TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ58 ቀናት በኃላ የቻይና 'ቤጂንግ የእንስሳት መጎብኛ (ዙ)' ዛሬ በይፋ ለህዝብ ተከፍቷል። ጎብኚዎች የእንስሳት መጎብኛውን ከመጎብኘታቸው አንድ ቀን በፊት ትኬታቸውን በኦንላይ መግዛት እንደሚችሉም ተነግሯል።

#BackToWork #ChinaDaily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሁቤይ ግዛት ከውሃን ቀጥላ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ የተጎዳችው #Xiaogan ከተማ ሰዎች ወደቀደመው ህይወታቸው እየተመልሱ ነው።

#BackToWork
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BackToWork

በቻይና ህይወት ወደመደበኛው ሁኔታ እየተመለሰ ይገኛል። ዛሬ ከባለፉት ቀናት እጅግ በተሻለ መልኩ በተለያዩ ከተሞች እንቅስቃሴዎች ጨምረዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቻይና ዴይሊ ያጋራቸው ምስሎችም ይህንኑ የሚጠቁሙ ናቸው።

ሀገሪቷ ከወራት በኋላ በትላንትናው ዕለት አዲስ ሞት እንዳልተመዘገበ አሳውቃለች፤ 'አንዳንድ አካላት አሁንም ከሀገሪቱ የሚወጡ ሪፖርቶች ላይ እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው።

የቻይና ዜጎች ከከተማ እንዲወጡ እንዲሁም እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዷል ፤ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ የቱሪስት መዳረሻዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

ከሶስት ሺ በላይ ዜጎቿን የተነጠቀችው ቻይና በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷልም ብላለች።

ምንጭ፦ ቻይና ዴይሊ፣ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia