TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrYaredAgidew

ዶክተር ያሬድ አግደው ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውና የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ህክምና በሚሰጥበት ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስራ መጀመራቸውን አሳውቀዋል። ዶክተሩ ለሁሉም መልካም ዕድል ተመኝተዋል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EkaKotebeHospital

የኮሮና ቫይረስን በማከም ስራ ላይ ለተሰማሩ ሃኪሞችና ባለሙያዎች ከከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች የማርና በግ ስጦታ ተበረከተላቸው።

የከፋ ዞን አስተዳደርና የአገር ሽማግሌዎች በአዲስ አበባ ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው የኮሮናቫይረስን በማከም ስራ ለተጠመዱ ባለሙያዎች ግምቱ ከ100 ሺህ ብር በላይ የሆነ የማርና በግ ስጦታ ዛሬ አበርክተዋል።

የከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች ተወካይ አቶ አድማሱ አቱሞ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ሀኪሞችና ባለሙያዎች እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ሳይሳሱ ለኅብረሰተባቸው እያዋሉ ነው።

''በዚህ አበርክቷቸውም ፈጣሪ ከጎናቸው እንዲሆን እንመኛለን፣ ለሞራል እንዲሆናቸው የበረከት ምሳሌ የሆኑትን የማርና በግ ስጦታ አበርክተናል'' ብለዋል።

ሀኪሞችና ባለሙያዎች ጥረታቸው ለፍሬ በቅቶ ታማሚዎች አገግመው ለቤታቸው እንዲበቁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EkaKotebeHospital የኮሮና ቫይረስን በማከም ስራ ላይ ለተሰማሩ ሃኪሞችና ባለሙያዎች ከከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች የማርና በግ ስጦታ ተበረከተላቸው። የከፋ ዞን አስተዳደርና የአገር ሽማግሌዎች በአዲስ አበባ ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው የኮሮናቫይረስን በማከም ስራ ለተጠመዱ ባለሙያዎች ግምቱ ከ100 ሺህ ብር በላይ የሆነ የማርና በግ ስጦታ ዛሬ አበርክተዋል። የከፋ ዞን የአገር…
#DrDerejeDuguma #DrYaredAgidew

የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ከከፋ ዞን አባቶች፣ ወጣቶችና የዞኑ አስተዳደር ስለቀረበላቸው ስጦታና መልካም ምኞት ምስጋና አቅርበዋል።

"እኛም ለእናንተ መልዕክት አለን" ያሉት ዶክተር ያሬድ፤ ''ለእኛ ያላችሁን ፍቅርና አክብሮት ራሳችሁን ከወረርሽኙ በመጠበቅ ልታሳዩን ይገባል'' ብለዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በበኩላቸው ''የከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች ወረርሽኙን ለመከላከል ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎችም አካባቢዎች አርዓያ የሚሆን ነው'' ብለዋል።

ከእነዚህ የከፋ ዞን ደግ አድራጊዎች በመማር በሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች ያሉትም ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኅብረተሰቡ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግም ባለፈ ራሱን ከአካላዊ ንክኪ በመጠበቅ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በደቡብ ሱዳን በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አስር (10) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 45 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 739 ሰዎች ሲሞቱ 6,201 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ65,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በኳታር በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ14,000 በለጧል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 687 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በአይርላንድ የእንቅስቃሴ ገደብ በሁለት ሳምንት ተራዝሟል፤ እስከ መስከረ ድረስ ትምህርት ቤቶች አይከፈቱም ተብሏል።

- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት 218 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። ይህ የሟቾች ቁጥር ከየካቲት መጨረሻ በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛ ቁጥር ነው።

- በሩዋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 249 ደረሰ። ባለፉት 24 ሰዓት 6 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሌላ በኩል ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 109 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,097፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 672

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 411፣ ሞት 17፣ ያገገሙ 150

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 601፣ ሞት 28፣ ያገገሙ 31

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 442፣ ሞት 31፣ ያገገሙ 39

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 133፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 66

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 45፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 912 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ #ከኬንያ የተመለሰና #በሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። ታማሚ 2…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዙ ስለተረጋገጠው የ25 ዓመት ወጣት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አጥናው ካውዛ ፦

- በደቡብ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው ወጣት በዛሬው ዕለት በጤና ሚኒስቴር መገለጫ የተገለፀው ሁለተኛው ታማሚ ነው።

- ወደ ሱማሌ ክልል ናሙና ተልኮ ምርመራ ተደርጎ የናሙናው ውጤት ሳይጠናቀቅ ሰዎቹ ከሞያሌ ወደ ደቡብ ክልል እንዲንቀሳቀሱ ነው የተደረገው።

- ቫይረሱ እንዳለበት የተረጋገጠው የ25 ዓመት ወጣት የከምባታ ጠምባሮ ዞን ነዋሪ ነው፤ ከኬንያ ነው የተመለሰው፤ ወጣቱ ትላንት ለሊት ወደ 11:30 #ሀዋሳ ገብቶ ነበር። 11:45 በሌላ መኪና ወደ ሀላባ ሄዷል፤ በኃላም በጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ክትትል ተደርጎበት #ሀላባ ላይ ተይዟል።

- ከወጣቱ ጋር ወደ ሀላባ በአንድ መኪና የሄዱ ሰዎች በሙሉ ተለይተው ተይዘዋል። ሌሎች ከእሱ ጋር አብረውት ከሞያሌ የመጡም የተወሰኑ ሰዎች ተለይተው ተይዘዋል። አሁንም ቀሪ የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
'ሞተዋል' እየተባለ ሲነገር የከረመው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በህዝባዊ መድረክ ላይ ታዩ!

(አሐዱ ቴሌቪዥን,KCNA,YONHAP)

የመሞታቸው ጉዳይ በርካቶችን ሲያጠራጥር የሰነበተው የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከ21 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ መድረክ የሚታዩበትን ምስል የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አስተላልፏል።

ኪም ጆንግ ኡን ከፒዮንግያንግ በስተሰሜን 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የተገነባው 'ሰንቾን የማዳበርያ ፋብሪካ' የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ሪቫን ሲቆርጡ ታይተዋል። በስነ ስርዓቱ ላይ እህታቸው ኪም ዮ ጆንግም ተገኝተው ነበር ተብሏል።

የ36 ዓመቱ መሪ የልብ ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ተከትሎ በጠና ታመዋል የተባለው መረጃ ሐሰት ነው ሲል የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንታዊ ጽሕፈት ቤት ማስተባበሉ ይታወሳል።

ወጣቱ መሪ ቀርተው የማያውቁበት የአያታቸው የልደት በዓልን አለመታደማቸው በጠና ታመዋል የሚለው መረጃ እንዲበረታ ማድረጉን ነው የቢቢሲ ዘገባ የጠቆመው።

በተመሳሳይ አገሪቱ ያደረገችው የሚሳኤል ሙከራ ላይ አለመገኘታቸው ሌላው የመታመማቸውን ጥርጣሬ ያበረታ ጉዳይ ነበር። ኪም ጆንግ ኡን ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ከ21 ቀናት በፊት የፖለቲካ ጉባኤን እየመሩ ነበር።

@tikvahmagBot @tikvahethmagazine
በሱዳን በአንድ ቀን ብቻ 91 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸዉ ተረጋገጠ !

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ትናንት በሰጠዉ መግለጫ ተጨማሪ 91 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።

በዚህ መሰረት ባጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት በሀገሪቱ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በ14 ግዛቶች 533 መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 36 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 46 ግለሰቦች ማጋገማቸዉን አስታዉቀዋል።

የጤና ሚንስቴር ዜጎች እራሳቸውን ከቫይረሱ ለመከላከል በጤና ሚንስቴር የሚወጡ መመሪያዎችን መተግበር ይጠበቅባችኋል ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሀገራችን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 2,016 የላቦራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች #አለመኖራቸው ተረጋግጧል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DrLiaTadesse

በሀገራችን ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች 69 ደረሱ!

በትላንትናው ዕለት ሶስት (3) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ዘጠኝ (69) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 20,770
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 2,016
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 0
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 59
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 3
• አጠቃላይ ያገገሙ - 69
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 133

#DrLiaTadesse #MoHEthiopia #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#correction

በዛሬው መግለጫ ላይ ጠቅላላ የተደረገ ላቦራቶሪ ምርመራ ቁጥር 19,857 ሳይሆን 20,770 መሆኑን ከይቅርታ ጋር ለማሳወቅ እንወዳለን - #EPHI

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#RUSSIA

ሩሲያ በአንድ ቀን ብቻ 9,623 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ። አብዛኞቹ በዋና ከተማዋ #ሞስኮ የሚኖሩ ናቸው። ይህ ቁጥር ወረርሽኙ ሩሲያ ከደረሰ በኋላ ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 57 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በመላ አገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,222 ማሻቀቡን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል።

የሞስኮ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሰርጌይ ሶብያኒን የከተማው ነዋሪዎች ራሳቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ለይተው እንዲያቆዩ ተማፅነዋል።

በኮሮና ቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው እጅግ የከፋ ደረጃ አለመድረሱን ገልጸዋል። ሁኔታው ከከፋ በሞስኮ ከተማ ለመንቀሳቀስ የሚሰጥ ፈቃድ ሊቀነስ እንደሚችልም ከንቲባው ገልጸዋል።

በሞስኮ ከተማ ነዋሪዎች ከመንግሥት ልዩ ፈቃድ ካላገኙ በቀር ከቤታቸው መውጣት የሚችሉት ዕቃ ለመሸመት፣ ውሾቻቸውን ለማንሸራሸር እና ቆሻሻ ለመጣል ብቻ ነው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopi
#EGYPT

በግብፅ በትላንትናው ዕለት 358 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መያዛቸውን #egypttoday ዘግቧል፡፡ ይህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 5 ሺህ 895 አድርሶታል፡፡

የጤና ሚንስቴር ቃል አቀባይ ካሊድ መጋህድ እንደገለጹት በ24 ሰዓታቱ 14 ታማሚዎች ሕይወት አልፏል ፤ ይህም በግብፅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱትን ሰዎች ቁጥር 406 አድርሶታል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ 79 ሰዎች ማገገማቸውና ከሆስፒታል መውጣታቸው ነው የተነገረው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,112 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 105 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በሌላ በኩል ትላንት 14 ተጨማሪ ሰዎች ከኮቪድ-19 ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 686 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia