TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሀዋሳ አሮጌ ገበያ በተነሳ የእሳት አደጋ በአንድ ሼድ ዉስጥ የነበረ ሸቀጥ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገለፀ።

የእሳት አደጋው ምሽት 7፡00 ሰዓት አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት እንደተነሳ ተገልጿል።

ቃጠሎው ከጀመረ ሰዓት አንስቶ በህብረተሰቡ እና በፀጥታ ሀይሉ ሰፊ ርብርብ ቃጠሎውን መቆጣጠር በመቻሉ ወደሌላ ሼድ እንዳይዛመት ሆኗል።

ዛሬ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬ በቃጠሎው የደረሰውን አደጋ እና ነጋዴዎቹን በስፍራው በመገኘት ጎብኝተዋል።

ምክትል ከንቲባው ከተማ አስተዳደሩ በቃጠሎው ንብረት የወደመባቸውን ነጋዴዎች በተቻለ አቅም በፍጥነት መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በዚህ አደጋ በሰው ህይወት እና በአካል ላይ ጉዳት አለማድረሱን የተነገር ሲሆን የአደጋው መንስኤና የደረሰው የንብረት ውድመት መጠን ተጣርቶ ይገለፃል መባሉ ከሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ !

ሰአሊ ሎሬት ሻምበል የክብር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የክብር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ክቡር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ ፦

- ሻምበል ለማ ጉያ ከአባታቸው አቶ ጉያ ገመዳ ከእናታቸው ከወ/ሮ ማሬ ጎበና በ1921 በቢሾፍቱ ደሎ ቀበሌ ተወለዱ፡፡

- በአየር ሃይል ተምረው በከፍተኛ ነጥብ ተመርቀዋል፡፡ በአስመራ ከተማ በአየር ሃይል መምህርት አገልግለዋል፡፡

- በሀገራችን ታሪክ በስዕሉ ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነችው ሥዕል ያለስተማሪ መፅሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡

- አርቲስት ለማ ጉያ 'አፍሪካ አርት ጋለሪ' አቋቁመዋል፡፡ የጋለሪውን መታሰቢያ በኒልስን ማንዴላ ሃውልት በማጀብ አራት የጋለሪ ቤቶችን በመገንባት ለህዝብ ምንግዜም ክፍት ሆነው ስራዎቻቸውን ወጣቱ ትውልድ እንዲማርበት አድርገዋል፡፡

- በቆዳ ስራ የሚቀርጹት የፖርትሬት ምስል ታዋቂነትን አትርፎላቸዋል፡፡ በተለይ በፍየል ቆዳ ላይ ሙሉ በሙሉ ፀጉሩ ሳይነሳ ተፈጥሮአዊ ወዙንና መልኩን ይዞ የፊትን ገፅ ብቻ በቀለም በመስራት የበርካቶችን አድንቆት አትርፈዋል፡፡

- በህይወት ዘመናቸው ወደ 1ዐ ሺህ የሚጠጉ የስዕል ውጤቶችን ለሀገራቸው አበርክተዋል፡፡

- የአርቲስት ለማ ጉያ ሶስት ሴቶች ልጆቻቸውና ሁለት ወንድ ልጆቻቸው አምስቱም የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ናቸው፡፡

- የባህል እሴቶቻችን ከሃሀር አልፈው እንዲነበቡ፣ አንዲታወቁና እንዲገለፁ ያደረጉ የጥበብ ጀግና ነበሩ፡፡

- በርካታ ትምህርት ቤቶችን በማሰራትም ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

- የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስቱ በ2007 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት በሥነ-ጥበብ ዘርፍ ሰጥቷቸዋል፡፡

(የክብር ዶክትሬት በተቀበሉበት ወቅት ከተፃፈላቸዉ ግለታሪክ ተቀንጨቦ የተወሰደ)

የለማ ጉያ ድንቅ የቆዳ ላይ ሥዕሎች👇
https://telegra.ph/BBC-10-26-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ኡራኤል አካባቢ ባለው የባቡር ሀዲድ ላይ በደረሰ ቀላል የእሳት አደጋ ምክንያት አገልግሎት መስጠት ማቆሙን ETHIO FM 107.8 ዘግቧል።

በባቡር ሃዱ ላይ ጪስ ነገር መታየቱን ተከትሎ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰው የማጥፋት ስራ ላይ ናቸው፡፡

በከተማዋ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት እንዳሉት በአካባቢው የተፈጠረው አደጋ ለማጣራትና በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳት አደጋ መኪናዎችና ሰራተኞች ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ተናግረዋል፡፡

አደጋው በስፍራው ከተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል።

ባቡር ሀዲዱ አካባቢ የተፈጠረው ጢስ መነሻው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን በስፍራው ከሚገኙ የእሳት አደጋ ሰራተኞች መረጃው ወደ ማዕከል እንደተላከ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለንም ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ግን የእሳት አደጋ መኪኖች ወደ ስፍራው አቅንተው አደጋዉን ለመቆጣጠር በጥረት ላይ ሲሆኑ የባቡር አገልግሎት በዚሁ አደጋ ምክንያት መቋረጡን ተረጋግጧል።

በአካባቢው ለተሳፋሪዎች ቲኬት ይሸጥበት የነበረው የመገናኛ ቲኬት ቢሮ ተዘግቷል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

ለ7 ሳምንታት ተቋርጦ የቆየው በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የሚደረገው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ነገ እንደሚቀጥል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዛሬ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ፥ “በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሚደረገው ድርድር መቀጠል የ3ቱ አገሮች መሪዎች በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ከሰላማዊ እና አግባቢ መፍትሔ ለመድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ይጠቁማል" ብለዋል። #DW

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ የተናገሩት ፦

"የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተያየት ነገ በሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ አሉታዊ ጫና አያሳድርም።

ድርድሩ ራሱን የቻለ ነው ፤ ሦስቱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት እየተደራደሩ ያሉበት ጉዳይ ነው። ፕሬዚደንቱን አይመለከትም።

የሚመለከታቸው ነገር ካለ እንድንስማማ መገፋፋትና መደገፍ ፣ እኛ የተስማማንበትን ነገር መቀበል ብቻ ነው።

ከዚህ ውጭ ይሄ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ እየተደረገ ያለ ጉዳይ ስለሆነ የሌላ የማንም ሰው ጉዳይ ሊሆን አይችልም"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,628
• በበሽታው የተያዙ - 364
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 607

በአጠቃላይ በሀገራችን 93,707 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,437 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 48,150 ከበሽታው አገግመዋል።

314 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ይህ በፎቶ የምትመለከቱት ትላንት አ/አ አፍሪካ ህብረት አካባቢ የደረሰ አደጋ ነው። የመንገድ ላይ ፖል ወደቆ በሚሄድ መኪና ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል።

በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አልደረስም።

አደጋው የደረሰበት የቤተሰባችን አባል እኔ ላይ የሆነው በሌሎች ላይ እንዳይደረስ ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል ብሏል።

ቴሌ/መብራት ኃይል በየአካባቢው ያቆሟቸውን እንጨቶች ደህንነት ማረጋገጥ ካልቻሉ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አፍሪካ ህብረት አካባቢ የደረሰው አደጋ !

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርስቲዎች መከፈት እና የሰላም ጉዳይ ፦

በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ ተማሪዎች ተቀብለው ሥራቸውን የሚጀምሩትን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የፖሊስ አባላትን ያካተተው ስልጠናው የመማር ማስተማር ሂደት ሊያውኩ ይችላሉ የተባሉ ስጋቶች ተነስተው ውይይት ይደረግባቸዋል።

የሰላም ሚኒስትር ደዔታ የሆኑት ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው በተለይም ከወራት መቋረጥ በኃላ የሚጀመረው የዘንድሮ ዓመት ትምህርት ያለምንም መስተጓጎልና ችግር እንዲቀጥል ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ዶክተር ሳሙዔል ክፍሌ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ባህሪ ፣ ያለፈው ዓመት እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁናዊ ሁኔታ እና ፈተናዎች ዙሪያ መነሻ ጥናት ማቅረባቸውን AMN ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የ2012 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ተፈታኞች በኦንላይን ምዝገባ ማካሄድ መጀመራቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የኦንላይን ምዝገባው በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።

ተማሪዎች በአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመገኘት በወቅቱ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ዳይሬክተሯ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምዝገባው እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም የሚቀጥል ይሆናል።

@tikvahethiopiaBOt @tikvahethiopia
#NewsAlert

ሰኔ 16/2010 ለጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት ያጠፉ አምስት (5) ግለሰቦች በተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ከ5 እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን etv ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOt @tikvahethiopia
#UPDATE

ትላንት ህይወታቸው ያለፈው የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ሥነ ስርዓት ሀሙስ በቢሾፍቱ እንደሚፈፀም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ሰኔ 16/2010 ለጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት ያጠፉ አምስት (5) ግለሰቦች በተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ከ5 እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን etv ዘግቧል። @tikvahethiopiaBOt @tikvahethiopia
ሰኔ 16/2010 ዓ/ም በዶከተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተከሰሱ 5 ተጠርጣሪዎች ተፈርዶባቸዋል ፦

• 1ኛ ተከሳሽ (ጌቱ ግርማ) 23 አመት ጽኑ እስራት፣
• 2ኛ ተከሳሽ (ብርሃኑ ጁፋር) 22 አመት ጽኑ እስራት፣
• 3ኛ ተከሳሽ (ጥላሁን ጌታቸው) የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣
• 4ኛ ተከሳሽ (ባህሩ ቶላ) 17 አመት ጽኑ እስራት፣
• 5ኛ ተከሳሽ (ደሳለኝ ተስፋዬ) 5 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ለነገ የተጠራው ሰልፍና የመንግስት ምላሽ !

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ እና ጥቃት ለመቃወም ነገ ጥቅምት 18 በአማራ ክልል ከተሞች እና ጥቅምት 22 በአ/አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል።

ፓርቲው ስለጠራው ሰልፍ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከቀኑ 8:00 ላይ በዋና ጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በሌላ በኩል ፦

በትላንትናው ዕለት የአማራ ክልል መንግስት በአማራ ክልል የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አይደለም፤ ወቅቱንም ያላገናዘበ ነው ብሎታል።

ሰልፉ ህጋዊ ባለመሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች መደበኛ የእለት ከእለት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪውን አቅርቧል።

ይህንን ተላልፎ ሰልፍ የሚወጣ አካል ካለ ግን የጸጥታ አካላት ፤ ፓሊስና ሚሊሻ ስርዓት እንዲያስይዙ የክልሉ መንግስት ትዕዛዝ መስጠቱን ገልጿል።

የአማራ ክልራ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ፥ "የገጠመን ችግር ሰልፍ በማድረግ ብቻ የምንፈታው አይደለም ፤ በሰልፍ ለውጥ የሚመጣ ቢሆን የክልሉ መንግሥት ፊት ሁኖ ይመራው ነበር" ብለዋል።

የተጠራውን ሰልፍ በራሳቸው መንገድ ለመጠቀምና አማራ ክልልን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ እየሠሩ የሚገኙ የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች አሉ የክልሉ መንግሥትም ተጨባጭ መረጃ ደርሶታል ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪ ከክልሉ ውጭ የሚኖረው አማራ ደኅንነቱ የሚጠበቀው በበሰለ የፖለቲካ ውይይት እና ድርድር እንዲሁም ህገወጦችን በአንድነት ሁኖ በመታገል ለዘላቂ መፍትሔ በመስራት ነው እንጂ በሰልፍ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

እንዲህ አይነት ሁኔታ በዘፈቀደ የሚጠራ ሰልፍ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ዜጎችን ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርግ ካልሆነ በስተቀር መፍትሄ ሊሆን የሚችል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

*የከሰዓቱን የአብንን መግለጫ ተከታትል እናሳውቃለን!

@tikvahethiopiaBOT