TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ የኪንሻሳ ሶስትዮሽ ድርድር መግለጫ አወጣች።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

"...የታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዓመት ሙሌት በመርሆዎች መግለጫ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ይከናወናል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በግድቡ የሁለተኛ ዓመት ኑሌት ዙሪያ ተገቢውን መረጃ ለመቀያየር ዝግጅቷን በተደጋጋሚ ገልፃለች።

ሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ሳይደርስ ግድቡ መሞላት የለበትም በሚል የሚቀርብ አቋም የህግ መሰረት የሌለው እንዲሁም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።

የግድቡ አሞላል እና ተያያዥ የውሃ አለቃቅ ስርዓት ላይ ለመስማማት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ዝግጁ ብትሆንም ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር እና ውጤቱ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብ እና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያጸና አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረሰ የሚል ግትር አቋም ይዘዋል።

ኢትዮጵያ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የሆነ የአሁን እና የወደፊት የአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት #አትፈርምም።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia