"...በጃዋር ላይ የቀረቡት ክሶች ከማንነቱ እና ስብዕናው ጋር የማይገናኙ ናቸው" - ወ/ሮ አርፋሴ ገመዳ
"ስታር ትሪቢዩን" የተባለ የአሜሪካ ጋዜጣ ፥ ወይዘሮ አርፋሴ ገመዳ በባለቤታቸው አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ የቀረቡት ክሶች ከማንነት እና ስብዕናቸው ጋር የሚገናኙ አለመሆናቸውን ስለመናገራቸው ዘግቧል።
"ህዝባችን ለረጅም ጊዜ የሰቆቃ ኑሮ የገፋ በመሆኑ ጃዋር የህዝቡ ህይወት እንዲሻሻል በሰላማዊ መንግድ ሲታገል የቆየ ነው" ያሉት ወይዘሮ አርፋሴ ፥ "ጃዋር ሚኒሶታን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ለዚሁ አላማ ነበር" ብለዋል።
አቶ ጃዋር፥ ለህዝቡ ህይወት መሻሻል ሲል የአሜሪካን ዜግነት ትቶ ወደኢትዮጵያ በመመለስ በሰላማዊ ፖለቲካ ውስጥ በመሳተፉ በአሁኑ ጊዜ ሀገር አልባ ሆኗል ያሉት ወ/ሮ አርፋሳ፥ ለህዝባዊ አላማው ብሎ የአሜሪካን ዜግነቱን በመቀየሩ በጉዳዩ ላይ ጠንካራ የአሜሪካን መንግስትን ድጋፍ ለማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
ወይዘሮ አርፋሴ እና አቶ ጃዋር ፥ የአራት ዓመት ልጅ ያላቸው ሲሆን ልጁ አባቱ ለምን እንደጠፋ ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ እና አሰቃቂው የህይወቴ አካል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#ItsMyDam🇪🇹
"...በጉዳዩ ላይ ይጮሃሉ ፣ ያስፈራራሉ ፣ ማስፈራሪያው ድሮም የነበረ ነው" - የውሃ ጥናት ባለሞያ ፈቅ አህመድ ነጋሽ
ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚነሱ ጫናዎችን ተቋቁማ የመጀመሪያውን የውሃ ሙሌት አካሂዳለች።
አሁን ኢትዮጵያ ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ነው።
ለ2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት የተያዘው ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ጫና እያበረቱ ይመጣሉ።
የውሃ ጥናት ባለሞያው ፈቅ አህመድ ነጋሽ ፥ "... ግድቡ እስከተገነባ ድረስ የውሃ ሙሌቱን መከልከል እንደማይቻል ግብፆቹም ሆነ ሱዳኖች ጠንቅቀው ያውቃሉ" ብለዋል።
ባለሞያው ፥ "...በጉዳዩ ላይ ይጮሃሉ ፣ ያስፈራራሉ ፣ ማስፈራሪያው ድሮም የነበረ ነው፤ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ደግሞ ማስፈራሪያ ሲኖር ይፈራል ፤ ሀገራቶቹ ድንገት ወደግጭት ይገቡና ኃላ የራሳችን ችግር ይሆናል ብለው ስለሚፈሩ፥ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ይፈጥራሉ የሚል እምነት ስላላቸው ነው"ሲሉ ገልፀዋል።
አክለውም፥ "የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን እንደሉአላዊነት በቆጠረው ጉዳይ ላይ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ፤ መሀል ላይ የሚፈጠሩ የፖለቲካ ጉዳዮች የሚያመጣቸው ውዥንብሮች ቢኖሩም ህዝቡ ግን ምንጊዜም ከድጋፍ ወደኃላ አይልም" ሲሉ ለዋልታ ቲቪ ተናግረዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Attention
ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚሞተው ሰው ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት 25 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,190 የላብራቶሪ ምርመራ 2,054 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 934 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 219,381 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,025 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 163,956 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 850 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose

#April6RWANDA
"...እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6/1994 በጊዜው የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጁቬናል ሃብያሪማናንና የቡሩንዲውን አቻቸውን ሲፕሬን ንታርያሚራን የያዘ አውሮፕላን ተመትቶ 2ቱን ፕሬዚዳንቶች ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የተሳፈሩት ሁሉም ሰዎች አለቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ሃብያሪማና የሁቱ ጎሳ ተወላጅ መሆናቸው በወቅቱ ስልጣን ይዘው የነበሩት ሁቱዎች ለረጅም ዓመታት በሩዋንዳ የመንግሥትን ስልጣን ይዘው በቆዩት ቱትሲዎች ተበድለናል ከሚል እሳቤ ጋር ተደምሮ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲዘምቱ አደረጋቸው፡፡
በ100 ቀናት የማጥቃት እንቅስቃሴ ከ800 ሺ በላይ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች ተገደሉ፡፡
በወቅቱ የመንግሥት ስልጣን በተነጠቁት ቱትሲዎችና ስልጣን በጨበጡት ሁቱዎች መካከል የእርስ በእርስ ጦርነት እየተደረገ ነበር::
የሁቱ ፖለቲከኞች ለአውሮፕላን አደጋ 'ሩዋንዳ አርበኞች ግንባር'(RPF) በሚል ስያሜ ሲንቀሳቀስ የነበረውና ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ይመራ የነበረውን ቱትሲ መራሹን የአማጺያን ቡድን ተጠያቂ ሲያደርጉ፤ የካጋሜው 'የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር' በበኩሉ "ሁለቱን ፕሬዚዳንቶች የያዘው አውሮፕላን ተመትቶ እንዲወድቅ የተደረገው የሁቱ ፖለቲከኞች ባቀነባበሩት ሴራ ሲሆን፤ አደጋውም ሁቱዎች ቱትሲዎችን ለመጨፍጨፍ ቀድመው ያዘጋጁት ምክንያት ነው" በማለት ይሞግታሉ።
የአደጋውን ምክንያቶች ለማጣራት የተካሄዱ ምርመራዎችም ሁለቱን ፕሬዚዳንቶች የያዘውን አውሮፕላን መትተው የጣሉት እነማን እንደሆኑና ከድርጊቱ ጀርባም የትኛው ወገን እንደነበረ መለየት አልቻሉም፡፡
ዛሬ ላይ 800 ሺ ዜጎቿን በአስከፊው የዘር ጭፍጨፋ ያጣችው ሩዋንዳ አስቀያሚው ድርጊት የጣለባትን ጠባሳ ተሻግራ በልማት እንዲሁም በዕድገት ለሌሎች የዓለም አገራት ተምሳሌት ሆናለች። " - አንተነህ ቸሬ
@tikvahethiopia

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ የኪንሻሳ ሶስትዮሽ ድርድር መግለጫ አወጣች።
ከመግለጫው የተወሰደ ፦
"...የታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዓመት ሙሌት በመርሆዎች መግለጫ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ይከናወናል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በግድቡ የሁለተኛ ዓመት ኑሌት ዙሪያ ተገቢውን መረጃ ለመቀያየር ዝግጅቷን በተደጋጋሚ ገልፃለች።
ሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ሳይደርስ ግድቡ መሞላት የለበትም በሚል የሚቀርብ አቋም የህግ መሰረት የሌለው እንዲሁም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
የግድቡ አሞላል እና ተያያዥ የውሃ አለቃቅ ስርዓት ላይ ለመስማማት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ዝግጁ ብትሆንም ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር እና ውጤቱ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብ እና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያጸና አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረሰ የሚል ግትር አቋም ይዘዋል።
ኢትዮጵያ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የሆነ የአሁን እና የወደፊት የአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት #አትፈርምም።"

TIKVAH-ETHIOPIA
በአፋር እና ሱማሊ ክልል መካከል ያለው ውጥረት ፦ የአፋር ክልል መንግስት ፦ - በክልሉ "ሀሩቃ" በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መቁሰላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። - በአርቡ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል። - የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በዚያኑ ዕለት ምሽት "ገዋኔ"…
የሃይማኖት መምህሩ በአፋር እና ሱማሊ ክልል መካከል 'ሰላም' እንዲወርድ ጥሪ አቀረቡ !
የሃይማኖት መምህሩ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በአፋር እና ሶማሊ ክልል መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ነው አሉ።
ቁስለኞችም ከቀን ወደቀን እየጨመሩ ከህክምና አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።
የ2ቱ ክልል መሪዎች በአፋጣኝ ወደንግግር መጥተው ግጭቱን ሊያስቆሙት ይገባልም ብለዋል።
ሁለቱንም ክልሎች የሚያስተዳድሩት ኃላፊዎች ያላቸው ስብእና እና የፖለቲካ ተቀባይነት መሰል ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከምን ግዜውም በላይ የሚያስችላቸው በመሆኑ በፍጥነት ወደጠረጴዛ ሊመጡ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
ባህላዊ እና ኃይማኖታዊ የግጭት መፍቻ መንገዶችም እድል ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል።
የፌዴራል መንግስት ቸልተኝነት ለግጭቱ መባባስና ለንፁሃን ሞት የራሱን ሚና እየተወጣ ይገኛል ሲሉ ወቅሰዋል።
ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ ሁለቱም ህዝቦች መጎዳት ብቻ ሳይሆን መሪዎቻቸውን ከተጠያቂነት የሚድኑ አይሆንም ሲሉ አስገንዝበዋል።
ኡስታዝ አቡበክር ፥ የክልሎቹ መሪዎች ፈቃደኝነት ካለ በግል ሆነ በቡድን ለሚደረጉ የግጭት መፍቻ ጥረቶች የድርሻቸው ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸው ገልፀው ፥ "ለአስርት አመታት በሄድንበት መንገድ እየሄድን ሰላም እንደማይመጣ በመረዳት የክልሎቹን ህዝቦችና መሪዎች ወደ መፍትሄ እንዲመጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል።

#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ከነገ ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃን ማድረግ እንደሚችሉ አሳወቀ
የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ እጣ ድልድል መርሐ-ግብር እየተከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የእጣ ድልድሉ በምርጫ ቦርድ እና ብሮድካስት ባለሥልጣን በጋራ በተዘጋጀ መድረክ ነው እየተከናወነ የሚገኘው።
ፓርቲዎች በተደለደለላቸው እጣ መሠረት ከመጋቢት 30 እስከ ግንቦት 23 በመገናኛ ብዙኃን ነፃ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ ሊሰማ የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ለጊዜው ታገደ።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በእነ ስብሃት ነጋ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሊያሰማው የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ለጊዜው ታገደ።
ምስክርነቱ የታገደው የተከሳሽ ጠበቆች በምስክር አሰማም ሂደቱ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው ነው።
ዐቃቤ ህግ የአቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ የ42 ተጠርጣሪዎችን የጊዜ ቀጠሮ እየተመለከተ ላለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ከዚህ ቀደም ባቀረበው አቤቱታ፤ የቅድመ ምርመራ የምስክርነት ሂደቱ በዝግ ችሎት እና በስውር እንዲሆን ጥያቄ አቅርቦ ነበር። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ይህንን አቤቱታ ተቃውመው ለችሎት አቤት ቢሉም መቃወሚያቸው ውድቅ ተደርጓል።
ጠበቆቹ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ ፤ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የቅድመ ምርመራ የምስክር መስማት ሂደቱ ታግዶ እንዲቆይ በዛሬው ውሎው ወስኗል።
ችሎቱ “የይግባኝ ክርክሩ መልስ እስኪያገኝ ድረስ መዝገቡ ተዘግቶ ይቆያል” ሲል በዛሬው ውሎው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ዛሬ መጋቢት 29 በነበረው ችሎት ፤ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ 39 ተጠርጣሪዎች በአካል ተገኝተው ተከታትለዋል። በዛሬው ችሎት ሰሎሞን ኪዳኔ እና ብርሃነ ጸጋዬ በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል።

እናት ፓርቲ የታሰሩበት ዕጩ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ አሳሰበ።
የእናት ፓርቲ በአማራ ክልል፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደባይ ጥላት ወረዳ ፣ ቁይ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ ሐውልቱ ጸጋዬ ፈንታሁን ቁይ ፖሊስ ጣቢያ መጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ ከታሰሩ ዛሬ 4ኛ ቀናቸውን እንደሆነ አስታወቀ።
ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፥ "... ይህ ኢፍትሐዊ ጉዳይ ፓርቲችንንም ሆነ ደጋፊዎቻችንን እጅግ ያሳዘነ ተግባር ሲሆን ፓርቲያችን በሀገራችን ሊያሰፍን ለጀመረው ሰላማዊና ፍትሐዊ ሽግግር እንቅፋት እየሆነበት ይገኛል" ብሏል።
በምርጫ አዋጁ አንቀጽ 42 መሠረት ዕጩው ያለመከሰስ መብት ያላቸው እንደሆነ ቢታወቅም የወረዳው አስተዳዳሪ እና የብልጽግና ዕጩ ተፎካካሪው ፖለቲካዊ እንድምታ ባለው አኳኋንና በማንአለብኝነት እንዲታሰሩ አድርገዋል ሲል ከሷል።
እናት ፓርቲ ፥ "ዕጩው አቶ ሐውልቱ ጸጋዬ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ በሥነ ምግባር የተመሰገኑ፣ በማስተማርና በማስታረቅ እንጂ በጸብ መነሾ የማይታወቁ ሆነው ሳለ የፖለቲካ ሾተላዮች በእስር ውለው እንዲያድሩ፣ በርካሽ ውንጀላ በጎ ተጽዕኗቸውም እንዲደበዝዝ ለማድረግ እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ" ብሏል።
ከዚህ ቀደም በፓርቲው ዕጩዎች ላይ በአርባ ምንጭ ፣ ሰቆጣ ፣ አዊ (ዚገም) ይህ ተግባር መሞከሩንም አስታውሷል።
ፓርቲው ፥ "ይህ ሆን ተብሎና ታቅዶ ለማሸማቀቅ የተጎነጎነ ሴራ መሆኑን በጽኑ ይገነዘባል" ብሏል።
ይህን ጉዳይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቂያለሁ የሚለው እናት ፓርቲ ፥ መፍትሔ ሳይገኝ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል አስረድቷል።
ፓርቲው በቀጣይ ሕጋዊ መንገዶችን ያለመታከት እንደሚሞክር የገለፀ ሲሆን ዕጩው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።

#Ethiopia ኢትዮጵያ ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ የኪንሻሳ ሶስትዮሽ ድርድር መግለጫ አወጣች። ከመግለጫው የተወሰደ ፦ "...የታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዓመት ሙሌት በመርሆዎች መግለጫ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ይከናወናል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በግድቡ የሁለተኛ ዓመት ኑሌት ዙሪያ ተገቢውን መረጃ ለመቀያየር ዝግጅቷን በተደጋጋሚ ገልፃለች። ሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ሳይደርስ ግድቡ…
"...ግድቡን ‘እናጠቃለን’ በሚል ተደጋግመው የሚሰሙ ዛቻዎች እውን ይሆናሉ የሚል ግምት የለኝም" - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
ኪንሻሳ በተካሄደው የህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደት ግምገማ ላይ ያተኮረ መግለጫ በዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተሰጥቷል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በመግለጫቸው ፥ ሱዳን የድርድሩን አካሄድ የመቀየር አላማ እንደነበራት ገልፀው፥ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት እንዳይመራ እና ሌሎች ተዋንያኖች አብረው ድርድሩን እንዲመሩ ትፈልግ ነበር ብለዋል፤ ግብጽ ይህን “የሱዳንን ሃሳብ ትደግፍ ነበር ነገር ግን ኢትዮጵያ ይህን አልተቀበለችም ሲሉ አሳውቀዋል።
በድርድር ወቅት “የሱዳን ህዝብ ውሃ አጥቷል፣ ካርቱም ውሃ አጥሯል የሚል ነገር አንስተው ነበር” ብለዋል “ነገሩ ትክክል እንዳልሆነ መረጃ ለመለዋወጥ እውነተኛ ያልሆኑ ክሶችን ማቆም ይገባል” በሚል ምላሽ መስጠታቸውን ጠቁመዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ፥ በየዕለቱ 90 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደ ሱዳን እና ወደ ታችኞቹ የተፋሰሱ ሃገራት ይፈሳል ያሉ ሲሆን፥ ይህ ሮዛሪየስ ግድብ ውስጥ ጭምር ውሃ ያላት ሱዳን “እንድትጠማ የሚያደርግ አይደለም፤ ኢትዮጵያ ኃይል ከማመንጨት ውጪ የሱዳን ህዝብ እንዲጎዳ አትፈልግም” ብለዋል።
ሱዳን በአቢዬ ግዛት የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣላት ስለመጠየቋ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ፥ ሰላም አስከባሪ ጦሩ በተመድ መሰማራቱን ገልፀው ጉዳዩ ከውሃ አጠቃቀም ጋር ይሁን ከግድብ ጋር እንደማይገናኝ እና ኪንሻሳ ላይ በነበረው የግምገማ መድረክ አለመነሳቱን ተናግረዋል።
ግድቡን ‘እናጠቃለን’ በሚል ተደጋግመው የሚሰሙ ዛቻዎች እውን ይሆናሉ የሚል ግምት እንደሌላቸውም ተናግረዋል፡፡
More: telegra.ph/AlAin-04-07-2 [AlAIN]

HERQA በተለያዩ ኮሌጆች ላይ እርምጃ ወሰደ።
ከHERQA የእውቅና ፍቃድ ሳያገኝ በድህረ ምረቃ እና በቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎችን ሲያስተምር የነበረው 'ሲፈን ኮሌጅ' እንዲዘጋ ተማሪዎቹንም እንዲበትን መወሰኑን ሸገር FM 102.1 ዘግቧል።
ሲፈን ኮሌጅ አዲስ አበባ ጀሞ አካባቢ በከፈተው ካምፓስ በማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በድህረ ምረቃ ደረጃ፣ በአካውንቲንግ ፋይናስን እና አድሚኒስትሬሽን በቅድመ ምረቃ ሲያስተምር ተደርሶበታል።
ይህ ኮሌጅ ከጥቂት ወራት በፊት በጉለሌ ክ/ከተማ በደንብ ማስከበር ፅ/ቤት(መንግስት ቢሮ) ውስጥ ተማሪዎችን ሲመዘግብ መገኘቱ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፥ሲፈን ኮሌጅ እውቅና እንዲሰጠው ቢጠይቅም ዝቅተኛውን መስፈር ማሟላት ባለመቻሉ ማስተካከል ያለበትን ጉዳይ እንዲያስተካክልና በሶስት (3) ወር ውስጥ እንዲያሳውቅ ተነግሮት እንደነበር ገልጿል። ነገር ግን የኤጀንሲውን ምላሽ ችላ በማለት እውቅና ሳይኖረው ተማሪዎችን በተለያዩ ዲፓርትመንቶች መዝግቦ ሲያስተምር በድንገተኛ ክትትል ተደርሶበት እርምጃ እንደተወሰደበት አሳውቋል።
ኮሌጁ የከፈተውን ካምፓስ እንዲዘጋ፣እያሰተማራ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲበትን፣አዲስ አበባ ውስጥ ለሚቀጥሉት 2 ተከታታይ ዓመት ምንም አይነት እውቅና እንዳይሰጠው ተወስኖበታል።
ኤጀንሲው ከሲፈን ኮሌጅ በተጨማሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ባሉ 5 ኮሌጆች (ፓራዳይዝ ቫሊ-ዲላ፣ ግሎባል ብሪጅ-ወ/ሶዶ)፣ግሬት ላንድ-ነቀምቴ፣ ዘመን-ደሴ)፣ራዳ -ደሴ) ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን / ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ገልጿል [ከላይ በደብዳቤ ይመልከቱ]
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች ተቋሙ የምዝገባ ፍቃድ እንዳለው ማረጋግጥ አለባቸው ሲል HERQA አሳስቧል።