"ከ3,000 በላይ የሆኑ ዜጎች በለይቶ ማቆያ መንገድ አልፈዋል" - አቶ ሙልጌታ ተስፋዬ
(በአሐዱ ሬዲዮ)
በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ የትግራይ ክልል ከሁሉም አካባቢዎች በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የእንቅስቃሴ ገደብ እና ማሻሻያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ከነዚህም መካከል ወደ ክልሉ መግባት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆይ የሚያስገደደው መመሪያ አንዱ ነው፡፡
በዚህም ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት አገልግሎት መሰጠቱን የክልሉ ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ ለአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል፡፡
በትግራይ ክልል እስከአሁን አንድም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አለመገኝቱን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አጫጭር መረጃዎች ፦
- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 674 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26,771 ደርሷል።
- የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ከዳኑ በኋላ የመጀመሪያቸውን የሚኒስትሮች ስብሰባ የመሩ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል፤ አገራቸው የወረርሽኙን ጣሪያ ማለፏን ተናግረዋል - #BBC
- ደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች፤ አራቱም #ከውጭ የገቡ ናቸው።
- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 4 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን አራቱም (4) ከውጭ ከገቡ ናቸው።
- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ቀንሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ289 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል።
- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ62,000 በላይ ሆኗል።
- በአሜሪካ የሥራ አጦች ቁጥር 30 ሚሊየን መድረሱን የአሜሪካ የሰራተኞች መስሪያ ቤት ያወጣው አዲስ መረጃ አሳይቷል - #BBC
- በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 10,403 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 297 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 5,647 ደርሷል።
- በግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት 12 ሰዎች ሲሞቱ፣ 269 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 5,537 ደርሷል። ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,381 ደርሷል።

#COVID19
የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦
- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,089፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 642
- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 396፣ ሞት 17፣ ያገገሙ 144
- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 601፣ ሞት 28፣ ያገገሙ 31
- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 375፣ ሞት 28፣ ያገገሙ 32
- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 131፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 59
- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26
- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 35፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

አዋጁ የወጣው በምክንያት ነው!
(በዶክተር ያቤፅ ከበደ-የህብረተሰብ ጤና ባለሞያ)
ድብቅ ጦርነት የከፈተብንን የኮሮና ቫይረስ እንዴት እንዋጋ ? የባለሙያ ምክሮችን በአግባቡ መተግበር ስርጭቱን ይቀንሰዋል ? አዎ!
ከበዓሉ ወዲህ የሚታየው መዘናጋት እጅጉን እያሳሰበን ነው። የምርመራ ምህዳሩ ገና እየሰፋበት ባለበት ስዓት፤ ህብረተሰቡ እያሳየው ያለው መዘናጋት ወደ የማንወጣው ትግል ውስጥ ሊከተን ነው።
የእጅ ጓንትን ማድረግ ለህብረተሰቡ የተሳሳተ የደህነት ስሜትን በመስጠት ለበለጠ መዘናጋት ያጋልጣቸዋል ፤ በአብዛኛው የሚረዳው የጤና ባለሙያዎችን ሲሆን እዲሁም ስራቸው ከግብይት እና ልውውጥ ጋር ለተያያዘዙ የህብረተሰብ ክፍል ነው።
የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች ፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች እና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታ አለበት።
እነኚህን እና የእጅ ንፅህናን መጠበቅ ባጠቃላይ የእኛ ህዝብ ላለው የኑሮ መስተጋብር የቫይረሱን ስርጭት ይቀንሰዋል።
እባካቹህ ለራሳችሁ አስቡ፤ ለእኛም አስቡ!

በሱዳን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 442 ደርሰዋል!
(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)
የሱዳን ጤና ሚንስቴር ትላንት ምሽት በሰጠዉ መግለጫ ተጨማሪ 67 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 3 ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉንና 7 ሰዎች ማገገማቸዉን ገልጿል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች 59 ከካርቱም ግዛት መሆናቸዉ ተገልጿል።
በዚህ መሰረት በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 442 መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 31 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 39 ግለሰቦች ማጋገማቸዉን አስታዉቀዋል።
በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቫይረሱ እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ በመሆኑ በሱዳን የሚኖሩ ዜጎች ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ጥንቃቄ እያደረጉ ቤት ውስጥ በመቆየትና እርስ በእርስ በመረዳዳት ይህን አስከፊ ጊዜ እንዲያልፉ ጥሪ አቅርቧል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ !
(በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን)
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የእስካሁን አፈፃፀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እየገመገመ ነው፡፡
የኮሚቴውን ሪፖርት እያቀረቡ ያሉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት (133) ደርሷል፡፡

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 912 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ #ከኬንያ የተመለሰና #በሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላንትናው ዕለት ሰባት (7) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ስድስት (66) ደርሷል።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 18,754
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 912
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 2
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 62
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 7
• አጠቃላይ ያገገሙ - 66
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 133
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 18,754
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 912
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 2
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 62
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 7
• አጠቃላይ ያገገሙ - 66
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 133
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST
አንድ ታማሚ ከኮሮና ቫይረስ አገገመ የሚባለው መቼ ነው?
አንድ ታማሚ ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በሽታ ሙሉ ለሙሉ አገገመ የሚባለው ለሶስት (3) ተከታታይ ቀናት ምንም አይነት ምልክት ሳይኖረው ሲቆይ እና በሚደረግለት ሁለት ተከታታይ የላብራቶሪ ምርመራ ነጻ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
ምንጭ፦ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

#BBC
ጤና ሚኒስቴር ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ሐረርጌ ጉባ ኮሪቻ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ የጉዞ ታሪክ እንደሌለውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት እየተጣራ ነው ብሎ ነበር።
በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ኮሪቻ በኮቪድ-19 እንደተያዘ የተነገረው ወጣት፣ ስላለበት ሁኔታ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።
በአሁኑ ሰዓት በሂርና ሆስፒታል ለይቶ ማከሚያ ውስጥ የሚገኘው ወጣቱ፤ በሆስፒታሉ ውስጥ ከእርሱ ውጪ ሌላ የኮቪድ-19 ታማሚ እንደሌለ ገልጿል።
በምዕራብ ሐረርጌ ነዋሪ የሆነው ይህ ወጣት ጤና ሚኒስቴር የጉዞ ታሪክ የለውም ይበል እንጂ እርሱ ግን በጅቡቲ በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሄድ ሲሞክር ጅቡቲ ላይ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ ተናግሯል።
"ጅቡቲ ደሂል የምትባል ቦታ 11 ቀን ነው የቆየነው። ከዚያ ፖሊስ [የጅቡቲ] ይዞን ወደ ኢትዮጵያ መለሰን" ካለ በኋላ፣ እርሱና ጓደኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ለ12 ቀናት በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መቀመጣቸውን አስረድቷል።
የ14 ቀን የለይቶ ማቆያ ቆይታ በኋላ ወደ ጭሮ ከዚያም ቤተሰቦቹ ወዳሉበት ስፍራ እንዳቀና እና እዚያም ለ14 ቀናት እንደቆየ ተናግሯል። በጤና ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ዕድሜው 23 እንደሆነ ቢገለጽም እርሱ ግን "19 እንኳ አልሞላኝም"ብሏል።
እንዴት የኮቪድ-19 ምርመራ እንደተደረገለት የተጠየቀው ይህ ወጣት፣በጉባ ኮሪቻ 12 ቀናት ከቆየ በኋላ ከእርሱ ጋር አብሮ የነበረ ጓደኛው ስለታመመ ወደ ጭሮ እንዲመጣ በጤና ጽህፈት ቤት ሰዎች እንደተደወለለትና እንደተመለሰ ይናገራል። ጭሮ ከደረሰ በኋላ ናሙና ተወስዶ ሲመረመር ቫይረሱ እንዳለበት እንደተነገረው ገልጿል።
MORE:https://telegra.ph/BBC-05-01

#MutahiKagwe
በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 411 ደረሱ!
ባለፉት 24 ሰዓት 1,434 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አስራ አምስት (15) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 411 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ ስድስት ሰዎች ከኮቪድ-19 ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች አንድ መቶ ሃምሳ (150) መድረሳቸው ተገልጿል።

በጅቡቲ ያገገሙ ሰዎች 672 ደረሱ!
ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 30 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 672 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል 329 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 1,097 ደርሰዋል።

- በሩሲያ በ24 ሰዓት ውስጥ 7,933 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ቁጥሩ እስካሁን ሪፖርት ከተደረጉት የአንድ ኬዞች ከፍተኛው ነው። በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 114,431 ደርሰዋል።
- በደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ስምንቱ (8) ከውጭ የገቡ ናቸው።
- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 63 ሰዎች ሲሞቱ 1,006 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በUAE በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ13,000 በልጧል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 557 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል (እስካሁን በአንድ ቀን ሪፖርት ከተደረገው ከፍተኛው ነው)
- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት የ281 ሰዎች ሞት ሲመዘገበ 1,781 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።
- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ስድስቱ (6) ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው።
- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ከቻይና ቤተ ሙከራ መውጣቱን የሚያመለክት ማስረጃ መመልከታቸውን በመግለጽ የአገራቸው የደኅንነት ተቋማት ከሚሉት ጋር ተቃርነዋል። ቀደም ሲል የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንት መስሪያ ቤት ዳይሬክትር ጽህፈት ቤት የወረርሽኙ ቫይረስ ከወዴት እንደመጣ ገና ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጾ ነበር - #BBC
- ህንድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የጣለችውን የእንቅስቃሴ ገደብ ከሚያዚያ 26 በኃላ በሁለት ሳምንት ልታራዝም እንደሆነ ተሰምቷል።

#EPHI
ኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከመጋቢት 03 ቀን 2012 ዓ.ም ይፋ ከተደረገበት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በኮሮና ቫይረስ መታመማቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 2,516 ሰዎች ተለይተዋል ሲል የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ገለጸ።
ከእነዚህ መካከል 1,953 ሰዎች ክትትላቸውን አጠናቅቀው ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆን፣ 521 ሰዎች ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ ብሏል።
በሀገራችን እስካሁን በቫይረሱ መታመማቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ውስጥ 42ቱ (31%) የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች መሆናቸው ተረጋግጧል ሲል ገልጿል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከ300 በላይ ለሚሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት (የማስፈጠር) ፕሮግራም አካሄደ!
የረመዳን ፆመን በማስመልክት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ቤተሰቦችን ማዕድ የማጋራት (የማስፈጠር) ፕሮግራም ከአስሊ መንዲ ሬስቶራንትና ከተባበሩት አረብ ሃገራት ኢሚሬት (UAE) ጋር በመተባባር በዛሬዉ ዕለት አካሂዷል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ እና የተባበሩት አረብ ሃገራት ኢሚሬት የኢትዮጵያ ምክትል ክቡር አምባሳደር አቶ ሳውድ አልቴናጂ አማካኝነት ተይዘው የሚወሰዱ ምግቦችን (take away)ና ለአንድ ወር ያህል የሚሆኑ አስቤዛዎችን በመያዝ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ባለው ጃዕፋርና ኮልፌ የሚገኘው ቢላል መስጂዶች ለሚኖሩ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ300 በላይ ለሚሆኑ ህብርትስብ ክፍሎች ምግብ በማደል ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

#FilsanAbdullahi
"የማህበራዊ ሃላፊነት በሁሉም ተቋማት እንዲጎለብት በማድረግ ፤ እንዲሁም ባለሃብቶች መሰል ድጋፎችን ማድረግ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዋነኛ ሃላፊነት አድርገው መንቀሳቀሰስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ህብረተሰቡ በግለሰብ ደረጃ ጎሮቤት ጎሮቤቱን በማስታወስና በመደገፍ የቆየ እሴቱን ማጎልበት ይኖርበታል፡፡ ይህን ማድርግ ከቻልን ይህ አስቸጋሪ ወቅት ማንንም የከፋ ችግር ላይ ሳይጥል ልንሻገረው እንችላለን፡፡ የተባበሩት አረብ ሃገራት ኢሚሬትና አስሊ መንዲ ሬስቶራንት ላደረጉልን ድጋፋና ቀና ምላሽ እናመሰግናለን!" - ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ

ጣልያን የሟቾች ቁጥር ከትላንት ቀንሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ269 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል፤ 1,965 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ።
በነገራችን ላይ በጣልያን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ ዛሬ ለስድስተኛ ጊዜ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር በቫይረሱ ከተያዙት በልጦ ተመዝግቧል።

በደ/ብ/ብ/ህ/ ክልል አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ!
(የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ)
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ ነዋሪነቱ በከምባታ ጠምባሮ ዞን የነበረ የ25 አመት ዕድሜ ያለውና #ከኬንያ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሀላባ ዞን ለይቶ ማከሚያ ውስጥ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ)
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ ነዋሪነቱ በከምባታ ጠምባሮ ዞን የነበረ የ25 አመት ዕድሜ ያለውና #ከኬንያ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሀላባ ዞን ለይቶ ማከሚያ ውስጥ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር የተላለፈ መልዕክት ፦
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ (1) ሰው መገኘቱን ገልጿል። የክልሉ ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው ግለሰቡ ነዋሪነቱ በከምባታ ጠምባሮ ዞን የነበረ የ25 አመት ዕድሜ ያለው ወጣት ሲሆን ምርመራ በተደረገለት ወቅት ከኬንያ የመጣ ስለመሆኑም አስረድቷል።
ግለሰቡ በአሁኑ ሰዓት በሃላባ ዞን ለይቶ ማከሚያ ውስጥ ሕክምና በመከታተል ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ቢሮው አስታውቋል። ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሌሎች ግለሰቦች ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ስለመሆኑም ቢሮው በመግለጫው አመልክቷል።
ስለሆነም መላው የዞናችን ሕዝብ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ካጋጠሟቸው ያለምንም ድንጋጤ በተረጋጋ ሁኔታ ለሚመለከተው የጤና ባለሙያ እንዲጠቁሙ እና ከዚህ አስከፊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ራሳቸውን እና ኅብረተሰቡን እንዲከላከሉ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል።

#DrAdeyTsegaye #DrTsionFirew
የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በኢትዮጵያ እንዳይስፋፋ በማማከር ላይ የሚገኘው የዳያስፖራ የጤና ተመራማሪዎች አማካሪ ካውንስል የኮሮና ቫይረስን በከፍተኛ ሁኔታ በዋናው ቦታ-በኒውዮርክ ከተማ በመፋለም ላይ ለሚገኙ 2 ወጣት ሃኪሞች ምስጋና አቀረበ።
ካውንስሉ በ6ኛው ቨርቹዋል ሳምንታዊ ስብሰባው ላይ ለተገኙት ለድንገተኛ ክፍል ሃኪም ለዶ/ር ጽዮን ፍሬው (በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ህመም አገግማ ወደ ስራ የተመለሱ) እና ለጽኑ ህሙማን ክፍል ሃኪም ለዶ/ር አደይ (የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ልጅ) ለራሳቸው ሳይሳሱ እያደረጉ ላሉት አስተዋጽኦ ያለውን ከፍተኛ አድናቆት አቅርቧል።
ሁለቱም ወጣት ሀኪሞች በቅርቡ ታዋቂው The Wall Street Journal' ጋዜጣ ላይ ምሳሌ ስለመሆናቸው (Apr 7 & 14) ተዘግቧል።
(አምባሳደር ፍፁም አረጋ)