#April6RWANDA
"...እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6/1994 በጊዜው የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጁቬናል ሃብያሪማናንና የቡሩንዲውን አቻቸውን ሲፕሬን ንታርያሚራን የያዘ አውሮፕላን ተመትቶ 2ቱን ፕሬዚዳንቶች ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የተሳፈሩት ሁሉም ሰዎች አለቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ሃብያሪማና የሁቱ ጎሳ ተወላጅ መሆናቸው በወቅቱ ስልጣን ይዘው የነበሩት ሁቱዎች ለረጅም ዓመታት በሩዋንዳ የመንግሥትን ስልጣን ይዘው በቆዩት ቱትሲዎች ተበድለናል ከሚል እሳቤ ጋር ተደምሮ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲዘምቱ አደረጋቸው፡፡
በ100 ቀናት የማጥቃት እንቅስቃሴ ከ800 ሺ በላይ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች ተገደሉ፡፡
በወቅቱ የመንግሥት ስልጣን በተነጠቁት ቱትሲዎችና ስልጣን በጨበጡት ሁቱዎች መካከል የእርስ በእርስ ጦርነት እየተደረገ ነበር::
የሁቱ ፖለቲከኞች ለአውሮፕላን አደጋ 'ሩዋንዳ አርበኞች ግንባር'(RPF) በሚል ስያሜ ሲንቀሳቀስ የነበረውና ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ይመራ የነበረውን ቱትሲ መራሹን የአማጺያን ቡድን ተጠያቂ ሲያደርጉ፤ የካጋሜው 'የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር' በበኩሉ "ሁለቱን ፕሬዚዳንቶች የያዘው አውሮፕላን ተመትቶ እንዲወድቅ የተደረገው የሁቱ ፖለቲከኞች ባቀነባበሩት ሴራ ሲሆን፤ አደጋውም ሁቱዎች ቱትሲዎችን ለመጨፍጨፍ ቀድመው ያዘጋጁት ምክንያት ነው" በማለት ይሞግታሉ።
የአደጋውን ምክንያቶች ለማጣራት የተካሄዱ ምርመራዎችም ሁለቱን ፕሬዚዳንቶች የያዘውን አውሮፕላን መትተው የጣሉት እነማን እንደሆኑና ከድርጊቱ ጀርባም የትኛው ወገን እንደነበረ መለየት አልቻሉም፡፡
ዛሬ ላይ 800 ሺ ዜጎቿን በአስከፊው የዘር ጭፍጨፋ ያጣችው ሩዋንዳ አስቀያሚው ድርጊት የጣለባትን ጠባሳ ተሻግራ በልማት እንዲሁም በዕድገት ለሌሎች የዓለም አገራት ተምሳሌት ሆናለች። " - አንተነህ ቸሬ
@tikvahethiopia