TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኤርትራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 31 ደረሱ!

ዛሬ በኤርትራ ለ14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 31 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ወቅታዊውን የኮሮና ወረርሽኝን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን ለአንድ ወር የሚቆይ ሀገራዊ የጸሎት ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

በአሁን ሰዓት ከአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት አባቶች ሀገር አቀፍ የጸሎት እና የምህላ ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት እያካሄዱ ይገኛሉ። በስርነ ስርዓቱ ላይ የሀገር መሪዎች እና የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ስነስርዓቱን በEBC, FANA, Addis Tv, Walta በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ። ሁሉም በያለበት እንደየእምነቱ ፈጣሪ ይራራልን ዘንድ ልመናውን ያቅርብ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TAXIYE

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመጋታ ታክሲዬ ሞተረኞቹን በነፃ ለጤና ቢሮ እና ለሆስፒታሎች የመልዕክት አገልግሎት እንደሚሰጡና ለዚህም አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክቱ ገልጿል።

ድርጅቱ ለሞተረኞቹ ስለ ሰራው አስፈላጊነት እና አጠቃላይ አሰራሮች እንዲሁም ራሳቸውን እና የሚያገለግሉትን ህብረተሰብ ከኮሮና ቫይረስ ስለሚከላከሉበት መንገድ በቂ ግንዛቤ በህክምና ባለሞያዎች እንደተሰጣቸውም ነው ያስታወቀው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ የፃፉት በማስመሰል በፎቶሾፕ የተቀነባበረ 'የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳረፉ' ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያው እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በፈረንሳይና አሜሪካ ወረርሽኙ እየከፋ ነው!

- የኮሮና ቫይረስ ሪፖርት ከተደረገ ወዲህ በፈረንሳይ በአንድ ቀን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዝግቧል። በፈረንሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 833 ሰዎች ሞተዋል። በአጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችም 8,911 ደርሰዋል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም ከ10,000 መብለጡን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ይፋ አድርጓል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 355,000 በላይ ሆኗል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ወደፅኑ ህሙማን ክፍል ገቡ!

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ወደ ሆስፒታል ከገቡ በኃላ የህመማቸው ሁኔታ ስለጠነከረባቸው ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል እንደገቡ ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1, BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይታጠቡ

👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ

🙅🏽‍♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ይቀንሱ

አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አይውጡ

🚶‍♀_____🚶አካላዊ ርቀቶትን በእጅጉ ይጠብቁ

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia #HaimG
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrTedrosAdhanomGhebreyesus

በሁለት (2) የፈረንሳይ ተመራማሪ ሐኪሞች የተሰጠውን የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት የሚል ሃሳብ የዓለም ጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር " ዘረኛ" ሲሉ ተችተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም " አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም" ብለዋል።

የሕክምና ባለሙያዎቹ ክትባቱ መሞከር ስላለበት ጉዳይ አስተያየት የሰጡት በቴሌቪዥን ይካሄድ በነበረ የቀጥታ ክርክር ወቅት ነው። ይህ የሐኪሞቹ አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አፍሪካውያንንን " መሞከሪያ አይጥ" አድርጎ ማሰብ ነው ብሏቸዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለኮሮና ቫይረስ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ መናደዳቸው ተስተውሏል። ከዚያም "የቅኝ ግዛት አብሾ" አልለቀቃቸውም ሲሉ መልሰዋል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከሳይንቲስት እንዲህ አይነት አስተያየት መስማት የተዋረደ፣ አሳፋሪ ነው።

እንዲህ ዓይነት ነገርን በማንኛውም ሁኔታ እናወግዛለን። እናም የማረጋግጥላችሁ ነገር ይህ በጭራሽ አይሆንም" ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሴኔጋል 10 ተጨማሪ ሰዎች ከቫይረሱ አገገሙ!

በሴኔጋል 10 ሰዎች ማገገማቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም 92 ደርሰዋል። እስከትላንትናው ዕለት መጋቢት 28/2012 ዓ/ም ድረስ በሴኔጋል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 226 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በDRC በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 180 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጨማሪ 19 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ተመዝግቧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 180 ደርሰዋል። ከአስራ ዘጠኙ (19) አዲስ ኬዞች 18 ከኪንሳሻ ሲሆን አንደኛው ከቦካቩ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጣቸውን የኦፕሬሽን አገልግሎቶች የማያቋረጥ መሆኑን ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ገልጿል።

በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ምክንያት ከወትሮ በተለየ በየአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቹ በአገልግሎት ፈላጊ ደንበኞች ቀጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።

በአብዛኛው ክልሎችና በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በተደረገው ምልከታ በተለይ የቅድመ ክፍያ ካርድ ለማስሞላት በርካታ ደንበኞች በየቀኑ ረጅም ሰልፎች ተሰልፈው መመልከቱን አስታውቋል።

አብዛኛው ደንበኞች የቅድመ ክፍያ ቆጣሪያቸው ሂሳብ እያለውም ተቋሙ አገልግሎት ሊያቋርጥ ይችላል በሚል ፍርሃት ቀድመው ለመሙላት እየተሰለፉ እንደሚገኙም ነው ያስታወቀው።

ይህ ደግሞ አሁን ከተከሰተው ወረርሽኝ አኳያ መሰል ሰልፎች ለበሽታው የሚያጋልጥ መሆኑ መገንዘብ እንደሚያስፈልግም አስታውቋል።

በመሆኑም የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንኞቹ የካርድ መሙላትን ጨምሮ ሌሎች የኦፐሬሽን ሥራዎች የማያቋረጥ መሆኑን በመገንዘብ በሚቀርባቸውና ወረፋ በሌላቸው ማዕከላትና እንዲገለገሉ አስገንዝቧል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስት ኮሮፖሬት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GAMBELA

በጋምቤላ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠርና ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ለ81 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

ይቅርታ የተደረገላቸው በቀላል ወንጀል እስከ ሶስት ዓመት ተፈርዶባቸው ያሉና በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በአመክሮ እስከ አንድ ዓመት የቀራቸው መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ ክልል ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጋላጭ የሆኑ 1,601 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ አድርጓል።

በይቅርታ የተለቀቁት ታራሚዎች አንድ ሶስተኛውን የማረሚያ ቤት ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ፣ መልካም ስነምግባር ያሳዩ እና ለይቅርታው ብቁ በመሆናቸው የተለዩ ናቸው።

ምንጭ፦ የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሩዋንዳ ዘር ማጥፋት 26ኛ ዓመት መታሰቢያ!

ከዛሬ ሀያ ስድስት ዓመት በፊት ሩዋንዳ እጅግ አስከፊውን የሰው ልጆች የዘር ጭፍጨፋ አስተናግዳለች። ዛሬ ሁሉም ነገር አልፎ በዘር ጭፍጨፋው የረገፉትን ዜጎች እያሰበች ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BackToWork

በቻይና ህይወት ወደመደበኛው ሁኔታ እየተመለሰ ይገኛል። ዛሬ ከባለፉት ቀናት እጅግ በተሻለ መልኩ በተለያዩ ከተሞች እንቅስቃሴዎች ጨምረዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቻይና ዴይሊ ያጋራቸው ምስሎችም ይህንኑ የሚጠቁሙ ናቸው።

ሀገሪቷ ከወራት በኋላ በትላንትናው ዕለት አዲስ ሞት እንዳልተመዘገበ አሳውቃለች፤ 'አንዳንድ አካላት አሁንም ከሀገሪቱ የሚወጡ ሪፖርቶች ላይ እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው።

የቻይና ዜጎች ከከተማ እንዲወጡ እንዲሁም እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዷል ፤ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ የቱሪስት መዳረሻዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

ከሶስት ሺ በላይ ዜጎቿን የተነጠቀችው ቻይና በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷልም ብላለች።

ምንጭ፦ ቻይና ዴይሊ፣ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሊቢያ የመጀመሪያው ሰው ከቫይረሱ አገገመ!

አንድ (1) ሞትና አስራ ዘጠኝ (19) በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡባት #ሊቢያ በትላንትናው ዕለት የመጀመሪያውን ከኮሮና ቫይረስ ያገገመ ሰው ሪፖርት አድርጋለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ አንድ የ9 ወር ህጻንን ጨምሮ ተጨማሪ ስምንት (8) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 264 ሰዎች ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ የዘጠኝ (9) ወር ህጻን የተያዘ ሲሆን እናቱም ቫይረሱ ተገኝቶባታል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል አንዱ ኤርትራዊ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 52 አድርሶታል ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia