓለም ከሰሯቸው ስራዎች ባሻገር በእስልምናው ዓለም በርካታ የጥበብ ስራዎችን አበርክተዋል፦
-የለኝ በጎ ሥራ
-ሙሐመድ ተብዬ
-እመስገጃሽ ላይ ታገሺ
-ውዴታ እስከጀነትና ሌሎችም የተካተቱበት ሶስት አልበሞችንና በርካታ ነጠላ ነሺዳዎችን አበርክተዋል።

ሙሐመድ አወል ሳላህ ከሚታወቁበት የጥበብ ሥራ በላቀ መልኩ የበጎ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው የቅርብ ወዳጆቻቸው ይመሰክራሉ።

ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት የሆኑት ሙንሺድ ሙሐመድ አወል ሳላህ ለረጅም ግዜ የዘለቀ ልብ ታማሚ የነበሩ ሲሆን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ትላንት ሌሊት ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ህይወታቸው እንዳለፈች ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል።

የቀብር ስርዓታቸው ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር ዛሬ ነሐሴ 17 ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይፈፀማል።

የመረጃ ባለቤት: ሚንበር ቲቪ

@tikvahethiopia
#MoretEnaJeruWoreda

ትላንት ምሽት በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ አንድ ሰው ሲሞት 7 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።

አደጋው የደረሰው በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ ጅሁር ኮሲያንባ ቀበሌ መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ቦንቡ የፈነዳው በቀበሌው "ሰርጠሶስ" በሚባል መጠጥ ቤት ውስጥ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሰባት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው የደረሰው።

የጅሁር ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ዘነበ ሰሙ ፥ ፍንዳታው በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ መከሰቱን ለኤፍ ቢ ሲ አረጋግጠዋል ፥ በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 4 ሰዎች ደብረ ብርሀን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

"የቦንብ አደጋውን ያደረሰው ግለሰብ ማን እንደሆነ በማጣራት ላይ ነን" ሲሉም አክለዋል።

@tikvahethiopia