TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች #1

ከላይ ፦

1. የኦሮሚያ ክልል ከተሞች፣ ዞኖች ፖሊስ መምሪያ ስልኮች
2. በሲዳማ ክልል (ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ)
3. የአማራ ክልል የዞኖች፣ የብሄረሰብ አስተዳደሮች፣ እና ከተሞች ፖሊስ
4. የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
5. ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የፀጥታ ቢሮዎችን የስልክ ቁጥሮች ማግኘት ትችላላችሁ።

* የሌሎች የከተሞች ፣ የዞኖች የፀጥታ ቢሮ ስልኮች በቀጣይነት ይቀርባሉ።

የምንኖርበትን አካባቢ የፀጥታ አካላት ስልክ ቁጥሮች በእጅ ስልካችን ላይ የመመዝገብ ባህልን እናዳብር።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለዉን የህግ ማስከበር እርምጃ እንጂ የእርስ በርስ ጦርነት አይደለም አለ መከላከያ ሚኒስቴር።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

'አጥፊው ቡድን' እየተወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ የሀሰት መረጃዎችን እየነዛ ነው ብለዋል።

ቡድኑ እያሰራጨ ያለው የሃሰት መረጃ ጭንቀቱን እና ተስፋ መቁረጡን የሚሳይ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የትግራይ እና ኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን የሃሰት መረጃዎችን በመለየት ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጎን መቆም አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የመከላከያ_ሰራዊቱ_ማስጠንቀቂያ

መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ልዩ ሀይል እና የትግራይ ሚሊሻ አባላት የጥፋት ቡድኑ ከለላ ከመሆን ይልቅ ለሀገር መከላከያ እጃቸውን እንዲሰጡ አሳስቧል።

እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የማይሰጡ ከሆነ መከላከያው "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ" ለመደምሰስ እንደሚገደድ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ፈንድቶ በ1 ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

* የታረመ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሰራዊቱ በታላቅ ጥንቃቄ እና በሙያዊነት የሀገር ማዳንና ህግን የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊቱ 'ጥፋተኛውን ቡድን' ብቻ ነጥሎ ነው እያጠቃ የሚገኘው ተብሏል።

መከላከያው ንፁሃንንና መሰረት ልማት ላይ ጥቃት ይፈፅማል እየተባለ በጥፋት ኃይሉ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሰራዊቱ የማንንም የውጭ ኃይል ድጋፍ ሳይፈልግ የጥፋት ቡድኑን የመደምሰስ ቁመና አለው ብሏል።

"መከላከያ ሰራዊቱ የትኛውንም ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ ድጋፍ አያስፈልገውም ፤ ቡድኑን ለማጥቃት የውጭ ድጋፍ አልጠየቀም አይጠይቅምም" ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ፥ "የትግራይ ህዝብ ጦርነት የሰለቸው ነው፣ ሰላምና ልማት ፈላጊ ነው ፣ ሀገሩንም አይወጋም ፣ በጠቅላላው በዚህ ጦርነት ላይ #አልተሳተፈም" ብለዋል።

ይህ ብቻም ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ሰራዊቱ በደረሰበት ቦታ ለሰራዊቱ ያለውን ክብር በግልፅ እያሳየ እና እየደገፈ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነቱ የእርስ በእርስ ጦነርት አይደለም ፤ ጦርነቱ እየተደረገ ያለው ከጥፋተኛው ቡድን ጋር እና ህግን የማስከበር ብቻ ነው ሲሉም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ፈንድቶ በ1 ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። * የታረመ @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ወድቆ የተገኘ ቦንብ ፈንድቶ በ 1 ግለሰብ ላይ 'ቀላል የአካል ጉዳት' ማድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ጥዋት 2፡00 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው ጉዳቱ የደረሰው።

በደረሰበት ጉዳት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ግለሰብ የታክሲ ረዳት ሲሆን ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ እንደገባ እና በማዳበሪያ የተጠቀለለ እቃ ተመልክቶ በእግሩ ሲረግጠው ከዚያ በኋላ ራሱን እንደሳተ ተናግሯል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተባለ።

ይህን የገለፁት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጄር ጄነራል መሀመድ ተሰማ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "የህወሃት ቡድን በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ ወረረችን በማለት ህዝቡን እያደናገረ ነው" ብለዋል።

በተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን 'ድጋፍ አጠናክሮ' እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREAirForce

የአየር ኃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ሜ/ጄ ይልማ መርዳሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የህወሓት ቡድን ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል ብለዋል።

አየር ኃይሉ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ኢላማዎችን ያለምንም ከልካይ አውድሟል ሲሉ ተናግረዋል።

ሜ/ጄ ይልማ ፥ "ፓይለቶቻችን የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ ይገኛሉ" ብለዋል።

አሁንም ይህ የጥፋት ኃይል ህግ ፊት እስኪቀርብ ድረስ ያለምንም ከልካይ ተፈላጊ ኢላማዎችን እናጠቃለን ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የጋዜጠኞች መታሰር'

የAddis Standard አዘጋጅ መድሃኔ እቁባሚካኤል እንደገና ለእስር መዳረግ፣ የአውሎ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው መታሰር እንዳሳሰባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገለፁ።

ኮሚሽነሩ ከሚዲያ ጋር የተገናኘ ጥፋት ጠፍቶም ከሆነ ፍትሃዊ በሆነ መንገድና ስርአትን በተከተለ ሁኔታም እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ የEPA ጋዜጠኞች ሃፍቱ ገ/እግዚአብሔር ፣ ፀጋዬ ሃዱሽ እና አብርሃ ሃጎስ እንዲሁም የOMN ጋዜጠኛ የሆነው ኡዲ ሙሳ ተጨማሪ 4 ጋዜጠኞች መታሰር ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

ቅዳሜ እለት ጥቅምት 28/2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው መድሃኔ ቢለቀቅም ሰኞ እለት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም እንደገና እንደታሰረም ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ሲፒጄ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እንዲፈታ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጥሪ አቅርቧል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አርማው እንዲከበር ጠየቀ !

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በግጭቱ የተጎዱ የጦር ሰራዊት አካላትን የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የሚሰጡ እና ጉዳተኞችን በአቅራቢያ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያደርሱ 3 አምፑላንሶቹ ላይ ጥቅምት 30 ቀን 2013 "በዳንሻ አከባቢ" የታጠቁ ሃይሎች ተኩስ በመክፈት ጉዳት እንዳደረሱበት አሳውቋል።

ከጥቅምት 24 ጀምሮ ከአስር በላይ አምፑላንሶችን በማሰማራት በሁለቱም ወገኖች በግጭቱ የተጎዱ ወገኖቹን እያገለገለ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ ድርጊቱ አለም አቀፍ መርህ እና የቀይ መስቀል አርማ አጠቃቀም ህግን የጣሰ ነውም ብሎታል።

ማኅበሩ በጎፈቃደኞች ፣ ሰራተኞች ሌሎች የህክምና አካላት በግጭት ወቅት የግጭት ተሳታፊ ያልሆኑትንና ተሳታፊ መሆናቸውን ለዘለቄታ ያቆሙ ሰዎችን ህይወት መታደግ እንዲችሉ ሰብዓዊ እንቅስቃሴያቸው እንዳይታወክ ጠይቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል!

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,183
• በበሽታው የተያዙ - 400
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 981

አጠቃላይ 100,727 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,545 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 62,497 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

292 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፥ አሁን ችግሩ ያለው በ2ቱ መንግስት መካከል ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት ፈላጊዎችና ኢትዮጵያን በሚበትኑ ሰዎች መካከል ነው ብለዋል።

የተፈጠረው ሁኔታ በኢትዮጵያ ህዝብ እና በጁንታው መካከል ነው ፤ ዝም ብሎ የፖለቲካ ጨዋታ አይደለም ሲሉ ገልፀዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ "ችግሩ በአብይ መንግስት እና በትግራይ መንግስት መካከል ነው የሚባል ነገር የለም ፣ እንደዚህ ወርዶ መቀመጥም የለበትም፣ እሱ ከሆነ ሁለቱን አስወግደህ ለምን ኢትዮጵያን አታስቀጥልም ? ችግሩ ግን ያ አይደለም" ሲሉ ለዶቼ ቨለ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የሰላም ጥሪ በሚመለከት'

የሰላም ጥሪ ከኦፕሬሽን በፊት መጀመር ነበረበት አሁን ወደዛ መመለስ እንደማይቻል ተገልጿል።

ቀፎውን ተነክቶ ንቡ ከተነሳ በኃላ ንቡን ወደ ቀፎው መመለስ አይቻልም። ንቡ የሚፈልገውን ነገር ካደረገ በኃላ ነው ወደ ቀፎው የሚመለሰው ተብሏል።

አሁን ያለው ሁኔታ ወደኃላ የሚመለስ አይደለም።

የሚፍለጉት ሰዎች ስም ዝርዝራቸው ተቀምጦ እጅ ሲሰጡ ያን ጊዜ ሰላም ይፈጠራል ተብሏል።

መከላከያው በሀገር አንድነት ላይ የመጣን ነገር በድርድር መፍታት አይቻልም ብሏል።

* መከላከያ ሰራዊት
* ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
'የUNHCR ሪፖርት'

ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ለሸሹ 7,000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የነብስ አድን እርዳታ ለማድረስ እየጣረ መሆኑን የተመድ የስደተኛ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ማሳወቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

UNHCR በፌዴራል መንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ሱዳን ከደረሱት አብዛኛውዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን ገልጿል።

በገዳሪፍ ሉጅ እና በከሰላ ክፍለ ሀገር ሀም ዳየት በጊዜያዊ መጠለያዎች አርፈው ለጊዜው ምግብና ውሃ እየቀረበላቸው ነው።

በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ሁኔታ የሚፈናቀለው የሰላማዊ ሰው ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል በመገመትም በሌሎች የአካባቢው ሀገራት ተመሳሳይ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን UNHCR አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PMOEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እውቅና ያላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጨምሮ ሁሉም ግለሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንፀባርቅ እና ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#BREAKING

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ 'በወንጀል የተጠረጠሩ' የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን አሳወቀ።

በዚህም መሰረት፦

- ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
- አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
- አቶ አባይ ፀሃዬ
- ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
- አቶ ጌታቸው ረዳ
- አቶ አፅበሃ አረጋዊ
- አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ ጨምሮ ሌሎችን ግለሰቦችን ያለመከሰስ መብታቸውን ምክር ቤቱ አንስቷል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች የጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋትና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው ተብሏል።

* በአጠቃላይ 38 ግለሰቦች ናቸው።

በሌላ በኩል፦

የህ/ተ/ም/ቤት አቶ ፍቅሩ ገ/ሕይወትን የምርጫ ቦርድ አባል አድርጎ ሾሟል። (HoPR)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot