CONGRATULATIONS!
ዛሬ ባህር ዳር እና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠኗቸውን 12 ሺህ 300 ተማሪዎችን አስመርቀዋል።
ከዚህ ውስጥ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 780 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስመርቋል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 520 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
PHOTO : FANA BROADCASTING
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#UPDATE
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማምሻውን እንዲያገኝ መስመሩን ለመቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ለኢዜአ አስታውቋል።
ኃይል የተቋረጠው የክረምቱ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር አካባቢ አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በመውደቁ መሆኑ ትላንት ተገልጿል።
የወደቀውን የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በሌላ የመተካት ስራው ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ የአካባቢውን መስመር ከኮተቤ ከሚወጣው መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት ዛሬ ማምሻውን ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
መስመሩን አገናኝቶ ሃይል ለመልቀቅ የሚከናወናው ስራ ትናንት ማምሻውን ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ማጠናቀቅ ሳይቻል ቀርቷል።
በዛሬው እለት መስመሩ ተስተካክሎ አካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አረጋግጧል።

ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም ሥራ ይጀምራል የተባለውን የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታልን ምክትል ጠቅለይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን መጎብኘታቸውን የጤና ሚስቴር አስታውቋል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለኮቪድ 19 ሕክምና አገልግሎት እየተዘጋጀ ያለው የአዲስ አበባ ኮቪድ 19 ፊልድ ሆስፒታል በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስር በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በዓለም ምግብ ፕሮግራም እና በዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተሠራ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለኮቪድ 19 ሕክምና አገልግሎት እየተዘጋጀ ያለው የአዲስ አበባ ኮቪድ 19 ፊልድ ሆስፒታል በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስር በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በዓለም ምግብ ፕሮግራም እና በዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተሠራ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር ነው! የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እንደሚቀየርና ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ቅዳሜ ሰፊ ማብራሪያ በኮሚሽኑ እንደሚሰጥ ለኢዜአ ገለፁ። ለደንብ ልብሱ መቀየር አሁን ያለው የደንብ ልብስ በቀላሉ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ምግባር ችግር የተባበሩ ፖሊሶች ልብሱን ለብሰው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በምክንያትነት…
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲሱን የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል!
አዲሱ የደንብ ልብስ ይፋ በተደረገበት ሥነ-ሥርዓት ላይ በእንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የፖሊስ የደንብ ልብስን መቀየር እንደ ሀገር የተጀመረው ሪፎርም አካል መሆኑን ገልፀዋል።
PHOTO : EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲሱ የደንብ ልብስ ይፋ በተደረገበት ሥነ-ሥርዓት ላይ በእንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የፖሊስ የደንብ ልብስን መቀየር እንደ ሀገር የተጀመረው ሪፎርም አካል መሆኑን ገልፀዋል።
PHOTO : EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalPoliceCommission
በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ለህዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።
ምንጭ፦ #MayorofficeAA

ዳግም የተቋረጠው "የዳታ ኢንተርኔት" አገልግሎት!
ወላይታ ሶዶ ከተማ ጨምሮ በሌሎች የወላይታ ዞን ከተሞች ፣ በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ፣ ደቡብ ኦሞ (ሃመርና ኦሞራቴ) ሀሙስ ነሃሴ 21/ 2012 ጀምሮ የዳታ ኢንተርኔት አግልግሎት መቋረጡን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
የWiFiና ብሮድባንድ አገልግሎት ግን አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ነው።
ከሳምንታት በፊት በወላይታ ዞን በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ለበርካታ ቀናት የዳታ ኢንተርኔት አግልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አይዘነጋም።
የአሁኑ በምን ምክንያት የዳታ ኢንተርኔት ሊቋረጠ እንደቻለ የሚያውቁትም ሆነ የሰሙት ነገር እንደሌለ የገለፁልን የቲክቫህ አባላት የኢንተርኔት በተደጋጋሚ መቋረጥ በእጅጉ እያማረራቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፣ በማታው እና በክረምት መርሐ-ግብር ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4, 288 ተማሪዎቹን ዛሬ አስመርቋል።
PHOTO : Mekelle University

ዩኤኢ (UAE) ከእስራኤል ጋር የሚደረጉ ግኙነቶችን ለመከልከል በ1972 ያወጣችውን አዋጅ ሻረች!
ዩኤኢ ከእስራኤል ጋር የሚደረጉ የትኞቹንም ዓይነት ግኙነቶች ለመከልከል እኤአ በ1972 ያወጣችውን አዋጅ መሻሯን አል አይን ዘገበ።
ዩኤኢ ይህን ያደረገችው ከእስራኤል ጋር አዲስ የሁለትዮሽ የግንኙነት ምዕራፍ መጀመሩን ተከትሎ ነው፡፡
ከሳምንት በፊት የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ሼህ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አልናህያን አዋጅ ቁጥር 15/72ትን በአዋጅ ቁጥር 04/20 ሽረዋል፡፡
የአዋጁ መሻር የሃገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር በምጣኔ ሃብት እና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ እንዲተባበሩ ለማድረግ የሚያስችል ነው እንደ ሃገሪቱ የዜና አገልግሎት (WAM) ገለጻ፡፡
ከአሁን በኋላ በየተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) የሚገኙ ተቋማት እና ግለሰቦች በእስራኤል ከሚገኙ ግለሰቦች እና ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ በጋራ መስራት የሚችሉ ይሆናል፡፡
የእስራኤል ምርቶችን ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማስገባት ፣ መነገድ ፣ መሸጥ መለዋወጥም ይቻላል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን

ነሃሴ 23/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 758 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 41 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,002 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 212 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 36 ከአርሲ
- 33 ከምዕራብ ወለጋ
- 32 ከቄለም ወለጋ
- 24 ከባሌ
- 22 ከነቀምቴ ከተማ ይገኙበታል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 182 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 646 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 69 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5,491 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 59 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት፦
- 16 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 12 ከሰ/ወሎ ዞን
- 8 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን
- 6 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 5 ከደ/ጎንደር ዞን
- 5 ከባህር ዳር ከተማ
- 4 ከደሴ ከተማ
- 2 ከደ/ወሎ ዞን፣ 1 ከጎንደር ከተማ
@tikvahethiopiaBot

ባለፉት 24 ሰዓት 701 ሰዎች ከኮቪድ-19 ሲያገግሙ ፤ 1,514 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል !
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,194 የላብራቶሪ ምርመራ 1,514 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 701 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 49,654 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 770 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,116 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,194 የላብራቶሪ ምርመራ 1,514 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 701 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 49,654 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 770 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,116 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 23/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,085 የላብራቶሪ ምርመራ 125 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት ፦
- ከአማሮ 47
- ከጋሞ 20 (ጋርዳ ማርታ 11፣ ከምባ ከተማ 5፣ አርባምንጭ 2 እና ዲታ 2)
- ከጉራጌ 17 (ወልቂጤ 10፣ ገደባኖ ጉታዘር 7)
- ከወላይታ 14 ( ሶዶ 9፣ ኪንዶ ኮይሻ 3፣ ሆቢቻ 1 እና አረካ 1 )
- ከጎፋ 11 (11ዱም ከኡባ ደብረጸሀይ) ፣
- ከየም 8
- ከደራሼ 4
- ከካፋ 1 (ጨና)
-/ከደቡብ ኦሞ 1(በናጸማይ)
- ከአሌ 1
- ከቡርጂ 1 ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡
አጠቃላይ በደቡብ ፦
-1,225 በቫይረሱ የተያዙ
-9 ሞት
-478 ያገገሙ
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 451 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 33 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 15 ከሀዋሳ ከተማ
- 9 ከማልጋ ወረዳ
- 7 ከአርቤጎና ወረዳ
- 1 ከአለታ ወንዶ ከተማ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በሲዳማ፦
- 1,392 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 552 ያገገሙ
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 474 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 47 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።
አጠቃላይ በድሬዳዋ ፦
- 958 በቫይረሱ የተያዙ
- 20 ሞት
- 764 ያገገሙ
#Afar
በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 361 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን ስምንት (8) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ በአፋር ፦
- 906 በቫይረሱ የተያዙ
- 231 ያገገሙ
@tikvahethiopiaBOT

ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ!
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዛሬ ማረፉን አውሎ ሚዲያ ዘግቧል።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ በድንገት የታመመ ሲሆን ባለፈው ማክሰኞ ከአይደር ሆስፒታል በአስቸኳይ ወደ ጥንቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህክምና የተላከ ሲሆን ዛሬ አመሻሹን ማረፉን ቤተሰቦቹ አሳውቀዋል።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ለሞት ያበቃው የደም ካንሰር ነው የተባለ ሲሆን ለቀናት የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነበር።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ እስከእለተ ሞቱ ድረስ በድመፂ ወያነ ቴሌቪዥን እየሰራ የነበረ ሲሆን ቀደም ሲል ለበርካታ አመታት በአዲስ አበባ ፋና ሬዲዮ እና ፋና ቴሌቪዥን ሰርቷል።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።