TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦

• በጅቡቲ 513 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 31 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኬንያ 441 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 164 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ታክሲዎች ከመደበኛ የመጫን አቅማቸው በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል። 12 ሰው የመጫን አቅም ያለው ሚኒባስ ታክሲ 6 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ተደርጓል፡፡

ሌሎች ተጨማሪ ወንበር ያላቸው እንደ ዶልፊን ታክሲዎች እንደወንበራቸው አቅም በግማሽ ቀንሰው ይጭናሉ፡፡

በሃይገር ባስ የተሳፋሪ ቁጥር በወንበር ልኩ በግማሽ ብቻ እንዲጭኑ የተደረገ ሲሆን፥ 14 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች 40 ሰው ይጭን የነበረ መደበኛ አውቶቡስ 30 ሰው ብቻ የሚጭኑ ይሆናል፡፡

ረጃጅሞቹ የተማሪ አውቶቡሶች 30 ሰው ብቻ እና አጫጭሮቹ የተማሪ አውቶቡሶች 20 ሰው ብቻ እንዲጭኑ፤ እንዲሁም ደብል ዴከር አውቶቡሶች 50 ሰው ብቻ እንዲጭን ተወስኗል፡፡

ታክሲዎችና ሃይገር አውቶቡሶች የመጫን አቅማቸው ወደ መደበኛው እስኪመለስ ቀደም ሲል የነበረው ታሪፍ በእጥፍ አድጎ ተሳፋሪዎች እንዲከፍሉ ተደርጓል ፡፡

የአንበሳ እና የሸገር አውቶቡሶች ታሪፍ በነበረበት የሚቀጥል ሆኖ መንግስት በሚያደርገው ድጎማ እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡

ማንኛውም ከተፈቀደው ሰው በላይ ጭኖ ውጭ ሲሰራ የተገኘ ታክሲም ሆነ የሃይገር አውቶቡስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ይቀጣል።

በተጨማሪም የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ እስከመጨረሻው እንዲታገድ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ተጠያቂ የሚደረጉም ይሆናል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተሪያት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከነገ መጋቢት 29/2012 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣይ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ታክሲም ሆነ ሃይገር አውቶቡስ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት በፊት እና ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንዳይሰጥ ትእዛዝ ተላልፏል። አንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች በተለመደው የአገልግሎት መስጫ ሰዓታቸው አገልግሎት ይቀጥላሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተሪያት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከተቋቋመው ንዑስ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው የሕግ ማስከበርና የደኅንነት ንዑስ ኮሚቴውን የቅድመ ዝግጁነት ሥራና ክንውን በተመለከተ ግምገማ አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊቱ ኮቪድ19 ሊያስከትል ለሚችለው የመጨረሻ አስከፊ ሁኔታ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት ማካሄዱንም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SPHMMC

የዱከም ነዋሪ የሆኑት 65 ዓመት ሴት በሌላ ተጓዳኝ ሕመም ምክንያት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ለአንድ (1) ቀን ቆይተው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በሽታ ምልክት በማሳየታቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ አንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚዋ በአሁኑ ሰዓት በኮተቤ ኤካ ሆሰፒታል ቀጣይ ሕክምናቸውን አንዲከታተሉ ተልከዋል፡፡

ለታማሚዋ የሕክምና አገልግሎትን ሲሰጡ ከነበሩ በርካታ የጤና ባለሙያዎች መካከል በወቅቱ አስፈለጊውን አልባሳት (PPE) አልተጠቀምንም ወይም አጠቃቀማችን በቂ አይደለም ያሉ ሰባት (7) ባለሙያዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ባለሙያዎች መካከል ሁለቱ (2) ታማሚዋን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡

እኝሁ ሴት በዛሬው የጤና ጥበቃ ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ የተገለጹት 44ኛዋ ታማሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

(ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጣልያን የ24 ሰዓት ሪፖርት ፦

የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው በ111 ጨምሯል። ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 636 ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 16,523 ደርሷል።

በሌላ በኩል ከመጋቢት 17/2012 ዓ/ም በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሪፖርት ተደርጓል። ባለፉት 24 ሰዓት ሪፖርት የተደረገው 3,599 ፖዘቲቭ ኬዝ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GONDAR

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ስፒሻላይዝድ ሆስፒታል ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን ህክማና ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሰራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

ሆስፒታሉ ለበሽታው ህክምን ለመስጠጥ ባለ ሶስት መቶ (300) የህሙማን አልጋዎች ያሉት የኮሮና በሽታ ህክመና መስጫ ማዕከል አዘጋጅቷል፡፡

የህክምና ምርመራ መሳሪያ ለመግጠም ነገ የምርመራ መሳሪያው ተገጣጣሚ አካላት ወደ ማዕከሉ እንደሚገቡ ተገልጿል።

ምንጭ ፦ የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከነቀምቴ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በሽታ ተጠርጥረው ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ እስፔሻላዝድ ሆስፒታል ከመጡ 4 ሰዎች የተወሰዱ ናሙናዎች ሁሉም ነፃ [ኔጌቲቭ] መሆናቸው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UGANDA

በዩጋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 231 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተግኝተዋል። በአሁን ሰዓት በዩጋንዳ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ቁጥር 52 ነው።

ምንጭ፦ ዩጋንዳ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RWANDA

ሩዋንዳ ዛሬ አንድ (1) ተጨማሪ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሪፖርት አድርጋለች። ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከዚህ ቀደም ቫይረሱ ከተገኘበት ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበረው ነው። አጠቃላይ በሩዋንዳ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 105 ደርሰዋል። 4 ሰዎች አገግመው ከህክምና ማዕከል መውጣታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 31 ደረሱ!

ዛሬ በኤርትራ ለ14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 31 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ወቅታዊውን የኮሮና ወረርሽኝን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን ለአንድ ወር የሚቆይ ሀገራዊ የጸሎት ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

በአሁን ሰዓት ከአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት አባቶች ሀገር አቀፍ የጸሎት እና የምህላ ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት እያካሄዱ ይገኛሉ። በስርነ ስርዓቱ ላይ የሀገር መሪዎች እና የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ስነስርዓቱን በEBC, FANA, Addis Tv, Walta በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ። ሁሉም በያለበት እንደየእምነቱ ፈጣሪ ይራራልን ዘንድ ልመናውን ያቅርብ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TAXIYE

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመጋታ ታክሲዬ ሞተረኞቹን በነፃ ለጤና ቢሮ እና ለሆስፒታሎች የመልዕክት አገልግሎት እንደሚሰጡና ለዚህም አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክቱ ገልጿል።

ድርጅቱ ለሞተረኞቹ ስለ ሰራው አስፈላጊነት እና አጠቃላይ አሰራሮች እንዲሁም ራሳቸውን እና የሚያገለግሉትን ህብረተሰብ ከኮሮና ቫይረስ ስለሚከላከሉበት መንገድ በቂ ግንዛቤ በህክምና ባለሞያዎች እንደተሰጣቸውም ነው ያስታወቀው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ የፃፉት በማስመሰል በፎቶሾፕ የተቀነባበረ 'የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳረፉ' ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያው እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በፈረንሳይና አሜሪካ ወረርሽኙ እየከፋ ነው!

- የኮሮና ቫይረስ ሪፖርት ከተደረገ ወዲህ በፈረንሳይ በአንድ ቀን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዝግቧል። በፈረንሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 833 ሰዎች ሞተዋል። በአጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችም 8,911 ደርሰዋል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም ከ10,000 መብለጡን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ይፋ አድርጓል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 355,000 በላይ ሆኗል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ወደፅኑ ህሙማን ክፍል ገቡ!

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ወደ ሆስፒታል ከገቡ በኃላ የህመማቸው ሁኔታ ስለጠነከረባቸው ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል እንደገቡ ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1, BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይታጠቡ

👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ

🙅🏽‍♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ይቀንሱ

አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አይውጡ

🚶‍♀_____🚶አካላዊ ርቀቶትን በእጅጉ ይጠብቁ

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia #HaimG
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrTedrosAdhanomGhebreyesus

በሁለት (2) የፈረንሳይ ተመራማሪ ሐኪሞች የተሰጠውን የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት የሚል ሃሳብ የዓለም ጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር " ዘረኛ" ሲሉ ተችተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም " አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም" ብለዋል።

የሕክምና ባለሙያዎቹ ክትባቱ መሞከር ስላለበት ጉዳይ አስተያየት የሰጡት በቴሌቪዥን ይካሄድ በነበረ የቀጥታ ክርክር ወቅት ነው። ይህ የሐኪሞቹ አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አፍሪካውያንንን " መሞከሪያ አይጥ" አድርጎ ማሰብ ነው ብሏቸዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለኮሮና ቫይረስ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ መናደዳቸው ተስተውሏል። ከዚያም "የቅኝ ግዛት አብሾ" አልለቀቃቸውም ሲሉ መልሰዋል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከሳይንቲስት እንዲህ አይነት አስተያየት መስማት የተዋረደ፣ አሳፋሪ ነው።

እንዲህ ዓይነት ነገርን በማንኛውም ሁኔታ እናወግዛለን። እናም የማረጋግጥላችሁ ነገር ይህ በጭራሽ አይሆንም" ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሴኔጋል 10 ተጨማሪ ሰዎች ከቫይረሱ አገገሙ!

በሴኔጋል 10 ሰዎች ማገገማቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም 92 ደርሰዋል። እስከትላንትናው ዕለት መጋቢት 28/2012 ዓ/ም ድረስ በሴኔጋል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 226 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በDRC በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 180 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጨማሪ 19 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ተመዝግቧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 180 ደርሰዋል። ከአስራ ዘጠኙ (19) አዲስ ኬዞች 18 ከኪንሳሻ ሲሆን አንደኛው ከቦካቩ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot