TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የሶማለኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ሊከፍት መሆኑን ገለፀ !

በዛሬው ዕለት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በህክምና ዶክትሬት እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 347 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

በምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ፣ የጅግጅጋ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር በሽር አብዱላሒ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተው ነበር።

በዛሬው የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፊሬው ተገኝ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሶማለኛ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምር ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የጀመረው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመው ህዝቦችን ከማስተሳሰር አንፃር ሌሎችም ሊከተሉት ይገባል ብለዋል። (SRTV)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,454
• በበሽታው የተያዙ - 629
• ህይወታቸው ያለፈ - 19
• ከበሽታው ያገገሙ - 724

በአጠቃላይ በሀገራችን 92,858 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,419 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 46,842 ከበሽታው አገግመዋል።

306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

"...አሁን የመጣው የአንበጣ መንጋ ታይቶም አይታወቅም" - አቶ ክንደያ ግደይ (የትግራይ አርሶ አደር)

የበረሀ አንበጣ መንጋ በትግራይ ክልል ካሉት 7 ዞኖች 4ቱን ወሯል።

በ29ኝ ወረዳዎች 79ኝ ቀበሌዎች የሚገኝ ሰብልና የተፈጥሮ ሀብት በአንበጣው ጉዳት ደርሶበታል።

አስተያየታቸው ለDW ከሰጡ ገበሬዎች መካከል የ70 ዓመት እድሜ ያላቸው አቶ ክንደያ ግደይ ለDW ተከታዩን ብለዋል ፦

"ልጅ እያለሁ መኮኒ ፣ ማይጨው እና ወጅራት በአጠቃላይ የሸፈነ ትልቅ የአንበጣ መንጋ መጥቶ አስታውሳለሁ ፤ ይህ 60 ዓመታት ያለፈው ታሪክ ነው ፤ እንደኔ እንደኔ አሁን የመጣው ግን ታይቶም አይታወቅም።"

ከትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ በተገኘው መረጃ በክልሉ ካለ አጠቃላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት 77,000 ሄክታር የሚሆነው በአንበጣ መንጋ ተወሯል።

በተለይም በዚህ ሁለት ሳምንት የአንበጣ መንጋው በስፋት እየተስፋፋ ይገኛል።

አምና በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ትግራይ የገባው የአንበጣ መንጋ ብዛት 18 ሲሆን ዘንድሮ ግን ከመስከረም ወዲህ ባሉ ቀናት ብቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አንበጦች የያዘ 21 መንጋ ወደ ክልሉ ገብቷል።

አንበጣው እስካሁን በትግራይ ውስጥ አጠቃላይ በቁጥር ተለይቶ ያልታወቀ ጉዳት በግብርና ምርት ላይ ማድረሱን ከ #DW ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካፍ በማረጋገጫው ኢትዮጵያን ክለቦችን አካቷል !

ካፍ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ቡድኖችን ይፋ አድርጓል ።

በዚህም መሰረት መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንደሚሳተፉ ካፍ ይፋ ባደረገው የማረጋገጫ መረጃ ላይ ታይቷል ።

Via @tikvahethsport
#AmboUniversity

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ ብሎ በሰየመውና በግቢው ዋና በር ፊት ለፊት የተሰራው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ዛሬ ተመርቋል፡፡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ያሰራው ይህ ሀውልት ሲመረቅ ቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

(OBN)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ቅጥር ለመፈፀም 2 ቋንቋዎችን እንደግዴታ ያስቀመጠበት ህግ አልወጣም ሲል ገልጿል።

ቅጥርን በተመለከተ ሁለት ቋንቋዎችን መቻል እንደግዴታ ተቀምጧል እየተባለ የተናፈሱ መረጃዎች ከእውነት የራቁ ናቸው ተብሏል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ የተናገሩት ፦

"የአ/አ ከተማ አስተዳደር በቻርተር የሚተዳደር እና ቻርተሩ በ1995 በአዋጅ የቻርተር አዋጅ 361 ተብሎ በግልጽ እንደተቀመጠው "አማርኛ" የከተማ አስተዳደሩ የስራ ቋንቋ ሆኖ እንደሚያገለግል በግልጽ ተቀምጧል።

ይህ ቻርተር የወጣው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለሆነ አዋጁ ባልተሻሻለበት ሁኔታ ስራ ለመቀጠር ሁለት ቋንቋ እንደግዴታ ነው እየተባለ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ ስራ ለመቀጠር እንደግዴታ ያወጣው ህግ ባለመኖሩ ምናልባት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ 2 ቋንቋ መቻልን እንደግዴታ የሚያስቀምጡ ማስታወቂያዎችን ካሉ ትክክል ባለመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ እርምጃ ይወስዳል።"

Via FBC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ የሃይቅ - ቢስቲማ - ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አስጀምረዋል።

በይፋ የግንባታ ስራው የጀመረው መንገድ 74 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል።

ግንባታውን የሚያከናውኑት ፓወርኮን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና አሰር ኮንስትራክሽን በጋራ ናቸው።

የግንባታው ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት እንደሆነ ታውቋል።

የመንገድ ግንባታው በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

የኳታር መንግስት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ሽብርተኝነትን በፋይናንስ መደገፍን ለመከላከል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 20/2019 “ማንኛውም ዜጋ ወደ አገሪቱ ሲገባም ሆነ ሲወጣ ከ 50,000 በላይ የቀጠር ሪያል ካሽ እና ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ውድ ጌጣ ጌጦችን ለጉምሩክ መስሪያ ቤት ማሳወቅ እንደሚገባው” ደንግጓል።

ከላይ የተጠቀሱ ንብረቶች ሳያሳውቁ ከሀገር ለመውጣት ወይም ለመግባት መሞከር ፣ የተሳሳተ መረጃ መስጠት ወይም ደግሞ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ንብረቱን ከመወረስ አልፎ እስከ 3 ዓመት እስር ወይም ከ100,000 እስከ 500,000 የኳታር ሪያል ቅጣት እንደሚያስከትል በህጉ ተቀምጧል።

በመሆኑም በኳታር ነዋሪ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ዜጎች ከአገሪቱ ስትወጡም ሆነ ስትገቡ የምትይዙትን ከ50,000 በላይ የሆነ የቀጠር ሪያል የገንዘብ መጠን (በኳታር ሪያል፣ በውጭ አገር ገንዘቦች፣ በቼክ እና የመሳሰሉት) እንዲሁም ከላይ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን በላይ ዋጋ ያላቸውን ውድ ንብረቶች (ወርቅ ፣ ብር ፣ ፕላቲኒዬም፣ ዳያመንድ እና የመሳሰሉትን) በጉምሩክ ጣቢያዎች በማስመዝገብ (declare በማድረግ) ከማንኛውም ህጋዊ ርምጃ ራሳችሁን እንድትጠብቁ በዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ሀገር መቼም አትረሳችሁም" - መከላከያ ሰራዊት

መከላከያ ሰራዊት በተለያየ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ለማተራመስ በየጫካው ፣ በየቀበሌው ፣ በየመንደሩ ተወትፈው የንፁሃንን ደም በማፍሰስ እና ህዝብን በማሸበር ስራ ላይ ተጠምደው ያሉ አጥፊ ሀይሎችን ለመደምሰስና የህዝቦችን ሰላምና አንድነት እንዲሁም ሀገሪቱን ለማዳን ህይወታቸው እየገበሩ ላሉ መላ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ምስጋና አቅርቧል።

መከላከያ ሰራዊት ፥ "በግዳጅ ያላችሁ ፈጣሪ ብርታት እና ፅናት ይስጣችሁ። ለተሰዋችሁ ደግሞ በቀኙ ያስቀምጣችሁ። ኢትዮጵያ በናንተና በመልካም ህዝቦቿ ታፍራ እና ተከብራ ትቀጥላለች! ድል ለጀግኖች" ሲል በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አንበጣ ያደረሰውን ጉዳት እና እየተወሰደ የሚገኘውን የመከላከል ርምጃ ፣ ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ተገኝተው መመልከታቸውን አሳውቀዋል።

ዶክተር አብይ ፥ አርሶ አደሮቹ ያለባቸውን ወቅታዊ ችግር ማዳመጣቸውን ፣ መንግሥት ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ቃል መግባታቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ "ጫሊ" በተገኙበት ሰአት የሸህ ሰይድ ኢብራሂም ጫሊ መስጅድን በመጎብኘት በጫሊ ሀሪማ በአሁኑ ሰአት ያሉትን ሸህ ሀጂ መሀመድ ነጅብን መዘየራቸውን የወረባቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,045
• በበሽታው የተያዙ - 485
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 701

በአጠቃላይ በሀገራችን 93,343 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,426 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 47,543 ከበሽታው አገግመዋል።

339 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን ተማሪዎችን ማስተማር ጀመሩ !

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ የመምህራንን ጫና ለመቀነስ እኔም አስተምራለሁ የሚለውን ንቅናቄ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማስተማር ጀምረዋል።

ሚኒስትሩ በሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፊዚክስ ትምህርትን አስተምረዋል።

በትምህርት ቤቱ በሚወጣ መርሃ ግብር መሰረትም ለ45 ቀን የማስተማር ስራውን እንደሚከውኑ ገልፀዋል።

ሌሎችም በመምህርነት ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችም በመምህራን ላይ የሚኖረውን ጫና ለመቀነስ በበጎ ፍቃደኝነት የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጀምረዋል። #MoE

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ እና የ12 ክፍል የገጽ ለገጽ የማካካሻ ትምህርት ተጀምሯል።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዳግማዊ ሚንሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት በመገኘት ትምህርት በይፋ አስጀምረዋል።

ተማሪዎች ከጤና ባለሙያዎች እንዲሁም መምህራን የሚሰጣቸውን ምክር እና አቅጣጫ በአግባቡ እንዲተገብሩ አሳስበዋል።

ለተማሪዎች የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በትምህርት ቤቱ የተደረገውን የትምህርት ዝግጅት ምክትል ከንቲባዋ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ዛሬ ከአ/አ በተጨማሪ በመላ ሀገሪቱ ለሚቀጥሉት 45 ቀናት የ8ኛ እና የ12 ክፍል የማካካሻ ትምህርት ተጀምሯል።

Via Addis Ababa Press Secretary
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia