#ወልዲያ
የወልዲያ ከተማ ሰላም መሆኗን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
በፀጥታ ስጋት ምክንያት ከተማይቱን ለቀው ወደአጎራባች ከተሞች የሄዱ ዜጎች መኖራቸው የታወቀ ሲሆን የከተማ አሰተዳደሩ ነዋሪዎቹን ለመመለስ እንደሚሰራ ገልጿል።
በአሁን ሰዓት በከተማዋ ምንም የተለየ የፀጥታ ችግር እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን የከተማው የፀጥታ ኃይል እና ወጣት በቀንና በማታ ጥብቃ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅት ተችሏል።
በተለይም በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የመግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ፍተሻና ጥበቃ እየተደረገ ነው።
በፕሮፖጋንዳ እና በሀሰተኛ መረጃ ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ሰዎች ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሄዱበት ከተማ ጋር ንግግር እየተደረገ ይገኛል።
ሁሉም የከተማው ነዋሪው አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ እና ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ እራሱን እንያቅብ ጥሪ ቀርቧል።
በአሁን ሰዓት የሀገር መከላከያ፣ የአማራ እና የሌሎች ክልል ልዩ ኃይሎች በጋራ በጉባላፍቶ ወረዳ እና በራያና ቆቦ ወረዳ አካባቢ ግዳጅ ላይ ተሰማርተው ስምሪት ወስደው ትግል ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደከተማው እየቀረበ ያለ የተለየ ሁኔታ እንደሌለ እና ሰላማዊ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መቀጠሉን የወልዲያ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
በትግራይ ክልል ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ግፍና እንግልት በመቃወም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች ሠላማዊ ሠልፍ ማካሄቸው ተሰማ።
ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት መስሪያ ቤት ተገኝተው ነው ድምፃቸውን ያሰሙት።
'በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚደረግ ጥቃት ይቁም፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምፃችንን ይስማ' እና ሌሎችንም መፈክሮች በመያዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል ተብሏል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከሚደርስባቸው ግፍና በደል እንዲታደጋቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ስደተኞቹ ከዚህ ቀደምም በተለያየ ጊዜያት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲሁም ለተመድ የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) በደብዳቤና በአካል በመገኘት መልዕክት ብናስተላለፍም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።
በትግራይ ክልል በሚገኙ ስደተኞች ላይ ግፍና እንግልቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣ ስደተኞች እየተገደሉና በየጫካው በሽሽት ላይ ያሉትም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል። #ENA

#Update
በወልቃይት ግንባር ፣ በዋግ ግንባር፣ በራያ ግንባር ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በምስራቁ ቀጠና ላይ ከባድ ውጊያ ስለመኖሩ ተሰምቷል።
የአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ውጊያ ባለበት ግንባር ሁሉ ህወሓት ሽንፈትን እየተከናነበ እንደሚገኝ እየገለፀ ይገኛል። ነገር ግን ከውጊያ ስትራቴጂ አንፃር ቦታዎችን መያዝ እና መልቀቅ ሊኖር እንደሚችል በማንሳት እስካሁን ህወሓት አሸንፎ የያዘው ቦታ እንደሌለ ገልጿል።
በቆቦ እና ዙሪያዋ ውጊያ መኖሩን ያሳወቀው የአማራ ክልል መንግስት ህወሓት ላይ ድል እየተጎናፀፍን ነው ብሏል። የህወሓት ኃይል ይዧቸዋለሁ ባላቸው ቦታዎች ውጊያ መቀጠሉን የህወሓትም የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች መኖራቸውን አሳውቋል።
ውጊያ እየተደረገ ያለው እጅግ ከከፍተኛ የሰው ቁጥር ነው ፤ በብዛት ሆነው ነው እየመጡ ያሉት ብሏል የክልሉ መንግስት።
እየተደረገ ባለው ጦርነት ከፍተኛ የሰው ቁጥር እያለቀ ነው የሚለው የአማራ ክልል ህወሓት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እድሜያቸው ያልደረሰ ልጆችን በግዳጅ እያዘመተ ይገኛል ብሏል።
የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን መላክ የለባቸውም የተላኩትም የት እንደደረሱ መጠየቅ አለባቸው ሲል ገልጿል። የአማራ ክልል ህዝብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝቡ ለህልውና ዘመቻው እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን አንስቷል።
በሌላ በኩል ከፌዴራልና ክልል የፀጥታ ኃይሎች ጋር ጦርነት ላይ ነኝ የሚለው የህወሓት ኃይል በተለያዩ ግንባሮች ወደፊት እየተጠጋ መሆኑን እየገለፀ ሲሆን የተለያዩ ቦታዎችንም እየተቆጣጠርኩ ነው ብሏል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እድሜያቸው ያልደረሱ ልጆች በጦርነቱ ውስጥ እየማገደ ነው ለህልውናችን ስልን ጦርነቱን እንቀጥላል ብሏል።

"ግጭት ይብቃ፤ ሰላም ይንገስ" - የጭልጋ አባቶች
በአይከል ከተማና አካባቢዋ በአኩን ሰዓት አንፃራዊ ሰላም እንዳለ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ ሁሉም አካል ስለ ሰላም የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ በትላትናው ዕለት የጭልጋና አካባቢዋ የሃይማኖት አባቶች በከተማዋ ጎዳናዎች በመዘዋወር ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የምህላ ፀሎትም በከተማዋ ተጀምሯል።
ከዚህ በፊት ተቋርጦ የቆየው የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ለማህበረሰቡ ክፍት ሁነው አገልግሎት እንዲሰጡም የሃይማኖት አባቶቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በአማራ እና ቅማንት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ልዩነት የሚሰብኩና ግጭትን ለማባባስ የሚሰሩ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ መልዕክት ተላልፏል። ስለጭልጋና አካባቢዋ ሰላም ይመለከተኛል የሚል አካል ሁሉ ስለ አካባቢው ሰላም አብክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ከመተማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በተገኘው መረጃ የታወጀው ምህላ ፀሎት ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል ተብሏል።

ማርቲን ግሪፍትስ የኢትዮጵያ ጉብኝት ፦
የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።
ግሪፍትስ በኢትዮጵያ የስድስት ቀናት ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን የመጀመሪያው ቀን ጉብኝታቸው ዛሬ ተጀምሯል።
በጉብኝቱ ወቅት ግሪፍትስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን እና ከሰብአዊና ለጋሽ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቅርቡ የተሾሙት አስተባባሪው፥ በስራቸው የመጀመሪያውን ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በማድረጋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ማርቲን ግሪፍትስ በቆይታቸው በትግራይ እና አማራ ክልሎች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅሀፈት ቤት አሳውቋል።

#Ethiopia #Sudan
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችንና ወታደራዊ ሰፈሮችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታወቀ።
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችንና ወታደራዊ ሰፈሮችን በድንበር አካባቢ የጦር ሰፈር ለመገንባት እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን እና ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ ስለማይጠቅማት ከድርጊቷ መቆጠብ አለባት ሲሉ አምባሳደር ዲና አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ የድንበሩን ጉዳይ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እያስረዳች መሆኑን የገለፁት አምባሳደር ዲና፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምክትል ፀሃፊነት የፖለቲካና የሠላም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስለድንበር ጉዳዩ ገለፃ እንደተደረገላቸው አምባሳደር ዲና ኣሳውቀዋል።
ሃላፊዋ ድርጅቱ የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እንደሚከታተለው መግለፃቸውን አስታውሰዋል።
መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።

የፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁሙ መቀጠሉን ቢገልፅም ህወሓት ዳግም "ቀልድ" ሲል አጣጥሎታል።
የፌዴራል መንግስት አሁንም ቢሆን ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁሙን አክብሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስገንዝቧል።
የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም የህወሓት ኃይል ወደ አፋር እና አማራ ክልል በመግባት ትንኮሳ እየፈፀመ መሆኑን ፣ ትግራይ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊዎችን እንደሚገድል ፣ እርዳታ እንዳይደርስ እያደረገ መሆኑን ፣ ህፃናትን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁንም የመንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም እንደቀጠለ መሆኑን ያነሱት ቢለኔ ፥ ይህ ማለት ግን ትንኮሳ ሲፈፀምበት ምላሽ አይሰጥም ማለት እንዳልሆነ ተናግረዋል።
የፀጥታ ኃይሎች ትንኮሳና ጥቃት በመፈፀም ሳይሆን ለሚደርስባቸው ትንኮሳ ምላሽ በመስጠትና በመከላከል፣ የሲቪሎችን ደህንነት በመጠበቅ ተሰማርተው ይገኛሉ ብለዋል።
መከላከያውና የፀጥታው አካላት የራሳቸው እይታ አላቸው ሲቪሎች ሊረዱት የማይችሉት ወታደራዊ ግምገማዎች እና እርምጃዎች አሉ ይህም በነሱ በኩል ቢገለፅ ጥሩ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የህወሓቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተኩስ አቁሙን እና የጥሞና ጊዜውን ቀልድ ነው ሲሉ ድጋሚ ያጣጣሉት ሲሆን እንደማይቀበሉትም ተናግረዋል።
"ትግራይን አንቆ ይዞ የጥሞና የሚባል ጊዜ የለም ፤ መንበርከክ የሚባል ቃል በትግራይ መዝገበ ቃላት ውስጥ የለም" ሲሉም ተናግረዋል።
በጦርነቱ ድል እንደነሱ ሲናገሩ የተደመጡት አቶ ጌታቸው "እየተከተልን እርምጃ መውሰድ ነበረብን እሱን አድርገናል፤ እያንዳንዱን ኢንች የትግራይ መሬት ነፃ እናወጣለን ኤርትራ የያዘችው መሬትም አለ ይህንንም ነፃ እናወጣዋለን በዚህ ጥርጣሬ የለንም" ብለዋል።

ቴዲ አፍሮ የክብር ዶክትሬት ሊሰጠው ነው።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ አፀደቀ።
ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
ቴዲ አፍሮ ነገ ወደ ጎንደር በመሄድ ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን የሚቀበል ይሆናል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 24 በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5,710 ተማሪዎችን ያስመርቃል።

#ItsMyDam🇪🇹
በ Mygerd.com በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
እስካሁን 898 ሰዎች ባደረጉት ስጋፍ 114,435 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል፡፡ 47 ሰዎች ደግሞ ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡

#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020
ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።
በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦
- ሀብታም አለሙ
- ነፃነት ደስታ
- ወርቅውሃ ጌታቸው
በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦
- ጌትነት ዋለ
- ለሜቻ ግርማ
- ታደሰ ታከለ
ድል ለሀገራችን🇪🇹ኢትዮጵያ !
@tikvahethsport

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 6,803 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 476 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ አምስት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 326 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ፦ • የሀገር መከላከያ መቐለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞችን ለቆ ከወጣ ሳምንት ሊሆነው ነው። እስካሁን በክልሉ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት ፍፁም አዳጋች ሆኗል። ዓለም አቀፍ ለጋሽ ተቋማት አሁንም በትግራይ ክልል ችግር ላይ ለወደቁ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ፈታኝ ሁኔታዎች ስለመኖራቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ። እንደተለያዩ ዓለም አቀፍ…
#Tigray
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ የተናጠል የተኩስ አቁም አቅድርጎ ሰራዊቱን ወደ ኃላ መሳቡን ማሳወቁ አይዘነጋም።
ለተኩስ አቁሙ የተለያዩ ሀገራት እንዲሁም ተቋማት ድጋፋቸውን ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወቃል።
ተኩስ አቁሙ ይዘልቅ ዘንድ ግጭትም እንዲገታ ተግባራዊነቱ በሁሉም የግጭቱ ተሳታፊዎች እንዲሆን ሲጠየቅም ነበር።
በወቅቱ "ህወሓት" የተናጠል ተኩስ አቁሙን "ቀልድ" ሲል አጣጥሎት ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጡ አይዘነጋም፤ ነገር ግን ህወሓት ምላሽ ያገኘ አይመስልም።
ዛሬ በድጋሚ ህወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ ከዚህ ቀደም ያወጣውን ባለ7 ነጥብ አቋም አሻሽሎ አቅርቧል።
ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎቱን አለኝ ያለው ህወሓት ፤ ዳግም ባወጣው የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት እና የሽግግር ሂደት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።
በዚህኛው የተኩስ አቁም ለማድረግ ያወጣው ቅድመ ሁኔታ ፦
- በትግራይ የተቋረጡ የኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮምዩኒኬሽን፣ የባንክ ፣ የትራንስፖርት ፣ የጤና እና የንግድ እንቅስቃሴዎች መጀመር አለባቸው።
- የአገር መከላከያ አባላት የሆኑትን ጨምሮ ማንነታቸውን መሠረት ተደርጎ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በመላው አገሪቷ የትግራይ ተወላጆች የጅምላ እስር ይቁም።
- የ2013 ዓ.ም. እና የ2014 ዓ.ም. በጀት ይለቀቅ፡ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ።
- የሰብዓዊ እርዳታ ለማድስ ለሁሉም አይነት የትራንስፖርት አማራጮች በርካታ መተላለፊያ ኮሪደሮች ክፍት መደረግ አለባቸው የሚሉት ይገኙበታል።

ህወሃት ከጦርነት ድርጊቱ እንዲታቀብና የሰብአዊ ዕርዳታ እንዳያስተጓጉል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠየቁ።
አቶ ደመቀ ጥያቄውን ያቀረቡት ከካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኖ ጋር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
በትግራይ ክልል ስላለው ፖለቲካዊና ሰብአዊ ሁኔታ በተመለከተ የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኖ ሀገራቸው የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ እንዲደረስ የሚትፈልግ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ደመቀ ፤ የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ እንዲዳረስ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ያሳለፈ መሆኑን ጠቅሰው ፤ የህወሃት ቡድን ግን የሰላማዊ መንገድን ከመከተል ይልቅ የዕርደታን መተላለፊያዎች በመዝጋት በአማራና በአፋር ክልል አዲስ ጦርነት መክፈቱን አስረድተዋል፡፡
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ መንግስት በክልሉ ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር እንዲሁም ሲያደርግ የቆየውን የሰብአዊ ድጋፎች ዕውቅና ከመስጠት መቆጠቡ ፤ ኢትዮጵያን ያሳዘነ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
ካናዳን ጨምሮ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተውን የተኩስ አቁም ውሳኔን ህወሃት እንዲያከብር ጫና እንድደረግበት እና የቡድኑ ጥፋት ድርግቶች እንዲወገዙ አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/MoFA-Ethiopia-07-29