TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ከደቂቃዎች በፊት ደቡብ ሱዳን ተጨማሪ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙን አሳውቃለች!

ባለፉት 24 ሰዓት 100 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ዩናይትድ ኪንግደም /UK/ የ4,419 ሰዎችን ሞት ሪፖርት አድርጋለች፤ ዛሬ ሪፖርት ከተደረገው ውስጥ 765 ሰዎች (ባለፉት 24 ሰዓት) በሆስፒታል የሞቱ ናቸው። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26,097 ደርሷል። UK ከአሜሪካና ከጣልያን ቀጥላ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የሞተባት ሀገር ሆና ተመዝግባለች።

- በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ወደ ሆስፒታል ካቀኑ የዩናይትድ ኪንግደም ህመምተኞች መካከል አንድ ሶስተኛው መሞታቸውን አንድ ጥናት ይፋ አድርጓል - #BBC

- ደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች፤ አምስቱ (5) ከውጭ የገቡ ናቸው። ሀገሪቱ ከ15 በታች ኬዝ ስታስመዘግብ 11ኛ ቀኗ ነው።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ከትላንት ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ427 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል።

- የጁቬንቱሱ አጥቂ ፓውሎ ዲባላ በ6 ሳምንታት ውስጥ ለ4ኛ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ #ፖዘቲቭ ሆኖ ተገኝቷል።

- የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት 4.8 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። እአአ 2014 ላይ ከታየው ውድቀት ወዲህ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። ዛሬ የወጣ አሀዝ እንደሚያሳየው፤ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሥራ አጥ ሆነዋል። በአሜሪካ ታሪክ ንግድ የተቀዛቀዘበት ወቅት መሆኑም ተመልክቷል። የአገሪቱ እድገት 30 በመቶ ወይም ከዛ በላይም ሊገታ እንደሚችል ተገምቷል - #BBC

- በሩዋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 225 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 13 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሌላ በኩል 3 ሰዎች አገግመዋል፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 98 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቁጥሮች ሊያዘናጉን አይገባም!

(በዶክተር መክብብ ካሳ)

ለኮቪድ-19 ክትባት የመስራቱ ሂደት ከተሳካ በብዛት አምርቶ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ወራትን ይወስዳል፡፡ ስለዚህ አሁን ያለን ብቸኛው አማራጭ በቫይረሱ እንዳንያዝ ጥንቃቄ ማድረግ ነወ፡፡

በቫይረሱ የተያዘ አንድ ግለሰብ ከ 4 እስከ 6 ለሚሆኑ ሰዎች ሊያስተላልፍ እንደሚችል አዲስ የተደረገ ጥናት ያሳያል፡፡ ይህም ቀድሞ ይታሰብ ከነበረው እጅጉን ከፍ ያለ ነው፡፡

ከቀናት በፊት በእንግሊዝ በተደረገ ጥናት ህዝቡ ቤት በመቆየቱ አንድ ሰው ወደ ሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ ምጣኔ ወደ 1 ወርዷል፡፡ የግድ ካልሆነ ከቤት አንውጣ፡፡

በቫይረሱ ተይዘን በጣም ቀለለ ቢባል በአማካይ ሁለት ሳምንታት ህመም ላይ ያቆየናል፡፡ ከበድ ሲል ደግሞ ለወራት ጤና ተቋማት ውስጥ እንድንቆይ ከዚያም አልፍ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ጥናት እንዳሳየው ከሀያ ህሙማን አንዱ የፅኑ ህሙማን ክፍል ህክምና ያስፈልገዋል፡፡ ይህን እንደቀላል አንመልከተው!

የምናደርጋቸው ጥንቃቄዎች በየቀኑ ከምንሰማቸው ቁጥራዊ መረጃዎች ጋር አናያይዛቸው፡፡ ሁልጊዜም ጥንቃቄ አይለየን፡፡

አንሰላች! አንዘናጋ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኮቪድ-19 ውጪ ያሉ ሌሎች ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎችን በ @tikvahethmagazine ላይ ታገኛላችሁ!

ትክክለኛው የTIKVAH-MAGAZINE የቤተሰብ አባላት ቁጥር ከ179,000 በላይ ነው፤ በሀሰተኛ ገፆች እንዳትታለሉ!

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tikvahethmagazine
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,408 ላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 131 ደርሷል።

የታማሚ ዝርዝር ሁኔታ ፦

የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊት የባህር ዳር ነዋሪ፤ የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት ናት።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ዘጠኝ (59) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በየመን የኮቪድ-19 ሞት ተመዘገበ!

(በቢቢሲ የቀረበ)

በየመን በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። ሁለቱ ሟቾች ወንድማማቾች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በደቡባዊ ኤደን ሆስፒታል ውስት መሞታቸው ተሰምቷል። መንግሥት በስፍራው አምስት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸውን ገልጿል።

ከአምስት (5) ዓመታት በላይ የተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት የየመንን የጤና ስርዓት ያደቀቀው ሲሆን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመዋጋት ምንም ዝግጅት አለመደረጉም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚልዮን በልጧል - #WorldoMeters

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 268 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከመጋቢት 11 በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 17,842
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,408
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 1
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 67
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 59
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 131

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው!

(በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት)

በኢትዮጵያ ከመጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 131 ሰዎች ውስጥ 69 (53%) ሰዎች በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ከነበሩ መንገደኞች ውስጥ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በአየር እና በየብስ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ማንኛውም መንገደኛ ለ 14 ቀናት በተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ የሚቆዩና ጊዜያቸውንም ሲያጠናቅቁ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ እየተደረገላቸው እንዲወጡ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልል ከሚገኙ የለይቶ ማቆያ ቦታዎች በተገኘው መረጃ መሰረት ከ16,000 በላይ ከውጭ ሀገር ተመላሾች ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡ ሲሆን የ14 ቀን ቆይታ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከኮሮና ቫይረስ ነጻ የሆኑ 5,342 ሰዎች ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2 የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች ኮቪድ-19 ተገኘባቸው!

(በሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

በጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ድንገተኛ ምርመራ የተደረገላቸው የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው ሁለት (2) ቻይናዊያን ሲሆኑ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሹፌሮች ናቸው።

ከሁለቱ (2) ቻይናዊያን ጋር በስራቸው ምክንያት ቅርበት ያላቸው 35 የምድር ባቡሩ ሰራተኞች ተለይተው የምርመራ ናሙና ተወስዶላቸዋል።

የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ጥላሁን ሳርካ ለሸገር ኤፍ ኤም እንደተናገሩት 'የናሙና ውጤቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ይደርሳል ብለን እየጠበቅን ነው' ብለዋል።

ወደ ጅቡቲ ባቡር እየዘወሩ የሚሄዱ ሰራተኞች ደርሰው ሲመለሱ 'ከሙቀት መለኪያ' በስተቀር ተጨማሪ ምርመራ አካሂደው እንደማያውቁ ኢንጂነር ጥላሁን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 15 ሰዎች ማገገማቸው ተገልጿል፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 144 ደርሷል።

እንዲሁም 777 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 396 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በኬንያ የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ያገገሙ ሰዎች 642 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 43 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 642 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል 437 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 1,089 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኢራን ከ40 ቀን በኃላ ዝቅተኛውን የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች ፤ ባለፉት 24 ሰዓት 983 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 94,640 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 601 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 601 ደርሷል።

በሌላ በኩል አስራ አንድ (11) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 31 ደርሰዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የሰው ህይወት አላለፈም፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሀያ ስምንት (28) ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
ኮሮና ቫይረስና አጭበርባሪዎች!

ከዚህ ቀደም በስልክ እየደወሉ አይን ያወጣ የማጭበርበር ስራን እየሰሩ ያሉ ግለሰቦች እንዳሉ አሳውቀን ነበር።

እኚህ ግለሰቦች የተለያዩ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በመጠቀም በተለያዩ ስልኮች ላይ እየደወሉ የማጭበርበር ስራ እየሰሩ እንደሆነ በተደጋጋሚ ጠቁመናል።

አሁን ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ 'ከሬድዮ ነው የምንደውለው የ85,000 ብር ሽልማት ከቢጄአይ ጋር በመተባበር ሽልማት አዘጋችተናል፤ ቅድሚያ 950 ብር ላኩ' በማለት በውሸት ሕዝቡን እያታለሉ ይገኛሉ።

በመሆኑ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከእንደዚህ አይነት አጭበርባሪዎች እና በዚህ የጭንቅ ወቅት ህዝብን አታለሉ ገንዘብ ለማግኘት ከሚሯሯጡ ግለሰቦች እራሳችሁ ጠብቁ።

#Tsi
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን በአንድ ቀን 4,693 ሰዎች አገገሙ!

በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4,693 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ማገገማቸው ሪፖርት ተደረገ። በሌላ መረጃ የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ቀንሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ285 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። በተጨማሪ 1,872 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሩሲያው ጠ/ሚ በኮቪድ-19 ተያዙ!

የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሃይል ሚሹስቲን በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ማያዛቸውን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጊዜው ስራቸውን አቁመው እራሳቸውን አግልለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሃል ሚሹስቲን ከበሽታው አገግመው ወደ ስራቸው እስኪመለሱ ድረስ ምክትላቸው አንድሬ ቡሎሶቭ ተክተዋቸው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia