TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ROBE

"ከነሱ እንዳትገዙ... ቤት አታከራዩ... ያከራያችሁም አስወጧቸው ተብሎ በትክክልም የተከራየው እቃውን እያጋዘ ወደሌላ አካባቢ እየሄደ ነው። አሁን እራሱ አብዛኛው ሰው በራሱ ሀገር ስደተኛ ሆኖ ነው ያለው።" (ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የሮቤ ከተማ ነዋሪ)
.
.
"በወቅቱ ሶስት ሰዎች በአንድ ቦታ ሲቀበሩ፤ በርካታ ሰዎች በአንድ ቦታ ሲሞቱ በተፈጠረ ስሜታዊነት የተባለው ነገር ተደርጎ ካልሆነ በቀር እንደሀገርም ሆነ እንደ ብሄር የተፈጠረ ነገር የለም። ተሰጠ የተባለው ትዕዛዝ ተግባራዊ አይሆንም። ህዝቡ ተስማምቶበታል። በዚህች ሀገር ቻይና መጥቶ ከእኛ ጋር እየሰራ ባለበት ሁኔታ፣ ከአውሮፓውያን ጋር አብረን እየሰራን ባለንበት ሁኔታ የሀገራችን ብሄሮችና ብሄረሰቦች በእኩልነት አብሮ ሊኖርና በጋራ ለመጠቀም ሁሉም መብት አለው።" ሃጂ ቃሲም ኡስማን (የሮቤ ከተማ ነዋሪና የሀገር ሽማግሌ)
.
.
"በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተለቀቁ ያሉ መረጃዎች የባሌንም ሆነ የሮቤን ከተማ የሚወክሉ አይደሉም። የሆነ ቡድን ተሰባስቦ ተዕዛዝ ሊያወጣ ይችላል። የትኛውም ብሄር ቢሆን በከተማችን እስካሁን ምንም ችግር ደርሶበት አያውቅም። መልካም የሚባል የአብሮነት ህይወት ነበረው። ነገር ግን አሁን የተፈጠረው ችግር ከብሄር የሚያያዝና ቤት መከራየትን አብሮነትን የሚከለክል አይደለም።...ከአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ጋር በተያያዘ ተደርጎ በነባረው ሰልፍ ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ሰው በስሜት የተለያዩ ነገሮችን ሊያስተላልፍ ይችላል። የሮቤን ከተማ ነዋሪ ለማፈናቀል ነው እየተባለ በማህበራዊ መገናኛዎች የሚተላለፉ መረጃዎችን መቀበል ተገቢ አይደለም።" አቶ ግድም ኡመር (የሮቤ ከተማ ከንቲባ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA

በዛሬው እለት በአዳማ፣ በሰበታና በሞጆ ሁከት ለመፍጠር ቢሞከርም በህዝቡና በፀጥታ ሀይል ትብብር #መክሸፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡ #etv

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ፕሮግራሙን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።

የኢኖቬሽን ሳምንቱ እስከ ጥቅምት 22ቀን 2012 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ኤግዚቪሽኑ የተመድ 2030 አጀንዳ እና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063ን ለማሳካት ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ለአጀንዳዎቹ መሳካት የአፍሪካውያንን የፈጠራ ስራዎች ወደ ገበያው እንዲገቡ እና የስራ እድል ለመፍጠር መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። የአይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ አቶ አያሌው ግዛት በበኩላቸው፥ አፍሪካ የነገሮች መገኛ ብቻ ሳትሆን የቴክኖሎጂ መፍለቂያም በመሆኗ አፍሪካውያን አፍሪካን በቴክኖሎጂ ማበልፀግ ላይ ትኩረት እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ጥላቻ ህይወትን ሽባ ያደርጋል፤ ፍቅር ግን ይፈውሳል። ጥላቻ ህይወትን ግራ ያጋባል፤ ፍቅር ደግሞ አንድነትን ይፈጥራል። ጥላቻ ህይወትን ያጨልማል፤ ፍቅር ደግሞ በብርሃኑ ጨለማን ይገፋል። ወንድሜ ሆይ!! በህይወት ዘመንህ ደስተኛና ተወዳጅ ለመሆን ከፈለክ ማንንም አትጥላ!" ማርቲን ሉተር ኪንግ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ንብረትነታቸው የገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህብረ ንብረት የሆኑ የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎች በሰሜን ሸዋ ዞን መራህ ቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ ውስጥ መቃጠላቸውን የድርጅቱ ባለቤት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-29

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአፍሪካ አገራትን የሰላም ማስከበር ተልእኮ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ፎረም ትላንት በአዲስ አበባ ተጀመረ። ለመጪዎቹ ሶስት ቀናት በሚቆየው ፎረም ላይ ከስምንት አገራት የተወጣጡ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። በመከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ዲሪባ መኮንን ፎረሙን ሲከፍቱ እንዳሉት ፎረሙ በአፍሪካ አገራት በሰላም ማስከበር ተልእኮ ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና የሚሻሻልበትን መንገድ ከመቀየስ ባሻገር በአቅም ግንባታ ረገድ የባለሙያዎች ልምድ ልውውጥ ይደረግበታል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

• በኢህአዴግ ውህደት ምክንያት የህዝቡን ሰላም ባያናጉት ጥሩ ነው። ስጋትና አለመረጋጋት መፈጠሩ ለአገሪቱም ጥሩ አይደለም፤ በሚፈጠረው ግጭትም የህዝቡ ደህነት እየከፋ እንዲሄድ ነው የሚያደርገው።

• የኢህአዴግ ውህደት አህዳዊ ስርዓትን ለማምጣት ነው የሚለው ስጋት ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር አብሮ የሚሄድ አስተሳሰብ አይደለም የሚል እምነት አለኝ።

• ኢህአዴግ አንድ ውህድ ፓርቲ ከሆነ ፌዴራሊዝሙን ያጠፋዋል የሚለው ሀሳብ ቦታ የሌላውና ትርጉም የማይሰጥ ነው።ብዙ የፌዴራል አገሮች አንድ ፓርቲ በምርጫ ተፎካክሮ ካሸነፈ በፌዴራል ስርዓት ስር ያሉ የክልል መንግስታትንም ያስተዳድራል።

• የኢህአዴግ አሰራር አግላይ ነው የነበረው።አራት አህት ድርጅቶች በሚያወጡት ፖሊሲ አባል ያልሆኑት ጭምር ተግባር ላይ እንዲያውሉ ግዴታ ይጥሉባቸው ነበር:: ይህ አካሄድ ኢህአዴግ አሳፋሪ ድርጅት መሆኑን ያሳያል።

• ሁልጊዜ መደራደርና ሰጥቶ መቀበል በፖለቲካው ሂደት ያለ ነገር ነው።አንድ ጊዜ ሲከተሉት የነበረው መስመር ፍጹማዊ አይደለም። ሁሌም የሚሻሻልና የሚቀየር መሆኑን መገንዘብ ያሻል።

• የኢህአዴግ እህት ፓርቲዎች ሁኔታውን ተመልክተው ወደ ስምምነት ቢመጡ ጥሩ ነው የሚል አስተያየት አለኝ። ለአገሪቱ ሰላም መስፈን የጋራ አገራዊ ሀላፊነት አለባቸው።ይህ ሁሉ ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል።

የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ(ኢሰዴፓ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን

More👉https://telegra.ph/ETH-10-29-2

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ሙዘይ መኮነን እንደተናገሩት በባሌ ሮቤ፣ ዶዶላ፣ አዳማ እና ሌሎችም አካባቢዎች ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅንጅት እየሠሩ በመሆናቸው አንጻራዊ ሠላም እየታዬ ነው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ከጥቅምት 16/2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ግጭት እንዳልተከሰተም ነው ጄኔራል ሙዘይ ያስረዱት፡፡

ሠራዊቱ እያደረገ ባለው ጥረትም በዶዶላ ከተማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ያሉትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረሰብ ክፍሎች ሕጋዊ ከለላ እንዲገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ይህንኑ ሐሳብ በችግሩ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችም ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡ ስጋት ይታይባቸዋል በሚባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት እንዳይከሰትም የቅድመ መከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል ጄኔራሉ፡፡

የምሥራቅ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዘውዱ በላይ ደግሞ በሀረር፣ ድሬዳዋ እና አሰበ ተፈሪ ከተሞች ኅብረተሰቡን እያረጋጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ሠላማዊ እንቅስቃሴዎች እየታዩ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችንም ከኅብረተሰቡ ጋር በውይይት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው›› ብለዋል ጄኔራል ዘውዱ፡፡ እየታዬ ያለው አንፃራዊ ሠላም እንዲደናቀፍ የሚሠሩ ግለሰቦች እንዳሉ ማረጋገጣቸውንም ለአብመድ ጠቁመዋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-29-3

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር ፍቅሬ እንቁስላሴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የሀዘን መግለጫ፦

በሕብረተሰብ ጤና ት/ ቤት፤ ጤና ሰይንስ ኮሌጅ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ፍቅሬ እንቁስላሴ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ትላንት ጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ የሕብረተሰብ ጤና ት/ ቤት እንዲሁም የጤና ሰይንስ ኮሌጅ ሰራተኞች፣ በፕሮፌሰር ፍቅሬ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለስራ ባለደረቦቻቸው በማህበሩ ስም መፅናናትን እየተመኘን የስርዓተ ቀብር መርሀ ግብሩ በቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በነገው ዕለት ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት የሚከናወን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በሕብረተሰብ ጤና ት/ ቤት፤ ጤና ሰይንስ ኮሌጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት የሁለተኛ ቀን መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛን። ፕሮግራሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።

PHOTO: Abel Mulgeta(ቲክቫህ ቤተሰብ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በባሌ ዞን ጥይት ሲያዘዋውር እጅ ከፍንጅ የተያዘው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጠ!

በባሌ ዞን "ዲንሾ" ወረዳ በህገወጥ መልኩ የ “ካርባይን” ጦር መሳሪያ ጥይቶችን ሲያዘዋውር እጅ ከፍንጅ የተያዘ ግለሰብ በአስራትና በገንዘብ ተቀጣ። የዲንሾ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ንጉሴ አለሙ እንደገለጹት ግለሰቡ በሁለት ዓመት ከሦስት ወር እስራትና በ1 ሺህ ብር እንዲቀጣ የተወሰነው በዲንሾ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው። ተጠርጣሪው የተፈረደበት 298 የካርባይን ጥይቶችን ከሻሻመኔ ከተማ ወደ ባሌ ሮቤ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ጭኖ ስጓዝ ዲንሾ ከተማ ላይ እጅ ከፍንጅ በመያዙ ነው። የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና የአካባቢው የጸጥታ አካላት ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት ባደረጉት ፍተሸ ግለሰቡ እጅ ከፍንጅ ሊያዝ መቻሉን ኮማንደሩ አስታውሰዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በተያዘው የትምህርት ዘመን(2012)በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በተጀመረው የምገባ ፕሮግራም ከ10 ሺ በላይ እናቶች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለፀ። የቢሮው የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ክትትል ትግበራ ቡድን መሪ አቶ ዓቢይ ተፈራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በምገባ ፕሮግራሙ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ለአንድ ተማሪ በቀን ቁርስና ምሳን ጨምሮ 14 ብር በአማካይ በጀት ተመድቧል። በዚህም 300 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎች ተጠቃሚዎች ናቸው። በምገባ ፕሮግራሙ ተማሪዎችን በመመገብና የተማሪ ወላጆችን ደግሞ ለመደጎም እየተሠራ መሆኑንም የቡድን መሪው ጠቅሰው፣ በፕሮግራሙ ከ10ሺ በላይ እናቶች የሥራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

የአይ ኤስ-አይ ኤስ (ISIS) መሪ አቡ በከር አል-ባግዳዲ መገደልን መሰረት በማድረግ “በከፍትኛ የተጠንቀቅ ሁኔታ” እየሰራ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር ገለፀ። ይሁንና ተጨባጭ የሆነ የአደጋ መረጃ ከሌለ በስተቀር ማስጠንቀቅያ የማውጣት ዕቅድ እንደሌለው አክሎ ገልጿል።

የUS ልዩ ወታደራዊ ኃይል በሰሜን ምዕራብ ሶርያ በጥንቃቄ ባካሄደው ተልዕኮ ባግዳዲንን መግደሉን ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ካስታወቁ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል። “የፀጥታ ተቋማችን በንቃት መከታተሉን ይቀጥላል። ለሚከሰቱ ሁነቶች ምላሽ መስጠቱን እንቀጥላለን” ይላል መግለጫው። በኩርዶች የሚመራው የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች እንደሚለው የባግዳዲ ቀኝ እጅ የነበረው የዳዕሽ ቃል አቀባይ አቡ ሐሰን ዐል-ሙሓጂርም በዩናይትድ ስቴትስ ተልዕኮው ተግድሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች ግን ገና አላረጋገጡትም።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትስስር ለማጠናከርና አዳዲስ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ያለመ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ በምክክር መድረኩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ በአገራችን ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች እና የዩኒቨርስቲዎቹ የዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሮች ከየአሜሪካ ፐብሊክ ላንድ ግራንት ዩኒቨርስቲዎች ማህበር ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

Via የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኃይማኖት መሪዎች የሰላም ጥሪ!

የፌደራልና የክልል መንግሥታት የብዙኃኑ ፍላጎት ሰላም መሆኑን ተረድተው ለዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት እንዲሰሩ የኃይማኖት መሪዎች ተማፀኑ፡፡

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠው መግለጫ የተገኙ የእምነት መሪዎች ሰሞነኛውን ግጭትና ጥቃት በምሬት በማውገዝ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

እንባ እየተናነቃቸው መግለጫ ሲሰጡ የተስተዋሉት አባቶች በኢትዮጵያ ሰው በአደባባይ ሲገደልና ሲታረድ እንደማየት ቀውስ የለም ብለዋል፡፡

በክልሎች መንግስታት መካከል የሚታየው ውጥረት የፖለቲካ ኃይሎች የሚፈጥሩት አጀንዳ መሆኑን ኣባቶቹ አስምረውበታል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት አካላት እርስ በርሳቸው እርቅ እንዲፈፅሙም በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡

የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላት የኢትዮጵያን ሰላም ሁሌም ነቅተው እንዲጠብቁና ተገቢ ያልሆኑ አዝማሚያዎችን ቀድመው በመገንዘብ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰሞኑን የተከሰተው ግጭት ኃይማኖታዊ ገፅታ እንዲላበስ እየተደረገ ያለው በሌሎች ኃይሎች እንጅ ፍፁም ሃይማኖታዊ መሠረት እንደሌለው እንገልፃለን ሲሉም አሳስበዋል፡፡

Via #AHADUTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለሐያት ሪጀንሲ የባለ 5 ኮኮብ ለኤልያና ሆቴል ደግሞ የባለ 4 ኮኮብ ደረጃ ሰጠ። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እያካሄደ በሚገኘው የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ምዘና ሲካሄድባቸው ቆይቶ ውጤታቸው ለተጠናቀቀ ሁለት ሆቴሎች በዛሬው ዕለት የኮከብ ደረጃ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የባለ 5 ኮከብ እንዲሁም የኤልያና ሆቴል የባለ 4 ኮከብ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ባሳለፍነው ነሃሴ 2011 ዓ.ም 12 ባለ አራት፣ 13 ባለ ሶስት፣ 31 ባለሁለት እንዲሁም 27 ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ በአጠቃላይ 81 የኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Via ETHIO FM 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሠጠው መግለጫ፦

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን ልጆቻችን፤- 

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ባሳለፍነው ሳምንት በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በአሮሚያ ብሔራዊ ክልል በተፈጠረው ሁከት፣ አለመረጋጋት እና ግጭት ምክንያት ሕይወታቸው ባጡት ወገኖቻችን የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለሟቾች ቤተሠቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንም ፈጣን ፈውስን እንዲያገኙ እየተመኘን በጸሎታችንም እንደምናስባችሁ ለመግለጽ እንወዳለን!! እንደሀገር እየታየ ያለው ያለመረጋጋት እና የግጭት አዝማሚያ ተወግዶ  ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታና ወደሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ፣ ሁከትንና ግጭትን ከሚያባብሱ ሀሳቦችና ድርጊቶች በመታቀብ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ  በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/የኢትዮጵያ-የሃይማኖት-ጉባኤ-ተቋማት-10-29

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለኢትዮጵያውያን ርዳታ በኢትዮጵያውያን!

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ለተገደሉ ቤተሰቦች፤ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በሐገር ፍቅር ቴአትር ቅጥር ግቢ ውስጥ የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ትናንትና ጀምሮ ዛሬም ቀጥሏል። 25 በሚደርሱ በጎ ፈቃደኞች የተጀመረውን የርዳታ ማሰባሰብ ተግባር በዋናነት «የጉዞ አድዋ» መርኃ-ግብር አዘጋጆች አስተባባሪ ናቸው። ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተዉ አለመረጋጋት የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ከትናንትና ማክሰኞ አንስቶ የተጀመረዉ ርዳታ ማሰባሰብ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የኮሚቴዉ አስተባባሪዎች ገልጠዋል። ከገንዘብ ውጪ የዕለት ርዳታ በቁሳቁስ የሚሰበሰበው ሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ውስጥ ነው። ዛሬም እየተኪያሄደ ነው። የቁሳቁስ ርዳታውን መንግሥት ተረክቦ እንደሚያጓጉዝ አዘጋጆቹ ገልጠዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ የሰባት ዓመት እስራት ተፈረደበት!

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ከአምስት ዓመታ በፊት በዕንቁ መጽሔት በተመሰረት ክስ ማክሰኞ ጥቅምት 18/2012 በዋለው ችሎት ጥፋተኛ በመባሉ በሰባት ዓመት እስራታ እና ሰባት ሽሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ተፈርዶበታል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዘ ክስ መስርቶበት የነበረ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ ከ2004 እስከ 2006 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ 179ሽሕ 411 ብር ከ65 ሳንቲም ለመንግስት መክፈል የነበረበትን ግብር ስወራ አድርጓል የሚል ክስ ተመስርቶበት ነበር።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው ችሎቱ ጥፋተኛ ያላቸው ጌታቸር እሸቴ እና ፍፁም ጌታቸው በ12 አመት ፅኑ እስራት ቶፊቅ ሽኩር እና ሸምሱ ሰይድ ደግሞ የ11 አመት ፅኑ እስራት ቅጣት ዛሬ ተላልፎባቸዋል። በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተው 38 ሰዎች ላይ የነበረ ቢሆንም ከ4ቱ ውጭ ያሉት በምህረት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለታራሚዎቹ ደህንነት በማለት የቅጣት ውሳኔው ባሉበት ማረምያ በደብዳቤ የወሰነ ሲሆን ለቤተሰብ እና ጋዜጠኞች ውሳኔው በፅህፈት ቤት ተነቧል።

Via ሳምራዊት አመለወርቅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia