በኮቪድ-19 የተያዙ ኢንተርን ሃኪሞች!
ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ጀምሮ አስራ አምስት (15) የሚሆኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርን ሃኪሞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ በህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
በቫይረሱ መያቸው ከተረጋገጠው ኢንተርን ሃኪሞች መካከል ሰባቱ (7) ሴቶች ሲሆኑ የቀሩት ስምንቱ (8) ደግሞ ወንዶች ናቸው።
በህክምና ላይ እንደሆኑ የነገሩን ኢንተርን ሃኪሞቹ ስላሉበት ሁኔታ ነግረውናል ፣ አስተያየቶችን ሰጥተውናል ፣ ጥያቄዎችን አንስተዋል ፣ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ጉዳዮችንም ጠቁመዋል በነገው ዕለት እንመለስበታለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የሰብዓዊ መብቶች የአያያዝ ሁኔታ ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንዳይሄድ ኢሰመጉ አሳሰበ!
በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑን አጋጠሙ ከነበሩ የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጠኝነቱ አጠራጣሪ የሆነ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) አስታውቋል።
ከነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም አመሻሽ ጀምሮ በአሳሳ፣ በአዳባ፣ በዶዶላ፣ በሻሸመኔ፣ በባሌ ሮቤ፣ በጊኒር ፣ በአሰቦት ፣ በጭሮ ፣ በአወዳይ እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች የዜጎች ህይወት ተቀጥፏል።
ይህ ተመጣጣኝነቱ አጠያያቂ የሆነ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንዳይወስደው መንግስት በቂ ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባ ኢሰመጉ አሳስቧል።

የተማሪ ወላጆች ቅሬታና የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ!
(በሸገር ኤፍ ኤም 102.1)
ከትላንት ነሃሴ 20/2012 ጀምሮ የ2013 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል። በርካታ ወላጆች የአከፋፈል ሁኔታው እየተነገራቸው እንዳልሆነ ፣ ትምህርት ቤቶች እንደፈለጉት እንደሚያስከፍሏቸው ይናገራሉ።
አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከመመዝገቢያ ጋር የአንድ ወር፣ የሶስት ወር የሚጠይቁ አሉ ተብሏል። የወላጆች ትልቁ ጥያቄ አሁን የሚከፈለው ክፍያ ተማሪዎች በመስከረም ወር ትምህርት እንደሚጀምሩ ታውቆ/ተረጋግጦ ነው ? ወይስ መቼ እንደሚጀመር ይታወቃል ?
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ምላሽ ፦
አከፋፈሉ እንደየትምህርት ቤቶቹ ይለያያል (በወር ፣ በተርም ፣ በሴሚስተር የሚያስከፍሉ አሉ) በዘንድሮው ዓመት ልዩ ነገር ማድረግ አይችሉም።
ከዚህ በፊት በየወሩ የሚያስከፍሉ ከሆነ አሁን በየወሩ ነው መቀጠል ያለባቸው ፣ ከዚህ በፊት በተርም የሚያስከፍሉ ከሆነ በተርም ይቀጥላሉ፣ ከዚህ በፊት በሴሚስተር የሚያስከፍሉ በሴሚስተር ይቀጥላሉ።
ከዚህ ውጭ ግን ከዚህ በፊት በወር ሲያስከፍሉ የነበሩት ወቅታዊ ሁኔታን ተገን አድርገው በሴሚስተር ነው የምናስከፍለው የሚሉ ከሆነ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥቆማ መስጠት ይቻላል።
ወላጆች የወር፣ የተርም፣ የሴሚስተር ክፍያ ከከፈሉ በኃላ ኮቪድ-19 ስርጭቱ ቢጨምርና ትምህርት ቢቋረጥ አገልግሎት ላላገኘንበት ክፍያ ከፍለናል ቢሉ ኃላፊነቱን ማን ይወስዳል ?
የዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ምላሽ፦
እኛ መልካሙን አስበን ነው ፣ የዓለም ሁኔታም የሚያሳየው ኮሮና የመሻሻል ባያሳይም ስራዎች ይቀጥላሉ ፣ አሁንም እየቀጠሉ ናቸው፣ ኮሮናን በመላመድ ስራዎች ይቀጥላሉ ፣ ኮሮና እስኪጠፋ ከቆየን የትምህርት ስርዓቱ አደጋ ውስጥ ይገባል ፣ ይህ ሆነ ማለት ደግሞ የሚቀጥለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ይጎዳል ፣ ጉዳቱ የሚታየው የዛሬ 30ና 40 ዓመት ስለሆነ ዝም ብለን አናየውም። በከፍተኛ ጥንቃቄም ቢሆን እንሄድበታለን። ይህ ብዙም አያሰጋንም።
@tikvahethiopiaBot

TIKVAH-ETHIOPIA
በኮቪድ-19 የተያዙ ኢንተርን ሃኪሞች! ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ጀምሮ አስራ አምስት (15) የሚሆኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርን ሃኪሞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ በህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል። በቫይረሱ መያቸው ከተረጋገጠው ኢንተርን ሃኪሞች መካከል ሰባቱ (7) ሴቶች ሲሆኑ የቀሩት ስምንቱ (8) ደግሞ ወንዶች ናቸው። በህክምና ላይ እንደሆኑ የነገሩን…
በኮቪድ-19 የተያዙ ኢንተርን ሃኪሞች!
ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ አንስቶ ብቻ በትንሹ 15 የሚደርሱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢነተርን ሃኪሞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ የህክምና ክትትል እየተደረገለቸው ይገኛል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ከሆኑት በኮቪድ-19 የተያዙ ኢነተርኖች መካከል አንዳንዶቹ እንደነገሩን አሁንም ምርመራ ቢደረግ ሌሎች ተጨማሪ ኢነትርን ሃኪሞች ሊያዙ ይችላሉ ቁጥሩ በዚህ የሚያበቃ አይደለም ብለዋል።
ይህ ሁኔታ መፍትሄ የማይበጅለት ከሆነ በጤና ስርዓቱ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ቀላል አይሆንም፣ የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታት አዳጋች እየሆነ ይመጣል ብለውናል።
ኢንተርን ሃኪሞቹ እንዴት በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደቻሉ ፣ በስራቸው ወቅት ምን አይነት ጥንቃቄ ሲያደርጉ እንደነበር ፣ በኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ውስጥ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መልዕክታቸውን አድረሰዋል፣ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል telegra.ph/TikvahIntern-08-27

#UPDATE
ጳጉሜ 4 በትግራይ ክልል ለሚካሄደው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ እስከዛሬ ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም ባለው ጊዜ 2.6 ሚሊዮን መራጮች መመዝግባቸውን የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ይህም ቁጥር እስካሁን በትግራይ ክልል ታሪክ ትልቁ የመራጮች ቁጥር መሆኑንም ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ገልፀዋል።
መደበኛው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ነሃሴ 21/2012 የሚጠናቀቅ ቢሆንም በተለያየ ምክንያት መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ቅዳሜና እሁድ መመዝገብ እንዲችሉ ዕድል መመቻቹትን ተነግሯል።

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለስልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ መስጠቱን ለአል ዐይን ገልጿል፡፡
ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ ያለባቸው የመንግስት ሹመኞች በተደጋጋሚ እንዲያስመዘግቡ ቢጠየቁም ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡
ባለስልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስቀምጡ ያስቀመጠው ቀነ ገድብ ባለፈው ሀምሌ 30 ለሁለተኛ ጊዜ በማለፉ ምክንያት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድርጉን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በቀነገደቡ ማስመዝገብ ያልቻሉ አንድ መቶ ሰማንያ አራት (184) የፌደራና የአዲስ አባባ መገኘታቸውንና እነሱም በህግ ይጠየቃሉ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡ ኮሚሽኑ የባለስልጣናቱን ስም ዝርዝር ግን ይፋ አላደረገም - #AlAin
@tikvahethiopiaBOT

በኳታር ሁሉም መስጊዶች ክፍት ሊደረጉ ነው!
የኳተር መንግስት የኮሮና ስርጭትን ለመቀነስ የጣላቸውን ክልከላዎች እያላላ እንደሆነ ይታወቃል።
አሁን የአራተኛ ደረጃ (Phase Four) ማሻሻያዎች በሁለት ዙር ተግባራዊ እንደሚደረጉ ታውቋል።
የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን በዚህም ሁሉም መሰጊዶች ክፍት እንደሚደርጉ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኳተር መንግስት የኮሮና ስርጭትን ለመቀነስ የጣላቸውን ክልከላዎች እያላላ እንደሆነ ይታወቃል።
አሁን የአራተኛ ደረጃ (Phase Four) ማሻሻያዎች በሁለት ዙር ተግባራዊ እንደሚደረጉ ታውቋል።
የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን በዚህም ሁሉም መሰጊዶች ክፍት እንደሚደርጉ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም የምስጋና ስጦታ !
ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ከዛሬ ነሃሴ 21 እስከ 23 ለሶስት ቀን በተከታታይ ከጥዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ፦
- የ1 ጊጋ ባይት (በቀን 341 ሜ.ባ)
- የ40 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ድምፅ ጥሪ (በቀን 13 ደቂቃ)
- የ100 የሀገር ውስጥ SMS (በቀን 33 መልዕክት) ስጦታ እንዳበረከተ መግለፁ ይታወቃል።
ነገር ግን በርካታ ሰዎች የ1 ጊጋ ባይት ኢንተርኔት ስጦታው እንዳልደረሳቸው/እንዳልሰራላቸው/ እስካሁንም ከሞሉት ካርድ ላይ ሲቆርጥ እንደነበር አሳውቀዋል፣ አሁንም እያሳወቁ ይገኛሉ።
ውድ ቲክቫህ አባላት በዚህ ጉዳይ ከኢትዮ ቴሌኮም ማብራሪ ጠይቀን ለጊዜው ምላሽ አላገኘንም፤ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ስናገኝ እናሳውቃችኃለን።

የትምህርት ቤት ክፍያ የተጨመረባቸውና የአከፋፈል ስርዓቱ የተቀየረባቸው የተማሪ ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵየ ቅሬታቸውን አሰምተዋል!
ትላንት ነሃሴ 20/2012 ጀምሮ የ2013 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መጀመሩን ተከትሎ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የወራዊ ክፍያ ጭማሪ እንዲሁም የአከፋፈል ሥርዓቱ እንደተቀየረ ቅሬታቸውን አድርሰውናል፡፡
እኛም ይህንን የወላጆች ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርበናል፡፡ ድርጊቱ ተገቢነት የሌለውና አስፈላጊው ክትትል የሚደረግበት እንደሆነ የነገሩን በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ናቸው፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ ትምህርት ቤቶች ከዚህ ቀደም ሲያስከፍሉበት በነበረው መሰረት( የወር ሲያስከፍሉ የነበሩ የወር፣ የተርም ሲያስከፍሉ የነበሩ የተርም) የክፍያ ሥርዓታቸውን ሳይቀይሩ ምዝገባውን ማካሄድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘም በ2012 ከነበረው ክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንዳልተፈቀደ የገለጹ ሲሆን ወላጆች እንዲህ አይነት ችግር ካጋጠማቸውም በአከባቢው ወዳለ ትምህርት ቢሮ ማመልከት ይችላሉም ብለዋል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም መግለጫ እንደሚሰጡም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩን ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም አቅርበን ነበር፡፡ የቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠ አቅጣጫ መኖሩን የገለጹ ሲሆን ቅሬታ ያላቸው ሰዎች ቅሬታቸውን ከወረዳ ጀምሮ ባሉ መዋቅሮች ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ባሉ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ በወላጆች በተነሱት ቅሬታዎች ላይ በቢሮው የተያዘ አቅጣጫ እንዳለ የጠየቅናቸው አቶ አበበ 'ቅሬታ ያላቸው አካላት መዋቅሩን ተከትሎ ቢያቀርቡ መፍትሔ ያገኛሉ' ሲሉ ነው ምላሻቸውን የሰጡን፡፡

ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 524 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 44 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4,124 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 134 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 29 ከጉጂ
- 22 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 12 ከአሰላ ከተማ
- 12 ከምዕራብ ሀረርጌ
- 11 ከምስራቅ ሸዋ
- 11 ከምስረቅ ሀረርጌ
- 5 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 5 ከነቀምቴ ከተማ ይገኙበታል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 348 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት መካከል ፦
- 17 ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 5 ከአሶሳ ከተማ
- 5 ከባንቢስ ወረዳ
- 3 ከጉባ ወረዳ
- 3 ከዛይ (ያሶ) ወረዳ ይገኙበታል።
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 341 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 805 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,630 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 21 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 14 ከጎንደር ከተማ
- 5 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 4 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።

ባለፉት 24 ሰዓት የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ 1,186 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,060 የላብራቶሪ ምርመራ 1,186 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 518 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 46,407 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 745 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,829 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,060 የላብራቶሪ ምርመራ 1,186 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 518 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 46,407 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 745 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,829 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,681 የላብራቶሪ ምርመራ 88 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት ፦
- ከጎፋ 26 (መለኮዛ ወረዳ 16፣ ሳውላ ከተማ 6፣ ኡባ ደብረጸሀይ 4)፣
- ከጌዴኦ 21 (ዲላ 12፣ ወናጎ ወረዳ 5፣ ይረጋጨፌ 2፣ ገደብ 1 እና ቡሌ 1)፣
- ከአማሮ 10፣
- ከወላይታ 9 (ዳሞት ጋሌ 4፣ ኪንዶ ኮይሻ 2፣ ሻንቶ 2 እና ከቢጠና 1)፣
- ከጋሞ 6 (ቁጫ አልፋ 3፣ አርባምንጭ 2 እና ገረሴ 1)፣
- ከጉራጌ 6 (አበሸጌ 3 እና እንደጋኝ 3) ፣
- ከሸካ 6 (6ቱም ከማሻ ከተማ) ፣
- ከኮንሶ 2 (2ቱም ከካራት ከተማ)
- ከስልጤ 1(ሁልባረግ) ፣
- ከባስኬቶ 1 ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡
አጠቃላይ በደቡብ ፦
- 1,046 በቫይረሱ የተያዙ
- 9 ሞት
- 406 ያገገሙ
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 405 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 28 ከሀዋሳ ከተማ
- 4 ከማልጋ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 1,327 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 460 ያገገሙ
#Afar
በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 462 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 41 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ በአፋር ፦
- 883 በቫይረሱ የተያዙ
- 231 ያገገሙ

የ4 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አሳዛኙ አደጋ!
የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ዉኃ ከከባቸዉ መንደሮች ለማምለጥ የሞከሩ አራት የደቡብ ክልል ፤ የዳሰነች ወረዳ ነዋሪዎች ሞቱ።
የአካባቢዉ ባለስልጣናት ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንዳሳወቁት አራቱ ሰዎች በዉኃ የተበሉት ዉኃ ከከበባት ቶል-ታሌ ቀበሌ ወደ ደረቅ መሬት በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ጀልባቸዉ ተገልብጣ ነዉ።
ከሟቾቹ ሁለቱ እናት እና ልጅ ሁለቱ ደግሞ አዛዉንቶች ነበሩ።
በውኃ ተከበው የነበሩ ሌሎች 200 ነዋሪዎች ግን ከክልሉ በተላኩ ጀልባዎች ርዳታ ሙሉ በሙሉ ወደ ደረቅ አካባቢ መሻገራቸዉን ተሰምቷል።
የኦሞ ወንዝ ሙላት ከዳሳች ወረዳ አርባ (40) ቀበሌዎች መካከል 28ቱን አጥለቅልቋል። ከ15 ሺሕ በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅሏል።
የዉኃ ሙላቱ ከ30 ዓመት ወዲሕ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ ያሁኑ የመጀመሪያዉ መሆኑን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
PHOTO : FILE

'ፎሬይን ፖሊሲ' የተሰኘው መፅሄት ትላንት ምሽት እንደዘገበው የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ በከፊል እንድታቆም ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል ብሏል።
ይህም የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳንን በህዳሴ ግድብ ዙርያ ለማወያየት የጀመረው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ተቃውሞ ገጥሞት መቆሙን ተከትሎ የመጣ ነው ብሏል።
ፖምፔዎ ፍቃዳቸውን ያኖሩበት ይህ ውሳኔ በዚህ ሳምንት እንደተወሰነ መፅሄቱ ገልፆ በዚህም አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምታደርገው ድጋፍ ውስጥ 130 ሚልዮን ዶላሩን ልትቆርጥ አስባለች ብሏል።
ለፀጥታ እና ደህንነት ፣ ለፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ፣ ለወታደራዊ ስልጠና ፣ ለሰዎች ዝውውር ቁጥጥር እና ሌሎች ልማት ስራዎች የሚውሉ ድጋፎች ሊቋረጡ ከሚችሉት ውስጥ ተካተዋል ተብሏል።
በሌላ በኩል ዘገባው አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፎች እንዲሁም የጤና እርዳታዎች አይቋረጡም ብሎ የኮንግረስ ምንጮቹን ጠቅሶ ፅፏል።
https://foreignpolicy.com/2020/08/27/trump-africa-gerd-dam-us-halts-foreign-assistance-funding-ethiopia-over-dam-dispute-egypt-sudan/
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት (AP)

#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በበይነ መረብ (Virtual) ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ ያስቻላቸው የድህረ ምረቃ (ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎቹን ፣ እንዲሁም ከኮሮና ወረርሽኝ መከሰት በፊት ትምህርታቸውን አጠናቀው ምረቃቸው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ በወረርሽኙ ምክንያት የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ሳይካሄድ የቆዩትን በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና መደበኛ ያልሆኑ መርሃ-ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በበይነ መረብ (Virtual) ስነ-ስርዓት ያስመርቃል፡፡

የአሜሪካ የሥራ ሚኒስቴር እንደገለፀው ባለፈው ሳምንት 1ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፣ የሥራ እጥነት ድጎማ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ይህም የአሜሪካ አሰሪዎች ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፣ ሰራተኞችን ማስወጣት እንደቀጠሉ ያመለክተል ተብሏል።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፣ በየሳምንቱ የሥራ አጥነት ማመልከቻ የሚያስቡት ሰዎች ብዛት፣ አንድ ሚሊዮን ገደማ ይሆናል።
የቫይረሱ ወረርሽኝ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዳከሙ በፊት ከነበረው፣ በ200,000 ከሚገመት የሥራ አጥነት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ግን፣ የበዛ እንደሆነ ተገልጿል።
Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ይህም የአሜሪካ አሰሪዎች ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፣ ሰራተኞችን ማስወጣት እንደቀጠሉ ያመለክተል ተብሏል።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፣ በየሳምንቱ የሥራ አጥነት ማመልከቻ የሚያስቡት ሰዎች ብዛት፣ አንድ ሚሊዮን ገደማ ይሆናል።
የቫይረሱ ወረርሽኝ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዳከሙ በፊት ከነበረው፣ በ200,000 ከሚገመት የሥራ አጥነት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ግን፣ የበዛ እንደሆነ ተገልጿል።
Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ዳይክተሮች እና የስራ ክፍሎች ተወካዮች በተገኙበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2012 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም እቅድ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።