በእነ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ 74 ሰዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።
በክስ መዝገቡ ላይ ፦
- ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
- ጄነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሳኤን፣
- ሜ/ ጄነራል ዮሀንስ ወ/ጊዮርጊስ
- ብ/ጄነራል ምግባይ ሀይለ
- ሜ/ጄነራል ሀለፎም አለሙ
- ሜ/ጄነራል ሀለፎም እጅጉ
- ሜ/ጄነራል አታኸልቲ በርሄ
- ሜ/ጄነራል ማሾ በየነ
- አቶ ሀዱሽ አበበ እና ቢኒያም ተወልደ ጨምሮ 74 ሰዎች ተካተውበታል።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች ፦
• የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ
• በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችል የትግራይ ማእከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ በማደራጀትና በመምራት
• በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣በፌዴራል ፖሊስ እና በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ እንዲሁም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ ላይ ጥቃት በማድረሳቸዉ ነዉ፡፡
ዐቃቤ ህግ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸዉን ከ500 በላይ የሰዉ ምስክሮችን፣ ከ5ሺህ ገፅ በላይ የሆነ የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የቴክኒክና የቪዲዮ ማሰረጃዎችን አያይዞ ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡
ክሱ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 272829 የሽብር መዝገቡ ተከፍቶ ጉዳዩን እየተመለከተዉ ይገኛል፡፡
#የፌዴራል_ጠቅላይ_አቃቤ
@tikvahethiopia

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ታዘዘ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ደጀኔና ጣፋና አቶ ሀምዛ አዳነ ( ቦረና ) ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ አዘዘ፡፡
አራቱ ተከሳሾች በሶስት ቀጠሮ በራሳቸው ፍቃድ ፍርድ ቤት አንቀርብም በማለታቸውን ተከትሎ ዓቃቢህግ በባለፈው ቀጠሮ በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱም ዛሬ ማረሚያ ቤቱ እንዲያቀርባቸው ያዘዘ ቢሆንም ዛሬም አንቀርብም በማለት መቅረታቸው ተሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም አራቱ ተከሳሾች በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ በማዘዝ ለሀምሌ 30 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡
ይህ መረጃ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን የምትከታተለው ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ነው።

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከጸጥታ አካላት እና ከአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ ትኩረቱ የነበረው በአ/አ ከተፈጠረው ክስተትና ከንግድ ቤት መታሸግ ጋር በተያያዘ ነበር።
የትግራይ ተወላጅ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ቤቶቹ መታሸግ ከማንነት ጋር የተያያዘ አንድምታ እየፈጠረባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ መቐለ ከተማን ሰኔ 21 ቀን 2013 ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኙ ፣ ሆቴሎች ፣ መጠጥ ቤቶች እና ምሽት ቤቶች ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በመደገፍ የተጠረጠሩ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።
እርምጃ የተወሰደባቸው ቤቶች በከተማዋ የዘር ፍጅት እንዲከሰት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በሆቴል ቤታቸው በማስቀመጥ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ሲሆን ከነበረው ክስተት ጋር በተያያዘ መንግስት ከ8 በላይ ባለ ኮከብ ሆቴሎች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ክለቦች እንደዚሁም ምግብ ቤቶችን ጨምሮ በድርጊቱ ተሳትፎ የነበራቸው ከረንቦላ ቤቶች ታሽገዋል።
ከትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተካሄደው ውይይት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የሴክተር ተቋማት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ሰለሞን ኃይሌ ፥ ሰላማዊ የሆነው የንግዱ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ይጠበቃል ፤ ከንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቀው እራሱን ከህወሓት ቡድን ማራቅ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
"የትግራይ ተወላጅ የሆነ በሙሉ በሀገር የተከሰተውን ህመም ሊጋራ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/Addis-Ababa-07-28
Credit : #ETHIO_FM

"...ወደ አሜሪካ ለመሄድ ሙከራ አላደረኩም፤ አሜሪካ መንግስትም ጣልቃ አልገባም" - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና በሚቀጥለው ሳምንት ወደአሜሪካ ሀገር እንደሚሄዱ ገለፁ።
ፕሮፌሰሩ ወደ አሜሪካ የሚጓዙት በዚያ ከሚገኙ የፓርቲያቸው አስተባባሪዎች ጋር ለመገናኘትና ገንዘብ ለማሰባሰብ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች ላይ በአሁን ሰዓት ፕሮፌሰር መረራ አሜሪካ (ዋሽንግተን ዲሲ) መሆናቸውን የሚገልፁ ፣ በመንግስት በረራ እንዳያደርጉ ተከልክለው እንደነበርና በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ጉዞ ስለማድረጋቸው መረጃዎች እየተሰራጩ ሲሆን መረጃው ሀሰተኛ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ሪፖርት አድርጓል።
ፕሮፌሰር መረራ በአሁኑ ሰዐት አዲስ አበባ እንደሚገኙ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ አሜሪካ ለመሄድ ሙከራ እንዳላደረጉ የአሜሪካ መንግስትም ጣልቃ እንዳልገባ ተናግረዋል።
ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አሜሪካ ተጉዘው በዚያ ከሚገኙ የኦፌኮ አስተባባሪዎች ጋር እንደሚገናኙ እና ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ተናግረዋል።

የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል አልሸባብ ላይ እርምጃ ወሰደ።
የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል በአሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድኑን አባላት መግደሉን አሳውቀ።
አሸባሪው ቡድን በትላንትናው ዕለት በሸቤሌ ዞን ሙስተሂል ወረዳ በድንበር አከባቢ ከነመሣሪያዎቻቸው ገብተው፣ ጥቃት ለመፈፀም በተዘጋጁበት ወቅት የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል በወሰደው እርምጃ ከቡድኑ አባላት ውስጥ አንዱ ሲገደል በሌላኛው ላይም ጉዳት ደርሶበት በሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል የህክምና ባለሙያዎች እርዳታ እየተደረገለት መሆኑንና ሌሎቹ የአሸባሪው ቡድን አባላት ከድንበር መሸሻቸውን የሶማሊ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሁሴን ሀሺ ገልፀዋል።
ዶ/ር ሁሴን የሀገሪቱንና ክልሉን ሰላም በተለይ በድንበር አካባቢ ሰላም ለማጠናከር ሌተ ቀን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የሱማሊ ክልል ቴሌቪዥን

#BritshCouncil
ብሪቲሽ ካውንስል ከከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ሻምፒዎኖች እና ከዩዝ ፕሪንት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ለመቀነስና ለመከላከል የሚሰሯቸውን አስተማሪ ስራዎች ለማቅረብና ለመወያየት የሚያስችል መድረክ ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
ውይይቱ ነገ ሃሙስ ሃምሌ 22 ከቀኑ 9:00 እስከ10:00 ሰዓት በዙም እና በፌስቡክ ላይ ይተላለፋል ተብሏል።
የውይይቱ ተካፈይ ለመሆንም ይህን ሊንክ በመጠቀም ፦ bit.ly/3BvXVmk መመዝገብ እንደሚቻል ብሪቲሽ ካውንስል ገልጾልናል።
የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ለሚከናወኑ ስራዎች ተጨማሪ ድጋፍ የሚያደርጉ ልዩ ፈጠራዎችን የሰሩ ታዋቂ ወጣቶች እንዲሁም ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት በውይይቱ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ፕሮግራም ተይዟል።

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,039 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 233 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 98 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

200 ገደማ የሚሆኑ የትግራይ ክልል ተወላጅ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነገ ወደ ሰመራ ዩኒቨርስቲ እንደሚሸኙ ተገለፀ።
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጠው ቃል፥ ተማሪዎቹን ለመሸኘት የወሰነው፤ ለመጀመሪያ ዓመትና ነባር የጤና ሳይንስ ተማሪዎቹ ከትላንት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እረፍት መስጠቱን በይፋ ማሳወቁን ተከትሎ ነው።
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ፥ በአካባቢው ባለው ጦርነት የደህንነት ስጋት በመኖሩ ተማሪዎቹ ወደ የቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ከውሳኔ ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የቀሩትን የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን፤ በሰመራ በኩል ወደ ትግራይ ለመሸኘት መወሰኑን አስታውቀዋል።
ዶ/ር አበበ፥ ዩኒቨርስቲው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር መወያየቱን ገልፀው፥ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ሰመራ ዩኒቨርስቲ ካደረሰ በኋላ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተወካዮች ተማሪዎቹን ለመረከብ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል።
በስምምነቱ መሰረት የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን ነገ ወደ ሰመራ ዩኒቨርስቲ ለማጓጓዝ 4 የራሱን አውቶብሶች መመደቡን ገልፀዋል።
በአካባቢ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎቹ በወሎ አድርገው ሰመራ እስከሚገቡ ድረስ በመከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እጀባ እንደሚደረግላቸው አመልክተዋል።
በወልድያ አካባቢ ባለ የፀጥታ ስጋት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ግቢውን ለቅቀው መውጣት የጀመሩት ካለፈው ቅዳሜ ነው።
በርካታ ተማሪዎች በራሳቸው ውሳኔ ዩኒቨርስቲውን ለቅቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄዳቸው፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳስተጓጎለው የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን መሐመድ ተናግረዋል።
ምንጭ፡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

#Shebelle
ሸበሌ የምትሰኝ የኢትዮጵያ መርከብ ከ11 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ስኳርና ሩዝ ይዛ በርበራ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።
መርከቧ ከህንድ ሀገር የጫነችውን ስኳርና ሩዝ ይዛ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ድርሻ ባላት የበርበራ ወደበ እያራገፈች ነው።
በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ታሪክ የኢትዮጵያ መርከቦች ወደ በርበራ ወደብ ጉዞ ሲያደርጉ ከ20 ዓመታት በኋላ ሸበሌ መርከብ ሁለተኛ ናት።
ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ ከ20 ዓመታት በኋላ ጊቤ መርከብ በበርበራ ወደብ የመጀመሪያ ጉዞ አድርጋ ነበር፤ በዚህ ጉዞም 11 ሺ 200 ሜትሪክ ቶን የፍጆታ ዕቃ ለሶማሌላንድ ገበያ አጓጉዛ ነበር።
NB : በበርበራ ወደብ፤ ዲ ፒ ወርልድ 51 በመቶ፣ ሶማሌላንድ 30 በመቶ እና ኢትዮጵያ ደግሞ 19 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል ።
#አልአይን_ኒውስ

#MekelleUniversity
መቐለ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ሀገር ሰራተኞቹን እየሸኘ ነው።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከላፈው እሁድ ዕለት አንስቶ ከትግራይ ክልል ውጭ የመጡ ከ4,800 በላይ ተማሪዎችን በአፋር አድርጎ ወደቤተሰቦቻቸው እየሸኘ ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው ከተማሪዎች በተጨማሪም የውጭ ሀገር ዜጋ ሰራተኞቹንም እየሸኛቸው ይገኛል።
ዩኒቨርስቲው ከሃምሌ 20 ቀን 2013 በኃላ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎቹን የሚቀልብበት እና የሚያስተዳድርበት በጀት እንደሌለው አሳውቆ ነበር።
በሌላ በኩል የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የሆኑ ከ7 ሺህ 500 በላይ ዜጎች እስካሁ ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የዩኒቨርሲቲው የባንክ አካውንት በመታገዱ ያለፈው በጀት ዓመት የሰኔ ወር እና የአዲሱ በጀት ዓመት የሃምሌ ወር በጀት ባለመለቀቁ ፣ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ባንክ ባለመኖሩም ሰራተኞቹ ከሰኔ ወር ጀምሮ ደሞዝ አላገኙም።
የዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት #ለጀርመን_ድምፅ በሰጠው ቃል መሰረት ከ7,500 በላይ ሰራተኞቹ መካከል ከ5,500 በላይ ሰራተኞች የሰኔ ወር ደሞዝ ያላገኙ ናቸው።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ደሞዝ ስላልተከፈላቸው እራሳቸውን ጨምሮ በነሱ ስር ያለው ቤተሰብም ጭምር ችግር ላይ መሆኑን በኮርፖሬት ኮሚኒኬሽኑ በኩል ገልጿል።

አቶ ለማ መገርሳ ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ?
ከትላንት በስቲያ ጀምሮ የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ በአሜሪካ ድምፅ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ላይ ቀርበው ቃለምልልስ ሰጡ እየተባለ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን የዝግጅት ክፍሉ አሳወቀ።
አቶ ለማ ቀደም ሲል በማህበራዊ ሚዲያዎች እርሳቸው እንዳሉበት ተጠቅሶ የተሰራጨን ሌላ ወሬ መነሻ አድርገው ስማቸው ያለ አግባብ እየተነሳ መሆኑን ጠቅሰው ማስተባበያ ሰጡ ተብሎ ነበር የተወራው።
አቶ ለማ መገርሳ ለቪኦኤ ቃለ ምልልስ እንደሰጡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን የቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ክፍል ገልጿል።
ለቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ምንም ዓይነት ቃለ ምልልስ አልሰጡም ብሏል።
የቪኦኤ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዋና አዘጋጅ የሆነው ነሞ ዳንዲ ፥ “በቪኦኤ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት በኩል እንኳንስ አቶ ለማን አግኝቶ ቃለ ምልልስ ማድረግ ይቅርና ሐሳቡም አልቀረበም የተደረገም ሙከራ የለም’ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
VIDEO : ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መከላከያን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ በመግለፅ ላይ ይገኛል።
ከላይ የተያያዘው ቪድዮ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ጎባ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶችን የሚያሳይ ነው። ትክክለኛው ቁጥራቸውን በውል ማወቅ ባይቻልም ወጣቶችን የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ ይታያል።
በተመሳሳይም ከሌሎች በርካታ አካባቢዎች ወጣቶች መከላከያን እና የክልል ልዩ ኃይሎችን እየተቀላቀሉ መሆኑ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ ፤ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ደግሞ ወጣቶችን የማሰልጠን ስራ እየተሰራ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
ቪዲዮ : አለማየሁ ባዩ (የቲክቫህ ቤተሰብ)