TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray #AddisAbaba #COVID19

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የነሃሴ 21 ሪፖርት እንደሚያሳየው በከተማው 640 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ህይወታቸው ካለፈው 17 ሰዎች መካከል 10 ሰዎች በአስክሬን ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን 7 ሰዎች ከጤና ተቋም ናቸው።

በሌላ መረጃ፦

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 21/2012 ሪፖርት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም ከ706 የላብራቶሪ ምርመራ 56 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ 101 ሰዎች አገግመዋል።

ከነዚህ 56 ሰዎች መካከል 22 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 5 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 29 የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።

እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 44,600 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 3,552 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል ፣ 2,184 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

ፍርድ ቤት አርቲስትሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል በተጠረጠሩት ከበደ ገመቹ እና አብዲ ዓለማየሁ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት የ15 ቀን ጊዜ ሰጠ።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቂያለሁ ብሎ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ አስረክቧል።

በችሌቱ አንደኛው ተጠርጣሪ አብዲ ዓለማየሁ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት ወቅት በቦታው አልነበርኩም ያለ ሲሆን ሌላኛው ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ በበኩሉ አርቲስቱ ሲገደል ከበደ ገመቹና አብዲ ዓለማየሁ አብረውት እንደነበሩ አስረድቷል።

በዚሁ መሰረትም ፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የክስ መመስረቻ አስራ አምስት (15) ቀን ጊዜ መጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከነሃሴ 26/2012 ዓ/ም ጀምሮ በኳታር የግል የትምህርት ተቋማት እና ስልጠና ማዕከላት እስከ 50 በመቶ አቅማቸው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ።

የኳታር መንግስት የኮሮና ቫይረስ የአራተኛ ደረጃ (Phase Four) ማሻሻያዎች በሁለት ዙር ተግባራዊ እንደሚደረጉ ማሳወቁ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም (01 September 2020) የሚጀምር ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ  ከአራተኛ እስከ 14ኛ  የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል።

ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድና አቶ በቀለ ገርባ ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት አልቻልንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ፍርድ ቤቱ በጓደኛ የመጠየቅ  መብት ቢኖራቸውም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለም።

አንደኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ጃዋር መሃመድ ከልጄ እና ከባለቤቴ ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንድገናኝ ይፈቀድልኝ  ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ በሳምንት ሁለት ጊዜ በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲገናኙ አዟል።

12ኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ጆሮዬን ታምሚያለሁ የተሻለ ሆስፒታል ልታከም  ብለው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤት በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ እንዲመቻችላቸው አዟል።

ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ ምስክሮችን ለማድመጥ ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via Tarik Adugna (ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ነሐሴ 22/2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሔዱ የመሬት ወረራዎችን እና ኢ-ፍትሀዊ የሆነ የመኖሪያ ቤቶችን ክፍፍል በሚመለከት በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረው መግለጫ በፖሊስ መበተኑን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ናትናኤል ፈለቀ እንደተናገሩት ከቀናት በፊት ስለስብሰባው ለሰላም ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ በደብዳቤ ያሳወቁ ቢሆንም ዛሬ ነሐሴ 22/2012 በራስ ሆቴል ሊሰጥ ነበረው መግለጫ ግን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስለ መግለጫው መረጃ የለኝም በሚል መግለጫው እንዳይካሔድ መከልከሉ ታውቋል።

Via Addis Maleda
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር በወንዝ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በጎርፍ በመውደቁ ምክንያት ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

የአካባቢው መስመር ከኮተቤ ከሚወጣ መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት እስከ ማምሻው ድረስ ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዩኤኢ (UAE) ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለመምህራኖቿ የኮሮና ምርመራ እያደረገች ነው!

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች ከመመለሳቸው አስቀድማ የግል ትምህርት ቤት መምህራንን እየመረመረች ነው፡፡

205 የግል ትምህርት ቤቶች በሚገኙባት አቡዳቢ ከ15 ሺ የሚበልጡ መምህራን ተመርምረዋል፡፡

ምርመራው ሁሉንም የትምህርት ተቋማቱን መምህራን እና የስታፍ አባላት እስኪያዳርስ ድረስ እንደሚቀጥልም ነው ዘ ናሽናልን ዋቢ አድርጎ አል አይን የዘገበው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 22/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 725 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 34 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሱማሌ፦
- 1,128 በቫይረሱ የተያዙ
- 23 ሞት
- 693 ያገገሙ

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,642 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 255 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 58 ከምዕራብ ሀረርጌ
- 54 ከምዕራብ አርሲ
- 23 ከሰሜን ሸዋ
- 17 ከለገጣፎ ከተማ
- 16 ከአዳማ ከተማ
- 15 ከሞጆ ከተማ
- 14 ከጉጂ ይገኙበታል

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
- 5,843 በቫይረሱ የተያዙ
- 42 ሞት
- 1,762 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 266 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት መካከል ፦
- 1 ከቡለን ወረዳ
- 3 ከአሶሳ ከተማ
- 10 ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 3 ከባንቢስ ወረዳ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፦
- 546 በቫይረሱ የተያዙ
- 274 ያገገሙ

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 376 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 97 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,972 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 143 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 42 ከሰ/ወሎ ዞን
- 31 ከዋግ ኽምራ ብ/ሰብ ዞን
- 19 ከጎንደር ከተማ
- 12 ከባህር ዳር ከተማ
- 9 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBot
ባለፉት 24 ሰዓት 1,733 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,766 የላብራቶሪ ምርመራ 1,733 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 586 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 48,140 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 758 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 17,415 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 22/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,604 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ አራት (54) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ፦

- ከጌዴኦ 12 (ዲላ 7፣ ይርጋጨፌ 3፣ ወናጎ 2) ፣
- ከደቡብ ኦሞ 11 (ጂንካ 5፣ በናፀማይ 4፣ ሀመር 1፣ ማሌ 1)፣
- ከወላይታ 10 (ዳሞት ወይዴ 9 ፣ ሶዶ 1)፣
- ከከምባታ ጠምባሮ 8 (ዱራሜ 5፣ አዲሎ ዙሪያ ወረዳ 2 እና ዳንቦያ 1)፣
- ከጉራጌ 5፣ ከጋሞ 2 (1 ቦረዳ 1 አርባምንጭ) ፣
- ከምዕራብ ኦሞ 2 (2ቱም ከሜኒት ጎልዲያ)
- ከደራሼ 2 ፣
- ከጎፋ 1 (ዛላ) እና ሃላባ 1 ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡

አጠቃላይ በደቡብ ፦
- 1,100 በቫይረሱ የተያዙ
- 9 ሞት
- 453 ያገገሙ

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 523 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 32 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም (32) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።

አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 1,359 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 502 ያገገሙ

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 294 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በድሬዳዋ ፦
- 911 በቫይረሱ የተያዙ
- 20 ሞት
- 751 ያገገሙ

@tikvahethiopiaBOT
በትላንትናው ዕለት (ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም) በተለያዩ ሚዲያዎች "በችግር ውስጥ የሚገኙ ከ25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያና ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነው" በሚል የተሰራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቆናል።

በውጭ ያሉ ዜጎችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ፣ የረድኤት ድርጅቶች እንዲሁም የሚኖሩባቸው ሀገራት መንግስታት እየደገፉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም ከየሀገራቱ መንግስታት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

'ከ25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሊመለሱ ነው' የሚለው መረጃ ከኢዜአ የተወሰደ ሲሆን መረጃው ትላንት (በፌስቡክ ገፃቸው እና ድረ ገፃቸው) ተስተካክሏል።

@tikvahethmagazine ላይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ምንጭ አድርገን የተለዋወጥነው መረጃም ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ አድርገናል። ሌሎች የሚዲያ ተቋማትም የኢዜአን መረጃ ዳግም ተመልክታችሁ መረጃችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኞች አስተዳደር ኃላፊ በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ መስጠቱን #BBC አስነብቧል። ፍርድ ቤቱ ኃላፊው በ24 ሰዓት ተይዘው እንዲቀርቡ ነው ትዕዛዝ የሰጠው።

ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ ያሉ የOMN ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳና ሌሎች አራት (4) ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤት እንዲያመጡ የተሰጠው ተደጋጋሚ ትዕዛዝ ተፈፃሚ ባለመሆኑ ነው።

ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 20/2012 ዓ/ም በነበረው ችሎት ላይ ተጠርጣሪዎቹ ለምን የኮቪድ-19 ምርመራ እንዳልተደረገላቸው ኃላፊው ፍርድ ቤት መጥተው ያስረዱ ቢልም አስተዳዳሪው ዛሬ በነበረው ችሎት ላይ ሳይቀረቡ ቀርተዋል፣ ተወካይም አላኩም ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 በሽታ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በቤት ሆኖ የኮቪድ-19 ህክምና ለማግኘት ፍቃደኛ የሆነ፣

2. ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት፣

3. በቤት ውስጥ የቆይታ ጊዜ አጋዥ ወይም ረዳት ያለው እንዲሁም እራሱን መርዳት የሚችል፣

4. የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማግኘት ወይም ማሟላት የሚችል፣

5. በተመሳሳይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሌላ ሰው የግል ንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ ማሸፈኛ ጭንብሎችን ማግኘት የሚችል እንደሆነ፣

6. ኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከሌሎች ተዷጋኝ በሽታዎች ማለትም የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ፣ አስም፣ ኤች አይቪ፣ ቲቢ፣ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ካሉባቸው ሰዎች ጋር አብሮ የማይኖር ከሆነ፣

7. የኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከቤት ላለመውጣት ወይም ማናቸውም ጠያቂ ወደቤት እንዳይመጣ ለማድረግ ማረጋገጫ የሚሰጥ ከሆነ፣

8. እራሱን ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ለይቶ ማቆየት የሚያስችል ክፍል ወይም ከቤተሰብ አባላት በ2 ሜትር ርቀት ላይ መቆየት የሚያስችል ክፍል ያለው እንደሆነ፣

9. በጤና ቡድን በቋሚነት ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆነ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tigray #COVID19

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 22/2012 ሪፖርት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም ከ418 የላብራቶሪ ምርመራ 63 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል፤ ተጨማሪ 139 ሰዎች አገግመዋል።

በቫይረሱ ከተያዙት 63 ሰዎች መካከል 15 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 7 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 41 የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።

እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 45,018 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 3,615 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል ፣ 2,323 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትላንት (ነሃሴ 22/2012 ዓ/ም) ስብሰባ አካሂደዋል።

በስብሰባ ሂደቱ ታዛቢ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፣ አውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ ተወካዮች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የወከላቸው ባለሞያዎች ተገኝተው ነበር።

በስብሰባው ላለፈው አንድ ሳምንት በሃገራቱ ባለሙያዎች በትላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሞላል እና ውሃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ ሲከናወን የነበረው የባለሙያዎች ድርድር ሪፖርት ቀርቧል። የሃገራቱ ባለሙያዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ በበይነ መረብ ስብሰባቸውን አካሂደዋል።

በቀጣይ በሚኖረው ሂደት በሚመለከት ሃገራቱ የድርድሩ ሂደት የሚገልጥ ደብዳቤ ለደቡብ አፍሪካዋ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ናዴሊ ፓንዶር ለመላክ ተስማምተዋል።

በዚህ መሰረት ሱዳን የምትሰጠው ማረጋገጫ የሚጠበቅ ሆኖ የሶስትዮሽ ስብሰባው መስከረም 4 እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia